ባንካችን ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ከሚያደርጋቸው እንቅስቃሴ አካል የሆነውንና ለሁለተኛ ጊዜ ከአለም አቀፉ የሴቶች ቀን “ማርች 8” ጋር በተያያዘ ”እችላለሁ’’ በሚል መሪ ቃል በሴት ባለተሰጥኦዎች መካከል በግጥም፤በሙዚቃ፤ በቲክቶክ የማህበራ ሚዲያ አነሳሽነት እንዲሁም ሴት የስራ ፈጣሪዎች መካከል ባከናወነው ውድድር በየዘርፉ ከ1ኛ-3ኛ ለወጡት ተወዳዳሪዎች ሚያዚያ 20 ቀን 2015 ዓም. በማሪዮት ኢንተርናሽናል ሆቴል ባዘጋጀው መርሃ ግብር ላይ ሽልማትና የምስክር ወረቀት አበርክቷል፡፡

በዚህ መርሃ ግብር የድምፅ፤የግጥምና የቲክቶክ ተወዳዳሪች ተሰጥኦ ያላቸው እንስቶች እንዲወዳደሩ በማድረግ ስራቸውን ካቀረቡት 37 የድምፅ ተወዳዳሪዎች፤ 326 የግጥም ተወዳዳሪዎች እና 18 ቲክቶከሮች መካከል በዳኞችና በአድማጭ ተሳታፊዎች ከፍተኛ ድምፅ ያገኙት ሶስት ሶስት አሸናፊዎች ተለይተው ለሽልማት በቅተዋል፡፡

በሥነስርዓቱም በሶስቱም ዘርፍ 1ኛ ለወጡት የብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)፣ 2ኛ ለወጡት የብር 60,000.00(ስልሳ ሺህ ብር) እንዲሁም 3ኛ ለወጡት የብር 30,000.00 (ስላሳ ሺህ ብር) ሽልማት የተበረከተ ሲሆን በፕሮግራሙም ላይ አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ስራዎቻቸውን አቅርበዋል፡፡በዚህም

በግጥም ዘርፍ
1ኛ ዮዲት መኮንን
2ኛ በአምላክ በለው
3ኛ ፋንታነሽ አበባው
በሙዚቃ ዘርፍ
1ኛ ህይወት ሰለሞን
2ኛ ሀመልማል ቃለአብ
3ኛ ኤደን አበባየሁ
በቲክቶክ ዘርፍ
1ኛ ዮርዳኖስ ሽመልስ
2ኛ በእምነት ከፍያለው
3ኛ ወንጌላዊት እንድርያስ


በሌላ በኩል የውድድሩ ሌላኛው አካል በነበረው የተሻለ የሥራ ፈጠራዎችን የማቅረብ ውድድር ላይ ለአሸናፊዎቹ ከገበያው በአነሰ የወለድ ምጣኔና ካለመያዣ እስከ ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) ድረስ ብድር መመቻቸቱ ተገልጿል፡፡በዚህም ዘርፍ ለ50 የስራ ፈጣሪ ሴቶች ለእያንዳቸው የ500,000 (አምስት መቶ ሺ ብር) ብድር በድምሩ 25,000,000(ሀያ አምስት ሚሊዮን ብር) ብድር መዘጋጀቱም ተገልጿል፡፡
#Ican #Adeysaving #zaharasaving #women saving