TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#update ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ20 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚገነባ ትምህርት ቤት #የመሰረተ_ድንጋይ አስቀመጡ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮ ቴሌኮም...

"በ846 ወረዳዎች ለሚገኙ የቴሌኮም አገልግሎት የመግዛት አቅም ለሌላቸው #ሴቶች 70,000 የሞባይል ቀፎዎችን ከሲም ካርድ ጋር በስጦታ ለማበርከት ዝግጅታችንን #አጠናቀናል።"

#Ethiopia #Women
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update መቅዲሹ፤ በደረሰው ጥቃት 19 ተገደለዋል። ትናንት ምሽት በአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ፍንዳታ በደረሰባት የሶማሊያ ዋና ከተማ #ሞቃዲሾ ዛሬም ተኩስ መቀጠሉ እየተነገረ ነው። በፍንዳታው የደረሰውን ጨምሮ እስካሁን ቢያንስ 29 ሰዎች መገደላቸው ተዘግቧል። በርካቶችም ተጎድተዋል። ትናንት ምሽት አንድ አጥፍቶ ጠፊ እንቅስቃሴ በሚበዛበት መንገድ ዳር ከሚገኝ ሆቴል አቅራቢያ በመኪና ውስጥ ባጠመደው ፈንጂ ራሱን ሲያጋይ እሳቱ ተዛምቶ ጉዳቱን እንዳሰፋውም ተጠቅሷል። ከፍንዳታው በኋላ የሶማሊያ ኃይሎች በአካባቢው ወደ አንድ ሕንፃ ተጠግተው ከመሸጉ #የአልሸባብ ታጣቂዎች ጋር መታኮስ መቀጠላቸውንም ተገልጿል። ሆቴሉ ውስጥ የአልሸባብ ታጣቂዎች ሰላማዊ ሰዎችን አግተው መቆየታቸውን የሶማሊያ መንግሥት የዜና አውታር ዘግቧል። የሀገሪቱ የፀጥታ ኃይል ባልደረባ አብድራህማን አሊ ለፈረንሳይ የዜና ወኪል የተጎዱ ሰዎችን የማዳን ሥራ እየተከናወነ መሆኑን፣ ተኩሱ በመቀጠሉም የሟቾች ቁጥርም ሊጨምር እንደሚችል አመልክተዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“የዛሬዎቹ ኢትዮጵያውያን እንደ ትናንቶቹ ኢትዮጵያውያን በሕይወት መስዋዕትነት ብቻ ሳይሆን እየኖርን በመስራት በደም የተቀበልናትን አገር ነፃነቷን ጠብቀን #ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ ጠንክረን መስራት ይጠበቅብናል” ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስጦታ!

@medachat ነገ በድጋሚ የሚካሄደውን የሮፍናንን "የኔ ትውልድ" የሙዚቃ ኮንሰርት እንድታደሙ ለ10 የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ነፃ ትኬት አዘጋጅቶልናል!

በሜዳ ቻት እስከ ምሽቱ 5 ሰዐት ድረስ #Adwa123 ብላችሁ ለላካችሁ 10 ሰዎች ትኬቶቹን እናስረክባለን!

MedaChat App ስልኮት ላይ ተጭኗል?? ካልተጫነ በዚህ ያገኛሉ www.bit.ly/medachatapp

በመቀጠል በሜዳ ቻት APP በኩል በ @tsegab_wolde የMedaChat UserName #Adwa123 ብላችሁ ላኩልኝ!

ማሳሰቢያ፦ መልዕክቱን አንዴ ብቻ ላኩ! ተደጋግሞ ቢላክ ተቀባይነት የለውም! አንዴ ብቻ!! -- #Adwa123
#update ፍኖተ ሰላም የሚገኘው ኃይሉ ዓለሙ ኮሌጅ የእውቅና ፈቃድ ባልተሰጠበት #በፋይናንስና #አካውንቲንግ የትምህርት መስክ በዲግሪ መርሃ ግብር መዝግቦ ሲያስተምር በመገኘቱ ተማሪዎቹን እንዲያሰናብት የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ውሳኔ ማስተላለፉን ተሰምቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሊቀመንበርነታቸው ወረዱ‼️

የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሺር ከገዥው #ናሽናል_ኮንግረስ_ፓርቲ ሊቀመንበርነታቸው መውረዳቸው ተገልጿል። በምትካቸውም የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አህመድ ሞሃመድ ሃሩን ፓርቲው አጠቃላይ ጉባኤ እስከሚያካሂድ የአልበሺርን ቦታ መረከባቸው ነው የተነገረው። ሀሩን በዚህ ሳምንት የሱዳን ገዥ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸው ይታወሳል።

በሱዳን ከታህሳስ ወር 2018 ጀምሮ እስከዛሬ ያልተቋረጠው የዜጎች ተቃውሞ አልበሺር ከፓርቲ ሃላፊነታቸው እንዲለቁ ማስገደዱን ተንታኞች እየገለጹ ቢሆንም ፕሬዚዳንቱ ከዚህ ቀደምበተቃውሞ ፍራቻ ሳይሆን በምርጫ ብቻ ስልጣናቸውን እንደሚለቁ መናገራቸው ይታወሳል። ሱዳን በ2020 ምርጭ እንደሚታካሂድ ይጠበቃል።

