TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
የግብይት ስፍራዎቹ ህገወጥ ናቸው‼️

በአዲስ አበባ ሰሞኑን በተለያዩ አካባቢዎች የተሰሩ #በእንጨትና #ሸራ የግብይት ስፍራዎች በሙሉ #ህገወጦች በመሆናቸው #እንደሚፈርሱ የመዲናዋ ንግድ ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ #መስፍን_አስፋው ከfBC ጋር በጉዳዩ ባደረጉት ቆይታ ሰሞኑን በመዲናዋ የተገነቡት ግንባታዎች የከተማዋን ገጽታ የሚያበላሹና ህገወጥነትን የሚያበረታቱ ናቸው ብለዋል። ምክትል ኃላፊው የግብይት ስፋራዎቹ ከንግድ ቢሮው እውቅና ውጪ የተገነቡ በመሆናቸው ነው እርምጃው ያስፈለገው ብለዋል።

በመደበኛ ያልሆኑ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ለነበሩና ተመዝግበው ግብር ለሚከፍሉ 2 ሺህ 400 ነጋዴዎች ብቻ በጥናት የተለየ የንግድ ቦታ ማመቻቸቱን ተናግረዋል። እነዚህም ቢሆኑ ምንምዓይነት ግንባታ ማካሄድ እንደማይችሉ አቶ መስፍን ገልጸዋል።

ሆኖም በአዲስ አበባ ከተማ ለትራፊክ አደጋ በተጋለጠ መልኩ እና የከተማዋን ገጽታ በሚያጎድፍ ሁኔታ ከሰሞኑ እየተሰሩ ያሉ ግንባታዎች ህገ-ወጥ ናቸው ብለዋል። የግብይት ስፍራዎቹም በምሽትና በስውር ተሰርተው እንሚያድሩም ነው ምክትል ኃላፊው የተናገሩት።

በመሆኑም ቢሮው ግንዛቤ ከማስጨበጥ ጎንለጎን የተሰሩትን የግብይት ማዕከላት ከጸጥታ አካላት ጋር በመሆን ማፍረስ መጀመሩን ገልጸዋል። በተፈቀዱ ቦታዎች ላይ ለመስራትም ነጋዴው ማህበረሰብ ንግድ ፍቃድ አውጥቶ በህግ መሰረት መሄድ እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።

በህገወጥ መልኩ በእንጨትና ሸራ የተሰሩ የግብይት ስፍራዎችን የማፍረስ ስራውም እንደሚቀጥል ምክትል ኃላፊው ገልጸዋል።

ምንጭ፦ FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia