TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ከፓዊ⬆️

"በዛሬው እለት የፓዊ ወጣቶች በጎ አድራጎት ማህበር በወረዳው ሲያከናውን የቆየውን በጎ ስራዎች ማለትም የወባ መራቢያ ቦታዎች ውሃ የማፋሠስና የማጽዳት ፣ ለአረጋዊያን ቤት እድሳት፣ የተለያዩ በወረዳዋ የሚገኙ ማሽነሪዎች ፅዳትና ገንዘብ በማሠባሰብ ወላጅ አልባ ለሆኑ ህፃናት የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች ድጋፍ ስራን በማስፋት 300 መቶ ወጣቶች የምንሆን ወደ አጎራባቻችን ከተማና የዞናችን ዋና ከተማ ግልገል በልስ ማለዳ ላይ በመድረስ የጎዳና ላይ ፅዳት፣ ዲሽ ቦይ የማፋሰስ፣ የቢጫ ቤቶች ፅዳት፣ ግልገል በለስ መንሃሪያና የማንዱራ ወረዳ ፓሊስ ጣቢያ ፅዳትን በማከናውን ተመልሰናል። ምስጋና ለፓዊ ወጣቶች በጎ አድራጎት ማህበር አቅርብልኝ። #tespha get."

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከዲላ⬆️

"ሀይ ፀግሽ በፎቶ የምትመለከታቸው #ወጣቶች በዲላ ከተማ #የእስልምና እምነት ተከታዮች ሲሆኑ በጊዮርጊስ እና አቡኤ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ ስያፀዱ ነበር።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማስታወሻ📌የሁለተኛ ቀን የአፋን ኦሮሞ ትምህርት በ @tikvahethedu ላይ ገብታችሁ መከታተል ትችላላችሁ።

አስተያየት መስጫ አድራሻ፦
0919 74 36 30(Tsegab Wolde)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድሬዳዋ⬆️ኦብነግ ዛሬ #በድሬዳዋ ከተማ ከደጋፊዎቹ ጋር ውይይት አድርጓል። በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የተመከረ ሲሆን ይበልጥ ስለአንድነት እና ስለዘላቂ የክልሉ ሰላም ውይይት ተደርጓል።

©Haym(የስብሰባው ተካፋይ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከኮምቦልቻ⬇️

"በዛሬዉ ዕለት ማለትም ጿግሜ 4/2010
ዓ.ም። በኮምቦልቻ ከተማ 010 ቀበሌ የእልክብዬ ወጣቶች። በበጎ ፍቃደኝነት ረጂ ለሌላቸው ለ62 ተማሪዎች ሙሉ የትምህርት መርጃ መሳሪያ ከተለያዩ ሰዎች አሰባስበን ዛሬ ለተማሪዎቹ አስረክበናል። በተጨማሪም በጣም ለባሰባቸው ለ10 ልጆች ዩኒፎርም አስለክተን በመሰፋት ላይ ነው።ይሄ በጎ ስራችን በዚህ ብቻ አያቆምም ገና ይቀጥላል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በፍቅር #እንደመር በይቅርታ እንሻገር!

ጳጉሜ 4 የመደመር ቀን

በፍቅር እንደመር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና የጋምቤላ ክልሎች ከ550 በላይ ለሚሆኑ የህግ ታራሚዎች #ይቅርታ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።

ለህግ ታራሚዎቹ ይቅርታው የተደረገውም የ2011 ዓ.ም አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ መሆኑን የሁለቱም ክልሎች የማረሚያ ቤት
አስተዳደሮች ገልፀዋል።

የጋምቤላ ክልል የማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ሀላፊ ኮሚሽነር #ቲቶ_ሀዋርያ እንደተናገሩት፥ በክልሉ የተለያዩ ወንጀሎችን በመስራት ተፈርዶባቸው የነበሩ ከ370 በላይ ታራሚዎች ከእስር እንዲፈቱ ተደርጓል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ሀላፊ ኮሚሽነር አዲሱ ሀተሴም በክልሉ የተለያዩ ወንጀሎችን ሰርተው ተፈርዶባቸው የነበሩ 188 ታራሚዎች በይቅርታ መፈታታቸውን አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update⬆️በቅርቡ አንድ ክፍል #ኮንዶሚኒየም የተገዛላቸው #ያብስራ እና #እናቷ ሌላ 230,000 ብር በGo Fund me የተሰበሰበላቸውን ገንዘብ በአቶ ጌታቸው ንጋቱ አማካኝነት ለአዲሱ ዓመት ስጧታ ተብርክቶላቸዋል።

©ENF
@tsegabwolde @tikvahethiopia