#update ደብረ ብርሀን⬆️
"ዛሬ በደብረ ብርሀን በወሰን ተሻጋሪ በጎ ፍቃደኞች አማካኝነት ከደብረ ብርሀን ዩንቨርስቲ ማህበረሰብ የተሰበሰበ በጣም ብዙ አልባሳት፣ አንሳላ እና ሳሙና ለሀበሻ አረጋዋይን እና ምስኪኖች መርጃ ልማት መአከል አበርከተናል።"
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update ሶማሌ ክልል⬇️
የፌደራል መንግሥት የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስን ትጥቅ ለማስፈታት ዕቅድ እንደሌለው በሃገር መከላከያ የኢንዶክትሬኔሽንና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ሜጀር ጀነራል ሞሃመድ ተሰማ ለቢቢሲ ገለጹ።
ሜጀር ጀነራል ሞሃመድ ''የፌደራል የፀጥታ ኃይል የሶማሌ ክልልን የፀጥታ ኃይል ትጥቅ የማስፈታት ዓላማ ይዞ አልተንቀሳቀሰም። ልዩ ኃይሉ ቀድሞም እንዲሰለጠን እና እንዲታጠቅ ያደረገው የፌደራሉ መንግሥት ነው" ብለዋል።
ጨምረውም ልዩ ኃይሉ ሰልጥኖና ታጥቆ ከክልሉ መንግሥት ጋር ብዙ ሥራ መስራቱንና አሁንም እየሰራ መሆኑን ተናግረው፤ "በአሁኑ ወቅትም ልዩ ኃይሉ ፀጥታ የማስፈኑ ሥራ አካል ሆኖ እንዲሰራ የማድግ ተግባር እየተከናወነ እንጂ ትጥቅ የማስፈታት ዓላማም ሆነ ዕቅድ የለም'' ብለዋል።
የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና ተቺዎች የክልሉ ልዩ ፖሊስ አመሰራረት ምንም አይነት የህግ መሰረት የለውም ቢሉም፤ ሜጀር ጀነራል ሞሃመድ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉት ሁሉም ክልሎች ውስጥ የልዩ ኃይል አደረጃጀት እንዳለ አመልክተዋል።
"መደበኛ ፖሊስ፣ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻዎች አሉ። የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልልም እንደማንኛውም ክልል የልዩ ኃይል ፖሊሶችን አሰልጥኖ በማሰማራት ከፌደራል ኃይል ጋር የፀጥታ ማስከበር ሥራዎችን ሲሰራ ቆይቷል። በዚህም በአካባቢው የተሻለ መረጋጋት ተፍጥሯል።
ከሕጋዊ ዕውቅና ውጪ የተቋቋመ አልነበረም'' ብለዋል። ልዩ ፖሊስ የታጠቀው መሳሪያ የሌሎች ክልል ፖሊሶች ከሚታጠቁ መሳሪያ አንጻር ከባድ እና የዘመነ ነው እየተባለ ለሚነሳው ቅሬታም ሜጀር ጀነራል ሞሃመድ በሶማሌ ክልል የፀጥታ ችግር እንደነበረና ይህን ችግር ለመቅረፍ ከፌደራል የፀጥታ ኃይል ጋር ልዩ ኃይሉን የማጠናከር እና የማዘጋጀት ሥራ መከናወኑን ተናግረዋል።
"በዚህም የፀጥታ ችግሩንም ለመቅረፍ ተችሏል። አሁን ምንድነው መስተካከል ያለበት በሚለው ላይ መንግሥት በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት የሚከናወን ይሆናል። በወቅቱ ግን አስፈላጊ ነገር ስለሆነ የተደረገ ነገር ነው'' ብለዋል።
የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል በተደጋጋሚ በክልሉ ውስጥ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እንደሚፈጽም ዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋቾች እንዲሁም በሶማሌ እና ኦሮሚያ ክልል ድንበር አቅራቢያ የተፈናቀሉ ዜጎች በተደጋጋሚ ገልጸዋል።
ሜጀር ጀነራል ሞሃመድ የሶማሌ ልዩ ኃይል አባላት ብዛት እና አደረጃጀት ላይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል።
©BBC

#update ምስራቅ ሀረርጌ⬇️
በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሐረርጌ ዞን በማዩ ሙሉኬ ወረዳ የሶማሌ ልዩ የፖሊስ ኃይል በትንሹ 40 ያህል የኦሮሞ ተወላጆችን መግደሉና ከ40 በላይ በሚሆኑ ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ማድረሱ ይታወቃል፡፡
የኦሮሚያ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) በወረዳው በሶማሌ ልዩ ፖሊስ በተፈጸመ ጥቃት 40 ሰዎች መገደላቸውን ገልጸው፣ ድርጊቱ የተፈጸመው በቅርቡ ከሥልጣናቸው በፌዴራል መንግሥት እንደተወገዱ በሚናገሩ ሰዎች ትዕዛዝ ነው ብለዋል፡፡
በሶማሌ ልዩ ኃይል አባላት የሁለቱን ክልሎች አዋሳኝ በመጣስና ከበድ ባሉ መሣሪያዎች በመታገዝ ጥቃቱን መፈጸማቸውን አስታውቀዋል፡፡
በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ሐምሌ 28 እና 29 ቀን 2010 ዓ.ም. በተፈጸመው ግድያ፣ ዘረፋ፣ የአብያተ ክርስቲያናት ቃጠሎና ከቀዬ መፈናቀል ምክንያት፣ የአገር መከላከያ ሠራዊት ወደ ክልሉ በመግባቱ የሶማሌ ልዩ ፖሊስ ኃይል ማፈንገጡ ሲነገር እንደነበር ይታወሳል፡፡
በመሆኑም የመከላከያ ሠራዊቱ ጅግጅጋና ሌሎች ከተሞች መግባቱንና ቀድሞ የነበሩ የክልሉ አመራሮች ከሥልጣን በመውረዳቸው ቅር የተሰኘው ልዩ የፖሊስ ኃይል፣ ወደ ኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ማዩ ሙሉኬ ሄዶ ጥቃት ማድረሱን የተጎጂ ቤተሰቦች ገልጸዋል፡፡
ነሐሴ 5 እና 6 ቀን 2010 ዓ.ም. ቤት ለቤት በመግባት በሕፃናት፣ በአዛውንቶች፣ በወንዶችና በሴቶች ላይ ጥቃቱን መፈጸሙን ተጎጂዎች ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡
ልዩ የፖሊስ ኃይሉ ድርጊቱን እንዲፈጽም ያደረጉት ከሥልጣን እንዲወርዱ የተደረጉ አመራሮች መሆናቸውን፣ በተፈጠረው አደጋም 40 ያህል ግለሰቦች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልጿል፡፡ መንግሥት ልዩ ክትትልና ጥበቃ ካላደረገላቸው በስተቀር አሁንም ሥጋት ውስጥ መሆናቸውን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡
©ሪፖርተር

#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አዲሱን አመት በአገር ቤት እንዲያከብሩ ባደረጉት ግብዣ መሰረት ዳያስፖራዎች አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል። ዛሬ ማለዳ ላይ ከአሜሪካ፣ ካናዳ፣ ለንደንና ሳዑዲ አረቢያ የገቡትን የመጀመሪያ ዙር የዳይስፖራ አባላትን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊና የኢትዮጵያ የቱሪዝም ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ፍጹም አረጋና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች ተቀብለዋቸዋል።
©ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
©ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አቶ ተስፋዬ ኡርጌ⬇️
በብሄራዊ መረጃና ደህንነት መምሪያ አዛዥ ናቸው ተብለው በሰኔ 16ቱ የቦምብ ጥቃት በመምራትና በማስተባበር ተጠርጥረው ጉዳያቸው በፌደራል ፖሊስ ምርመራ ላይ የሚገኙት አቶ ተስፋዬ ዑርጌ በአሁኑ ወቅት በሃገሪቱ #በተለያዩ አካባቢዎች ከተከሰተው ግጭት የጦር መሳሪያና የገንዘብ ድጋፍ ጋር በተያያዘ #እጃቸው እንዳለበት መርማሪ ፖሊስ ገለጸ።
የፌደራሉ የመጀመሪያ ተረኛ 1ኛ የወንጀል ችሎት መርማሪ ፖሊስ ያከናወናቸውን ስራዎች አድምጧል።
በዚህም መርማሪ ፖሊስ በአዲስ አበባ እና በክልል የሚገኙ ተባባሪ ተጠርጣሪዎችን መያዣ የማውጣት፣ የምስክር ቃል የመቀበል እና ሌሎች ስራዎች ማከናወኑን ገልጿል።
በሃገር ውስጥና በውጭ ሃገር በተፈጸመው ጥቃት በመነሻነት እጃቸው አለበት የተባሉ አካላትን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከሃገራቱ ጋር እየተወያየ መሆኑንም ጠቅሷል።
የቀሪ ምስክሮችን ቃል ለመቀበል፣ በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠሩ ግጭቶች ላይ ከተጠርጣሪው ጋር ግንኙነትና እጃቸው አለበት የተባሉ ተጠርጣሪዎችን የማጣራት ስራ እና ሌሎች ቀሪ ስራዎችን ለማከናወንም 14 ተጨማሪ ጊዜ ጠይቋል።
የተጠርጣሪ ጠበቃ በበኩላቸው በቅድሚያ ተጠርጣሪውን የማረሚያ ቤት ልብስ በማልበስ በምስል አስደግፈው የሚለቁና የግለሰቡን ስም እየጠቀሱ ሚዛናዊ ያልሆነ ዘገባ የሚያቀርቡ የሚዲያ አካላት እንዲያስተካክሉ ትዕዛዝ ይሰጥልኝ ብለዋል።
በተጨማሪም መርማሪ ፖሊስ ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት አላቸው ያላቸውን አካላት አጠናቅቄያለሁ እያለና አቃቢ ህግ ክስ ለመመስረት ጊዜ እየጠየቀ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ሊጠይቅ አይገባም በማለትም ተቃውመዋል።
ከዚህ ባለፈም መርማሪ ፖሊስ የምርመራ ስራውን በፍጥነት እየሰራ አይደለም በማለት ፍርድ ቤቱ ከፍትህ ገጽታ አኳያ ሊያየው እንደሚገባም ተቀውሟቸውን አሰምተዋል።
ከዚህ ባለፈም ተጠርጣሪ የዋስትና መብት ተፈቅዶላቸው ምርመራው ቢቀጥል የሚፈጥረው ችግር የለም በማለትም የዋስትና መብታቸው እንዲከበርም ጠይቀዋል።
መርማሪ ፖሊስም ተጠርጣሪው በዋስ ቢወጡ የምርመራ ሂደቱን በማደናቀፍ ማስረጃ ሊያሸሹ ይችላሉ በማለት ዋስትናውን ተቃውሟል።
ጉዳዩን የተከታተለው ፍርድ ቤትም ማንኛውም ሚዲያ የሁለቱን ወገን ጉዳይ በሚዛናዊነት እንዲያቀርብ በማለትና ዋስትናውን በማለፍ ለፖሊስ ተጨማሪ 8 ቀን ሰጥቷል።
©FBC

#update በኦሮሚያ ክልል በ2011 በጀት ዓመት ከ1 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር መታደቁ ተገልጿል። ለስራ እድል ፈጠራውም 3 ነጥብ 283 ቢሊየን ብር ብድር ተዘጋጅቷል።
©OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
©OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኤርትራ⬇️
የአማራ ክልል ልዑካን ወደ አስመራ እንደሄዱ ተሰማ። ልዑካኑ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩ ይጠበቃል።
©አ.ብ.መ.ድ

#update ሀረሪ ክልል⬇️
የሀረሪን ክልል የሚያስተዳድሩት ሀብሊንና ኦህዴድ የክልሉ ህገ-መንግስት እንዲሻሻል ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተሰምቷል፡፡ የክልሉ ህገ-መንግስት የሚሻሻለው ጊዜውንና ወቅቱን የማይመጥን በመሆኑ ነው ተብለዋል፡፡
©Ma

#update አቶ ተስፋዬ ኡርጌ በአሁኑ ወቅት በሃገሪቱ #በተለያዩ አካባቢዎች ከተከሰተው ግጭት የጦር መሳሪያና የገንዘብ ድጋፍ ጋር በተያያዘ #እጃቸው እንዳለበት መርማሪ ፖሊስ ገለጿል።
◾️አቶ ተስፋዬ ኡርጌ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት መምሪያ አዛዥ ነበሩ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
◾️አቶ ተስፋዬ ኡርጌ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት መምሪያ አዛዥ ነበሩ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወንጀል ነክ መረጃ⬇️
ፍቅረኛውን የገደለው ግለሰብ በጽኑ እስራ ተቀጣ፡፡ በየካ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 17/18 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ልዩ ቦታው ኮተቤ ሀና ማሪያም በግምት ከሌሊቱ 10፡00 ሰዓት ሲሆን ነው ወንጀሉ የተፈጸመው፡፡
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 539/1/ሀ ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ነው ክስ የተመሰረተበት፡፡
የወንጀሉ የአፈጻጸም ሁኔታ እንደሚያስረዳው ተከሳሽ ይመኑ አለማየሁ ሰውን ለመግደል አስቀድሞ በማሰብ ህዳር 09 ቀን 2008 ዓ.ም
ከሟች ወ/ሪት ኩላኔ ገለልቻ ጋር አንድ ላይ በጓደኝነት በሚኖርበት ቤት ውስጥ ሟች ሌላ ወንድ ልታገባ ነው በሚል ቂም መነሻነት በጩቤ የግራ ፊቷን፣ አንገቷን እንዲሁም ሆዷን በመውጋት ከባድ አካላዊ ጉዳት ያደረሰባት በመሆኑ ከፍተኛ ደም በመፈፍሱ ምክንያት እና ወሳኝ የሰውነት አካሎቿ ስለተጎዱ ህክምና ሳይደረግላት ህይወቷ ወዲያውኑ ያለፈ በመሆኑ በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቢ ህግ የልደታ የወንጀልና ፍታብሄር ፍትህ አስተዳደር ዘርፍ የልዩ ልዩ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት የክስ መዝገብ ያስረዳል፡፡
የክሱን ሂደት ምርመራ እና ክትትል ሲያገናዝብ የቆየው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎትም ተከሳሽ የፌደራል ዐቃቤ ህግ የመሰረተበትን ክስ ማስረጃ እንዲያቀርብ ቢጠየቅም ተገቢውን ማስረጃ ማቅረብ አልቻለም፡፡ በዚህም መሰረት ዐቃቤ ህግ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አጠናቅሮ ለፍርድ ቤቱ ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱም የቀረበለትን ማስረጃ ከመረበረ በኋላ ተከሳሽን ጥፋተኛ ነህ ብሎታል፡፡
የግራ ቀኙን ክርክር የተመለከተው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎትም 4ኛ ወንጀል ችሎትም ሀምሌ 03 ቀን 2010 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ15 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎበታል፡፡
ምንጭ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ

TIKVAH-ETHIOPIA via @like
"አለመግባባት መፍትሄ የሚያገኘው በውይይት ወይም በኃይል ከሁለቱ መንገዶች በአንዱ ነው። የመጀመሪያው የሰው ባህሪ ሲሆን ሁለተኛው ግን የአራዊት ነው።"
ቺቸሮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቺቸሮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA አብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍል ሰላም ውሏል። ትላንት ችግር የነበረባቸውም ቦታዎች ሰላም ነው የዋሉት። በሁሉም ክልል ያላችሁ የቻናላችን ቤተሰቦች እናመሰግናለን ለዕለታዊው መረጃ።
ምሽቱን እና ለሊቱን ሰላም ያድርግልን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምሽቱን እና ለሊቱን ሰላም ያድርግልን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA via @like
#ሀጫሉ_ሁንዴሳ
.
.
.
"ኢትዮጵያ የ80 ብሄር ብሄረሰቦች ቅልቅል ውጤት ናት። በኢትዮጵያዊነቴ ማንም ሰው አንተ ኢትዮጵያን አትወድም አንተ ኢትዮጵያን ትወዳለህ ሊለኝ አይችልም።
.
.
ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው ምክንያቱም 80 ቀለም ስላለው"
ሀጫሉ ከFBC ጋር በነበረው ቆይታ ብዙ ጉዳዮችን አንስቷል። ከዛ መሀል መርጬ ነው ያቀርብኩላችሁ።
ከተናገራቸውን ንግግሮች መካከል ሌሎቹን በፅሁፍ ላቅርባቸው ወይስ ቆይታውን በድምፅ ወደናተ ላድርስ??
በድምፅ✳️
በፅሁፍ✅

#update ሱማሌ ክልል⬇️
መንግስት በሶማሌ ክልል ተከስቶ በነበረው ሁከት የተሳተፉ አካላትን በአፋጣኝ ለህግ በማቅረብ ተጎጂዎችን መካስ እንዳለበት የክልሉ የሃይማኖት አባቶች፣ የጎሳ መሪዎችና የአገር ሽማግሌዎች ጥሪ አቀረቡ፡፡
በክልሉ ተፈጥሮ የነበረው ሁከት እንዳሳዘናቸውና ድርጊቱ የሶማሌ ማህበረሰብ ነባር እሴትን ማይወክል መሆኑንም አክለዋል፡፡
እነዚህ የማህበረሰብ መሪዎች ይህን ያሉት ዛሬ ከአገር መከላከያ ሰራዊት ኢንዶክትርኔሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይርክተር ሜጀር ጀኔራል ማህመድ ተሰማ ጋር ወይይት ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡
ሁከቱን የፈጸሙት አካላት የተደራጁ ቡድኖች መሆናቸውን ጠቅሰው፤ መንግስት ይህን የፈጸሙ አካላትን በፍጥነት ለህግ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል፡፡

#ሀጫሉ_ሁንዴሳ ከፋና ጋዜጠኛ ጋር በነበረው ቆይታ በርካታ ጥያቄዎች ተነስተውለት መልሷል።
እኔም ዝግጅቱን ከሰማው በኋላ የአቅሜን ከዚህ በታች በፅሁፍ አስቀምጬዋለሁ።
.
ጥቂት ስለ ጂራ...?
ጂራ ማለት አለን ማለት ነው። የህዝቡን ስነ ልቦና ስታይው አለን የሚያስብል ነው።... ጂራ ኤርትራም ገብቷል። ህዝብ ተለያይቶ አይለያይም። ኤርትራዊያንም ጂራ ገብቷቸዋል ማለት ነው።
.
.
ስለ ስሙ...??
ሀጫሉ ማለት "ይብለጥ" ማለት ነው። አባቴ በልጅነቴ ፈጣን እና ንቁ ስለነበርኩ ያወጣልኝ ስም ነው። እኔ ከማንም እበልጣለሁ ብዬ አላስብም።"
.
.
ስለ ዶክተር አብይ...??
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ የሀገራችን ህዝቦች ዴሞክራሲ ምን እንደሚመስል ያዩ ይመስለኛል። ባልተለመደ መልኩ የሰው ልጅ የተሰማውን በአደባባይ እንደፈለገ እንዲናገር ...ከሀገራችን ህዝብ አምዕሮ በላይ የሆኑ ነገሮች ታይተዋል።
#ግን ህዝባችን ለመላመድ ጊዜ የሚያስፈልገው ይመስለኛል። ሲረገጥ፣ ሲጨቆን፣ ሲበደል የነበረ ህዝብ በአንድ ጊዜ እንደዚህ ፈሪሀ እግዚያቤር ያለው መሪ መጥቶ #እንደፈለክ ሁን ሲለው ያን እራሱ እንዴት አድርጎ መሆን እምደሚችል ላያቅበት ይችላል።
በአጠቃላይ ጥንቃቄ ያስፈልጋል ከመንግስትም ከህዝብም እንጂ በሂደት የሚስተካከል ይመስለኛል።
.
.
.
ስለ ሀምሌ 7 የሚሊኒየም አዳራሽ ዝግጅት...?
እኔ እንደዛን ዕለት ቦታና ወቅቱን መርጬ ያስተላለፍኩት መልዕክት ያለም አይመስለኝም። ጠቅላይ ሚንስቱር ግና እንደተመረጡ ...እያንዳንዱን በየፕሮፌሽኑ ልምድ ሲሰጡ ነበር አርቲስቱንም እንደዛው የህዝባችሁን ጩኸት አሰሙ ያመናችሁበትን ስሩ ብለው ነው የመከሩት። የሳቸው ምክር More ጉልበት ሆኖኛል። እኔ የዛን ቀን ምንም ሀጢያት አልሰራሁም። እኔ ኢትዮጵያ የማውቃት #አዲስ_አበባ ብቻ አይደለችም። ምናልባት ድግስ ሊኖር ይችላል አዲስ አበባ ላይ ...መተማ ላይ ኢትዮጵያዊ ከሞተ ኢትዮጵያዊ እየሞተ ነው ብሎ address ማድረግ ..ሀረር ላይ ኢትዮጵያዊ ከሞተ ኢትዮጵያዊ እየተገደለ ነው ስለዚህ መንግስት አንድ ነገር ማድረግ አለበህ ብሎ በጥበብ መልክ ለማስተላለፍ እኔ ቦታው ነው ቦታው አይደለም ብሎ ማሰብ ተገቢ ነው ብዬ አላምንም። እንግዳን መናቅ አይመስለኝም።
.
.
ሀጫሉ ዘረኛ ነው ይሉሀል??
#ዘረኛ ነህ ካልሽኝ ዘረኛ #አደለሁም። እኔ ያሳደገኝ እና የወጣሁት ከኦሮሞ ማህበረሰብ ነው። በኦሮሞ ማህበረሰብ #ዘረኝነት ይኮነናል። በገዳ ስርዓት ውስጥ ዘረኝነት ይኮነናል። ዘረኛ መሆንም #አልችልም። ዘረኛ ብሆን ኢንተቪው የምናደርገው በአስተርጓሚ ነው።
አፌን የፈታሁት በኦሮሚኛ ነው። ዘረኛ ስላልሆንኩ ነው በአማርኛ የማወራው። ለሌላውም ቋንቋ አድናቆት እና ክብር አለኝ።
በምን አይነት መልኩ ተረድተውኝ እንደዚህ እንዳዚህ እንዳሉኝ ሊገባኝ አይችልም። ምናልባት የሚመስለኝ እሱ የሚዘፍነው ኦሮሞ...ኦሮሞ...ኦሮሚያ እያለ ነው የሚል ከሆነ ኦሮሞና ኦሮሚያ ከኢትዮጵያ ውጭ አይደሉም። ኦሮሞ ሆኜ ስለ ሱዳን እና ስለ ኬንያ ብዘፍን ነው የሚያስወቅሰኝ። ለምሳሌ አንድ ዘፈን አለ የሻምበል በላይነህ ዘፈን...
ወልቃይት ጠገዴ፤ ሰሜን አርማጭሆ ዳንሻና ሁመራ
ሰውም ጎንደሬ ነው መሬቱም ያማራ ..ብሎ የሚዘፍነው ዘፈን አለ ይሄ ዘረኝነት ሊያስብለው አይችልም።
.
.
.
ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን እንዴት ታየዋለህ...??
ኢትዮጵያ painting ናት ለኔ። ኢትዮጵያን ስንስላት 80 ቀለሞችን ቀላቅለን ነው የምንስላት። እነዛ 80 ቀለሞች የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ናቸው። ለኔ ኢትዮጵያዊነት የ80 ብሄር ብሄረሰቦች ቅልቅል ውጤት ናት። በኢትዮጵያዊነቴ ማንም ሰው አንተ ኢትዮጵያን አትወድም አንተ ኢትዮጵያን ትወዳለህ ሊለኝ አይችልም። #ምክንያቱም ቅድመ አያቴ ቦንሲቱቃበታ ከዚህ #መቀሌን ነፃ ለማውጣት በእግሯ ስትጓዝ ኦሮሞ እዛ ስላለ አይደለም። እኔ የአያቴ አስክሬን ሲሸ ኝ አውቃለሁ ሲፎከርላት የነበረው በፈረስ .."ቦንሲቱ ጋፋ መቀሌ እየተባለ ቦንሲቱ ያኔ በመቀሌ ጊዜ..." እየተባለ ሲፎከርላት ነው አስክሬና ሲሸኝ የነበረው።
በህይወት የሌሉ ቅድመአያቶቼ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ለማስከበር አጥንታቸውን ከስክሰዋል።
ማንም ሰው ሀጫሉ #በኢትዮጵያዊነቱ ላይ እንደዚህ ያለ አቋም አለው የለውም የሚል መብት የለውም ምክንያቱም እኔ ስለማውቀው። ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው። ምክንያቱም 80 ቀለም ስላለው።
.
.
ስጋት አለኝ ስጋቴ ምንድነው ...ድሮ መንግስት ሀላፊነቱን ይረሳና ጡንቻውን የሚያሳይበት ነበር። ያን ነገር ምስኪን ህዝብ ለመቀየር ይሄ ነው የማይባል መስዋትነት ከፍሏል። ከከፈለ በኋላ አሁን ይመስለ ኛል በተወሰነ መልኩ ባልተጠበቀ መንገድ ህዝባዊነት የሚታይበት ነገር አለ ስጋቴ ምንድ ነው ይሄን መንግስት መያዝ እንዳያቅተው ነው ስጋቴ። ጥንቃቄ እንደሚፈልግ እና በጥንቃቄ ማየት እንዳለበት።
.
.
በቀጣይ ስለ ሚሰራው ስራዎች...??
አሁን ከመንግስት ትወርጅና ደግሞ misunderstanding ተፈጥሮ ልዩነት ማስፋት ሳይሆን በማጥበብ ሀገርን ማኖር እንደሚቻል #በመከባበር አንዱ ያንዱን ሀሳብ ለማድመጥ በመዘጋጀት በመተማመን፣ በመነጋገር አብሮ ለመኖር እንደሚቻል የሚያሳዩ ስራዎችን ለመስራት ነው ወደፊት የማስበው።
.
.
ጎንደር ተውልከድ ወይም መቀሌ ተወልደክ ቢሆን ኖሮ የአሁኑን አይነት ሰው ትሆን ነበር??
#ጎንደሬነቴ ክብሬ ነው! ማለቴ አይቀርም..
.
.
.
ከሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ምን ተማርክ?
(ሀጫሉ የኢትዮጵያ ባለውለታው ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ዘመንድ እንደሆነ ይታወቃል)
.
.
ኢትዮጵያዊነታቸውን እና ኦሮሞነታቸውን እንዴት እንዳካሄዱት ነው የተማርኩት።
.
.
.
ለኢትዮጵያ ህዝብ ምን ሙዚቃ ትጋብዛቸዋለህ??
.ጂራ...ጂራ...ጂራ...(የራሱን ሙዚቃ)
.
.
.
የነዋይ ደበበ - የክብሬ መመኪያ (በራሱ ድምፅም ትንሽ አንጎራጉሯታል)
የክብሬ መመኪያ ደስታና ህይወቴ
ሌላ ምን ሀብት አለኝ ሀገሬ ናት ሀብቴ
እሰይ እሰይ ...ዛሬም እሰይ ነገም እሰይ
#ኢትዮጵያ እምዬ...
ሀጫሉ ሁንዴሳ ከፋና ብሮድክስቲንግ FM 98.1 ጋር በነበረው ቆይታ!
ማሳሰቢያ ከይቅርታ ጋር፦ ምናልባት የቃላት ስህተት አፃፃፍ ላይ ካለ እርማት ስጡበት።

#update የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሑጃጆች ላይ የሚያደርሰውን እንግልት በመቃወም ዛሬ ምሽት ከ3 ሰዓት እስከ 5 ሰዓት የዘለቀ የትዊተር ዘመቻ ተካሂዷል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA via @like
#update ሀዋሳ⬇️
በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች የቆዩ ተፈናቃዮችን ወደቀደመ ኑሯቸው የመመለሱ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
በሀዋሳ ከተማ ሰኔ ወር ላይ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር በተለያዩ ጊዜያዊ መጠለያዎች ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ወገኞች ተጠልለው እንደቆዩ ይታወቃል፡፡
በዚህ ሳቢያ በሀዋሳ ከተማ በ7 ጊዜያዊ መጠለያዎች የቆዩት በድምሩ 3250 አባወራ/እማወራዎች መሆናቸውንም መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
ከዚህ ግጭት በኋላ የከተማ አስተዳደሩ፣ የክልሉ መንግስት፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች በሰሩት ሰፊ ስራ ከተማዋ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደቀደመ ሰላምና መረጋጋቷ ተመልሳለች፡፡
በዚህ ሂደት ውስጥ ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በካምፖች የሚገኙ ወገኖችን ማንነትና፣ የሚኖሩበትን አካባቢ የመለየት ስራ ተሰርቶ በአደጋ መከላከል norm/ስታንዳርድ ወይም መስፈርት መሰረት የገንዘብና የአንድ ወር ቀለብ ድጋፍ ተደርጓል፡፡
1ኛ. በዚህም የግል ቤት ላላቸውና ቤተሰብ ለመሰረቱ የ12ሺህ ብርና የአንድ ወር ቀለብ፣
2ኛ. የግል ቤት ላላቸውና ቤተሰብ ላልመሰረቱ 6 ሺህ ብር እና የአንድ ወር ቀለብ፣
3.ኛ በኪራይ ቤት ለሚኖሩና ቤተሰብ ለመሰረቱ 9 ሺህ ብርና የአንድ ወር ቀለብ፣
4ኛ. በኪራይ ቤት ለሚኖሩና ቤተሰብ ላልመሰረቱ 6ሺህ ብርና የአንድ ወር ቀለብ፣
5ኛ. በመንግስት ቤት ለሚኖሩ 6ሺህ ብርና የአንድ ወር ቀለብ፣
6ኛ. በካምፕ ውስጥ ለቆዩና የመኖሪያ አድራሻቸው ለማይታወቅ 6ሺህ ብርና የአንድ ወር ቀለብ ድጋፍ የተደረገ ከመሆኑም ባሻገር በግጭቱ ምክንያት ቤትና ንብረት ለተጎዳባቸው ግምት ተሰልቶ የማስጠገኛ ገንዘብና የቤት ቁሳቁስ ድጋፍም ይደረግላቸዋል፡፡
በዚህ አግባብ እስካሁን 2734 እማወራ/አባወራ ከካምፕ በመውጣት ወደ መኖሪያ ቀያቸው የተመለሱ ሲሆን የተሟላ መረጃ ሳይገኝላቸው የቀሩት ሰዎች በማጣራት ሂደት ውስጥ ያሉ ሲሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ ምላሽ የሚያገኙ ይሆናል፡፡
የከተማዋን ሰላምና መረጋጋት አስተማማኝ ለማድረግ ተፈናቃዮች ከሚኖሩባቸው አካባቢ ነዋሪዎች ጋር ምክክር በማድረግ በተሰራው ስራ ከዚህ በፊት የነበሩ ስጋቶች ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ተቀርፈዋል፡፡
በመጨረሻም የከተማ አስተዳደሩና የክልሉ መንግስት በአሁኑ ጊዜ ከፍተኛ ኃላፊነትና ተጠያቂነት በተላበሰ አኳሀን በግጭቱ የተጎዱ ዜጎችን መልሶ የማቋቋም ስራ መስራቱን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ይገልፃል፡፡
ሰላም ለመላው ህዝባችን፤ውበት ለከተማችን…!
©የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር

ስለእናት የበጎ አድራጎት ድርጅት-ነሀሴ 16/2010 ዓ.ም ልዩ የስነፅሁፍ ምሽት ተዘጋጅቷል።
ስልክ፦ 0943877655
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስልክ፦ 0943877655
@tsegabwolde @tikvahethiopia