TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
የባሕር ዳር ነዋሪዋ እና አደራ የተረከቡት አባት ለ20 ዓመታት #በአደራ የኖሩበትን ቤትና የቤት ኪራይ ለኤርትራዊ ባለቤቱ አስረከቡ!
.
.
የታሪኩ መነሻ ጊዜ 1991 ዓ.ም ነው፡፡ ቦታው ደግሞ ባሕር ዳር ከተማ፡፡ ትውልድ ኤርትራዊው አቶ አብርሃም ደስይበለኝ በባሕር ዳር ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ነበር የሚሰሩት፡፡ በወቅቱ በነበረው የፖለቲካ ችግር ምክንያት ግን ከስራ እና ከመኖሪያ ቦታቸው ተነስተውና ቤተሰቦቻቸውን ይዘው ከኢትዮጵያ እንዲወጡ ተደረጉ፡፡

ከአባቷ ጋር አብራ ወደ ኤርትራ እንድትሄድ የተደረገችው የዛሬዋ ባለታሪካችን ሰናይት አብርሃም በወቅቱ የትና ለምን እንደምትሄድ ባታውቅም ተወልዳ ያደገችበትን ቀየና ቤት እየተሰናበተች ነበርና ‹‹አደራ!›› ለባለአደራ ሰጠች፡፡
አደራው ደግሞ የአባቷ የስራ ባልደረባ ለነበሩት ለአቶ ተፈራ አባተ እና እነሰናይት ከሀገር ሲወጡ ግቢው ውስጥ ተከራይታ ለነበረችው ለወይዘሮ መዓዛ ሳሙኤል ነበር የተሰጠው፡፡ ወይዘሮ መዓዛ ለረዥም ዓመታት በአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ውስጥ ሲሰሩ ቆይተው አሁን ላይ በጡረታ ከተቋሙ ወጥተዋል፡፡

እንደ ዋዛ ከሀገር እንደወጡ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ያስቆጠሩት ሰናይት እና ቤተሰቦቿ አንድ ቀን ወደ ባሕር ዳር-ቀበሌ 8 እንደሚመለሱ እና ንብረታቸውን እንደሚያገኙ ተሰፋ ነበራቸው፡፡ ዘመን መመለሳቸውን ሲፈቅድ፣ ያለያያቸው የፖለቲካ ቁርሾ በፍቅር ሲሽር፣ ተስፋ ወደ እውነታ ተቀየረ፡፡

ሰናይት ያደገችበትን ቀየና ቤት ዳግም ለማየት በቃች፡፡ ‹‹አደራ የተሰጠን ቤቱን ጠብቆ ለማቆየት ቢሆንም በየጊዜው ከኪራይ የሚገኘውን ገንዘብ በተለያየ መንገድ ለባለቤቶቹ እንዲደርስ ስናደርግ ቆይተናል›› ያሉት አቶ ተፈራ ዛሬ ደግሞ ከ20 ዓመታት ቆይታ በኋላ 18 ሺህ ብር ቀሪ ኪራይ እና ቤቱን ለባለቤቷ በአካል አስረክበዋል፡፡