አልበሺር ባሳለፍነው ሳምንት ለአንድ ዓመት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያወጡ ሲሆን እሰተዳደራዊ መዋቅሩን በመበተን አዳዲስ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ሹመት ሰጥተዋል። በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ #ክልከላ ቢደረግም #ተቃውሞው እስከዛሬ ድረስ መቀጠሉን መረጃዎች ያሳያሉ።

ምንጭ፦ሲጂቲኤን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮጵያ ከሶስት አመት ብኋላ እአአ በ2021 የተፈጥሮ ጋዝ ወደ ውጪ መላክ #እንደምትጀምር በማዕድንና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር የነዳጅ ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ አስታወቁ። የተፈጥሮ ጋዙ በዓመት እስከ አንድ ቢለዮን የአሜሪካ ዶላር ያስገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅም ገለጹ፡፡ ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር #ኳንግ_ቱትላም በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለፁት፤ በሶማሌ ክልል የተገኘውን #የተፈጥሮ_ጋዝ የሚያለማው የቻይና ኩባንያ ሲሆን፣ የተፈጥሮ ጋዙ ከኢትዮጵያ ወደ ጅቡቲ የሚጓጓዘው በቱቦ ይሆናል ብለዋል፡፡

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ክቡር ፕረዝዳንት ለማ መገርሳ #ኢፍትሃዊነት እና #የአሻጥር ፖለቲካን የሚጸየፉ፣ በህዝቦች ወንድማማችነት፣ እኩልነት እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት በጽኑ የሚያምኑ ይንንም በተግባር ታግለዉ #ጠንካራ ሥብዕናቸዉን በተግባር ያረጋገጡ የህዝብ ልጅ ናቸዉ፡፡" አቶ አዲሱ አረጋ
.
.
.
ሠሞኑን አንዳንድ #አክቲቪስቶች እና ፖለቲከኞች የክቡር ፕረዝዳንት ለማ መገርሳን ንግግሮች ከተነገረበት አዉድ ዉጪ እና ትርጉም ጭምር አጣምመዉ በማቅረብ ፕረዝዳንት ለማን የአሻጥር ፖለቲካ አራማጅ አስመስለዉ በማቅረብ የማጥላላት ዘመቻቸዉን ተያይዘዉታል፡፡ ለአብነትም በአንድ መድረክ ስለ ከተማ ዲሞግራፊ የተነገረዉን ንግግር በአሻጥር ፖለቲካ ተርጉመዉ እያራገቡት ይገኛሉ፡፡

በዚህ መድረክ አንዱ ተሳታፊ በኦዲፒ የእስካሁን አጠቃላይ እንቅስቃሴ የኦሮሞ ህዝብ በኢኮኖሚ ሆነ በማህበራዊ እድገቱ እምብዛም እንዳልተሻሻለ አሁንም በገጠር በሞፈር እና ቀንበር እያረሰና የከብት ጭራ እየተከተለ እየኖረ እንደሆነ፣ ኦሮሞነት በገጠር እና በኋላ ቀር ኑሮ እየተመሰለ ነዉ የሚል ጠንከር ያለ ትችት አዘል ጥያቄ ከአንድ ተሳታፊ ለክቡር ፕረዝዳንቱ ተነስቶ ነበር፡፡ ለዚህም ጥያቄ ፕረዝዳንት ለማ ማብራሪያ ሲሰጡ ይህንን ችግር እንደ ፓርቲ ለመቀየር መስራት አለብን ከሚል ቅን ሀሳብ በመነሳት ኦሮሞነት በኋላ ቀር እና በገጠሬነት ብቻ ሳይሆን የከተማ ዘመናዊ ኑሮም መገለጽ እንዳለበት ተናግረዋል፡፡ በዚህም ረገድ ኦዲፒ ጠንክሮ በመስራት ላይ እንደሚገኝና ከኢትዮጵያ ሶማሌ በኦሮሞነታቸዉ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችን ጭምር በኦሮሚያ ከተሞች በህዝቡ ተሳትፎና ድጋፍ እንዲሰፍሩና የከተማ የኑሮ ዘይቤን እንዲለማመዱ መደረጉን፤ የልማት ተነሽ አርሶ አደሮች እና የአርሶ አደር ልጆች በከተማ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታን እንዲያገኙ መደረጉን፤ በኦሮሚያ ከተሞች የኦሮሞ ህዝብ ወደ ከተማ ኑሮ እየተሰባጠረ መምጣቱን፤ ወደ ፊትም የኦሮሞ የስነ ህዝብ ስብጥር (ዲሞግራፊ) በገጠር ብቻ ተወስኖ መቅረት እንደሌለበትና ህዝባችን በከተማም መኖር እንዳለበት ለዚህም ኦዲፒ ጠንክሮ እንደሚሰራ አጥብቀዉ ምላሽ ሠጥተዋል፡፡

