#update ባህር ዳር⬆️
ከውጭ ሀገር ሆነው አርበኞች ግንቦት-7ን ይመሩ የነበሩ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ ከሰዓት በኋላ ባሕር ዳር ገብተዋል፡፡
አመራሮቹ ባሕር ዳር ሲገቡም የድርጅቱ የሀገር ውስጥ አመራሮች እና የክልሉ መንግሥት ተወካይ ተቀብለዋቸዋል፡፡
ከፍተኛ አመራሮቹ ወደ ባሕር ዳር የመጡበትን ዓላማ አስመልክቶም መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ የአርበኞች ግንቦት-7 ሊቀ-መንበር ፕ.ር ብርሃኑ ነጋ ‹‹ሕዝቡ ለነጻነት ለከፈለው #መሰዋዕትነት ምሥጋና ልናቀርብ ነው›› ብለዋል፡፡
የድርጅቱ ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በበኩቸው ‹‹በባሕር ዳር በሚኖረን ቆይታ ስለድርጅታችን ቀጣይ አቅጣጫዎች እና ሥራዎች ለሕዝብ #የማሳወቅ ሥራ እንሠራለን›› ብለዋል፡፡
የአርበኞች ግንቦት-7 አመራሮች ነገ ቅዳሜ ረፋድ 2፡00 ጀምሮ በባሕር ዳር ዓለም-አቀፍ ስታዲዮም ንግግር ያደርጋሉ፤ ከሰዓት በኋላ ደግሞ ከቀኑ 8፡00 አንስቶ በአማራ ክልል ምክር ቤት አዳራሽ ከባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ጋር #ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
©AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia