TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
መከላለያ ሰራዊት🔝

የሀገር መከላከያ ሰራዊት በሀላይደጌ አሰቦት ዕጩ ብሄራዊ ፓርክ ውስጥ #ልምምድ ማድረግ በመጀመሩ የፓርኩ ስነ-ምህዳር መናጋቱን የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣ አስታወቀ።

ችግሩ የተፈጠረው የመከላከያ ሚኒስቴር ዓመታዊውን የመከላከያ ሰራዊት ቀን በፓርኩ ውስጥ ለማክበር በመወሰኑ ነው። የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ድርጊቱን ለማስቆም በርካታ ሙከራዎችን ቢያደርግም #አለመሳካቱን ገልጿል።

በታንክ፤ በመድፍ፤ በጄት እንዲሁም በሄሊኮፕተር ተኩስና ትርዒት የታጀበ ልምምድ የሚካሄድበት አካባቢ የግሬቪ ዜብራ፤ የሳላ፤ የሜዳ ፍየል፤ የተለያዩ አዕዋፋት እና የሰጎኖች ዋና መኖሪያ መሆኑን ባለስልጣኑ አስታውቋል።

ሰራዊቱ በመጭው እሁድ ከፍተኛ ድምፅ የሚያስተጋቡ የጦር መሳሪያዎችን በመጠቀም የተኩስ ትርዒት የሚያሳይ በመሆኑ በፓርኩ ስነምህዳር ላይ ከፍተኛ ችግር ይፈጠራል ያለው ባለስልጣኑ፣ መከላከያ ሚንስትር ለሚደርሰው ጉዳት #ሀላፊነት ይወስዳል ብሏል።

Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia