ASTU🔝
በአሁን ሰዓት የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከተማሪ ቤተሰቦች ጋር ወቅታዊውን የዩኒቨርሲቲ ሁኔታ አስመልክቶ ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ህፃን ሚሊዮን🔝
ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ #ዝናሽ_ታያቸው እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ህጻን ሚሊዮንን #በጉዲፈቻ ለማሳደግ ያቀረቡት ጥያቄ በፍርድ ቤቱ ተቀባይነት አገኘ።
ቀዳማዊ ቤተሰቡ ህጻን #ሚሊዮንን ከክበበ ህጻናት ማሳደጊያ ተቀብሎ #ለማሳደግ ጥር 14 ቀን 2011 ዓ.ም ለፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 7ኛ የወንጀል ችሎት የህጻናትና ሴቶች ጉዳይ በፅሁፍ ማመልከቻ አቅርቦ ነበር። በማመልከቻቸው አመልካቾች የተፈራረሙበት የጉዲፈቻ ውል #እንዲጸድቅላቸው ጠይቀዋል።
ቀዳማዊ ቤተሰቡ ለህጻኑ #መልካም አስተዳደግ እንደሚሰጥና ህጻኑን ለማሳደግ በቂ ኢኮኖሚያዊ አቅም እንዳለው ጠቅሷል። ፍርድ ቤቱም ህጻን ሚሊዮን ከሁለት አመት እድሜ በታች በመሆኑ ችሎት ፊት ቀርቦ አስተያየት መስጠት ስለማይችል ችሎቱ የተለያዩ ማስረጃዎችን መርምሮ፥ አመልካቾች ህጻኑን በጉዲፈቻ ቢያሳድጉት ችግር የለውም ወይም መልካም ነው ብሎ በመወሰን ጥር 14 ቀን 2011 ዓ.ም የተፈራረሙትን ውል ተሻሽሎ በወጣው የቤተሰብ ህግ 213/92 አንቀጽ 93 ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት አጽድቆላቸዋል።
የውሳኔውን ግልባጭም ጉዳዩን ችሎት ፊት ቀርበው ለተከታተሉት ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው እንዲደርሳቸው ተደርጓል። የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ለቀዳማዊ ቤተሰቡ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። አያይዘውም በጉዲፈቻ ልጅ ለማሳደግ መወሰናቸው ለሌሎች አርዓያ እንደሚሆንና ልጅ ማሳደግ ትልቅ ሃላፊነት መሆኑን እንዲሁም ህጻናትን በጉዲፈቻ ለማሳደግ ሁሉም እንዲያስብ ያደርጋል ብለዋል።
በእድሜያቸው ሶስት መንግስታት ማየታቸውን ያነሱት ፕሬዚዳንቷ ከፍተኛ የሃገር መሪዎችና ሃላፊዎች ፍርድ ቤት ቀርበው ጉዳያቸውን ሲያስፈጽሙ አይተው እንደማያውቁም ተናግረዋል። ቀዳማዊት እመቤቷ #ችሎት ፊት ቀርበው ጉዳያቸውን ማስፈጸማቸው ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል መሆኑን ያመላክታልም ነው ያሉት።
ምንጭ፦ fbc

#update በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ግዜ "ኢትዮጵያ አትተኛም" በሚል መሪ ቃል የዘጠኝ ኪሎ ሜትር #የምሽት ጎዳና ላይ የሩጫ ዉድድር የካቲት 30 ከምሽት አንድ ሰዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ ሊካሄድ ነው።
ከአዘጋጆቹ እንደሰማነው አላማዉ፦
1. የስራ ሰዓት ባህላችንን ማሳደግ
2. ወጣቶች ከቤተሰቦቻቸው፣ ከጓደኞቻቸው እና ከሚወዷቸው ጋር በመሆን ምሽታቸውን በመልካም እና በሚያንፅ ቆይታ አንዲያሳልፉ
3. ከዝግጅቱ ከሚገኝ ገቢም አካል ጉዳተኛና አረጋውያንን ለመርዳት ታቅዷል።
አዘጋጅ፦ ሚድ ናይት ራን ኢትዮጵያ እና የኢፌዲሪ ሠራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒሰቴር ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር።
አዘጋጆቹን በእነዚህ አድራሻዎች ማግኘት ይቻላል፦ www.midnightrunethiopia.com
ስልክ ቁጥር +251116674717/ +251933252222 facebook page https://www.facebook.com/Night-Run-Ethiopia-6125770525262/

