ባንካችን አቢሲንያ “መቆጠብ ያሸልማል” በሚል የአገር ውስጥ ቁጠባን የሚያበረታታ መርሀ ግብርን ለ4ኛ ግዜ፣ “እንሸልምዎ” በሚል መሪ ቃል የውጭ ምንዛሬ የሚያበረታታ መርሀ ግብርን ለ5ኛ ግዜ፣ ከታህሳስ 25 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ሰኔ 24 ቀን 2015 ዓ.ም አከናውኖ ባሳለፍነው ነሐሴ 04 ቀን 2015 ዓ.ም. በብሄራዊ ሎተሪ አዳራሽ የዕጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓት አከናውኖ ባለዕድለኞችን መለየቱ የሚታወስ ነው ፡፡

በዚህም መሰረት ዘመናዊ አይሱዙ ኤን.ፒ.አር ፣ዘመናዊ ትራክተር፣የ 5 ቀናት የቱርክ ሀገር ጉብኝትን ጨምሮ በሁለቱም ዝግጅቶች 187 ሽልማቶችን ያካተተው መርሀ ግብራችን በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ከ 8 ሚሊየን በላይ ደንበኞች በዕጣው የተሳተፉበትም ነበር ፡፡

እነዚህ ዕድለኞች በድሬደዋ፣ በደሴ፣ በሀዋሳ ፣በአዲስ አበባ እና በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ሲሆኑ ባንካችን አቢሲንያ በቃሉ መሰረት ለዕድለኞች በያሉበት ከተማ በደማቅ ስነ-ስርዓት አስረክቧል፡፡
በዚህ የእጣ መርሀግብራችን ለተሳተፉ በሙሉ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ ለባለ ዕድለኞች እንኳን ደስ አላችሁ እያልን መሰል የሽልማት መርሀ ግብር በቅርቡ በአይነት እና በይዘት ላቅ ብሎ ለመምጣት ዝግጅት ማጠናቀቃችንን እያበሰርን በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ የባንካችን ደንበኞች በነዚሁ ዝግጅቶቻችን ላይ በመሳተፍ የባንካችን አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ፣ እድላቸውንም እንዲሞክሩ እንጋብዛለን ፡፡
ባንካችን በጥቅምት 24 ቀን 2016 ዓ.ም. በስቴይ ኢዚ ፕላስ ሆቴል የባንኩ ተቀዳሚ ደንበኞች፣ የባንኩ የሥራ አመራር አባላት እና የተለያዩ የሚዲያ አካላት በተገኙበት ‘‘ለአቢሲንያ አሚን’’ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት በብራንድ አምባሳደርነት ከተሾመው ከአቶ ሙሐመድ ፈረጅ ጋር የፊርማ ስነ-ስርዓት አካሂዷል፡፡ ሊንኩን በመጠቀም ተጨማሪ ያንብቡ
https://www.bankofabyssinia.com/ifb-brand-ambassador/
ባንካችን አቢሲንያ በተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙ ተማሪዎችን የአፖሎ የተማሪ አምባሳደር በማድረግ፣ አፖሎን ለደንበኞች በማስተዋወቅ እና በምዝገባ ባሳኩት መጠን የኮሚሽን ክፍያ ለመክፈል አስፈላጊውን ዝግጅት ጨርሷል፡፡ ስለሆነም የአፖሎ አምባሳደር ለመሆን ፍላጎት ያላቸውን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አወዳድሮ ለመውሰድ ተዘጋጅቷል፡፡ ከተጨማሪ የገቢ ምንጭ ባለፈ ተማሪዎች ከዩኒቨርስቲ ተመርቀው ሲወጡ የሥራ ልምድ ይሆናቸው ዘንድ ያላቸውን ችሎታ የሚያሳድጉበት፤ እንዲሁም እንደሚያሳዩት ውጤትና ተነሳሽነት ሌሎች ሽልማቶችን የሚያገኙበትን አጋጣሚ አቢሲንያ ባንክ ፈጥሯል፡፡
የዚህ እድል ተሳታፊ ለመሆን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሊያሟሏቸው የሚገቡ ነጥቦች፣
የከፍተኛ ትምህርት እየተከታተላችሁ መሆኑን የሚገልፅ የተማሪ መታወቂያ፤
የአፖሎ አካውንት ባለቤት መሆን፤ ከ150 ቃላት ባልበለጠ ራሳችሁን የሚገልፅ አጭር ፅሁፍ እና
በቀላሉ ለመሙላት በተዘጋጀው የማመልከቻ ገጽ ከ150 ቃላት ባልበለጠ ለምን የአፖሎ አምባሳደር ለመሆን እንደፈለጋችሁ መግለፅ ብቻ ናቸው፡፡ ስለሆነም ከታች ያለውን መስፈንጠሪያ በመጠቀም ይመዝግቡ፡፡

https://apolsup.bankofabyssinia.com/studentAgent


ከአፖሎ ጋር ተፍ ተፍ በሉ፡፡
ከስራ በፊት ስራ ጀምሩ፡፡
ጠቀም ያለ የሪፈራል ኮሚሽንም አግኙ!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አፖሎን ሲጠቀሙ ከቁጠባ ተቀማጭ 9% ወለድ፣ ያለመያዣ ብድር እንዲሁም በአፖሎ ሲከፍሉ ቅናሾች የሚያገኙበት 100% ደህንነቱ የተጠበቀ ዲጂታል ባንክ ነው።
መተግበሪያውን ያውርዱ
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo

#Apollodigitalbank
#Apollodigitalproduct #AbyssiniaDigital #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
ባንካችን አቢሲንያ የባለ አክሲዮኖች 27ኛ መደበኛ እና 14ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔዎች ቅዳሜ፣ ኅዳር 8 ቀን 2016 ዓ/ም በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል አካሄደ፡፡
በጉባኤው ላይ የ2022/2023 የሒሳብ ዓመት ዓመታዊ ሪፖርት ለባለ አክሲዮኖች የቀረበ ሲሆን፣ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በቀረቡ ጥያቄዎች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡ የባንኩን ካፒታል ለማሳደግ በዲሬክተሮች ቦርድ በቀረበው ሐሳብ ላይ ተወያይቶ ጠቅላላ ጉባኤው ውሳኔ ያስተላለፈ ሲሆን፣ ለቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት የሚያገለግሉ የቦርድ አባላት ምርጫም ተከናውኗል፡፡ በእለቱ የጠቅላላው ጉባዔ ውሳኔ የሚያሻቸው ሐሳቦች ተንሸራሽረውና ውሳኔ ተሰጥቶባቸው ጉባኤው በተሳካ ሁኔታ ተጠናቅቋል፡፡
ባንካችን አቢሲንያ ተደራሽነቱን ለማስፋት በአገር ደረጃ የመጀመሪያ የሆነውን የቨርቹዋል ባንኪንግ ከፍቶ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ይታወቃል። አገልግሎቱን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ 23ኛውን የቨርችዋል ባንኪንግ ማዕከል በአዲስ አበባ ጀሞ 1 ታክሲ ተራ አካባቢ፣ 24ኛውን በደብረብርሀን ከተማ ሠማያዊ ሆቴል ፊትለፊት ወይም ሮሚና ካፌ አጥገብ፣ 25ኛውን በመቀሌ ከተማ ሸባ ኮሌጅ አካባቢ ከፍቶ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል!

#virtualbanking #bankinginethiopia #banksinethiopia #ITM #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
ለጥያቄና መልስ ውድድራችን ዝግጁ ኖት?

በቅርቡ በቴሌግራም ቻናላችን በየሳምንቱ ሽልማት የሚያስገኝ ውድድር የምንጀምር ሲሆን የምንጠይቃቸውን ቀላል ጥያቄዎች በመመለስ ይሳተፉ፤ ይሸለሙ፡፡ በየሳምንቱ አምስት አምስት አሸናፊዎች ይሸለማሉ! ዛሬውኑ የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ይሸለሙ!
https://yangx.top/BoAEth

#telegram #giveaway #contest #Boa #bankinginethiopia #banksinethiopia #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