#update አዲስ አበባ⬆️
በህብረተሰቡ ሲነሳ የነበረውን የአቅርቦት ችግር ለመፍታት እየሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አስታወቀ። ቢሮው በ49 ሚሊዮን ብር የተገዙ 47 ዘመናዊ አምቡላንሶችን ለጤና ጣቢያዎችና ለሆስፒታሎች የማከፋፈል ሥነ ሥርዓት እያካሄደ ይገኛል። በሥነሥርዓቱ የተለያዩ የከፍተኛ ተቁዋማት አመራሮች መልዕክት አስተላልፈዋል።
©የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update አግ 7⬇️
የ“አርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ” ሊቀመንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፤ 100 ያህል አመራሮችና አባላትን ይዘው በመጪው ሳምንት ወደ ሃገር ቤት እንደሚገቡ የታወቀ ሲሆን ንቅናቄው በሃገር ውስጥ በአዲስ አደረጃጀትና ቅርፅ እንደሚዋቀር ተገልጿል፡፡
ላለፉት 10 ዓመታት ያህል የትጥቅ እንቅስቃሴን ጨምሮ ዋና መቀመጫውን ኤርትራ በማድረግ ሁለገብ ትግል ሲያከናውን የቆየው “አርበኞች ግንቦት 7”፤ በቅርቡ በሃገር ውስጥ በተፈጠረው ምቹ ሁኔታና መንግሥት ባደረገው ጥሪ መሰረት፣ ወደ ሀገር ቤት ተመልሶ፣ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ መወሰኑ ይታወቃል፡፡
የንቅናቄው ሊቀ መንበርና ከፍተኛ አመራሮች በመጀመሪያው ዙር ከሰሞኑ ወደ ሃገር ቤት እንደሚመለሱ አቀባበል ለማድረግ የተዋቀረው ኮሚቴ የገለፀ ሲሆን በቀጣይም በኤርትራ ያሉ የሰራዊት አባላትና ሌሎች አመራሮች በተመሳሳይ ወደ ሃገር ውስጥ የሚመለሱበት ሁኔታ ይመቻቻል ብሏል፡፡
አመራሮቹ ወደ ሃገር ቤት በሚመጡበት ወቅትም ደጋፊዎቻቸው ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ጀምሮ ደማቅ አቀባበል እንደሚያደርጉላቸው የጠቆመው ኮሚቴው፤ ወደፊት አመራሮቹ ከህዝቡ ጋር በሰፊው የሚገናኙባቸው መድረኮች ይፋ ይደረጋሉ ብሏል፡፡
በሀገር ውስጥ በህቡዕ፣ በውጪ ሃገራት፣ በይፋ ሁለገብ የትግል እንቅስቃሴ ሲያደርግ ቆይቷል የተባለው “አርበኞች ግንቦት 7” በቀጣይ ራሱን ከንቅናቄ ወደ ፖለቲካ ፓርቲነት ቀይሮና በህጋዊነት ተመዝግቦ በዜግነት ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ስልት በመከተል ለምርጫ ውድድር እንደሚቀርብ ተገልጿል፡፡
ከሊቀመንበሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር ከሚመለሱት አመራሮች መካከል አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ፣ ዶ/ር ታደሰ ብሩ፣ አቶ ኤፍሬም ማዴቦ፣ ዶ/ር አዚዝ መሐመድ እና አቶ ነአምን ዘለቀ ይገኙበታል፡፡
በሀገሪቱ የጠቅላይ ሚኒስትር ለውጥ ከተደረገ በኋላ ከተወሰዱ የፖለቲካ ማሻሻያዎች አንዱ በሽብርተኝነት የተፈረጁ ድርጅቶችን ፍረጃ በማንሳት ወደ ሃገር ውስጥ እንዲገቡ የተደረገው ጥሪ ሲሆን በዚህ መሰረት እስካሁን ከ10 ያላነሱ ተፅዕኖ ፈጣሪ የፖለቲካ ድርጅቶች ወደ ሃገር ውስጥ ተመልሰዋል፤ 25 ያህሉም ለመመለስ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡
ወደ ሃገር ውስጥ ከተመለሱት መካከል የአፋር ብሔራዊ ንቅናቄ፣ የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ትብብር፣ የትግራይ ህዝብ
ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የአማራ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)፣ የኦሮሞ አቦ ነፃነት ግንባር፣ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ህብረት፣ የኦሮሞ ዲሞክራሲዊ ግንባር (ኦዴግ) እንዲሁም የኦጋኤን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) ይገኙበታል፡፡
ምንጭ፦ አዲስ አድማስ

#update እየሩሳሌም ሆቴል⬆️
የአርበኞች ግንቦት 7 አባላት እና ደጋፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ እየሩስሌም ሆቴል በዛሬው ዕለት ተወያይተዋል።
ተጨማሪ መረጃ እየተላከ ይገኛል እንደደረሰኝ አቀርባለሁ!
ፎቶ፦ ቢንያም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአርበኞች ግንቦት 7 አባላት እና ደጋፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ እየሩስሌም ሆቴል በዛሬው ዕለት ተወያይተዋል።
ተጨማሪ መረጃ እየተላከ ይገኛል እንደደረሰኝ አቀርባለሁ!
ፎቶ፦ ቢንያም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ቴዲ አፍሮ⬇️
የድምፃዊ ቴዲ አፍሮ የአዲስ አመት ዋዜማ ኮንሰርት #መሰረዙ ተሰምቷል። ኢትዮፒካሊንክ የተባለው የራድዮ ዝግጅት ከአዘጋጆቹ የቅርብ ሰዎች ሰምቻለሁ ብሎ ይፋ ባደረገው መረጃ የቴዲ አፍሮ የሚሊንየም አዳራሽ ኮንሰርት በዋዜማው አይደረግም። ኮንሰርቱ የማይደረግበት ምክንያት በግልፅ አልታወቀም።
*በመስከረም አጋማሽ የቴዲ ኮንሰርት በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ ከአዘጋጆቹ ተሰምቷል።

የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ በሰኔ 16 የድጋፍ ሰልፉ ላይ በደረሰው አደጋ ለተጎዱት ወገኖቻችን አስፈላጊውን የህክምና አገልግሎት ለሰጡ የጤና ተቋማት የማበረታቻ ሽልማት ሰጥቷል።

ከባህር ዳር⬆️
"ሰላም ፀግሽ እንዴት ነህ? ሰላም ለኢትዮጵያና ልጆቿ እናም ለሰውልጅ በሙሉ! እኔ አስራር አማን እባላለሁ ከባህርዳር ወሰን የለሽ የበጎ ፍቃደኛ ወጣች ቡድን "ደም ያስተሳስረናል" በሚል ደስ የሚል መፈክር መደመርን በተግባር ባረጋገጠመልኩ ደም እየለገስን ውለናል። ለአካባቢውም ሰዎች ትልቅ ምስጋና ይገባቸዋል በትልቅ ወኔ በመኪናቸው ጭምር በመምጣት ደም ለግሰዋል። "ደም ያስተሳስረናል" ደሜ ለወገኔ አሁንም ባንድነታችን ሰላማችን ይረጋገጣል። ትንሽ ብዥታ ያለባቸው ሰዎች ሊማሩበት ይገባል አጥፊውም እኛ ጠፊውም እኛ ከመሆን እነቆጠብ ለወጣቶች በሙሉ መልክቴ ነው።"

በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የተገዙ አምቡላንሶች ለጤና ጣቢያዎችና ለሆስፒታሎች የቁልፍ ርክክብ ሲደረግ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ መልዕክት አስተላልፈዋል።