ከዴሊቨር አዲስ ይዘዙ
በካርድዎ ይክፈሉ !

ለራስዎ ወይም ለወዳጅዎ ከዴሊቨር አዲስ ሲያዙ የአቢሲንያ ባንክን ቪዛ ካርድ እንዲሁም ቪዛና ማስተር ካርድን በመጠቀም ክፍያዎን ይፈጽሙ፡፡
#VISAcard #Mastercard #CardBanking #E_commerce #Deliveraddis #delivery #ThechoiceforAll
We Are Hiring!

Bank of Abyssinia seeks to hire applicants for the following positions;

1) Job Title: - Senior Credit Underwriter
Place of Work: Addis Ababa
2) Job Title: - Grade I Branch Business Manager-Grand Gato Branch and Office Equipment Technician
Place of Work: Dire Dawa District
3) Job Title: - Banking Business Officer
Place of Work: Adola Branch (Hawassa District)

Use the link below to apply for the vacancy
https://vacancy.bankofabyssinia.com
የ"አሚን አዋርድ" የሥራ ፈጠራ ውድድር አሸናፊ በሶማሊ ክልል ዋና ከተማ በሆነችው በጅግጅጋ ከተማ የአቀባበል ሥነ-ሥርዓት ተከናወነ፤
የ"አሚን አዋርድ" የሥራ ፈጠራ ውድድር በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ተከትሎ የአምስተኛ ደረጃን በማግኘት የብር 200,000 ተሸላሚ ለሆነው የጅግጅጋ ተወላጅ ተማሪ ሳልማን አሊ የእንኳን ደስ አለህ አቀባበል በጅግጅጋ ሎተስ ሆቴል በትላንትናው እለት የተከበሩ ገራድ ኩልምዬ ገራድ መሐመድ፣የሱማሌ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ አማካሪ ሸህ አህመድ መሐመድ አሊ፣የጅግጅጋ ከተማ ከንቲባ ኢንጂነር ዚያድ አቂል፣የሱማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ /ተወካይ/ አቶ አብዱላሂ አብዲ፣የሱማሌ ክልል ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መሐመድ ሁሴን፣የሱማሌ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙህዲን አበዲ ፋራሃ ፣ የሱማሌ ክልል ክህሎትና ስራ ፈጠራ ቢሮ ምክትል ሀላፊ ወ/ሮ ሂቦ አህመድ፣ የሱማሌ ክልል ሴቶች ጉዳይ ቢሮ ም/ኃላፊ ወ/ሮ ኡባህ አህመድ፣ የሱማሌ ክልል ኘሬዝዳንት ጽ/ቤት አማካሪ አቶ ካሣሁን መሐመድ ፣ የባንካችን የሸሪዓ አማካሪ ኮሚቴ ሊቀመንበር፣የባንካችን የበላይ የስራ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡
ተወዳዳሪው ‘‘Smart Home System Lighting And Surveillance’’ በሚል ድርጅት ስም አሸናፊ በመሆን ሽልማቱ ሊበረከትለት ችሏል፡፡
በኅዳር ወር 2015 ላይ በይፋ የተጀመረውና ላለፉት ወራት ሲካሄድ የቆየው "አሚን አዋርድ" የሥራ ፈጠራ ውድድር መጠናቀቁን ተከትሎ በሥራ ፈጠራቸው ይዘት እና ችግር ፈቺነታቸው ለተመረጡ 5 ተወዳዳሪዎች የእውቅናና የሽልማት መርሐ-ግብር የተከናወነ ሲሆን፣በውድድሩ ላይ ከ1ኛ - 5ኛ ለወጡ ተሳታፊዎች በአጠቃላይ በሽልማት መልክ ከተሰጠው ብር 2.5 ሚሊዮን የገንዘብ ሽልማት ባሻገር ከ6ተኛ- 20ኛ ለወጡ ተሳታፊዎችም የማበረታቻ ሽልማት ተሰጥቷል፡፡
በዚህ የአቀባበል ሥነ-ሥርዓት ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተወዳዳሪው የጅግጅጋ ከተማን ወክሎ ባስመዘገበው ውጤት ደስ መሰኘታቸውንና በተጨማሪም ላስመዘገበው ውጤት እውቅናን የሰጡ ሲሆን ባንካችን በስራ ፈጠራ ዙሪያ እየሰራ ያለውን ተጨባጭ ስራ በማድነቅ መሰናዶው እንዲቀጥል ከባንካችን ጎን እንዲሆኑ፤ተወዳዳሪውም የፈጠራ ውጤቱን ወደ ተግባር ለመቀየር በሚያረገው ጥረት ሂደት ምንግዜም በራቸው ክፍት መሆኑንና ሌሎችም የፋይናንስ ተቋማት የአቢሲንያ ባንክን ዓርአያ በመከተል ወጣት የስራ ፈጣሪዎችን እንዲያበረታቱ በመድረኩ ገልጸዋል፡፡