TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#update ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ⬇️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር በአዛዥነት እና ስታፍ ኮሌጅ ያሰለጠናቸውን ከፍተኛ መኮንኖችን ሲያስመርቅ ከተናገሩት ዋና ዋና ነጥቦች:-

• ነፃነትና ስርዓት አልበኝነት ባለመለየት #መረን የወጣ ሕግና ስርዓትን የማያከብር የመንጋ ፖለቲካ ኢትዮጵያ ውስጥ መቆም ይኖርበታል፡፡

• ሕጋዊ ስርዓትን እያደከምን በመንጋ የሚሰጥ ፍትሕ ተከትለን የፍትሕ ስርዓቱን በግል ስሜት መንዳት የለብንም፡፡

• ሕግ አልባና አመጽን የሚታገስ ስርዓት እንደ አገር መቆጠራችንን ከንቱ ስለሚያደርግ አገራዊ አንድነታችንን በሕግ አግባብ ማስጠበቅ የዘወትር ተልዕኮአችን ይሆናል፡፡

#ዘመናዊነት የሕግ የበላይነት ማክበር ነው፡፡

• እንደመር፣ በይቅርታ አንድ አገር እንገንባ ስንል ከመረን እንውጣ፣ ሕግ አናክብር በየከተማው ሽፍታ ይበራከት ማለት አለመሆኑን በአንክሮ ማስገንዘብ እፈልጋለሁ፡፡

• የይቅርታው ዓላማ በለፍንበት መንገድ ያጠናውን ለማግኘት እንጂ የገነባነውን አገር ለማፍረስ ስላልሆነ እያንዳንዱ ዜጋ ይህ ከአብራኩ የወጣውንና በአነስተኛ ደሞዝ ሕይወቱን እየገበረ የአገር አንድነትን የሚያስጠበቀውን ኃይል የመውደድ፣ የማክበር፣ የሞራል ድጋፍ
የመስጠት ኃላፊነት አለበት፡፡

• በጄኔራል ሰዓረ መኮንን ያየነውን የመከላከያ አንድነት እና የለውጥ ኃይል መሆኑን የማስቀጠል ፍላጎት በሁሉም ጄኔራል መኮንኖች እንዲደገም፣ በጡረታ የተገለሉ ጄኔራሎች ለወታደር ጡረታ ስለማይሰራ በየትኛውም ጊዜ ችግር ካጋጠመን እናት አገር ጥሪ ልታቀርብላችው ስለሚትችል ቀርባችሁ ሁኔታ እያያችሁ በመምከር፣ በማገዝ፣ በመደገፍ፣ ወገናዊነታችሁን ማረጋገጥ እንዲትችሉ፣ እንዳትበተኑ፣ አንድ ሆናችሁ አንዲት ኢትዮጵያን እንዲታጠናከሩ አደራ ማለት እፈልጋሉ፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ዘመናዊነት የሕግ የበላይነት ማክበር ነው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia