በቅርቡ በቴሌግራም ቻናላችን በየሳምንቱ የአንድ አመት የቴሌግራም ፕሪምየም የሚያስገኝ ውድድር የምንጀምር ሲሆን የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል እና የምንጠይቃቸውን ቀላል ጥያቄዎች በመመለስ ይሳተፉ፤ ይሸለሙ፡፡ በየሳምንቱ አስር አሸናፊዎች ይሸለማሉ!

#telegram #giveaway #contest #Boa #bankinginethiopia #banksinethiopia #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢድ-አል አደሃ (አረፋ) በዓል አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም፣ የጤና እንዲሁም የደስታ እንዲሆን እንመኛለን።

አቢሲንያ አሚን ዕሴትዎን ያከበረ!

#BankofAbyssinia #Banking #BankingService #EidAlAdha #Eid2022 #Muslim #Holiday #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ #ዕሤትዎን_ያከበረ
ባንካችን አቢሲንያ በወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ማዕከሉ በኩል ለሁለተኛ ጊዜ ያዘጋጀው ‘‘አሚን አዋርድ የሥራ ፈጠራ ውድድር” ፍፃሜውን አገኘ፡፡
ባንካችን አቢሲንያ በወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ማዕከሉ በኩል ለሁለተኛ ጊዜ ያዘጋጀው ‘‘አሚን አዋርድ የሥራ ፈጠራ ውድድር” ችግር ፈቺ የሆኑ በርካታ የውድድር ሐሳቦችን በከፍተኛ ፉክክር ሲያሳትፍ ቆይቶ፤ አሸናፊዎችን በመሸለምና ዕውቅና በመስጠት ፍፃሜውን አገኘ፡፡
በዚህ ውድድር ከቀረቡት የውድድር ሐሳቦች መካከል የተቀመጠውን መለያ መስፈርት ያሟሉ 142 ተወዳዳሪዎች ሐሳቦቻቸው በውድድሩ ተሳታፊ እንዲሆኑ ተመርጠው የነበረ ሲሆን፣ ከነዚህም መካከል 126ቱ ተወዳዳሪዎች በግብርና ምርቶች ማሳደጊያ፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በዶመስቲክ ትሬድ፣ በሰርቪስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በሪሳይክል እና ኢ-ለርኒንግ መስኮች ላይ ምክረ ሐሳቦቻቸውን ማቅረብ ችለዋል፡፡ በውድድሩ ላይ የተለያዩ ምዕራፎችን በብቃት በማለፍ በብዙ መለኪያዎች ነጥረው የወጡ ከ1ኛ እስከ 5ተኛ ደረጃን በማግኘት አሸናፊ ለሆኑ ተወዳዳሪዎች ባንካችን ከብር 200,000 እስከ ብር 1,000,000 የፕሮጀክት ሐሳባቸውን መሬት እንዲያወርዱ የሚያግዛቸው የሥራ ማስኬጃ ሽልማት ከታላቅ ክብርና ምስጋና ጋር አበርክቶላቸዋል፡፡
‘‘አሚን አዋርድ የሥራ ፈጠራ ውድድር” ከባንካችን እሴቶች መካከል አንዱ የሆነው ማኅበራዊ ኃላፊነትን መወጣት በሚለው መርህ መነሻነት የተሟላ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቱን እየሰጠ በሚገኝበት ‘‘አቢሲንያ አሚን” በኩል የሚዘጋጅ መሆኑን ተከትሎ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎቱን በማስተዋወቅ ረገድም ከፍተኛ ድርሻ ነበረው፡፡ ከመጀመሪያው ዙር የውድድር መድረክ ትምህርት በመውሰድ ሁለተኛው ዙር ከቀደመው በተሻለ መልኩ የተሳካ አፈፃፀም እንዲኖረው ለማስቻል በቂ ዝግጅት በማድረግ፤ በላቀ ስኬት ለማጠናቀቅ ተችሏል፡፡
በመዝጊያ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የብሔራዊ ባንክ የባንኪንግ ሱፐርቪዥን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ፍሬዘር አያሌው በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን፣ በእለቱም ባንካችን ለተለያዩ 6 የበጎ አድራጎት ሥራ ላይ ለተሰማሩ ግብረ ሠናይ ድርጅቶች በአጠቃላይ የብር 3 ሚሊዮን የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡
የጥያቄና መልስ ውድድር ቅዳሜ ሰኔ 15 ከረፋዱ 4:30 በቴሌግራም ቻናላችን ይደረጋል፡፡ በየሳምንቱ አስር አስር አሸናፊዎች ይሸለማሉ! ዛሬውኑ የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ቴሌግራም ፕሪምየምን ይሸለሙ!

https://yangx.top/BoAEth

#telegram #giveaway #contest #Boa #bankinginethiopia #banksinethiopia #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
ፈጥነው የመለሱ 10 ሰዎች ይሸለማሉ!

ጥያቄ፡- አቢሲንያ ባንክ ስንት ቅርንጫፎች አሉት?


ማሳሰቢያ፡ መልስ ማስተካከል አይቻልም፡፡
- ተወዳዳሪዎች ከአንድ ጊዜ በላይ በተለያየ የቴሌግራም አካውንት መመለስ አይቻልም፡፡


#telegram #giveaway #contest #Boa #bankinginethiopia #banksinethiopia #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
የቴሌግራም ጥያቄና መልስ ውድድር ለተሳተፋችሁ ምስጋናችንን እያቀረብን፣ ቀጣይ ዙር የጥያቄና መልስ ውድድር ቅዳሜ ሰኔ 22 ከረፋዱ 4:30 በቴሌግራም ቻናላችን ይደረጋል፡፡ በየሳምንቱ አስር አስር አሸናፊዎች ቴሌግራም ፕሪምየም ይሸለማሉ! ዛሬውኑ የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ይሸለሙ!

https://yangx.top/BoAEth

#telegram #giveaway #contest #Boa #bankinginethiopia #banksinethiopia #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
የጥያቄና መልስ ውድድር ቅዳሜ ሰኔ 22 ከረፋዱ 4:30 በቴሌግራም ቻናላችን ይደረጋል፡፡ በየሳምንቱ አስር አስር አሸናፊዎች ይሸለማሉ! ዛሬውኑ የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ቴሌግራም ፕሪምየምን ይሸለሙ!


#telegram #giveaway #contest #Boa #bankinginethiopia #banksinethiopia #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
በአቢሲንያ ቪዛ ካርድዎ ላይ ከፊት እና ጀርባ የሚገኘውን ቁጥር እና የካርዱ አገልግሎት የሚያበቃበትን ቀን ብቻ በመጠቀም ካሉበት ሆነው ክፍያዎችን በኦንላይን በቀላሉ ማከናወን ይችላሉ።

አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!


#BankofAbyssinia #Banking #VisaCard #Visa #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
ፈጥነው የመለሱ 10 ሰዎች ይሸለማሉ!

ጥያቄ፡- በታዋቂ ግለሰቦች ስም የተሰየሙ ሶስት የአቢሲንያ ባንክ ቅርንጫፎች ጥቀሱ።


ማሳሰቢያ፡ መልስ ማስተካከል አይቻልም፡፡
- ተወዳዳሪዎች ከአንድ ጊዜ በላይ በተለያየ የቴሌግራም አካውንት መመለስ አይቻልም፡፡


#telegram #giveaway #contest #Boa #bankinginethiopia #banksinethiopia #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
ታላቅ የምሥራች፣ ከአቢሲንያ ባንክ!

በባንክ ቴክኖሎጂ ፈር ቀዳጅ የሆነው አቢሲንያ ባንክ ዛሬም በሀገራችን የመጀመሪያ የሆነውን ፈጣን የቪዛ ካርድ ህትመት አገልግሎት እንዲሁም የዲጂታል ቪዛ ካርድ አገልግሎትን እነሆ ብሏል።
ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በዚህ ሰዓት እነዚህ አዳዲስ አገልግሎቶች የዕለቱ የክብር እንግዳ የሆኑት የኢኖቬሽን የሚኒስቴር ዴኤታ ዶር. ይሽሩ አለማየሁ በተገኙበት በብሔራዊ ሙዚየም በሚገኘው የባንካችን ቨርቹዋል ባንኪንግ ማዕከል የምርቃት ሥነ ሥርዓቱ አየተካሄደ ይገኛል።
የፈጣን ቪዛ ካርድ ህትመት አገልግሎትን ለማግኘት፣ ደንበኞች ቅርንጫፍ መሄድ ሳያስፈልጋቸው በአቅርቢያቸው ወደሚገኘውን የ ቨርቹዋል ባንኪንግ ሴንተር በመሄድ የቪዛ ካርድ መጠየቅና ወዲያውኑ በስማቸው የተዘጋጀውን ካርድ መረከብ ይችላሉ፡፡
ይህንን አገልግሎት ለባንኩ የቀድሞ ደንበኞች፣ ለአፖሎ ተጠቃሚዎች፣ ካርድ ለጠፋባችው፣ የምትክ ካርድ አገልግሎት እንዲሁም አዲስ አካውንት በቨርቹዋል ባንኪንግ ሴንተር ለሚክፍቱ ወዲያውኑ ካርድ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል፡፡
አገልግሎቱን ልዩ የሚያደርገው
• በኢትዮጵያ የመጀመሪያ መሆኑ
• በቀን ለ24 ሰአት በሳምንት ለ 7 ቀናት የሚሰጥ መሆኑ
• በካርዱ ወዲያውኑ በ ATM እና POS ላይ ግብይት መፈፀም መቻሉ
ይህንን አገልግሎት በጀሞ፣ ብሄራዊ ሙዝየም፣ ጎፋ እና መሀል ሰሚት በሚገኙት ቨርቹዋል ባንኪንግ ሴንተሮቻችን ማግኘት እንደሚችሉ እየገለጽን ባንካችን የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት ወደ ሌሎቹ ቨርቹዋል ባንኪንግ ሴንተሮች የሚያስፋፋ ይሆናል፡፡
እንዲሁም የዲጂታል ቪዛ ካርድ አገልግሎት ለማግኘት ደንበኞች ስልካቸውን እንደ ATM ካርድ መገልገል የሚችሉ ሲሆን የአፖሎ መተግበሪያን በመጠቀም ቪዛ ካርዳቸውን ወደ ዲጂታል ቪዛ ካርድ በመቀየር ገንዘብ ከATM ለማውጣትም ሆነ POS ማሽኖች ላይ ለመክፈል ስልካቸውን ጠጋ በማድረግ መጠቀም ይችላሉ።