የሚገርመዉ ጉዳይ ኦሮሞ ህዝብ አኗኗር በኋላ ቀር የገጠር ኑሮ ብቻ መታወቅ የለበትም፣ ህዝባችን ኑሮዉ መሻሻል አለበት ገጠርም ከተማም መኖር አለበት የሚል ሃሳብ እንዴት የአሻጥር ፖለቲካ ሊሆን ይችላል? የኦሮሞን ህዝብ ኑሮ ለማሻሻል እና ወደ ከተሜነት ማዘመን የክልሉ መንግስት ግዴታ ነዉ፡፡ ለዚህ ደግሞ የክልሉ መንግስት የማንም ፈቃድ እና ቡራኬ አያሻዉም፡፡

ክቡር ፕረዝዳንት ለማ መገርሳ ኢፍትሃዊነት እና የአሻጥር ፖለቲካን የሚጸየፉ፣ በህዝቦች ወንድማማችነት ፣እኩልነት እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት በጽኑ የሚያምኑ ይንንም በተግባር ታግለዉ ጠንካራ ሥብዕናቸዉን በተግባር ያረጋገጡ የህዝብ ልጅ ናቸዉ፡፡ አምርረዉ የሚጠሉትንና ሲታገሉት የነበረዉን የሴራ እና የአሻጥር ፖለቲካ በማራማድ የኦሮሞን ህዝብም ሆነ በግላቸዉ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት የሚያስብ ስብዕና ፈጽሞ የላቸዉም፡፡

ነገር ግን ፕረዝዳንት ለማ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ፕረዝዳንት እንደመሆናቸዉ የኦሮሞን ህዝብ ኑሮ ለመለወጥ መስራት ግዴታቸዉ እንደሆነም መዘንጋት የለበትም፡፡ ስለሆነም ፕረዝዳንቱ የኦሮሞን ህዝብ የልማት እና የለዉጥ አጀንዳዎች ባነሱ ቁጥር በአሻጥር ለመክሰስ መሯሯጥ ኢ-አመክኖአዊ እና ተቀባይነት የሌለዉ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡

#AddisuArega

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በቅርቡ ራሳቸውን #ከህወሀት ያገለሉት አቶ #ዛዲግ_አብርሀ እህታቸው እስር ቤት እንደገባች ለአለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ገለፁ። "የታሰረችው እህቴ በመሆኗ ብቻ ነው። ህወሀት ውስጥ ሆኜ ስታገለው የነበረው አስተሳሰብ ይህ ነው" ሲሉም ለጋዜጠኛ ኤልያስ ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ይፈለጋል‼️

የአሜሪካ መንግሥት የቀድሞ የአል ቃኢዳ መሪ የኦሳማ ቢላደን ልጅ #ሀምዛ_ቢላደን ያለበትን ለሚጠቁማት 1 ሚሊየን ዶላር ሽልማት አዘጋጀች፡፡

ቢቢሲ እንደዘገበው ሀምዛ ቢን ላደን #የአል_ቃኢዳ ታጣቂ ቡድን መሪ ለመሆን በመዘጋጀት ላይ እንደሆነም ተነግሯል።

የኦሳማ ቢን ላደን ልጅ በአሁኑ ሰዓት በአፍጋኒስታንና በፓኪስታን ድንበር አቅራቢያ ሊኖር ይችላል የሚል ግምት መኖሩን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።

አሜሪካ እድሜው 30 ዓመት እንደሆነ የሚገመተውን ሀምዛ ቢን ላደን ከሁለት ዓመት በፊት በዓለም አቀፋዊ አሸባሪነት ፈርጃዋለች።

ከጥቂት ዓመታት በፊት በድምፅና በምስል በለቀቀው መልዕክት አሜሪካና ምዕራባዊ አጋሮቿ ላይ ጥቃት በመፈጸም የአባቱን ሞት እንዲበቀሉ ለተካታዮቹ ጥሪ አስተላልፏል።

በፈረንጆቹ 2011 የአሜሪካ ልዩ ኃይሎች ፓኪስታን አቦታባድ በሚገኘው የራሱ ግቢ ኦሳማ ቢን ላደንን መግደላቸው ይታወሳል።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopua
1,000,000$ ሽልማት‼️

የቀድሞውን የአል ቃኢዳ መሪ የኦሳማ ቢላደን ልጅ #ሀምዛ_ቢላደን ያለበትን ለሚጠቁም 1 ሚሊየን ዶላር ሽልማት አሜሪካ አዘጋጅታለች። የኦሳማ ቢን ላደን ልጅ በአሁኑ ሰዓት #በአፍጋኒስታንና #በፓኪስታን ድንበር አቅራቢያ ሊኖር ይችላል የሚል ግምት መኖሩን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአማራና በትግራይ ክልሎች ድንበር አካባቢ የመከላከያ ሰራዊት ታንኮች ተሰማርተው ማየታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። ከሁለት ቀን በፊት በዳንሻ ከተማ የሰው ህይወት ማለፉን ተከትሎ በአካባቢው ውጥረት ማገርሸቱ ይታወቃል።

Via elu
@tsegabwolde @tikvahethiopia