‹‹ባለፉት ዓመታት በአስመራ በነበረኝ ቆይታ አንድ ሰው ‹ኢትዮጵያዊ ነው!› ሲባል ሀገሩን ብቻ ሳይሆን ታማኝነቱንም መግለጫ›› ነው ያለችን ሰናይት ከተቀበለችው ገንዘብ በላይ የግቢው እና የቤቱ አያያዝ ልዩ ስሜት እንደፈጠረባት ተናግራለች፡፡ ከ20 ዓመታት በላይ በኪራይ ቤት መኖር ያልተለመደ ነው ባይባልም እንግዳ ነገር ለመሆኑ ግን አጠራጣሪ አይደለም፡፡ ወይዘሮ መዓዛ ሳሙኤል ግን ከኪራይ ያለፈ ቃል እና እምነት ተጥሎባቸዋልና የእርሳቸውንና የሌሎችን ተከራዮች ወርሃዊ ኪራይ ለአቶ ተፈራ እየሰጡ ግቢውንም እንደ እራሳቸው ንብረት እየተንከባከቡ አደራቸውን ዛሬ ለሰናይት አስረክበዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ብሄራዊ የደም ባንክ አገልግሎት ባለፉት ስድስት ወራት በአገር አቀፍ ደረጃ 106 ሺህ ከረጢት ደም ከበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች መሰብሰቡን አስታውቋል። በበጀት ዓመቱ አጋማሽ ከአዲስ አበባ ከተማ ብቻ 38 ሺህ ከረጢት ደም ከበጎ ፈቃድ ደም ለጋሾች በማግኘት የዕቅዱን 90 በመቶ ማሳካት ችሏል። የዕቅድ አፈጻጸሙ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ11 ሺህ ከረጢት ደም ብልጫ አለው።

via ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቴዲ ማንጁስ‼️

በሙስና ወንጀል በተጠረጠሩት አቶ #ቴዎድሮስ_አዲሱ (ቴዲ ማንጁስ) ላይ ዐቃቤ ህግ የ15 ቀናት የክስ መመስረቻ ጊዜ ጠየቀ።

መርማሪ ፖሊስ በአቶ ቴዎድሮስ ላይ ሲያደርግ የነበረውን ምርምራ አጠናቆ የምርመራ መዝገቡን ትላንት ለዐቃቤ ህግ አስረክቧል።

ዐቃቤ ህግ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል ችሎት እንደገለጸው፤ ተጠርጣሪው አቶ ቴዎድሮስ አዲሱ ባላቸው የህትመት ድርጅት ከኒያላ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር ጅግጅጋ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅና ከሶማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ ጋር የመማሪያ መጻህፍትን ለማተም ውል ፈጽመው እንደነበረ ገልጿል።

ሆኖም ተጠርጣሪው ከኒያላ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር ጅግጅጋ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅና ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ጋር በመመሳጠር በውሉ መሰረት መጽሐፉን ሳያስረክቡ ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ ቅድሚያ ክፍያ እንደተከፈላቸው ዐቃቤ ህግ ለችሎቱ አስረድቷል።

በዚህ መሠረት አቶ ቴዎድሮስ አዲሱ በመንግስትና በህዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸውን ዐቃቤ ህግ አስረድቷል። 

የተፈጸመው ወንጀል ውስብስብና ከባድ ከመሆኑም በላይ የተፈጸመው ወንጀል ከ10 ዓመት በላይ የሚያስቀጣ ስለሆነ በርካታ የሰነድ ማስረጃዎችን አሳባስቦ በማጠናቀቅ በቴዎድሮስ አዲሱ (ቴዲ ማንጁስ) ክስ ለመመስረት  የ15 ቀናት የክስ መመስረቻ ጊዜ ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

ግለሰቡ የተጠረጠሩብት ወንጀል ከባድ የሙስና ወንጀል ሲሆን የዋስትና መብት የሚያስከለክል በመሆኑ የተጠርጣሪው የዋስትና መብት ጥያቄያቸው ውድቅ እንዲደረግለት ዐቃቤ ህግ ችሎቱን ጠይቋል።

ተጠርጣሪው አቶ ቴዎድሮስ አዲሱ የህትመት ድርጅታቸው ለሰባት ወራት መታገዱንና ድርጅቱ መዘረፉን ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል።

የፍርድ ቤት እገዳ ሳይኖር ድርጅታቸው መታገድ እንደሌለበት ያመለከቱት አቶ ቴዎድሮስ የሶማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ የህትመት ስራ አሰርቷቸው 7 ሚሊዮን ብር እንዳልተከፈላቸውም ተናግረዋል።

በሶማሌ ክልል ፍርድ ቤት የታገደው የአቶ ቴዎድሮስ የህትመት ድርጅት ፖሊስ ለተጠርጣሪው ማሳወቅ እንደነበረበት የገለጸው ችሎቱ ከዚህ በኋላም ተጠርጣሪው ማወቅ የሚገባቸውን መረጃዎች ፖሊስ በወቅቱ እንዲያሳውቅ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው ፍርድ ቤቱ ዐቃቤ ህግ በተጠየቀው የ15 ቀናት የክስ መመስረቻ ጊዜ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለነገ ከሰዓት በኋላ ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።

አቶ ቴዎድሮስ አዲሱ በሌላ መዝገብ  ከሐምሌ 26 እስከ 30 ቀን 2010 ዓ.ም በጅግጅጋ እና አካባቢው ተከስቶ በነበረው ሁከትና ብጥብጥ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለው የነበረ ቢሆንም ፖሊስ በጉዳዩ ላይ ምርመራውን ባለማጠናቀቁ የተጠርጣሪው ጠበቃ የግለሰቡን ፍትህ የማግኘት መብት የሚጎዳ መሆኑን ፍርድ ቤቱ አመዛዝኖ የክስ መዝገቡ እንዲዘጋ መጠየቁ ይታወሳል።

ፍርድ ቤቱም ከተጠርጣሪው ጠበቃ የቀረበውን የክስ መዝገቡ እንዲዘጋ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ተጠርጣሪው በ80 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ውሳኔ መስጠቱ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ አቶ ቴዎድሮስ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ምርመራ እየተካሄደባቸው በመሆኑ ከእስር #አልተፈቱም

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሕወሃት ሥራ አስፈጻሚ አባል #አስመላሸ_ወልደሥላሴ በኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ውስጥ በአማካሪነት መመደባቸውን ሪፖርተር አስነብቧል፡፡ በፓርላማው የመንግሥት ተጠሪ ሚንስትር የነበሩት አስመላሽ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ከሃላፊታቸው እንደተነሱ ይነገራል፡፡ ምደባው በኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ባዶ የነበረውን የሕወሃት ውክልና ይሞላል ተብሏል፡፡ አዲስ ዋና ተጠሪ እስኪመረጥ ድረስ በቅርቡ ምክትል ተጠሪ ሆነው የተመረጡት የኦዴፓው ጫላ ለሚ ተክተው ይሰራሉ፡፡

via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዳማ🔝

7ኛው የመከላከያ ሰራዊትን ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ በአዳማ ከተማ እየተከበረ ይገኛል። በዓሉ ” ህገ መንግስታዊ ታማኝነታችንና ህዝባዊ ባህሪያችን ጠብቀን የተጀመረው ሀገራዊ ለውጥ እናስቀጥላለን ” በሚል መሪ ቃል ነው በሀገር አቀፍ ደረጃ በመከበር ላይ ያለው። በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም እየተከበረ ባለው የመከላከያ ሰራዊት ቀን ላይም የጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ፣ የኦሮሚያ ክልል ርእስ መስተዳድር አቶ #ለማ_መገርሳ የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር #አይሻ_መሀመድ፣ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል #ሰዓረ_መኮንን ጨምሮ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች፣ ሚኒስትሮችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
OBN Live! 7ኛውን #የመከላከያ_ሰራዊት_ቀን አከባበር #ከአዳማ በቀጥታ በኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ መከታተል ትችላላችሁ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንኳን አደረሳችሁ፤ እንኳን አደረሰን!

#የመከላከያ_ሰራዊት_ቀን!

#TIKVAH_ETHIOPIA ለመላው የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት በሙሉ እንኳን ለ7ኛ ጊዜ ለሚከበረው #የመከላከያ_ሰራዊት_ቀን በሰላም #አደረሳችሁ#አደረሰን ለማለት ይወዳል!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠንካራ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ባይኖር ኖሮ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በሚነሱ #አለመረጋጋትና ግጭቶች ኢትዮጵያ የመፈራረስ ዕጣ ይገጥማት እንደነበር የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ገለጹ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
OBN Live!! 7ኛውን የመከላከያ ቀን አስመልክቶ የተዘጋጀውን ድንቅ ወታደራዊ ትርኢት ተመልከቱ!

