መከላለያ ሰራዊት🔝
የሀገር መከላከያ ሰራዊት በሀላይደጌ አሰቦት ዕጩ ብሄራዊ ፓርክ ውስጥ #ልምምድ ማድረግ በመጀመሩ የፓርኩ ስነ-ምህዳር መናጋቱን የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣ አስታወቀ።
ችግሩ የተፈጠረው የመከላከያ ሚኒስቴር ዓመታዊውን የመከላከያ ሰራዊት ቀን በፓርኩ ውስጥ ለማክበር በመወሰኑ ነው። የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ድርጊቱን ለማስቆም በርካታ ሙከራዎችን ቢያደርግም #አለመሳካቱን ገልጿል።
በታንክ፤ በመድፍ፤ በጄት እንዲሁም በሄሊኮፕተር ተኩስና ትርዒት የታጀበ ልምምድ የሚካሄድበት አካባቢ የግሬቪ ዜብራ፤ የሳላ፤ የሜዳ ፍየል፤ የተለያዩ አዕዋፋት እና የሰጎኖች ዋና መኖሪያ መሆኑን ባለስልጣኑ አስታውቋል።
ሰራዊቱ በመጭው እሁድ ከፍተኛ ድምፅ የሚያስተጋቡ የጦር መሳሪያዎችን በመጠቀም የተኩስ ትርዒት የሚያሳይ በመሆኑ በፓርኩ ስነምህዳር ላይ ከፍተኛ ችግር ይፈጠራል ያለው ባለስልጣኑ፣ መከላከያ ሚንስትር ለሚደርሰው ጉዳት #ሀላፊነት ይወስዳል ብሏል።
Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia

አምቦ ዩኒቨርሲቲ!
#የአምቦ_ዩኒቨርሲቲ በሎሬት #ፀጋዬ_ገብረመድህን ስም የባህል ማዕከል እንደሚያቋቁም አስታውቋል። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር #ታደሰ_ቀነዓ ለኢዜአ እንደገለጹት ማዕከሉ የሚቋቋመው የሎሬቱን ጨምሮ በኪነ ጥበብ ሥራዎች ላይ ጥናትና ምርምር ለማድረግና ተሰጥኦ ያላቸውን ጠቢባን ለማፍራት ነው።
“ማእከሉን ለሟቋቋም ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ሥራ ተገብቷል” ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ ማዕከሉን ለማቋቋም ከአዲስ አበባ፣ ከባህር ዳርና ከደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲዎች ልምድ ቀስሟል ብለዋል።
ከሎሬት ጸጋዬ ወጥ ሥራዎች መካከል የአቴቴ ሥርዓት፣ የገዳ ሥርዓት፣ ዝክረ መርካቶ፣የኩሽ ሕዝቦች ሥልጣኔ፣ዳግማዊ ቴዎድሮስ፣ ኦዳና አቡነ ጴጥሮስን የሚዘክሩት ተጠቃሽ ናቸው።
ከትርጉም ሥራዎቻቸው መካከል የዊሊያም ሼክስፒር ድርሰቶች ሃምሌትና ኦቴሎ ዘመን ተሻጋሪ ሥራዎች ይገኙበታል።
#የአምቦ_አካባቢ_ተወላጅ የሆኑት ሎሬት ፀጋዬ በ60 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም የተለዩት በ1998 ነበር።
ምንጭ፦ ኢዜአ

እንጠንቀቅ!!
#ኢትዮጵያ መስቀለኛ መንገድ ላይ ነች። ትንሽ ስህተት ሁላችንም ወደ #እልቂት ስለሚወስደን ከተቻለን #እንጠንቀቅ ካልሆነም በየቦታው እየገቡ ከመቀባጠር #እንቆጠብ!! ሁለት ህይወት የለም!! ኢትዮጵያ ከጥይት እሩምታ፤ ከቦንብ ፍንዳታ፤ ከእርስ በእርስ ግጭት #ብትርቅ የምትጠቀመው አንተ እና ምስኪን ትንንሽ ልጆችህ ናቸው!! ለራስህ ስትል ስለሰላም ሌት ተቀን ዘምር!! ኮሽ ሲል በቦሌ አድርጎ ከሀገር ከሚወጣ ሰው ጋር ህብረት ፈጥረህ ከወንድምህ እንዳትጣላ፤ እሳቱ ሚበላው አንተን ነውና!!
#የሰላም #የፍቅር #የአንድነት ቀን ይሁንልን!
#TikvahETHIOPIA #ቲክቫህኢትዮጵያ

#update ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ኢስተርን ኢንዱስትሪያል ዞንን ከጊኒው ፕሬዝደንት አልፋ ኮንዴ ጋር ጎበኙ። በጉብኝቱ ወቅት የኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና የኢንዱስትሪ ፓርኩ ኃላፊዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በገለፃውም ከ15 ሽህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሯል፤ በቀጣይ ይህንን እጥፍ ለማድረግ የማስፋፊያ ስራ እንደሚሰራ ተጠቅሷል፡፡ ከጊኒው ፕሬዝደንት ጋር የመጡ የልዑካን ቡድኑ አባላት ከኢንዱስትሪ ፓርኩ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ትልቅ ትምህርት እንደቀሰሙ ተናግረዋል፡፡
Via President Office
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via President Office
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጥረት ኮርፖሬት የቀድሞ አመራሮች‼️
የባህር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት በጥረት ኮርፖሬት የቀድሞ ከፍተኛ አመራሮች ላይ ከክልሉ የስነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን በቀረበው ጥያቄ መሰረት የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቀደ።
ፍርድ ቤቱ ዛሬ በዋለው ችሎት አቶ በረከት ስምኦን ኮሚሽኑ ያቀረበው ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮን በመቃወም የተጠረጠሩበትን ወንጀል ለይቶ እንዲያቀርብላቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።
ተጠርጣሪዎቹ የጥረት ኮርፖሬት የአክሲዮን ድርሻ ሽያጭ በህገ-ወጥ ፈፅመዋል ለተባለው በጥረት የመመስረቻ ደንብ መሰረት ያልተብራራ በመሆኑ ወንጀል ያልሆነን ጉዳይ ወንጀል እንደሆነ አድርጎ ማቅረብ እንደማይገባም ተናግረዋል።
አሁን ካለው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞም በአካባቢው የህግ ባለሙያ ለማቆም መቸገራቸውን ጠቅሰው የፍርድ ሒደቱ ሰብዓዊ መብታቸውን በማይጋፋ መልኩ እንዲካሔድ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።
የክልሉ ስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽንም የመያዝና የመክሰስ ህገ-መንግስታዊ መብት የሌለው በመሆኑ ፍርድ ቤቱ በኮሚሽኑ የተጠየቀውን የ14 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ ውድቅ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል።
የቀድሞው የጥረት ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታደሰ ካሳ በበኩላቸው “መንግስት ሳናጣራ አናስርም እያለ ፈፅሟችኋል የተባልነውን ወንጀል ሳያጣራ ጠርጥሮ ማሰሩ ተገቢ አይደለም” ሲሉ ተከራክረዋል።
የዳሽን ቢራ ፋብሪካ ጉዳይ በፌዴራል ደረጃ የተመዘገበ በመሆኑ መታየት ያለበት በክልሉ ሳይሆን በፌዴራል ደረጃ ሊሆን ይገባል በማለት ለፍርድ ቤቱ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
የክልሉ ስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ወንጀል መርማሪ በበኩሉ አቶ በረከት ተጠርጥረው የተያዙበት ምክንያት ፍርድ ቤት ሲቀርቡ እንደተገለጸላቸው በማስታወስ ዝርዝር ጉዳዩ ምርመራው ተጠናቆ ክስ ሲመሰረት በመደበኛ የፍርድ ሒደት እንደሚታይ አስረድተዋል።
ግለሰቦቹ የተጠረጠሩበት ወንጀል በመንግስታዊ ድርጅት ላይ ከባድ ጉዳት ማድረስ፣ የህዝባዊ ድርጅት ስራን በማያመች አኳኋን መምራትና ከባድ ጉዳት በማድረስ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው መሆኑንም ገልጸዋል።
ኮሚሽኑ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር የማዋሉ ጉዳይም ድርጅቱ ህዝባዊ በመሆኑ ለማየት የሚከለክለው የህግ አግባብ እንደሌለም ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።
በቀጣይ ከሚያከናውናቸው ቀሪ ስራዎች ውስጥ የዳሽን ቢራ ፋብሪካ ዱየት ቫሳሪ ለተባለ ኩባንያ ከ50 በመቶ በላይ ድርሻ የተሸጠበት ሰነድ ተጠርጣሪዎቹ ሲመሩት በነበረ ተቋም ባለመገኘቱ የምርመራ ስራውን ውስብስብ እንደሚያደርገውም ጠቁመዋል።
ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የሚያስረዱ ሰነዶችና የሰው ምስክሮች በተለያየ ቦታ የሚገኙ በመሆናቸውና፣ የዳሽን ቢራ ፋብሪካ ከሽያጭ ጀምሮ የተከናወኑ ተግባራት ኦዲት እየተደረገ በመሆኑ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተጠይቋል።
ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ካዳመጠ በኋላ የክልሉ ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የጠየቀውን ተጨማሪ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ በመፍቀድ ለየካቲት 15/2011 ዓ.ም እንዲቀርቡ ወስኗል።
Via ENA

ኢንጅነር ታከለ ኡማ‼️
ኢንጅነር #ታከለ_ኡማ በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ በተባለ ተቋም የአፍሪካ ከንቲባዎች እና መሪዎች አለም አቀፍ ትብብር የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና አስተባባሪ ሆነው ተመረጡ፡፡
ኢንጅነር ታከለ ኡማ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እየሰሩት ባለው የልማትና መልካም አስተዳደርን የማስፈን ስራዎች እና የጎዳና ላይ ልጆችን በዘላቂነት ለማቋቋም እየሰሩ ባለው ስራ የአፍሪካ የከንቲባዎች እና መሪዎች አለምአቀፍ ትብብር የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና አስተባባሪ ሆነው እንዲመረጡ እንዳስቻላቸው የተቋሙ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጂብሪል ዲያሎ አስታውቀዋል፡፡
ተቋሙ በቀጣይነት ኢትዮጵያ የተያያዘችውን የለውጥ ጉዞ እንደሚደግፍ ፕሬዚዳንቱ ገልፀዋል፡፡
በኢትዮጵያ እና አሜሪካ ያሉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን በማጣመር ወጣት የከተማዋ ነዋሪዎች የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ እንደሚንቀሳቀስ መናገራቸውን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ምንጭ፦ @mayorofficeAA (ትክክለኛ የከንቲባ ፅ/ቤት የቴሌግራም ቻናል።

#UpdateSport የቀድሞው የአርሰናል ክለብ አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር በሚቀጥለው ወር በአሰልጣኝነት ወይም የእግር ኳስ ዳይሬክተር በመሆን ወደ እግር ኳስ ስራቸው ሊመለሱ መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡ አርሰናልን ለ22 አመታት ያሰለጠኑት ፈረንሳዊው አርሰን ቬንገር ሶስት የፕሪሚየር ዋንጫ ካሸነፉበት የሰሜን ለንደኑ ክለብ ጋር የውድድር አመቱ ከመጀመሩ በፊት መለያየታቸው ይታወሳል፡፡ እንደ ዘ ታይምስ ዘገባ አርሰን ቬንገር ከአራት ያላነሱ የቅጥር ጥያቄዎች የደረሷቸው ሲሆን ሁሉም ግን ከእንግሊዝ ክለቦች ውጪ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ አሰልጣኙ ከሁለት አስርት አመታት በላይ ለመሩት አርሰናል ካላቸው ክብር የተነሳ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሚጫወት ተቃራኒ ክለብ ማሰልጠን አይፈለጉም ነው የተባለው፡፡ የፈረንሳዩ ፓሪስ ሴንት ጀርሜን ክለብ ከፖርቹጋላዊው የፓስ ሴንት ክለብ የእግር ኳስ ዳይሬክተር አንቴሮ ሄኔሪኬ ጋር መለያየቱን ተከትሎ አርሰን ቬንገርን ለቦታው እንደሚፈልገው ነው የተጠቆመው፡፡ ከፓሪሱ ክለብ ውጪ አንድ ስሙ ያልተገለፀ ብሄራዊ ቡድንም የአንጋፋውን አሰልጣኝ ግልጋሎት እንደሚፈልግ ታውቅል፡፡ አርሰን ቬንገር ለማራኪ እግር ኳስ ካላቸው ፍልስፍና ባየር ሙኒክ፤ኤሲ ሚላን እና ሪያል ማድሪድ በመሳሰሉ ታላላቅ የአውሮፓ ክለቦች ጋር ስማቸው ሲያያዝ እንደነበር ይታወሳል፡፡
ምንጭ፦ ዘ ታይምስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ ዘ ታይምስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጎንደር~አዘዞ‼️
በጎንደር ከተማ አዘዞ አካባቢ 50 በላይ እንስሳት ላይ የቃጠሎ አደጋ ማጋጠሙን የዓይን ምሥክሮች እና ፖሊስ ተናገሩ፡፡
በማዕከላዊ ጎንደር ነዋሪ የሆኑ የዓይን ምሥክሮች እንደተናገሩት ትናንት ምሽት በጎንደር ከተማ አስተዳደር አዘዞ አካባቢ ልዩ ሥሙ ግራር ሰፈር በሚባል ቦታ በእንስሳት ማድለቢያ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ 60 የሚደርሱ የደለቡ ከብቶች ተቃጥለዋል፤ በጣት የሚቆጠሩ ከብቶችን ብቻ በሕዝቡ ጥረት ማትረፍ ተችሏል፡፡
የዓይን ምሥክሮቹ እሳቱን ለመቆጣጠር የአካባቢው ነዋሪና የጎንደር ከተማ አስተዳደር ጥረት ቢያደረጉም መቆጣጠር የተቻለው በዳግማዊ ቴዎድሮስ አየር ማረፊያ የእሳት አደጋ መከላከያ ተሽከርካሪና ሠራተኞች እገዛ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡
የዓይን ምሥክሮቹ አደጋውን ማን እንዳደረሰው በግልጽ ባይታወቅም ከሰሞኑ የአካባቢው ግጭት ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ ግን እርግጠኛ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡
ሌሊቱን በአዘዞ አካባቢ ተኩስ እንደነበር ያስረዱት የዓይን ምሥክሮቹ ‹‹ተኩሱ ግን እሳቱን ለመቆጣጠር እንዲቻል ጥሪ ለማስተላለፍ ያለመ ነበር›› ነው ያሉት፡፡ በእሳት አደጋው በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን ገልጸው በብድር ገንዘብ ተደራጅተው በከብት ማድለብ የተሠማሩ ወጣቶችን ለፖለቲካ ጥቅም መጉዳት ተገቢ እንዳልነበር ተናግረዋል፤ መንግሥት በአፋጣኝ ወንጀለኞችን ለሕግ እንዲያቀርብም አሳስበዋል፡፡
በጎንደር ከተማ አስተዳደር የ5ኛ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ባለሙያ ምክትል ሳጅን ሙሐመድ ሰይድ ደግሞ ምሽት 5፡00 አካባቢ እሳት ቃጠሎው መነሳቱን አስታውሰው በማድለቢያና እንስሳት እርባታ ድርጅት ላይ በደረሰ ቃጠሎ 51 የቁም ከብቶች መሞታቸውን እንዳረጋገጡ ተናግረዋል፡፡ ምን ያክል ከብቶች እንደተረፉ ግን ማረጋገጫ እንደሌላቸው ነው መርማሪው ለአብመድ የተናገሩት፡፡
ቃጠሎው በደረሰበት አካባቢ የእንስሳት መኖ መኖሩ ለቃጠሎው መባባስ አስተዋጽኦ ማድረጉን የገለጹት ምክትል ሳጅን ሙሐመድ ‹‹የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ የምርመራ ሂደቱ እንደቀጠለ ነው፤ ወደፊት ውጤት ላይ ስንደርስ ለሕዝብ እናሳውቃለን›› ብለዋል፡፡ በአካባቢው ለእሳት መነሳት ምክንያት የሚሆን ተፈጥሯዊ ምክንያት እንዳልነበረ ግን ባለሙያው አስታውቀዋል፡፡
ድርጊቱን የፈጸሙ አካላትን በተመለከተ መረጃ መስጠት የሚፈልግ ሁሉ ለፖሊስ ጣቢያው ጥቆማ እንዲሰጥም አሳስበዋል፡፡
ምንጭ፦ አብመድ

ቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል🔝የአለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም በአሁን ሰዓት በቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ተገኝተው ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ።
