TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ከሎዳ⬆️

"ሰላም ጸግሽ! ዛሬ በዜይሴ/ኤ/ሎዳ የተደረገው ስብሰባ በሰላም ተጠናቋል። ስብሰባውም የተደረገው ልዩ ወረዳ ይስጠን በሚል ላይ ነው። ጥያቄያችንን በሰላማዊ መንገድ እናካሂዳለን፤ እስከመጨረሻውም ድረስ የምወሰደውን መስዋእትነትም እንከፍላለን ብሏል የሎዳ ቀበለ ሊቀመንበር አቶ አየለ ክሎ። እናም ጥያቄያችንን ምንም አይነት #ሁከትም ሆነ #ብጥብጥ ሳንፈጥር እስከመጨረሻው እንዘልቃለን ስል መልእክቱንም አስተላልፏል። እናም በልዩ ወረዳ መደረግ ዙሪያ ያልሆነ ነገር አርባምንጭ ላይ እንደሰሩም አንዳንድ የጠየኳቸው ግለሰቦች ነግረውኛል እሱም በንግግሩ መካከል ስያነሳ ሰምቸዋለሁ። ሰፋ ያለ ገለጻ አጠያይቄ እነግርሃለሁ።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ(አጋሮ) ነሀሴ 9/1967 - ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ!

©ናዬ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአቃቂ⬆️

"ዛሬ የአቃቂ ወንዝ ሞልቶ ወደ አስፓልቱ በመውጣቱ ህብረተሰቡ ስራ እንዳይገባ አስገድዶታል። በተለይ እንደምታየው ወደ ጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል አካባቢ። AB ነኝ ከአቃቂ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኢትዮጵያ የአገር ውስጥ የተፈናቃዮች ቁጥር ማሻቀቡን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ፡፡

የድርጅቱ የህፃናት ፈንድ እንዳስታወቀው በአገር ውስጥ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር 2.8 ሚሊዮን ደርሷል፡፡

ከስድስት ወራት በፊት 1.6 ሚሊዮን የነበረው የተፈናቃዮቹ ቁጥር በ1.2 ሚሊዮን ጨምሮ የእርዳታ ፈላጊዎችን ቁጥር እንዲያሻቅብ አድርጎታል፡፡

የኦሮሚያ፣ ደቡብና የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች ተፈናቃዮቹ የሚገኙባቸው አካባቢዎች መሆናቸው ተመልክቷል፡፡

የክረምቱን ጎርፍ ተከትሎም የሚፈናቀለው ህዝብ ቁጥር እንዳይጨምር ተሰግቷል፡፡

የአገር ውስጥ ተፈናቃዮቹን ለመደገፍ 111.8 ሚሊዮን ዶላር የሚያስፈልግ ሲሆን እስካሁን የተገኘው ድጋፍ ከ31 በመቶ እንደማይብልጥ ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

ሽንዋ ዩኒሴፍን ጠቅሶ እንደዘገበው ከአገር ውስጥ ተፈናቃዮች በተጨማሪ ኢትዮጵያ ከደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣ ሶማሊያና ኤርትራ የተሰደዱ ተፈናቃችን አስጠልላለች፡፡

በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚከሰቱ #ግጭቶችና የተፈጥሮ አደጋዎች የተፈናቃዮቹን ቁጥር እንዲጨምር አድርጎታል ተብሏል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update⬆️በጌዴኦና ጉጂ ህዝቦች መካከል በአባ ገዳዎች የወረደውን እርቀ ሠላም ተከትሎ በባህላዊ መንገድ ህዝብ ለህዝብ የማቀራረብ ተግባረ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

©የጌዴኦ ዞን መንግስት ከሚ.
@tsegabwolde @tikvahethiopia
update⬆️የቴፒ ከተማ የዛሬ ጥዋት ድባብ እና አጠቃላይ የከተማዋ ሁኔታ ከከተማው ነዋሪ አምደበት።
@tseabwolde @tikvahethiopia
#update ጅግጅጋ⬇️

በሶማሌ ክልል ሁከት ተከስቶ በነበረበት ጊዜ የተዘረፉባቸውና በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኙ ንብረቶቻቸው ቶሎ ስላልተመለሱላቸው ችግር ላይ መውደቃቸውን የጅግጅጋ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በበኩሉ የተዘረፉትን ንብረቶች ለባለቤቶቹ መመለስ እንዲቻል ኮሚቴ ማቋቋሙንና ተገቢው ማጣራት ከተደረገ በኋላ ንብረቶቹ እንደሚመለሱ አስታውቋል።

በሶማሌ ክልል መዲና ጅግጅጋና በሌሎች የክልሉ ከተሞች ተከስቶ በነበረው ሁከት በርካታ ንብረት ተዘርፏል።

©ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኮምቦልቻ⬆️

በኮምቦልቻ የሚኖሩ በአሁን ሰዓት ሰላማዊ ሠልፍ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

ከሚሰሙት መፈክሮች መካከል⬇️
◾️የጠፉ ወንድሞቻችን ይፈለጉልን
◾️መርከዛችን ህይወታችን ነው
◾️ፍትህ ለመርከዝ ወንድሞቻችን
◾️ሙሰኛ ፖሊሶች ለፍርድ ይቅረቡልን...
የሚሉት ይገኙበታል።

©webe
@tsegabwolde @tikvahethiopia