የመከላከያ ሰራዊት ቀን🔝
7ኛው የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት ቀን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል #አሶሳ ከተማ እና በአማራ ክልል #ባህርዳር ከተማ በፓናል ውይይት በመከበር ላይ ነው።
“ህገ መንግስታዊ ስረአታችንና ህዝባዊ ባህሪያችንን ጠብቀን የተጀመረውን ለውጥ እናስቀጥላለን'' በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል።
የምእራብ ዕዝ ምክትል አዛዥ አስተዳደር ብርጋዴል ጄነራል እንዳልካቸው ወ/ኪዳን በውይይቱ ላይ እንዳሉት በህገ መንግስታዊ መርሆዎች የተቋቋመው የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ የሚሰጠውን ተልእኮዎችን በላቀ ድል እየተወጣ ይገኛል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ሰራዊት ታሪካዊ አመሰራረት ላይ ያተኮረ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል። በፓናል ውይይቱ ላይ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ጨምሮ ከፍተኛ ባለስልጣናት የህዝብ ወኪሎ፣ የምእራብ ዕዝ እና የ22ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች፣ የሰራዊት አባላት እየተሳተፉ እንደሚገኙ ሪፖርተራችን ያለለት ወንድዬ ከአሶሳ ዘግቧል።
በተያያዘ ዜና በባሕር ዳር ከተማ ሙሉዓለም የባሕል ማዕከል 7ኛው የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት ቀን እየተከበረ ነው፡፡
በበዓሉ ላይ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላትና ከፍተኛ አመራሮች፣ የክልሉ መንግሥት ሰላምና ደኅንነት አባላትና አመራሮች፣ የክልሉ መንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ከፍሎች እየታደሙ ነው፡፡
የጠቅላይ ሚስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክረተሪያት ኃላፊ አቶ #ንጉሡ_ጥላሁን ጨምሮ ከፍተኛ ባለስልጣናትም በበዓሉ አከባበር እየተሳተፉ መሆኑን አብማድ ዘግቧል፡፡
ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ

#update በዛሬው እለት በትግራይ ክልል ጤና ቢሮ የመቐለ ደም ባንክ በ2010 ዓ.ም የስራ ዘመን ከደም ባንኩ ጋር በመሆን የደም ማሰባሰብ ስራ ላይ ሲሳተፉ ለነበሩ የደም ልገሳ ክለቦች፣ የጤና ተቋማት፣ የሀይማኖት ተቋማት፣ የትምህርት ተቋማት እና ግለሰቦች እውቅና የመስጠተ ኘሮግራም በመቐለ ከተማ በሚገኘው ሃፄ ዩሃንስ ሆቴል አዳራሽ እያካሄደ ይገኛል፡፡ የመቐለ ደም ባንክ በትግራይ ክልል የመጀመሪያው የደም ባንክ ተቋም በመሆን በ1997 ዓ.ም የተመሰረተ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በመቐለ ከተማ ለሚገኙ 28 የመንግሥትና የግል የጤና ተቋማት እንዲሁም በ100 ኪ.ሜ ርቀት ድረስ ለሚገኙ 2.6 ሚሊዩን አካባቢ ለሚገመት የማህበረሰብ ክፍል አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ በያዝነው አመት 4178 ዩኒት ደም ከበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች በማሰባሰብ ለተጠቃሚዎች ተሰቷል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኢሉ አባቦራ ዞን ቡኖ በደሌ ወረዳ ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የዲዴሳ ሆስፒታል ተመርቆ ተከፈተ፡፡ለሆስፒታሉ የሕክምና ቁሳቁሶችም ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ተገዝተዋል፡፡ ሆስፒታሉን መርቀው የከፈቱት የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ጠይባ ሀሰንና የኦሮሚያ ጤና ጥበቃ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ ናቸው፡፡
ምንጭ:- የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ:- የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia