TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ኢሳት‼️

የእንግሊዙ የዜና ማሰራጫ ቢቢሲ ኢሳትን በተመለከተ የሰራጨውን #የተሳሳተ ዘገባ ማረሙን ለኢሳት በጻፈው ደብዳቤ ገለጸ።

የቢቢሲ አለም አቀፍ አገልግሎት ዳይሬክተር ጄሚ አንገስ ኢሳት ለጻፈው የቅሬታ ደብዳቤ ትናንት በላኩት ምላሽ ቢቢሲ ባለፈው ወር ባሰራጨው ዘጋባ ኢሳት ሆን ብሎ #የዘር_ግጭት የሚጭር ቪድዮ #አዘጋጅቶ አሰራጭቷል በሚል በቢቢሲ ያቀረበው ዘገባ ያስተላለፈው መልዕክት ትክክል አለመሆኑን በመገንዘብ ማስተካከያ መደረጉን በደብዳቤያቸው ገልጸዋል።

በዚህም መሰረት በእንግሊዝኛ፣ አማርኛ፣ ትግርኛ እና ኦሮምኛ ቢቢሲ ያቀረበውን ዘገባ ማስተካከሉን አስታውቀዋል።

በማስተካከያውም የተባለው ቪድዮ የተዘጋጀው በሌላ አካላት እንደነበርና ኢሳት ወዲያውኑ ቪድዮውን ማውረዱንና #ይቅርታ መጠየቁን በቢሲ በማስተካከያው ላይ ጨምሯል።

ዳይሬክተሩ ቢቢሲ ማስተካከያ ለማድረግ በመዘግየቱ ይቅርታ ጠይቀው በዚሁ እንግሊዝኛ ተናጋሪ የቢቢሲ ጋዜጠኛ ተሰራ ያሉትን የተሳሳተ ዘገባ ኢሳትን ለመጉዳት ያለመ ነው የሚል እምነት እንደሌላቸው እምነታቸውን ገልጸዋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"አብራክ" ተገመገመ‼️

ኢትዮጵያን የሚንጣት #የዘር ፖለቲካን የወከሉ ገፀ ባህሪያት የተወከሉበትና የብሔር ፖለቲካና የብሔር ማንነት ጥልቀት፣ የፖለቲካ ከፋፋይነት ተደርሶበታል የተባለው “አብራክ” የተሰኘ መፅሐፍ ትናንት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተገምግሟል፡፡

Via Sheger FM 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA " የኢትዮጵያን ችግር በውጪ ጣልቃ ገብነት መፍታት አይቻልም " - የአሜሪካ የቀድሞ አምባሳደሮች በኢትዮጵያና ጊኒ የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉትና በትራምፕ አስተዳደር ረዳት የውጭ ጉዳይ የነበሩት ቲቦር ናዥ እንዲሁም በኢትዮጵያ፣ ላይቤሪያ እና ዛምቢያ አምባሳደር የነበሩት ዶናልድ ቡት ኢትዮጵያውያን ለውጪ ሀይል ግፊት የማይንበረከኩ መሆናቸውን ማስተዋላቸውንና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ…
#የዘር_ፖለቲካ !

አምባሳደር ቲቦር ናዥ ፦

" ዘርን መሰረት ያደረገ የፌዴራሊዝም ስርዓት ሊሰራ የሚችለው እንደ ስዊዘርላንድ ባሉ የተለያዩ ጎሳዎች ሳይጋጩ ሀብታቸውን መጠቀም በሚችሉባቸው ሀገራት ነው በኢትዮጵያ ግን የሚጋሩት ድህነት በመሆኑ ሁኔታው መልኩን ቀይሯል። "

.
.

አምባሳደር ዶናልድ ቡት ፦

" ይሄ ስርዓት [ዘርን መሰረት ያደረገ] ከተለያዩ ከሌሎች ጎሳዎች በጣም ብዙ ጥላቻ እንዲመጣ አድርጓል። ስለዚህ አሁን ኢትዮጵያውያን ሊያደርጉ የሚገባው ወደኃላ ተመልሰው እንዴት ልዩነታቸውን በተቻቻለ መንገድ እንደገና በሰላም አብረው መኖር እንደሚችሉ መላ መፈለግ ነው። "

* ኢትዮጵያ ውስጥ ሲተገበር የነበረው ዘርን መሰረት ያደረገ ስርዓት ሀገሪቱ አሁን ላለችበት መሰረት ነው ፤ ደርግ ሲወድቅ ይህንን ስርዓት ያመጣው ህወሓት ያመጣው ዘርን መሰረት ያደረገ ስርዓት ኢትዮጵያ ላይ አለመስራቱን ዲፕሎማቶቹ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የሚታየው ችግር የተባባሰው የፖለቲካ አመራሮች ከህዝቡ ድጋፍ ለማግኘት ሲሉ ዘርን በመጠቀማቸው ነው።

@tikvahethiopia