ፎቶ፦ ትዕግስት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ፦ ትዕግስት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት‼️
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መንግስት ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጋር የተፈራረመውን የኢትዮጵያውያን የስራ ስምሪት መግባቢያ ሰነድ #አፀደቀ፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው ሶስተኛ ልዩ ስብሰባው መንግስት ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጋር የተፈራረመውን የኢትዮጵያውያን የስራ ስምሪት መግባቢያ ሰነድ በአብላጫ ድምጽና በ26 ተቃውሞ አፅድቆታል፡፡
የመግባቢያ ሰነዱ 20 አንቀጾች ያሉት ሲሆን በኤምሬቶች ህግ መሰረት በቤት ውስጥ አገልግሎት ምድብ ውስጥ በሚገኙ ስራዎች እንዲሁም በግሉ ዘርፍ ለስራ የሚሰማሩ ሰራተኞችን ያካተተ ስምምነት ነው፡፡
በስምምነቱ መሰረት የሰራተኞች ምልመላና ስምሪት የሀገሪቱን ህግ ያከበረ እንዲሆን የማድረግ፣ የሰራተኞች መብትና ደህንነት እንዲጠበቅ እና ሰራተኞች ለጉልበት #ብዝበዛ እንዳይጋለጡ የማድረግ፣ ለስራ ውሎች የህግ እውቅና እና ተፈጻሚነት የመስጠት፣ ሰራተኞች ገቢያቸውን ወደ ሀገራቸው እንዲልኩ ማስቻል የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ግዴታ እንደተጣለበት በስምምነቱ ተጠቁሟል፡፡
ምንጭ፦ ኢፕድ

የአዲስ አበባ ከተማ ውሃና ፍሳሽ‼️
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን #በአፍሪካ_ህብረት የመሪዎች ስብሰባ የውሃ ችግር እንዳይከሰት ልዩ ኮማንድ ፖስት አቋቁሞ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።
ባለስልጣኑ መሪዎቹ ስብሰባ የሚያካሂዱበትን አካባቢ ጨምሮ ያርፉባቸዋል ተብለው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተለዩ 56 ሆቴሎች ውሃ በአግባቡ እንዲደርስ እየሰራ መሆኑን፥ የባለስልጣኑ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች የስራ ሂደት መሪ ወይዘሮ #ሰርካለም_ጌታቸው ተናግረዋል።
ኤፍ ቢ ሲ እንደዘገበው ይህ ስራም ከአቃቂ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ውጭ በሁሉም ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች የሆቴሎቹን ዝርዝር በመበተን ከጥር 15 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ እየተሰራ መሆኑንም ነው የተናገሩት።
በዚህ ሂደትም ሆቴሎቹ ውሃ የሚያገኙበትን መስመር የመፈተሽና ሲቋረጥ ያላቸውን የውሃ መጠን በመለየት በቦቴ ተሽከርካሪ ማቅረብ የሚያስችል ስራ ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰዋል።
ከጥር 29 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ በማዕከል የሚመራ ኮማንድ ፖስት እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት ድረስ እየሰራ ይገኛልም ነው ያሉት።
ኮማንድ ፖስቱ ሆቴሎቹ በሚገኙባቸው መገናኛ፣ መካኒሳ፣ አራዳ እና ንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለመንቀሳቀስ የሚያግዝ ባጅ በመያዝ እየሰራ ይገኛል።
ልዩ ኮማንድ ፖስቱ በዋናነት በስብሰባው ወቅት ለመሪዎቹ የውሃ አገልግሎት እንዳይቋረጥና በዚህ ሳቢያ የሃገሪቱ ገጽታ እንዳይበላሽ ለማድረግ የሚሰራ ነው።
ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM