TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
‹‹በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ከ80 ሺህ በላይ ዜጎች #ተፈናቅለዋል፡፡›› የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት
.
.
የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዛሬ በሠጠው መግለጫ ተፈናቃዮችን ለመርዳት ክልሉ 35 ሚሊየን ብር በመመደብ ድጋፍ ሲደረግ ቢቆይም አሁን ላይ ያለውን ችግር ሙሉ በሙሉ ለመቋቋም ከክልሉ መንግሥት አቅም በላይ እንደሆነ ገልጻል፡፡

ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ ችግሮች ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው #ተፈናቅለዋል፡፡ በአማራ ክልልም ከክልሉ ውስጥና በሌሎች ክልሎች የሚኖሩ ከ80 ሺህ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን የክልሉ መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ አድርጓል፡፡

የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ.ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አሰማኸኝ አስረስ እንዳሉት ከክልሉ ውጭ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ከኦሮሚያና ከሶማሌ ክልሎች እንዲሁም በክልሉ ውስጥ ደግሞ በተለይም በማዕከላዊ እና በምዕራብ ጎንደር አካባቢዎች ዜጎች በስፋት ተፈናቅለዋል፡፡

የመፈናቀል አደጋው ከተከሰተበት በተለይም ከሕዳር ወር ጀምሮ የክልሉ እና የፌዴራል መንግሥት በጋራ ተፈናቃዮችን በጊዜያዊና በዘላቂነት ለማቋቋም 35 ሚሊየን ብር በመመደብ ድጋፍ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ያስታወሱት አቶ አሰማኸኝ ‹‹አሁን ላይ ያለውን ችግር ሙሉ በሙሉ ለመቋቋም ከክልሉ መንግሥት አቅም በላይ ሆኗል›› ብለዋል፡፡

ተፈናቃዮቹ ለሰፋ ማኅበራዊ፣ ምጣኔ ሀብታዊ እና ሥነ ልቦናዊ ችግሮች በመጋለጣቸው ዘላቂ ድጋፍ እና እንክብካቤ እንደሚያስፈልጋቸው ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል፡፡ ይህንንም ለማድረግ የክልሉ መንግሥት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የሚመራ ግብረ ኃይል አቋቁሞ ድጋፍ የማሰባሰብ ሥራ መጀመሩን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፤ ‹‹ድጋፉ በተደራጀ እና በአንድ አግባብ እንዲሆን ይፈለጋል›› ሲሉም አሳበዋል፡፡

የሚደረገው ድጋፍ በገንዘብ፣ በዓይነት እና በዕውቀት ሊሆን እንደሚችል ያስረዱት አቶ አሰማኸኝ ከዚህ ቀደም ድጋፍ ያደረጉ አካላትን በማመስገን በተከፈተው የሒሳብ ቁጥር ሕዝቡ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

#የገንዘብ_ድጋፍ ማድረግ ለሚፈልጉ አካላት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የአደጋ መከላከል ፕሮግራሞችና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ማስተባበሪያ ኮሚሽን የባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000258250811 እንዲሁም በዓይነት ድጋፍ ለማድረግ ለሚፈልጉ አካላት በስልክ ቁጥሮች 0582180196፣ 0582181096፣ 0582181151፣ 0918701136፣ 0918340128 ወይም 0953600333 በመደወል መረጃ ማግኘት እንደሚቻል አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ🔝#የመከላከያ_ቀንን አስመልከቶ ዛሬ #በአዳማ ከተማ የተካሄደው የፓናል ውይይት!!

ፎቶ:- ሀዱሽ አብርሃ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ውድ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት...

የት ነው የምትኖሩት?? አካባቢያችሁ፤ ከተማችሁ ውስጥ ምን አይነት ተፈጥሯዊ ወይም ሰው ሰራሽ መስዕብ አለ?? እናተ ያያችሁት የኢትዮጵያ ድንቅ ቦታዎች ሌሎች እንዲያዩት የምትጠቁሙት ይኖር ይሆን??

• 4 ምርጥ ፎቶዎችን ከአካባቢው ስም ጋር አድርጋችሁ በመላክ የምትኖሩበትን አስተዋውቁን። የሀገር ውስጥ እና የውጭ #ቱሪስቶችን ወደ አካባቢያችሁ ጋብዙ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከስልጤ ዞን...

"ስልጤ ገርቤ በር የተጎዱ በርካታ #ፖሊሶች ጦራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልም መተዋል፡፡ እዛው ነው ምሰራው!"

#ቲክቫህኢትዮጵያ #tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኮ/ሌ በዛብህ ጉዳይ...‼️

(ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት)

"ኮ/ል በዛብህ ጴጥሮስን ሰኔ ላይ ኤርትራ ውስጥ በአካል አግኝቻቸዋለሁ። በመጪው ሰኔ ላይ እንደሚፈቱ መረጃ አለኝ" -- ኢንጅነር #ታደሰ

