ላልይበላ🔝
የአየርላንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ላልይበላ ገቡ። ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዮ ቫራድካር ላልይበላ ሲደርሱ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዮ ቫራድካር የአየርላንድና የኢትዮጵያን የ2019 አዲስ የትብብር መስኮችን ያስተዋውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። አየርላንድ ባለፉት 25 ዓመታትም በትምህርት ፣ በማህበራዊ ዋስትና ፣ 30 ሚሊዮን ዮሮ በመመደብ ስትሰራ ነበር። አየርላንድ ቅርሶችን ለመጠበቅና እና የገጠር ቱሪዝምን ለማበረታታት 1 ቢሊየን ብር መድባለች። ከላል ይበላ ጉብኝት በኋላ የአክሱም እና ከአፍረካ ሁለተኛውን የሽሬ አዲሀርሽ የስደተኞች መጠለያን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል ሲል የዘገበው አብመድ ነው።
via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia

በሾላ ገበያ የሚገነባው ባለፎቅ የመኪና ማቆሚያ ከመሬት በታች ሁለት ደረጃዎች ያሉት ባለ አምስት ፎቅ ህንጻ ለማልማት የቅድመ ግንባታ ዝግጅቶች እየተከናወነ ይገኛል፡፡ ፕሮጀክቱ ሲያበቃ ከ1 ሺህ ያላነሱ መኪናዎችን የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል፡፡
via TPMO
@tsegabwolde @tikvahethiopia
via TPMO
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በትላንት በስቲያ #በሽረ ከተማ ወደ #ሀዋሳ በማምራት ላይ የነበረ የመከላከያ ሰራዊት ኮንቮይ ላይ መንገድ የዘጉ ወጣቶች፣ ከመከላከያ ሀላፊዎች ጋር ተወያዩ። ከውይይቱ በኅላ የመከላከያ ኮንቮዩ ከጫነው ከባድ መሳሪያ ጋር እንዲንቀሳቀስ ስምምነት ላይ የተደረሰ ሲሆን፣ ወጣቶቹ #ይቅርታ ጠይቀዋል።
Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሕዳሴው ግድብ‼️
ህዳሴ ግድብ ውሀ የሚተኛበት ቦታ ላይ ያለው የደን ምንጣሮ ስራ ከብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) #ተነጥቆ ለአማራ እና ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወጣቶች ሊሰጥ ነው።
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሀይል እንዲያመነጭ የሚያስፈልገው ቦታ ወደሁዋላ 246 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚተኛ ሲሆን በጥቅሉ ደን የሚመነጠርበት ስፋት 180 ሺህ ሄክታር ስኩዌር ያህል ነው። ይህን ደን የመመንጠር ስራ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ከአራት አመት በፊት ለብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ሰጥቶት እንደነበር ይታወቃል። ለስራው ቅድመ ክፍያም ሜቴክ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል 2.7 ቢሊየን ብር ተከፍሎታል።
ሆኖም ሜቴክ ስራውን በሰብ ኮንትራት በማህበር ለተደራጁ ወጣቶች መስጠቱ የሚታወስ ነው። በበርካታ ማህበራት ከተደራጁ ወጣቶች ጋር የ56 ሺህ ሄክታር መሬት ደን ምንጣሮን በ700 ሚሊየን ብር እንዲሰሩለትም ውል አሰሯል። ነገር ግን እነዚህ ማህበራት ስራውን ከሰሩ በሁዋላ ሜቴክ የተመነጠረው መሬት አለካክ ተገቢ አይደለም በሚልና ሌሎች ማስፈራሪያዎች ለማህበራቱ 340 ሚሊየን ብር ቀሪ ክፍያ እንዳልፈጸመና ; በዚህም ሳቢያ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ሄዶ ማህበራቱ በግልጽ በሚታይ የፍርድ ቤቶች ኢ ፍትሀዊ አሰራር በሜቴክ ተሸንፈው ለኪሳራ ተዳርገናል ማለታቸውን የሚታወስ ነው። ሜቴክ ለደን ምንጣሮው ስራ ከኤሌክትሪክ ሀይል 2.7 ቢሊየን ብር ቢቀበልም ከሁለት ቢሊየን ብር በላይ የሚሆነውን ገንዘብ የት እንዳደረሰው ግልጽ አይደለም ተብሏል።
የሜቴክ የቀድሞ አመራሮች በተከሱበት ጉዳይም ይኸው ነገር መነሳቱ ይታወቃል። ዋዜማ ራድዮ ከተለያዩ ምንጮቼ ተረዳሁት እንዳለው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል የህዳሴው ግድብ አካባቢ የደን ምንጣሮን ውል ሙሉ ለሙሉ ከሜቴክ ነጥቆ የአማራና የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወጣቶችን ለማሰማራት እየተሰናዳ ነው። የስራው ውልም በቤኒሻንጉልና አማራ ክልል ያሉ ወጣቶችን አደራጅቶ ለመስጠትም ነው የታሰበው።
እንደ ራድዮ ጣቢያው ምንጮች ባከነ የተባለው ገንዘብ አስመልክቶ በህግ የ9 ሚታይ ይሆናል። የስራውን ውልና ተያያዥ ዝርዝር ጉዳዮችንም ለመጨረስ የሚመለከታቸው አካላት እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ተሰምቷል።
ምንጭ፦ ዋዜማ ራድዮ

ሻሸመኔ‼️
በሻሸመኔ ከተማ ያለው የውሃ ችግር ነዋሪውን እያማረረው ይገኛል። በከተማይቱ ውስጥ የሚኖሩ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት በተደጋጋሚ እንደጠቆሙት በውሃ እጦት ሳቢያ ከፍተኛ ችግር እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ገልፀዋል። የከተማ አስተዳደሩ ይህን ችግር እንዲፈታም ጠይቀዋል።

‹‹ስለ #ድብቅ_እስር_ቤቶች የማውቀው ነገር የለም፡፡›› የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር
የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ስለ ድብቅ እስር ቤቶች የማውቀው ነገር የለም ብሏል፡፡
በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ስር ያሉ 6 ማረሚያ ቤቶች ቃሊቲ፣ቂሊንጦ ፣ ዝዋይ፣ ሸዋሮቢት፣ ድሬዳዋና ቃሊቲ የሴቶች ማረሚያ ቤት ብቻ ናቸው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ጀማል አባሶ ጠቅላይ አቃቢ ህግ በምርመራ ያገኛቸው እስር ቤቶች ከእኛ እውቅና ውጭ ያሉ ናቸው ብለዋል፡፡
የሰብዓዊ መብት አያያዝን ለማሻሻልም ዘመናዊ ማረሚያ ቤቶችን እየገነባን ነው ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ጀማል አባሶ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አሳውቀዋል፡፡
ምንጭ፦ አብመድ

Audio
"ታጣቂዎች "መከላከያ ሰራዊት" ላይ ተኩስ ከፍተዋል" የመከላከያ ሰራዊት
.
.
በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ገንደ ውሃና ኮኪት በተባለ ቀበሌ ከመከላከያ ሰራዊት አባላት በተተኮሰ ጥይት 27 ሰዎች መመታታቸውንና ከእነዚህ ውስጥ ሰባት ሰዎች ደግሞ መሞታቸውን የዓይን እማኝ መሆናቸውን የተናገሩ ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምጽ ገለፁ። ግድያውንም በመቃወም ዛሬ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። የሆስፒታል ምንጮች ሰዎች መገደላቸውንና መቁሰላቸውን ነግረውናል። የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጦር ኃይሎች ምክትል ኢታማዦር ሹም ጀነራል #ብርሃኑ_ጁላ በበኩላቸው በአካባቢው በመንገድ ሥራ ላይ የተሰማራ ኩባንያን አጅቦ በመውጣት ላይ በነበረ የመከላከያ ሠራዊት አባላት የታጠቁ ሰዎች ተኩስ መክፈታቸውን ገልፀዋል።
ምንጭ፦ VOA

ገንደ ውሃ‼️
የገንደ ውሀ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ #አራጋው_ሰንታ ዛሬ ጠዋት ለAPው ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት በስልክ የተናገሩት፦
•እንደተባለው የህብረተሰቡ አቋም የሱር ኮንስትራክሽን መኪኖች ይፈተሹልን ነበር ምክንያቱም በህብረተሰቡ ዘንድ ድርጅቱ ትልልቅ የጦር መሳርያዎችን ከሱዳን ወደሌላ ክልልሎች ያስተላልፋል የሚል ጥርጣሬ ነበር። እነሱ ግን ይባስ ብለው በመከላከያ ታጅበው መጡ።
•በመሀል መከላከያዎች ህዝቡ ላይ መተኮስ ጀመሩ። አንድ ህፃን እና ሎሎች ሁለት ሰዎች እኛ ከተማ ላይ ሞተዋል። ኮኪት ከተማ ላይም የሞቱ ሰዎች አሉ። እነዚህ በሙሉ ንፁሀን ዜጎች እና ምንም መሳርያ ያልታጠቁ ነበሩ። ኮኪት ከተማ ላይ ግን የሞቱ የመከላከያ አባት እንዳሉ ሰምቻለሁ።
•ትናንት በተካሄደ ሰልፍ ህዝቡ ሱር ይፈተሽልን፣ ገዳዮች ለፍርድ ይቅረቡ እና ሰላም ይስፈን ብለው ጠይቀዋል።
በተጨማሪ...
የኮኪት ከተማ ነዋሪው ይመር ስለ ማክሰኞው ግድያ ለጋዜጠኛ ኤልያስ በስልክ የተናገረው፦
•የሱር መኪናዎች ገንደ ውሀ ላይ ህዝቡን አዘናግተው እንዳለፉ ሲወራ ህዝቡ ኮኪት ከተማ ላይ ሆኖ ጠበቃቸው። ይህ የሱር አካሄድ ጥርጣሬን ጫረ።
•ኮኪት ከተማ አቅራቢያ አንድ ድልድይ አለ። መከላከያዎች ድልድዩን አልፈው ብቅ እንዳሉ እና ህዝቡን እንዳዩት መተኮስ ጀመሩ። በዚህም ከአንድ ቤት ሶስት ሴቶች ተገድለዋል። በአጠቃላይ እኛ ከተማ ብቻ አምስት ሰው ሞቶ ስምንት ሰው ቆስሏል።
•ከከተማው አንድ ወይም ሁለት ኪሎሜትር ርቀት ላይ ባለ እና አንደኛ ጎራ በተባለ ተራራ ላይም ከባድ መሳርያ ተተኩሶ ሲነድ ነበር።
•ህዝቡ በመጀመርያ ድንጋይ ሲወረውር ነበር። ከዛ በሁዋላ ግን አስፓልት ላይ የቆመ ሰው ሲመታ አንድ ሁለት ጥይቶች ወደ መከላከያ ተተኩሰዋል። የሞቱ ወታደሮች እንዳሉ ግን አልሰማንም።
•በመጨረሻ መኪኖቹን ኑ ፈትሹ ተብሎ ሲፈተሹ የተባለው መሳርያ አልተገኘም። አዳር ላይ ምን ሲሰሩ እንዳደሩ ግን አይታወቅም። አሁን መከላከያዎች #ወጥተዋል፣ ድባቡም #የተሻለ ነው።
ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት

#Update የአዴፓ ማአከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት በምዕራብ ጎንደር ዞን የተከሰተውን የጸጥታ ችግር የሚያጣራ ግብረ ሀይል ወደ አካባቢው መላኩን አስታውቋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዴፓ‼️
የአዴፓ ማአከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት በ ምዕራብ ጎንደር ዞን በተከሰተ #የጸጥታ_ችግር ምክንያት የሰዎች ህይዎት በማለፉ የተሰማውን ሀዘን ይገልፃል፡፡
ዝርዝር ጉዳዮ ተጣርቶ አጥፊዎቹን ለህግ ለማቅረብ የሚያሰችል አጣሪ ግብረ ሀይል ተቋቁሞ ወደ ስፍራዉ ተንቀሳቅሷል። በቀጣይም ግብረ ሀይሉ የሚደርስበትን #የተጣራ መረጃ የምናደርስ ይሆናል፡፡
ፓርቲያችን ለሟች ቤተሰቦችና ወደጅ ዘመዶች መፅናናትን ይመኛል ፡፡
የአዴፓ ማእከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት

ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች‼️
በመላ አገሪቱ የሚገኙ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሊፈተሹ ይገባቸዋል ያሏቸውን የመወያያ አጀንዳዎች አቀርበዋል፡፡
ፓርቲዎቹ ከመወያያ አጀንዳዎቹ ባሻገርም እንዴት እንወያይ እና ማን ያወያየን በሚሉ የውይይት ስርዓትና ደንብ ላይም ላይ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ እየመከሩ ይገኛል፡፡
ፓርቲዎቹ ውይይት ልናደርግባቸው ይገባል ብለው ካቀረቧቸው አጀንዳዎች መካከል
1.የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉዳይ የተመለከተ
• ውይይቶች የሚመሩበት ሥርዓት እና ደንብ
• የሥነ-ምግባር ደንብ
• ለፖለቲካ ፓርቲዎች የሚደረግ ድጋፍ
• የጋራ ምክር ቤትን የማቋቋሚያ ጉዳይ
• ስለፖለቲካ ፓርቲዎች ውህደት ትብብር ጥምረት
• ያልተመዘገቡ ፓርቲዎች-ከውጭ አገር የመጡና በአገር ውስጥ ያሉ ፓርቲዎች ጉዳይ ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡
2.ምርጫ ቦርድን በተመለከተ
• ስለ ምርጫ ቦርድ አደረጃጀት
• የምርጫ አፈፃፀም ሂደቱን ስለማዘመን እና
• የሥነ-ዜጋና የመራጮች ትምህርት የሚመለከቱ ሀሳቦች ተነስተዋል፡፡
3. የምርጫ 2012 እና የአካባቢያዊ ምርጫ በሚመለከት
• የምርጫ መራዘምን የሚመለከት
• የ2012 ጠቅላላ ምርጫ
• የአካባቢ ምርጫ
• ሰላምና መረጋጋት
• ስለ ሰብአዊ መብት ጉዳይ በዚህ አጀንዳ ስር ያሉ ነጥቦች ናቸው፡፡
4.የዴሞክራሲያዊ ተቋማትን የማሻሻል ጉዳይን በተመለከተ
• የመገናኛ ብዙሃን ሕግ ማሻሻያ
• የመገናኛ ብዙሃን ገለልተኛነት እና አጠቃቀም
• የአቃቤ ሕግ፣ የፖሊስ፣ የደህንነት እና የመከላከያ ተቋማት ግንባታን ስለማሻሻል እና
• የዳኝነት ሥርዓቱን ስለማሻሻል የተመለከቱ ሀሳቦች የመወያያ አጀንዳ መሆን አለባቸው ተብለው በተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲች የቀረቡ ሀሳቦች መሆናቸውን የዘገበው ኢቢሲ ነው፡፡
©etv

#update በሁመራ ከተማ በሺህዎች ለሚቆጠሩ የኤርትራ ኦምሓጀር ነዎሪዎች የምሳ ግብዣ ተካሄደ፡፡ የሁመራ ከተማ ነዋሪዎች ይህንን የምሳ ግብዣ ያዘጋጁት ታህሳስ 29 ቀን 2011 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በተገኙበት ሁለቱን ሀገራት ሚያገናኘውን የሁመራ - ኦምሓጀርን መንገድ መከፈቱን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡ ሁለቱ ሀገራት በዚሁ አካባቢ በየብስ ትራስፖርት መገናኘት አሁን ላይ በኢትጵያና ኤርትራ ህዝቦች መካከል የተጀመረውን ሰላማዊ ግንኙነት የበለጠ እንደሚያጠናክረው ተግልጿል።
ምንጭ፦ FBC
@tsegabwole @tikvahethiopia
ምንጭ፦ FBC
@tsegabwole @tikvahethiopia
ድንገቴ እንግዳ-ኢንጂነር ታከለ‼️
ትላንት ጥር 1 ቀን 2011 ዓ.ም 90ኛ የጦቢያ ግጥምን በጃዝ ምሽት በራስ ሆቴል መዘጋጀቱን ተከትሎ የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ ኢንጅነር #ታከለ_ኡማ ድንገት በመምጣት የዝግጅቱ ታዳሚ ሆነው አምሽተዋል። "ይህ ፕሮግራም ያለ ማቆራጥ ሀሳብ እንደጉድ የሚጎርፍበት ስፍራ መሆኑን ሲወራ በመስማቴ ዛሬም እኔ ከሚፈሰው ሀሳብ ልታደም መጥቻለሁ። እንዳነዚህ ጠንከር ጠንከር ያሉ ሀሳቦች የሚፈሱበት ፕሮግራሞች ሊስፋፉ እና መንግስትም ሊደግፋቸው ይገባል።" ብለዋል ኢንጅነር ታከለ ኡማ በመድረኩ። በተያያዘም ትላንት በ90ኛ የጦቢያ ግጥምን በጃዝ ምሽት ላይ አቅራቢ ከነበሩት መካከል ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና አንዱ የነበሩ ሲሆን ባጋጠማቸው ከፍተኛ ችግር ምክንያት መምጣት ባለመቻላቸው ለመጣው ታዳሚ ሁሉ ይቅርታ ጠይቀዋል። 90ኛ የጦቢያ ግጥምን በጃዝ ምሽት እንደተለመደው የሀሳብ ከፍታን ከተዝናኖት ጋር በማዋሀድ ምሽቱን በድምቀት አሳልፎአል።
ምንጭ፦ Habl Media And Advertisement

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የመከላከያ እና የኦነግ ፍጥጫ‼️
#በምዕራብ_ወለጋ የታየውን የሰላም መደፍረስና የግጭት ቀጠና መሆኑን አስመለክቶ በመንግስት በኩል የተለያዩ መግለጫዎች ሲሰጡ እንሰማለን፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆኑ ምክትል ኢታማዦር ሹሙ እንደተናገሩት፣ ስምም ባይጠቅሱ ችግሩን የጎተተው ኦነግ መሆኑን የሚያመለክቱ መግለጫዎችን እየሰጡ ነው፡፡ የኦሮሞ ነፃነት ግንባርስ ምን ይላል? ሸገር የኦነግን የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ጠይቋል፡፡
ምንጭ፦ ሸገር 102.1