@tsrgabwolde @tikvahethiopia
ልዩ ሀይል💪ወታደራዊ ትርኢቱን በማቅረብ ላይ ይገኛል። 7ኛው #ሀገር_መከላከያ_ሰራዊት_ቀን

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአዳማ ነዋሪዎች እንዳትረበሹ...

እየሰማችሁት ያለው #የተኩስ ድምፅ በአሉን አስመልክቶ የተዘጋጀው ወታደራዊ ትርኢት አንዱ አካል ስለሆነ በምትሰሙት ተደጋጋሚ የተኩስ ድምፅ እንዳትረበሹ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አ.ሳ.ቴ.ዩ‼️

• በ25 ተማሪዎች ላይ የዲስፕሊን እርምጃ ወስዷል፤

• 14 የስታፍ አባላትንም ለይቶ ለዲስፕሊን የማቅረብ ሂደት ጀምሯል፤
.
.
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በዳግም ቅበላ ተማሪዎቹን ማስተማር መጀመሩን ገለጸ፡፡ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዳይማሩ በማድረጉ ሂደት ተሳትፎ ባላቸው 25 ተማሪዎች ላይ የዲስፕሊን እርምጃ መውሰዱን እና 14  የስታፍ አባላትንም ለይቶ #ለዲስፕሊን የማቅረብ ሂደት መጀመሩን ገልጿል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር #ለሚ_ጉታ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ጊቢ ውስጥ እየኖሩ ነገር ግን ለረዥም ጊዜ ክፍል ሳይገቡ መቆየታቸውን ተከትሎ ለአንድ ሴሚስተር እንዲቀጡ ሴኔቱ በወሰነው መሰረት ከጊቢ እንዲወጡ ተደርጎ ነበር፡፡ ሆኖም ተማሪዎች ከሄዱ በኋላ የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንትና ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ጨምሮ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተማሪዎች ከጊቢ በወጡበት ጊዜ ውስጥ መሰራት በሚገባቸው ዘጠኝ ያህል ነጥቦችን ለይቶ ቀንና ሌሊት ሲሰራ በመቆየቱ ለአንድ ወር ከ15 ቀን የነበረውን ከጊቢ ውጪ ቆይታቸውን ወደ ሦስት ሳምንት እንዲያጥር ተደርጓል፡፡ አብዛኛው ተማሪም ፒቲሺን ፈርሞ ይቅርታ ጠይቋል፡፡

እንደ ዶክተር ለሚ ገለጻ፤ ተማሪዎች ከጊቢ ውጭ በነበሩበት ጊዜ ከዩኒቨርሲቲው በቅርብ ርቀት ያሉ ወላጆችን በማወያየት ቤተሰብም ያላቸውን ጥያቄዎች አንስተው መልስ ተሰጥቶ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ በዚህም ተማሪዎቹ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እድል እንዲሰጣቸውና የሴሚስተር ቅጣቱ ቀርቶላቸው፤ አጥፊ ተማሪዎች ግን ተለይተው እርምጃ እንዲወሰድና ሌሎች ተማሪዎች በይቅርታ እንዲመለሱ መስማማት ተችሏል፡፡ ቤተሰብም ልጆቻቸውን እንደሚመክሩ ቃል ገብተው በሄዱት መሰረት የሴሚስተሩ ቅጣት በሴኔቱ ውሳኔ መሰረት እንደገና ተነስቶላቸው ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡

እንደ ዶክተር ለሚ ገለጻ፤ ከወላጆች ጋር በነበረው ውይይት ልጆቻችን ትምህርት እንዳይገቡ የሚያስፈራሩ አካላት አሉ፤ በጥቂት ተማሪዎች ተጽዕኖ ስር ወድቀዋልናም እርምጃ ሊወሰድ ይገባል የሚል ጥያቄ ከወላጆች ቀርቦ ነበር፡፡ ይሄንና ሌሎች መረጃዎችን መነሻ በማድረግም እርምጃ መውሰድ የተጀመረ ሲሆን፤ አጥፊና አስተባባሪ የሚባሉ ተማሪዎችን ለይቶ ለዲስፕሊን የማቅረብ ስራ እንዲከናወን፤ ከአካዳሚክ ስታፉም ሆነ ከአስተዳደር አካሉ በዚህ ላይ የተሳተፈ ፤ ተማሪዎች ወደክፍል እንዳይሄዱ የሚመክርና የሚያስተባብር ካለ፤ እነዚህን ለይቶ እርምጃ እንዲወሰድ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡ ይህ የእርምጃና የልየታ ስራ ተጠናቅቆ 25 ተማሪዎች የዲሲፕሊን ቅጣት ተጥሎባቸዋል፡፡ 5 የአካዳሚክ ስታፍና 9 የአስተዳደር ስታፍ አባላትም ተለይተው ለዲስፕሊን እንዲቀርቡ እየተደረገ ሲሆን፤ ተጨማሪ መረጃዎችን የማሰባሰብ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል፡፡

ከዚህ በኋላ ሰኞ እና ማክሰኞን ዳግም ምዝገባው ተካሂዶ ዕረቡ ዕለት ትምህርት መጀመሩን የገለጹት ዶክተር ለሚ፤ መመዝገብ ከሚገባቸው ተማሪዎች ውስጥ 93ነጥብ5 በመቶዎቹ ተመዝግበው ትምህርታቸውን መከታተል እንደቻሉና፣ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱም ጥሩ በሚባል ደረጃ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡ ቀሪዎቹም በተመሳሳይ ተመዝግበው ትምህርታቸውን እንደሚጀምሩ ያላቸውን እምነት በመጠቆምም፤ ተማሪዎች ባለው ጊዜ ውስጥ የሁለቱንም ሴሚስተር ትምህርት እንዲከታተሉ በሚያስችል መልኩ የትምህርት መርሃ ግብሩ እንደሚከለስም ገልጸዋል፡፡

ይሁን እንጂ አሁንም የዲስፕሊን እርምጃ የተወሰደባቸው ተማሪዎች ካልተመለሱ ክፍል አንገባም የሚሉ ጥቂት ተማሪዎች መኖራቸውን የጠቆሙት ፕሬዚዳንቱ፤ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲመጡ ዓላማቸው መማር እንደመሆነና ወክለው የመጡትም ራሳቸውን መሆኑን ተገንዝበው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ መክረዋል፤ ይሄን የሚያራምዱ ጥቂት ተማሪዎችም ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አሳስበዋል፡፡ ሆኖም ይሄን በመዘንጋት ዳግም ወደሌላ ችግር ለመግባት የሚታትሩ ተማሪዎች ካሉ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ ወላጆችም ይሄን ተገንዝበው ልጆቻቸውን ሊመክሩና መስመር ሊያሲይዙ እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡

እንደ ዶክተር ለሚ ገለጻ፤ ተማሪዎች ጥያቄ ማንሳትና ጥያቄዎቻቸውን በሕግና በስርዓት ለሚመለከታቸው አካላት አቅርበው መልስ የማግኘት መብታቸው ነው፡፡ ይሄን ሲያደርጉ ግን እየተማሩና የመጡበትን ዓላማ እየከወኑ መሆን እንዳለበት መረዳት አለባቸው፡፡ በዚህ ላይም ሁሉም አካል የድርሻውን መወጣት ያለበት ሲሆን፤ በተለይ ቤተሰብ ከፍተኛ ሚና ይጠበቅበታል፡፡ ምክንያቱም ወላጅ ልጁን ልኮ መቀመጥ ብቻ ሳይሆን የልጁን የትምህርት አቅምና ባህሪ በተለያየ አግባብ መከታተል ይኖርበታል፡፡ ዩኒቨርሲቲውም የመማር ማስተማር ሂደቱን ሰላማዊ ለማድረግ እና የተማሪዎችን ባህሪና ስነምግባር ለመከታተል የሚያስችሉ የተለያዩ ሰነዶች የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችን ልምድ በመውሰድ ተዘጋጅተዋል፤ አሰራሮችም ተዘርግተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም አስካሁን ከመልካም አስተዳደር ችግር ጋር የተገናኙ ጥያቄዎች ባይኖሩም፤ ለወደፊት መልኩን ቀይሮ ችግሩ እንዳይመጣ በዩኒቨርሲቲው አጠቃላይ ከአገልግሎት አሰጣጥ፣ ከጸጥታም ሆነ ሌሎች የመልካም አስተዳደር ችግሮች ካሉም እየተፈተሹ ክፍተቶች እንዳይኖሩ እየተሰራ ነው፡፡ ለአብነት ከጊቢ ጸጥታ ጋር በተያያዘ የጊቢውን ደህንነት ከማስጠበቅ አኳያ ወደ 200 የሚሆኑ የጸጥታ ሰራተኞቹን ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር ጠንካራ ስልጠና እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡ በመሆኑም በዩኒቨርሲቲው ከመምህራን ባሻገር ከተማሪዎች ጋር በቅርበት የሚሰሩ ፕሮክተሮች፣ የሕክምና ባለሙያዎች፣ የላይበራሪ አገልግሎት የሚሰጡና ሌሎችም አካላት ጋርም ሰፊ ውይይትና ግምገማ ተደርጎ ሃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸውም ተቀምጧል፡፡

ተማሪዎችን ለማነጽ ዋናው ጉዳይም በጭንቅላት ላይ መስራት እንደመሆኑ አነቃቂ ንግግሮችና ስልጠናዎችን እንዲያገኙ እየተደረገ ሲሆን፤ ባለፈው ሳምንት ወደ 600 ለሚሆኑ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች የቦርድ ሰብሳቢው አነቃቂ ንግግር አቅርበውላቸዋል፡፡ ለቀጣይ ቅዳሜም ዶክተር ምህረት ደበበ ተጋብዘዋል፡፡ ይሄን መሰል ሥራ ቀጣይነት ባለው መልኩ የሚሰራ ሲሆን፤ ተማሪውና ማህበረሰቡ እንዲዋሃድ፣ አንዱም አንዱን እንዲረዳ የሚደረግ ይሆናል፡፡

ምንጭ፦ አዲስ ዘመን ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ልዑክ በኢትዮጵያ የሚያደርገውን ጉብኝት ለመጀመር በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ የሚገባ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። የጉብኝቱ አላማ የሀገራቱን ታሪካዊ ግንኙነት እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ለማጠናከር ነው ተብሏል። የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ልዑኩ በኢትዮጵያ በሚኖረው ቆያታ በተለያዩ ዝግጅትቶች ተሳታፊ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። በዚህም ልዑኩ የፊታችን የካቲት 9 ቀን ባህርዳር፣ የካቲት 10 በአዳማ፣ የካቲት 12 በሀዋሳ እና የካቲት 14 ደግሞ በአዲስ አበባ ከተሞች በሚካሄዱ ባህላዊ #የሙዚቃ_ኮንሰርቶች ተሳታፊ ይሆናል ተብሏል። ለዚህ ባህላዊ የሙዚቃ ኮንሰርትም #ሁሉም ኢትዮጵያዊና ኤርትራዊያን ተሳታፊ እንዲሆኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥሪ አቅርቧል። በሚቀጥለው ወርም የሁለቱ ሀገራትን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ይበልጥ  ለማጠናከር የኢትዮጵያ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ልዑክ  ወደ ኤርትራ የሚያቀና መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia