#ለመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር ከ5 ቢሊየን ብር በላይ ገንዘብ ለማሰባሰብ መታቀዱ ተገለጸ።
++++
ለመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር ከ5 ቢሊየን ብር በላይ ገንዘብ ለማሰባሰብ መታቀዱ የተገለጸ ሲሆን አገልግሎቱን ለማስፋት እና የተጀመረውን የሕንጻ ግንባታ ለማጠናቀቅ የፊታችን የካቲት 01 ቀን 2017 ዓ.ም በሰይፉ ፋንታሁን ዩቱብና በሌሎችም መገናኛ አውታሮች የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብርን አስመልክቶ መግለጫ ተሰጥቷል።
በአዲስ አበባና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች 44 ቅርንጫፎችን ከፍቶ ደጋፊና ጧሪ የሌላቸው አረጋውያን፣የአእምሮ ሕሙማን፣ራሳቸውን ችለው መንቀሳቀስ የማይችሉ የአልጋ ቁራኛ የሆኑትን እና በጎዳና ላይ የወደቁትን በማንሳት ሰብአዊ ድጋፍ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን ለዚህም በቀን ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደሚያደርግ አቶ ብንያም በለጠ ተናግረዋል።
አክለውም የበጎ አድራጎት ማኅበሩ ለጀመረው ሕንጻ ማጠናቀቂያ ለመሰብሰብ ከታቀደው የገንዘብ ገቢ በተጨማሪም በአይነትና በተለያዩ ነገሮች ድጋፍ ማድረግ እንደሚቻልም ገልጸልዋል።
አያይዘውም መቄዶንያ መንግሥታዊ እና ሃይማኖታዊ ተቋማት እንዲሁም ግለሰቦች ተቋሙን በማገዝ ረገድ የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።