TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ሊበን ወረዳ‼️

ከተፈቀደለት ስምሪት ውጪ  46 ሺህ 516 ሊትር ነዳጅ ጭኖ ሲጓጓዝ ተደርሶበታል የተባለው የቦቴ አሽከርካሪ በገንዘብ #እንዲቀጣ መወሰኑን በጉጂ ዞን የሊበን ወረዳ ፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡

የፍርድ ቤቱ ዳኛ በለጠ ታዬ እንደገለጹት ውሳኔው የተላለፈው ለአማራ ክልል ደጀን ከተማ ከጅቡቲ የተጫነ ቤንዚልና ናፍጣ ወደ ሶማሌ ክልል ፊልቱ ከተማ ሲጓጓዝ በመያዙ ነው

ነዳጁ የተጫነው የታርጋ ቁጥሩ ኮድ 3  57142 ኢት ቦቴና ተጎታቹ እንደሆነ ለፍርድ ቤቱ  የቀረበው የክስ ማስረጃ ጠቅሰው አስረድተዋል፡፡

በቦቴውና በተጎታቹ ተጭኖ የተገኘው 24 ሺህ 363 ሊትር ቤንዚልን እና 22 ሺህ 153 ሊትር ናፍጣ ህዳር 28ቀን 2011 ዓ.ም. ምሽት 2.ሰዓት በህዝብ ጥቆማ ነገሌ ከተማ ውስጥ መያዙን  ዳኛው አስታውቀዋል።

ፍርድ ቤቱ #በነገሌ ከተማ በዋለው ችሎት አሽከርካሪው ሞገስ አሰፋን  በ13 ሺህ ብር እንዲቀጣ እንዲሁም የተጫነው ቤንዚልና ናፍጣ ለመንግስት ውርስ እንዲሆን መወሰኑን ገልጸዋል፡፡

“ጥፋቱ ከ10 እስከ 50 ሺህ ብር የሚያስቀጣ ቢሆንም አሽከርካሪው ከዚህ በፊት የክስ ሪከርድ ስለሌለበት ቅጣቱ ቀሎለታል” ብለዋል።

አስተያየታቸውን የሰጡት የጉጂ ዞን ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር ገመዳ ቱሉሳ ቅጣቱ ፍትሐዊ፣ ትክክልና አስተማሪ መሆኑን ተናግረዋል።

በኢኮኖሚ አሻጥር የኑሮ ውድነትን ለማባባስ የሚደረገውን እንቅስቃሴ  ለማጋለጥ የዞኑ ህዝብ የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ ሰሞኑን   በተፈጠረ የቤንዚል እጥረት በነገሌ ከተማ አንድ ሊትር  እስከ 80 ብር እየተሸጠ ሲሆን  የታክሲ ክፍያም ከሁለት ብር  ወደ አምስት ብር ከፍ ማለቱን ቀደም ሲል ኢዜአ  ዘግቧል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቅሬታ‼️

"በአማራ ክልል ዞኖች ውስጥ የምንገኘው በውሃ መስኖና ኢነርጅ መምሪያ የመስኖ ቡድን ሰራተኞች መዋቅሩ ይስተካከላል እየተባልን ከ3 ዓመታት በላይ ያለስራ በነፃ ደሞዝ እየተከፈለን ቆይተናል። በተደጋጋሚ ለአማራ ውሃ መስኖና ኢነርጅ ልማት ቢሮ ብናመለክትም ምላሽ የሚሰጠን አላገኘንም፡ በሰራተኞችም ሆነ በመምሪያ ሃላፊዎች የመስኖ ቡድንን ወይ መዋቅሩን አስተካክሉት ካለበለዚያ ቡድኑን አጥፉት የሚል ጥያቄ በየመድረኩ ቢነሳም ይሄ ከእኛ አቅም በላይ ነው የሚል ምላሽ ነው የሚሰጠው፡፡ ይህ የመስኖ ቡድን በውሃ መስኖና ኢነርጅ ቢሮ በኩል እስከ ዞን ብቻ የተዘረጋ ሲሆን በግብርና በኩል ግን የሰው ሃይሉን በዛ አድርጎ እስከ ወረዳ ድረስ መዋቅር ተሰርቶለታል፡፡ እንደዚህ አይነት መዋቅር በአማራ ክልል ብቻ የሚገኝ ሰራተኞችን እንደ ጡረተኛ በባዶው ደሞዝ ከመክፈሉ በተጨማሪ የእኛን /የሰራተኞቹን/ ስን ልቦና እየጎዳን ይገኛል፡፡ ይሄን ጉዳይ ርዕሰ መስተዳድሩ የሚያቁት ቢሆንም እስከ አሁን የተሰጠን ምላሽ የለም። እናም መስራት የሚችልን ጉልበት እና ጭንቅላት ተጠቀሙት፡ አትቀልዱበት። እባካችሁ፡ እባካችሁ የሚመለከታችሁ የፈደራልም ሆነ የክልል ባለስልጣናት መፍትሄ ስጡን እያልን እንገኛለን በየዞኑ የምንገኝ በውሃ መስኖና ኢነርጂ መምሪያ ውስጥ የምንገኝ የመስኖ ቡድን ባለሙያዎች! __ነኝ ከአዊ ዞን ውሃ መስኖና ኢነርጅ መምሪያ፡ እንጅባራ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ 22ዐ የጤና ባለሙያዎችን በትላንትናው ዕለት አስመርቋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዩጋንዳ‼️

የዩጋንዳ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች ከጉልበት በላይ ጉርድ ቀሚስ እንዳይለብሱ፣ ኩል እንዳይኳኳሉ እና ጌጥ #እንዳያደርጉ እገዳ አስተላለፈ፡፡

በዩጋንዳ የቡጋሜ ዩኒቨርሲቲ ነው የሞራል እሴቶችን በአስገዳጅነት ለመጠበቅ በሚል ነው ክልከላውን ያስተላለፈው፡፡ የጆሮና የአንገት ጌጥ፣ የእጅ አምባርና ሌሎች ጌጣ ጌጦችን እንዲሁም ሱሪዎችን አጫጭር ጉርዶችን እንዳይለብሱ ነው ዩኒቨርሲቲው የከለከለው፡፡ በቀጣዩ ወሰነ ትምህርት ማንም ተማሪ የተከለከሉትን አለባበሶች ተግብሮ እንዳይመጣም ማስታወቂያ ተነግሯል፡፡

ጥፋተኛ ሆነው የተገኙ በዩኒቨርሲቲው የሥነ-ምግባር ኮሚቴ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወሰድባቸውም ነው የተጠቆመው፡፡

የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ዲን ጆርጅ ሙፓጋሃሲ በእነዚህ ደንቦች ውስጥ ተማሪዎች እንዲያልፉ እያደረግን ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፡- አፍሪካኒውስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሪፐብሊኩ የጥበቃ ኃይል🔝

ጠቅላይ ሚነስትር ዶክተር #ዓብይ_አሕመድ በዛሬው ዕለት  ከሪፐብሊኩ የጥበቃ ኃይል አባላት ጋር ተገናኝተዋል።

የሪፐብሊክ የጥበቃ ኃይል የአገሪቱን ህገ መንግሥትና ህገ መንግስታዊ ስርዓት ከማንኛውም ጥቃት ለመከላከል በአዲስ የተቋቋመ የደህንነት መሳሪያ አካል መሆኑ ተገልጿል።

የሪፑብሊክ የጥበቃ ኃይል አባላት የመንግስት ባለስልጣናትንና እና ቤተሰቦቻቸውን የጥቃት ዓላማን አንግበው በሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ከሚሰነዘር ጠለፋና እንግልት ለመከላከል የተቋቋመ ነው።

ይህ የሪፐብሊክ የጥበቃ ኃይል በከፍተኛ የአመራር ስልጣን ላይ ያሉትን ኃላፊዎች ከማንኛውም ስጋት እና ጥቃቶች ለመጠበቅ አስፈላጊ የሆነውን ማንኛውንም ዘዴ መጠቀም ዋነኛ ተግባሩ ነው ተብሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጥበቃ አባላቱ ጋር በነበራቸው ቆይታ ላይም የሪፐብሊኩ የጥበቃ ኃይል አባላት የተሰጣቸውን ሃለፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን የሚያሳይ ትርዒት አቅርበዋል።

ባለፉት ስደስት  ወራትም ይህ ሃይል እራሱን በሰለጠኑ የደህንነት ባለሙያዎችና በተገቢው መንገድ ተግባሩን ለማከናወን የሚያስችሉ ቁሳቁሶችን እያደራጀና ስልጠናዎች እያደረገ መቆየቱን ከጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ምንጭ፦fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

“አባ ቶርቤ” በሚል መጠሪያ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በድብቅ በመንቀሳቀስ ሰዎችን ሲገድሉና ሲያስገድሉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች #በቁጥጥር ስር ዋሉ።

የኦሮሚያ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ እንዳስታወቀው፥ ብሄራዊ የመረጃ እና የደህንነት አገልግሎት ባደረገው ክትትል በዛሬው እለት ስድስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ተጠርጣሪዎቹ “አባ ቶርቤ” (ባለሳምንት) በሚል መጠሪያ በመደራጀት ሰላማዊ ዜጎችን፣ የመንግስት ባለስልጣናት እና የፀጥታ ሀይሎችን #ሲገድሉ እና #ሲያስገድሉ ነበር በሚል ነው ተጠርረው በቁጥጥር ስር የዋሉት።

የተጠርጣሪዎቹን ማንነትና ዝርዝር መረጃ እንደደረሰው ይፋ እንደሚያደርግም አስታውቋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከቤንሻንጉል ሕዝቦች ዴሞክራሲዊ ፓርቲ ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ጋር ዛሬ ታህሳስ 14 ቀን 2011 በጽ/ቤታቸው በወቅታዊ የክልሉ ሁኔታዎች ዙሪያ ተወያዩ። በውይይታቸውም የክልሉን የአስተዳደርና የልማት ችግሮችንና የግጭትና አለመረጋጋት መንስኤዎችን ለመቅረፍ የተጠናከረ እርምጃን አስፈላጊነት አንስተዋል። በሌሎች ክልሎች እንደታየውም አመራሮቹ የለውጥ እንቅስቃሴዎቹ ሰፊውን የክልሉን ነዋሪ በተለይም የክልሉን ወጣት አቅም በመጠቀም ወደ ክልል ደረጃ ለማውረድ ቃል ገብተዋል።

ምንጭ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ‼️

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ተቻችለው ለሀገራቸው ሰላምና አንድነት የበኩላቸውን እንዲወጡ የአዲስቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተርና የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆኑት አቶ ኦባንግ ሜቶ ጠየቁ፡፡

አቶ ኦባንግ ሜቶ በሀገራዊ  አንድነት ፣ ሰላምና መቻቻል ዙሪያ ትላንት ከአርባ ምንጭ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

”በሀገራችን  በአሁኑ ጊዜ እየተስተዋለ ያለው ግጭት ባለፉት 27 ዓመታት ለኢትዮጵያዊ አንድነት ትኩረት አለመስጠታችን ነው፣ ይህ ደግሞ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙ የነገይቱ ባለራዕዮችን እየተፈታተነ ይገኛል” ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ወደዚህች ምድር ብሔርን ምርጫ አድርጎ የመጣ ማንም እንደሌላ የተናገሩት አቶ ኦባንግ ሰው ማየት የሚገባው ሰው  መሆኑ እንጂ በዘርና በብሔር መሆን እንደማገባም አመልክተዋል፡፡

በሀገሪቱ የህግ የበላይነት እንጂ የዘር የበላይነት ሊኖር እንደማይገባ ጠቁመው ኢትዮጵያ እንድትለወጥ እያንዳንዱ ዜጋ ከብሔር አመለካከት ነፃ መሆን እንዳለበት አስረድተዋል ፡፡

”በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚገኙ ተማሪዎች የኢትዮጵያ እንጂ ተዋጽኦ አይደሉም፣ ደግሞ አንዳችን ያለአንዳችን መኖር አንችልም ስለዚህ ተማሪዎች የጥላቻ ሳይሆን የአንድነት ነፀብራቅ ልሆኑ ያገባቸዋል” ብለዋል፡፡

በሀገሪቱ የተለያዩ ግጭቶች ቢኖሩም የዴሞክራሲ መሠረት እየተጣለ መሆኑን የገለጹት  አቶ ኦባንግ የተፈጠረው በነፃነት የመናገር ዕድል  በመጠቀም ለሀገሪቱ አንድነት፣ ለሰላምና መቻቻል ሞጋቾች እንዲሆኑ ጠይቀዋል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ዳምጠው ዳርዛ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የበርካታ ብሄር ብሄረሰቦች ባለቤት እንደመሆኗ ባለፉት ጊዜያት በአንድነት ሳይሆን በልዩነት ላይ ትኩረት ሲደረግ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡

”ቀደምት አባቶቻችን በአንድነት ወግ ያደጉ በመሆናቸው የተለያዩ የሀገራችን ፈተናዎችን በድል ተወጥተው ለእኛ አስረክበዋል” ብለዋል፡፡

ወደ ቀድሞ የአንድነት ታሪክ ለመመለስ የመሪነት ሚና መጫወት ያለባቸው  የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማህበረሰብ መሆናችንን መዘንጋት እንደሌለባቸውም አመልክተዋል፡፡

”ብሔራዊ መግባባትና አንድነት ላይ ባለመሠራቱ በክልል የታጠሩ ነፃ አዉጪ የፖለቲካ ድርጅቶች እየተፈጠሩ እንጂ ብሔራዊ አመለካከት ያላቸው ጥቂቶች ናቸው”  ያለው ደግሞ በዩኒቨርስቲው የፕሮዳክሽን ምህንድስና የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ ግሩም አጅሬ ነው፡፡

ተማሪ ግሩም እንዳለው የዘር ፖለቲካ ባመጣው ጠባብ አመለካከት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ተቻችሎ ለመኖር እየከበዳቸው ይገኛል፡፡

በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ላይ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት ፣ ሰላምና መቻቻል አቶ ኦባንግ ገለፃ መስጠታቸው ራሱን እንዲያገኝ ያስቻለው መሆኑን ተናግሯል፡፡

የኤሌክትሮኒክስ ምህንድስና የአራተኛ ዓመት ተማሪ ሪሐና ኑሩ በበኩሏ “ሀገራችን በዘርና በብሔር በሽታ የታመመችው ከእኛ የተነሳ ነው ” ብላለች፡፡

ሆኖም አቶ ኦባንግ በአንድነትና ሰላም ዙሪያ ያደረጉት ገለጻ በካምፓስ ህይወታችን አንድነት በመፍጠር ተባብረው ለመኖር እንደሚያግዝ ተናግራለች፡፡

ምንጭ፦ ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"እኛ ሸሽተን የወጣነውን ትግል ባዶ እጁን ታግሎ ነፃ አውጥቶን ወደአገር የመለሰንን ህዝብ ትግል አስተምራለሁ ማለት #ውርደት ነው። ትግልን እንማርበት ከሆነ እንጂ።" ኦቦ ሌንጮ ለታ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢሉአባቦር ዞን‼️

በኢሉአባቦር ዞን ቡሬ ወረዳ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 43 #ክላሽንኮቭ ጠመንጃና 44 የጥይት ካዝና መያዙን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ታረቀኝ አሰፋ ለኢዜአ እንደገለፁት ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎቹ የተያዙት ከትላንት በስቲያ ሲሆን ከጋምቤላ ክልል በኮድ 3 -92943 ኢትዮጵያ ሲኖትራክ ተሽከርካሪ በአንድ ግለሰብ አማካኝነት ወደ መሀል ሀገር በመጓጓዝ ላይ እያለ በህብረተሰቡ ተሳትፎ በቡሬ ወረዳ ሲቦ ቀበሌ በተደረገው #ፍተሻ ነው።

ምንጭ፦ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰላም #የሁሉም_ነገር_መሰረት ነው!!
.
.
ሰላም ከሌለ ወጥቶ መግባት አይቻልም።

ሰላም ከሌለ ሰርቶ መብላት አይቻልም።

ሰላም ከሌለ መማር አይቻልም።

ሰላም ከሌለ ልጅ ወልዶ ማሳደግ አይቻልም።

ሰላም ከሌለ ስለሀገር አንድነት መነጋገር አይቻልም።

ሰላም ከሌለ እንቅልፍ ሊኖረን አይችልም።

ሰላም ከሌለ ስለሀገር ማሰብ አይቻልም።

ሰላም ከሌለ ስለፖለቲካ ማውራት አይቻልም።

ሰላም ከሌለ ስለብሄር ማውራት አይቻልም።

ሰላም ከሌለ ስለነገ ማሰብ አይቻልም።

TIKVAH-ETH ሠላም የሁሉ ነገር መሰረት መሆኑን ስለሚየምን ዘውትር ስለሰላም ይሰብካል!!

#ሼር #share
@tsegabwolde @tikvahethiopia