"እኔ ምንም መረጃ የለኝም። በግሌ የተሻለ (more powerful) የሆኑ መንገዶችን ሄጄ #ማረጋገጫ ያጣሁበት ጉዳይ ነው"-- ፕ/ር #በየነ_ጴጥሮስ
.
.
ኢንጅነር ታደሰ ይባላሉ። ባለፈው ሰኔ ወር ላይ ወደ ኤርትራ ተጉዘው እንደነበር እና በቆይታቸው ወቅትም በኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት ወቅት የሚያበሩት ጀት ተመትቶ የተማረኩትን ኢትዮጵያዊውን ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስን እንዳገኟቸው ለጋዜጠኛ #አልያስ_መሰረት ተናግረዋል፤ አክለውም "በአሁን ሰአት እንደ ሌሎች የጦር ምርኮኞች በቀይ መስቀል ስር ይገኛሉ። እኔም እዛ አግኝቻቸዋለሁ። ትንሽ ከእድሜ መግፋት ውጪ በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛሉ። ሰኔ ወር ሲመጣ እንደሚፈቱ መረጃ አለኝ። ዝርዝሩን የመንግስት ሰዎች ያውቃሉ" ብለዋል።

የኮ/ሌ በዛብህ ጴጥሮስ ታላቅ ወንድም ወደሆኑት ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ስለጉዳዩ በሰጡት ምላሽ፦ "እኛ ይህ መረጃ የለንም። እኚህ ያልካቸው ግለሰብ እንዴት access ሊኖራቸው እንደቻለ አላውቅም። በግሌ የተሻለ (more powerful) የሆኑ መንገዶችን ሄጄ ማረጋገጫ ያጣሁበት ጉዳይ ነው። ወንድሜ በህይወት አለ ወይስ የለም የሚለውን ለማረጋገጥ እንኳን ካደረግነው ጥረት አንፃር ሲታይ የዚህ ሰውዬ መረጃ በጣም extreme ነው። በኤርትራ በኩል ያለው ሁኔታ ሲጠቃለል በኮሎኔል በዛብህ ዙርያ መነጋገር አንፈልግም የሚል ነው። ከዚያም አልፎ ጉዳዩን sensitive አርጎ መናደድ አለ። እኛን አትጠይቁን አይነት ነገር ነው ያየነው። በህይወት ተይዞ የአስመራ መንገዶች ላይ parade የተደረገ ሰው ነው። የኛ አቋም ህይወቱ አልፏል ከተባለ ታውቃላችሁ እና አካሉ የት ነው እያልን ነው። ግን ይህንን ጉዳይ መወያየት አይፈልጉም። ከኢትዮጵያ መንግስት ወገን ደሞ አሁን የተጀመረውን ንግግር ያበላሽብናል የሚል ነገር አለ። ለማንኛውም ያልካቸውን ሰውዬ አገናኘኝ። ይህ ለኛ ትልቅ development ነው።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሰዎች ሕይወት ላይ እየደረሰ ያለው በደል እንዲቆም ምህላ እና ዱዓ እየተደረገ ነው። ምህላው እና ዱዓው እየተደረገ ያለው በምዕራብ እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች በተፈጠረው ግጭት ምክንያት በሰዎች ሕይወት እየደረሰ ያለው ጉዳት ምሕረት እንዲያገኝ ነው፡፡ በጎንደር ከተማ የሚገኙ የኦርቶዶክስ እና የእስልምና ሃይማኖት አባቶች በሁለቱ ዞኖች እየተስተዋለ ያለውን የሰዎች ሕልፈተ ሕይወት፣ መፈናቀል እና የንብረት ውድመት አውግዘዋል።

Via አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለመምህራን...‼️

የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል የሆናችሁ በሺዎች የምትቆጠሩ የመጀመሪያ ደረጃ፤ የሁለተኛ ደረጃ፤ እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን እንዳላችሁ ይታወቃል።

ጥያቄያችን፦ ከቀለም ትምህርቱ ጎን በክፍል ውስጥ ለተማሪዎቻችሁ #ስለሰብዓዊነት፣ ስለሀገር ፍቅር፣ ስለአንድነት፣ ስለመከባበር ትነግሯቸዋላችሁ?? ከተማሪዎች ጋር ቀርባችሁ ትነጋገራላችሁ?? ወይስ አስተምሮ ብቻ መውጣት ነው?? ተማሪዎች ቀኑን ሙሉ አብረዋችሁ እንደሚውሉ አታውቁም?? ትልቅ የአስተሳሰብ ለውጥ ለመፍጠር ምን ሰራችሁ?

•መምህራን በሀገር #ሰላም እና #እድገት ላይ ያላችሁ ድርሻ እጅግ በጣም ትልቅ ሊሆን ይገባል።

አስተያየት መስጠት ይቻላል @tsegabwolde

#ቲክቫህኢትዮጵያ #tikvahethiopia
#update የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ‹‹የሩሲያው ፕሬዝዳንት #ቪላድሚር_ፑቲን ዴሞክራሲ እንዳይዳብር በዓለም አቀፍ ደረጃ ስጋት ሆነዋል›› አሉ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ መካከለኛው አውሮፓን እየጎበኙ በሚገኙበት ወቅት ቻይናንም የአውሮፓን ፖለቲካ በፈለገችው መንገድ እየመራች ነው ሲሉ ወርፈዋል፡፡ በአውሮፓ የቻይናን እና የሩሲያን ፖለቲካዊ ተፅዕኖ መቀነስ ዒላማ ያደረገ ንግግርም አድርገዋል፡፡

ምንጭ፦ አልጀዚራ
@tsegabwolde @tikvahethiopia