TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
የትላንቱ አነጋጋሪ ጉዳይ⬇️

የሥራ ማቆም አድማ አድርገዋል በሚል የተጠረጠሩ 9 የኢትዮጵያ ሲቪል አቬሽን ባለሥልጣን ሠራተኞች በቁጥጥር ሥር ዋሉ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ሰሞኑን የሥራ ማቆም አድማ አድርገዋል በሚል የጠረጠራቸውን 9 የኢትዮጵያ ሲቪል አቬሽን ባለሥልጣን ሠራተኞች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታወቀ፡፡

ፖሊስ አንድ በር ያለውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሥራ ዕንቅስቃሴ ለማስተጓጎል ሕገወጥ የሥራ ማቆም አድማ አድርገዋል በሚል ወንጀል #በመጠርጠር እንደያዛቸው ገልጿል፡፡

የሀገርን ገፅታ ማበላሸት ብቻ ሳይሆን ኢኮኖሚው ላይም አሉታዊ ተፅዕኖ እንዲያደርግ በማሰብ ወንጀሉን ፈፅመዋል የሚለውም ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ካደረጉ ምክንያቶች ተጠቃሽ ነው ብሏል ኮሚሽኑ ለኢቲቪ፡፡

ፖሊስ የመብት ጥያቄ ቢኖራቸው እንኳ እየሰሩ መጠየቅ የሚችሉበትን መፍትሔ መከተል ነበረባቸው ብሏል።

©etv

📌በስራ ማቆም አዳማ ላይ ያሉ የተቋሙን ሰራተኞች አግኝቼ አውርቻለሁ። የነሱን ቅሬታ ወደ በኋላ አቀርበዋለሁ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia