የ"አሚን አዋርድ" የሥራ ፈጠራ ውድድር በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ተከትሎ የአንደኝነት ደረጃን በማግኘት የብር 1,000,000 ተሸላሚ ለሆኑትና በአዳማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለነበሩ ሦስት እንስቶች የእንኳን ደስ አላችሁ አቀባበል በናፍሌት ሆቴል በትላንትናው እለት የአዳማ ከተማ ከንቲባ አማካሪ አቶ ጌታቸው ባርቾ ፤ አቶ ሙሉጌታ ቃበቶ የአዳማ ከተማ አስ. የኮምዪኒኬሽን ፅ/ቤት ሃላፊ ፤ አቶ ፈለቀ ንጉሴ የአዳማ ከተማ አስተዳደር የስራ ፈጠራ ፅ/ቤት ምክትል ሃላፊ፤ ክብርት ረኢሳ ጁኔይዲ የአዳማ ከተማ አስ. የሴቶች እና ህፃናት ፅ/ቤት ሃላፊ፤ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖ. ተወካዮች፤ የባንካችን የሸሪያ ኮ/አባላት፤ የባንካችን የበላይ የስራ አመራሮች ጥሪ የተደረገላቸው የሀይማኖት አባቶች አባ ገዳዎች በተገኙበት ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው፡፡
እንስቶቹ ‹ግሪን ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ማዳበሪያ› በሚል በጋራ ባቋቋሙት ድርጅት ስም አሸናፊ በመሆን ሽልማቱ ሊበረከትላቸው ችሏል፡፡
ኅዳር ወር 2015 ላይ በይፋ የተጀመረውና ላለፉት ወራት ሲካሄድ የቆየው "አሚን አዋርድ" የሥራ ፈጠራ ውድድር መጠናቀቁን ተከትሎ በሥራ ፈጠራቸው ይዘት እና ችግር ፈቺነታቸው ለተመረጡ 5 ተወዳዳሪዎች የእውቅናና የሽልማት መርሐ-ግብር የተከናወነ ሲሆን፣ በውድድሩ ላይ ከ1ኛ - 5ኛ ለወጡ ተሳታፊዎች በአጠቃላይ ከሰጠው ብር 2.5 ሚሊዮን የገንዘብ ሽልማት ባሻገር ከ6ተኛ - 20ኛ ለወጡ ተሳታፊዎችም የማበረታቻ ሽልማት ሰጥቷል፡፡
በአቀባበል ስነስርአቱ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች አንስቶቹ አዳማ ከተማን ወክለው ላስመዘገቡት ውጤት ደስ መሰኘታቸውንና ፤ በተጨማሪም ላስመዘገቡት ውጤት እውቅናን የሰጡ ሲሆን ባንካችን በስራ ፈጠራ ዙሪያ እየሰራ ያለውን ተጨባጭ ስራ በማድነቅ መሰናዶው እንዲቀጥልና ሁልግዜን ከባንካችን ጎን በመሆን በተጨማሪም ተወዳዳርው ላሸነፉት ወጣቶች ምንግዜም በራቸው ክፍት መሆኑን በመድረኩ ገልፀዋል፡፡

ወደ ባንክ ቅርንጫፍ መሄድ ሳይጠበቅብዎ በቨርቹዋል ባንኪንግ ማዕከሎቻችን ከእሁድ እስከ እሁድ ለ24 ሰዓት የተሟላ የባንክ አገልግሎት ያግኙ።
#BankofAbyssinia #BankingServices #ITM #VirtualBanking #DigitalBanking #MoneyTransfer #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ

የዛይ ራይድ ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች የአቢሲንያ ባንክን እንዲሁም የውጭ ባንኮችን ቪዛ ካርድ በመጠቀም የአገልግሎት ክፍያቸውን በብር እንዲሁም በውጭ ሀገር ገንዘብ መክፈል የሚችሉበት አሠራር ተዘርግቶ አገልግሎቱ ተጀምሯል፡፡
አቢሲንያ በዲጂታል ክፍያ ግንባር ቀደም ከሆነው ከቪዛ ጋር የዲጂታል ንግድን (E-Commerce) ለማቀላጠፍ የሚያስችለውን የቪዛ ሳይበር ሶርስ Visa CyberSource Payment Gateway Technology የኦንላይን ክፍያ አማራጭ በማቅረብ በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ቀዳሚ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ፣ ዘመን ከወለዳቸው ቴክኖሎጅዎች ጋር ራሱን በማላመድ የዲጂታል ንግድን በኢ-ኮሜርስ የክፍያ አማራጭ አገልግሎቱን መስጠት ከጀመረ ከ2 ዓመት በላይ ሆኖታል፡፡
ባንካችን የዲጂታል ንግድን የሚያቀላጥፍ የክፍያ አማራጭ E-Commerce payment gateway ቴክኖሎጂን ለደንበኞቹ በማቅረብ የአገልግሎት አሰጣጡን በማቀላጠፍ አሁንም እየሠራ የሚገኝ ሲሆን፣ E-Commerce payment gateway ድረ-ገጽን (website) ወይም መተግበሪያዎችን (App) በመጠቀም በቪዛ አልያም በማስተር ካርድ ኦንላይን ክፍያዎችን መፈጸም የሚያስችል ቴክኖሎጂ ነው፡፡ በተለያዩ ንግድ ሥራ ላይ የተሠማሩ ተቋማት፤ በውጪ አገር ያሉ ደንበኞቻቸው አቢሲንያ payment gateway የክፍያ አውታር ጋር ዌብ ሳታቸውን ወይም መተግበሪያቸውን በማገናኘት ከመላው ዓለም በኦን ላይ ክፍያዎችን የሚቀበሉበት ሥርዐት ነው፡፡
ዛይ ራይድም በዚህ ረገድ ለደንበኞቹ የተሻለ አገልግሎት ለማቅረብ በማሰብ የትራንስፖርት አገልግሎት ክፍያን በቀላሉ በካርድ መፈጸም እንዲቻል አሰራሩን ከባንካችን ጋር በማስተሳሰር ተግባራዊ ያደረገው የዲጅታል ክፍያ ስርአት ዛሬ ይፋ ተደርጓል፡፡ዲያስፖራውን ጨምሮ ከውጭ ሀገር የሚመጡ ግለሰቦች እንዲሁም በዚህ ሀገርም የሚገኙ ተገልጋዮች ጥሬ ገንዘብ መጠቀም ሳያስፈልጋቸው የባንካችንን ቪዛ ካርድ እና የውጭ አገር ባንኮችን አለምአቀፍ ካርድ ተጠቅመው ክፍያ መፈጸም መቻላቸው፣ በዘርፉ ፈር ቀዳጅ የሚያደርገን ሲሆን፣ ለሀገራችንም የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ ነው ብሎ ባንካችን ያምናል፡፡
ይህ ቅንጅት ማንኛውም ሰው Zay Ride የስልክ መተግበሪያን ከPlayStore ወይም ከAppStore በማውረድ የአቢሲኒያ ቪዛ ካርዱንና አለምአቀፍ ካርዶችን ተጠቅሞ የጉዞ አገልግሎቱን ክፍያ በብር ወይም በውጭ ሀገር ገንዘብ በቀላሉ መክፈል ያስችለዋል፡፡

የሀዘን መግለጫ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ የነበሩት አቶ ዱባለ ጃሌ ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው አቢሲንያ ባንክ የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ለመግለጽ ይወዳል ። አቶ ዱባለ ጃሌ በኢትዮጵያ የባንክ ኢንደስትሪ ውስጥ ደማቅ አሻራ ያሳረፉ ታላቅ ሰው ነበሩ ። አቶ ዱባለ ጃሌ ያበረከቱትን አስተዋጽኦ ግምት ውስጥ በማስገባትና እኚህ አንጋፋ የባንክ ባለሙያ ከፍተኛ በሆነ የኩላሊት ሕመም እየተቸገሩ እንዳለ ባንካችን ተረድቶ፣ ለሕክምና ወጪያቸው ይረዳቸው ዘንድ የብር 1,000,000 (አንድ ሚሊዮን) ድጋፍ በባንካችን ዋና ሥራ አስፈፃሚ በኩል ተበርክቶላቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡ አቢሲኒያ ባንክ ለቤተሰቦቻቸውና የቅርብ አጋሮቻችው መፅናናትን ይመኛል።