TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
አሁን⬆️ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፣ በኮንግረስማን ክሪስ ስሚዝ የተመራ የልዑካን ቡድንን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው እያነጋገሩ ነው፡፡ የኢትዮጵያና አሜሪካ ግንኙነትን አንድ ምዕራፍ ከፍ የሚደርጉ የሁለትዮሽ ስምምነቶችን እንደሚፈፅሙ ይጠበቃል፡፡

©የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዶክተር #አብረሃም_በላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው #ተሹመዋል። ዶ/ር አብረሀም በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የሳይበር ቴክኖሎጂ ኢንጂነሪንግ ኢኒስቲቲዩት ዳይሬክተር ነበሩ።

©capital
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update መጪው አዲስ ዓመት “በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቋል። የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ፥ በዓሉ ከ25 ሺህ በላይ ህዝብ በሚገኝበት #በሚሊኒየም_አዳራሽ በድምቀት እንደሚከበር ተናግረዋል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ⬆️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በኮንግረስማን ክሪስ ስሚዝ የሚመራውን የአሜሪካ የልዑካን ቡድንን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ውይይታቸውም #በሁለትዮሽ እና #ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር ተብሏል፡፡ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድም በኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት እየታየ ስላለው የፖለቲካ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጦች ለልኡካን ቡድኑ እንዳብራሩላቸው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ ገልጸዋል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ⬆️

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የቬትናም ፕሬዝዳንት የሆኑትን ትራን ዳይ ኩዋንግን አመሻሽ ላይ በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡ ሁለቱ አገራት በባህል፣ በኢኮኖሚያዊ፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ አጀንዳዎች ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን የሁለቱን አገራት ትብብር የበለጠ ለማጠናከር #ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

ፈጣን እድገትን በአጭር ጊዜ ውስጥ ማሳካት ከቻሉት የምስራቅ እስያ አገራት መካከል አንዷ የሆነችው ቬትናም ከኢትዮጵያ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የጀመሩት እ.አ.አ 1976 መሆኑ ይታወሳል፡፡

©የጠቅላይ ሚንስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሱማሌ ክልል⬆️

የሱማሌ ክልል ከ10 አመት በፊት የቀየራቸውን #ሰንደቃላማና የክልሉን #መጠሪያ ስም እንደገና ሊጠቀም እንደሆነ የVOAው ጋዜጠኛ ሀሩን ማሩፍ ጠቆመ።

የቀድሞ የክልሉ ፕሬዘዳንት አብዲ ሞሀመድ ኡመር(አብዲ ኢሌ) ከዛሬ አስር አመት በፊት ክልሉን ለማስተዳደር ሲሾሙ የሱማሌ ክልልን ኢትዮጵያዊነት የበለጠ ለማረጋገጥ በማለት የክልሉን ስም "ከሱማሌ ክልል" ወደ "ኢትዮዽያ ሱማሌ ክልል" ቀይረውታል። በተጨማሪ አብዲ ኢሌ የክልሉን ሰንደቃላማ እንዲቀየር አድርገው ነበር።

©ሀሩን ማሩፍ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መግለጫ⬆️በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶች ሲከናወኑ መቆየቱን የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኢሶህዴፓ/አስታውቋል፡፡ ኢሶህዴፓ የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል ከላይ ባሉት ምስሎች ላይ ሙሉ መግለጫውን ማንበብ ትችላላችሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አርቲስት እና አክቲቪስት ታማኝ በየነ ነሀሴ 26 ወደ ሀገሩ ይገባል። ይህን ተከትሎም የአቀባበል ስነ ስርዓቱን በተመለከት በነገው ዕለት በጌትፋም ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሀርጌሳ⬇️

በሽሽት ላይ የነበሩ የተባሉ የሶማሌ ክልል ሁለት ባለስልጣናት ሶማሊላንድ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ዋዜማ ራድዮ ዘገበ።

የሶማሊላንድ ፖሊስ እንዳስታወቀው የኢትዮ ሶማሊ ክልል የፍትህ ቢሮ ሀላፊ #አብዲ_ጃማ እና የትምህርት ቢሮ ሀላፊ #ኢብራሒም_አደን መሀድ ሀርጌሳ ውስጥ ተይዘው በፖሊስ እጅ ይገኛሉ ተብሏል።

ሁለቱ ሀላፊዎች የክልሉ ፕሬዝዳንት አብዲ መሀመድ ዑመር (አብዲ ኢሌ) በፌደራል መንግስት ሀይሎች መያዛቸውን ተከትሎ ከጅጅጋ ወደ ጎረቤት ሶማሊላንድ እንደሸሹ #ጋሮዌ የተባለው የሶማሊላንድ ጋዜጣ ጠቅሶ ዋዜማ ዘግቧል።

በሌላ በኩል ለዓመታት በስደት የቆዩት የሶማሌ ክልል የመብት ተሟጋቾች የቀድሞ የፓርላማ አባል መሀመድ ድርዬ እና የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አብዲ ኢሌ አማካሪ አብዱላሂ ሁሴን ወደ ሀገር ቤት ተመልሰዋል። በሶማሌና ኦሮሞ ማህበረሰብ መካከል የነበረውን ግጭት ለመፍታት እንሰራለን ብለዋል። ለውጡን ለመደገፍም መዘጋጀታቸውን ተናግረዋለ።

@tsegabwolde @tikahethiopia