TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.7K photos
1.48K videos
5 files
3.42K links
加入频道
#ተጠናቀቀ

ማንችስተር ዩናይትድ 2-0 " PAOK "

አማድ

ቼልሲ 8-0 ኖህ

አዳራባዮ
ጉዩ
ዲሳሲ
ፊሊክስ
ሙድሪክ
ንኩንኩ

@Tikvahethsport      @kidusyoftahe
ዩናይትድ እና ቼልሲ ድል አድርገዋል !

በዩሮፓ ሊግ አራተኛ ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ ከ " PAOK " ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የቀያዮቹ ሴጣኖች የማሸነፊያ ግቦች አማድ ዲያሎ 2x ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ቼልሲ በበኩሉ በአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ከኖህ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 8ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት መርታት ችሏል።

የሰማያዊዎቹን የማሸነፊያ ግቦች ንኩንኩ 2x ፣ ጇ ፊሊክስ 2x ፣ ጉዩ ፣ ዲሳሲ ፣ ሙድሪክ እና አዳራብዮ ከመረብ አሳርፈዋል።

ማንችስተር ዩናይትድ ከ 3️⃣8️⃣0️⃣ ቀናት በኋላ በአውሮፓ መድረክ ያደረገውን ጨዋታ ማሸነፍ ችሏል።

ኢንዞ ፈርናንዴዝ በጨዋታው በሀያ ደቂቃዎች ውስጥ ሶስት ለግብ የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

ቼልሲ በአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ውድድር ባደረጋቸው ሶስት ጨዋታዎች 1️⃣6️⃣ ግቦችን በተጋጣሚው መረብ ላይ አስቆጥሯል።

ማንችስተር ዩናይትድ በዩሮፓ ሊጉ በ 6️⃣ ነጥቦች 1️⃣5️⃣ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

ቼልሲ በበኩሉ በአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ሶስቱንም ጨዋታዎች በማሸነፍ በ 9️⃣ ነጥቦች ውድድሩን እየመሩ ይገኛሉ።

@Tikvahethsport         @kidusyoftahe
" በተጨዋቾቼ ብቃት ተደንቂያለሁ " ኢንዞ ማሬስካ

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ዋና አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ በምሽቱ ጨዋታ ተጨዋቾቻቸው ባሳዩት ብቃት መደነቃቸውን ገልፀዋል።

" እውነት ለመናገር ውጤቱ በዚህ መልኩ ይጠናቀቃል ብለን አልጠበቅንም " ያሉት አሰልጣኙ " ተጨዋቾቼ ባሳዩት ብቃት ተደንቂያለሁ።" ሲሉ ተናግረዋል።

አሰልጣኙ አያይዘውም የምሽቱ ድል ቡድናቸው የፊታችን እሁድ በሊጉ ከአርሰናል ጋር ላለበት ተጠባቂ ጨዋታ ትልቅ መነሳሻ እንደሚሆነው ገልፀዋል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ቫን ኔስትሮይ እንዲቆይ እፈልጋለሁ “ ኦናና

የቀያይ ሴጣኖቹ ግብ ጠባቂ አንድሬ ኦናና የክለቡ ጊዜያዊ አሰልጣኝ ሩድ ቫን ኔስትሮይ በክለቡ እንዲቆይ እንደሚፈልግ ገልጿል።

“ ቫን ኔስቶሮይ ምርጥ ሰው እና ምርጥ አሰልጣኝ ነው አሞሪም ቢመጣም አብሮ ቢቆይ እወዳለሁ ውሳኔው የክለቡ ነው “ ሲል ኦናና ተናግሯል።

የሩድ ቫን ኔስትሮይ የማንችስተር ዩናይትድ የወደፊት ቆይታ በአዲሱ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም እንደሚወሰን ተገልጿል።

ቫን ኔስትሮይ ከትላንት ምሽቱ ጨዋታ በፊት ስለወደፊት ቆይታው ሲጠየቅ " አሁን ትኩረቴ ጨዋታው ላይ ነው በቅርቡ እንደማውቅ ተስፋ አለኝ " በማለት ተናግሮ ነበር።

@tikvahethsport          @kidusyoftahe
የአማድ ዲያሎ የዩናይትድ ቆይታ ?

ኮትዲቯራዊው የፊት መስመር ተጨዋች አማድ ዲያሎ በማንችስተር ዩናይትድ ቤት ለረጅም ጊዜ የመቆየት ፍላጎት እንዳለው ተናግሯል።

“ በዩናይትድ በጣም ደስተኛ ነኝ “ ያለው ዲያሎ ለማንችስተር ዩናይትድ በመጫወቴ ደስተኛ ነኝ በክለቡ ለረጅም ጊዜ ቆይቼ ታሪክ መፃፍ እፈልጋለሁ ብሏል።

ተጨዋቹ ለማንችስተር ዩናይትድ ተሰልፎ በተጫወተባቸው ጨዋታዎች ጥሩ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል።

አማድ ዲያሎ በቀያይ ሴጣኖቹ ቤት ያለው ኮንትራት በ 2025 ክረምት ላይ የሚጠናቀቅ ይሆናል።

@tikvahethsport          @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
“ የጨዋታው ኮከብ ዳኛው ነበር “ ጆዜ ሞሪንሆ ከሜዳቸው ውጪ ተጉዘው ጣፋጭ ድል የተቀዳጁት ፌነርባቼ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ዳኛውን “ የጨዋታው ኮከብ “ ሲሉ ሰይመውታል። በጨዋታው ግልፅ ፍፁም ቅጣት ምት ተከልክለናል በሚል ከፍተኛ ቅሬታ ያቀረቡት ሞሪንሆ “ የጨዋታው ኮከብ ማን ነው ከተባለ ዳኛው ነው “ ብለዋል። በስታዲየም ስለነበረው ሁኔታ ያስረዱት አሰልጣኙ “ የምወቅሰው የፌነርባቼ ደጋፊዎችን…
አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ቅጣት ተጣለባቸው !

ፖርቹጋላዊው የፌነርባቼ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ባለፈው ሳምንት ከነበራቸው የሊግ ጨዋታ በኋላ ለመገናኛ ብዙሀን በሰጡት ቃል ምክንያት ቅጣት እንደተጣለባቸው ተገልጿል።

አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ከጨዋታው በኋላ የነበረውን ዳኝነት በከፍተኛ ሁኔታ የተቹ ሲሆን የቫር ዳኛውን “ የጨዋታው ኮከብ “ ሲሉ ገልፀው ነበር።

አሰልጣኙ ቀጥለውም የተጫወትነው እግርኳስ ብቻ አይደለም ' ሲስተሙን ' ጭምር ነው ሲሉ በቱርክ ሊግ ያለውን አጠቃላይ ዳኝነት ተችተዋል።

የቱርክ እግርኳስ ፌዴሬሽን በበኩሉ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ በሰጡት አስተያየት ምክንያት የአንድ ጨዋታ እና 1,300 ፓውንድ ቅጣት መጣሉን አሳውቋል።

ጆዜ ሞሪንሆ የተላለፈባቸው የጨዋታ ቅጣት መልበሻ ቤት አለመግባት እና ለተጨዋቾች ትዕዛዝ አለመስጠትን እንደሚጨምር ተገልጿል።

@tikvahethsport          @kidusyoftahe
“ ተጨዋቾቹ ሁሉንም ጨዋታ እንዲያሸንፉ አልጠይቅም “ አርኔ ስሎት

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ዋና አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ከነገው የአስቶን ቪላ ጨዋታ በፊት ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ አድርገዋል።

አሰልጣኙ በቆይታቸው ምን አሉ ?

- " እያስመዘገብን በምንገኘው ውጤት አልተገረምኩም ምክንያቱም ጥራት ያለው እና ሁሉንም ጨዋታዎች ማሸነፍ የሚችል ቡድን እንዳለን አውቆ ነበር።

- ተጨዋቾቼ ሁሉንም ጨዋታዎች እንዲያሸንፉ አልጠይቃቸውም ይልቁንም ሁልጊዜም በየቀኑ ጠንክረው እንዲሰሩ አሳስባቸዋለሁ።

- የሊጉ መሪ መሆናችን አያኮራንም ምክንያቱም ከተከታዮቻችን ያለን የነጥብ ልዩነት ዝቅተኛ እንደሆነ እናውቃለን በተጨማሪም በሊጉ መሪ ስንሆን ለመጀመርያ ጊዜ አይደለም።

- ደጋፊዎቻችን በብራይተኑ ያሳዩትን ድንቅ ድባብ በሁሉም ጨዋታዎቻችን ላይ እንደሚያስመለክቱን እናውቃለን እነሱ ለቡድናችን ትልቅ ሚናን ይጫወታሉ።" ብለዋል።

አሰልጣኙ በቆይታቸው ወቅት በጉዳት ላይ የሚገኘው ዲያጎ ጆታ ከሀገራት ጨዋታ አንድ ሳምንት በኋላ ወደ እንደሚመለስ ገልፀዋል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
🔥ከባድ ትንቅንቅ የማያጣው የለንደን ደርቢ

ቼልሲ ከ አርሰናል ጋር! ቼልሲ በሜዳው የለንደኑን ጎረቤት አርሰናልን እሁድ ህዳር 1 ከምሽቱ 1፡30 ይገናኛሉ!

ጥሩ አቋም ላይ ያልው ቼልሲ በጉዳት ምክንያት ውጤት ያጣውን አርሰናልን ነጥብ ማስጣል ይችላል?

🏆 ማን ይሆን 3 ነጥብ ማሸነፍ የሚችለው!

👉 ይህንን ድንቅ ፍልሚያ ጨምሮ ሌሎች የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ይመልከቱ።

👉 ዛሬውኑ ፓኬጅዎን ያሳድጉ። ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት በቀጥታ ይከታተሉ!

ደንብና ሁኔታዎች ተፈፀሚነት አላቸው! ለበለጠ መረጃ
👇
www.dstv.com/en-et

#PremierLeagueallonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
Forwarded from HEY Online Market
iPhone 16 Pro Max
•256GB = 189,000 Birr
•512GB = 219,000 Birr

iPhone 15 Pro Max
•256GB = 154,000 Birr
•512GB = 164,000 Birr

Contact us :
0925927457 @eBRO4
0953964175 @heymobile
@Heyonlinemarket
ማውሮ ኢካርዲ ለረጅም ጊዜ ከሜዳ ይርቃል !

የቱርኩ ክለብ ጋላታሳራይ የፊት መስመር ተጨዋች ማውሮ ኢካርዲ በትላንቱ የቶተንሀም ጨዋታ ያጋጠመው ጉዳት ከባድ መሆኑ ተገልጿል።

ተጨዋቹ በጉልበቱ ላይ ያጋጠመው ጉዳት የ " ACL " ጉዳት መሆኑን ክለቡ በይፋ አስታውቋል።

ይህንንም ተከትሎ ማውሮ ኢካርዲ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት እስከ ውድድር አመቱ መጨረሻ ከሜዳ ሊርቅ እንደሚችል ተገልጿል።

አርጀንቲናዊው አጥቂ ማውሮ ኢካርዲ በውድድር አመቱ ለጋላታሳራይ ባደረጋቸው 7️⃣ የሊግ ጨዋታዎች 4️⃣ ግቦችን አስቆጥሮ 1️⃣ አመቻችቶ አቀብሏል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ብራዚል ጋርዲዮላን መሾም ትፈልጋለች !

የብራዚል ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላን በአሰልጣኝነት የመሾም ፍላጎት እንዳለው ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።

የብራዚል እግርኳስ ፌዴሬሽን ፔፕ ጋርዲዮላን ለመሾም ግፊት በማድረግ ላይ መሆናቸው ሲገለፅ አሰልጣኙን የመጀመሪያ ምርጫ ማድረጋቸውም ተነግሯል።

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በበኩላቸው የብራዚል ብሔራዊ ቡድንን የማሰልጠን ሀሳብን እንደሚወዱት ተገልጿል።

የፔፕ ጋርዲዮላ በማንችስተር ሲቲ የኮንትራት ማራዘም ጉዳያቸው የክለቡ 1️⃣1️⃣5️⃣ ክሶች እልባት ከማግኘታቸው በፊት እንደሚታወቅ ተጠቁሟል።

አሰልጣኙ ማንችስተር ሲቲ ከባድ ቅጣት የሚጣልበት ከሆነ በክለቡ የመቀጠላቸው እድል ከፍ እንደሚል ተዘግቧል።

@tikvahethsport          @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የፕርሚየር ሊግ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ? የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ 2024/25 የውድድር ዘመን የወርሀ ጥቅምት የወሩ ምርጥ ተጨዋች ስምንት እጩዎች ይፋ ተደርገዋል። በዚህም መሰረት :- ፋኩንዶ ቡናኖቴ ብሪያን ምቤሞ ዮስኮ ቫርዲዮል ኮል ፓልመር ማትዝ ሴልስ ቡካዩ ሳካ ክሪስ ዎድ ዳኒ ዌልቤክ በእጩነት መቅረብ ችለዋል። @tikvahethsport    …
የፕርሚየር ሊግ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ታወቀ !

የእንግሊዝ የፕርሚየር ሊግ የወርሀ ጥቅምት የወሩ ምርጥ ተጨዋች ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት የኖቲንግሀም ፎረስቱ የፊት መስመር ተጨዋች ክሪስ ውድ የወርሀ ጥቅምት የወሩ ምርጥ ተጨዋች ተብሎ መመረጡ ተገልጿል።

ተጨዋቹ በወሩ ባደረጋቸው ሶስት የሊግ ጨዋታዎች አራት ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
መድፈኞቹ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር እያፈላለጉ ነው !

ከብራዚላዊው ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ኤዱ ጋስፐር ጋር የተለያየው አርሰናል አዲስ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ማፈላለግ መጀመሩ ተገልጿል።

መድፈኞቹ አሁን ላይ የቀድሞ ተጨዋቾቻቸው ቶማስ ሮዝስኪ እና መርቲ ሳከርን በመመልከት ላይ መሆናቸውን ፉትመርካቶ ዘግቧል።

የቀድሞ የመድፈኞቹ ተጨዋቾች ቶማስ ሮዝስኪ እና መርቲ ሳከር አሁን ላይ እጩ ሆነው መቅረባቸው ተነግሯል።

ጄሰን አይቶ በጊዜያዊነት ኤዱ ጋስፐርን በመተካት የአርሰናል ስፖርቲንግ ዳይሬክተርነት ሚናን እንደሚረከብ መገለፁ ይታወቃል።

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe
ሉክ ሾው ወደ ልምምድ ተመለሰ !

የማንችስተር ዩናይትዱ የመስመር ተጨዋች ሉክ ሾው ከጉዳቱ በማገገም ወደ ልምምድ መመለሱ ተገልጿል።

እንግሊዛዊው የመስመር ተጨዋች ሉክ ሾው በተደጋጋሚ ጉዳት ምክንያት ለረጅም ጊዜ ከሜዳ ርቆ መቆየቱ የሚዘነጋ አይደለም።

ሉክ ሾው በቀጣይ ከሀገራት ጨዋታ እረፍት በኋላ በአዲሱ አሰልጣኝ ለሚመራው ማንችስተር ዩናይትድ ግልጋሎት ሊሰጥ እንደሚችል ይጠበቃል።

ሉክ ሾው በዘንድሮው የውድድር ዘመን በጉዳት ምክንያት ለቀያይ ሰይጣኖቹ ምንም ጨዋታ ማድረግ እንዳልቻለ ይታወቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የፕርሚየር ሊግ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ማን ይሆናል ? የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ 2024/25 የውድድር ዘመን የወርሀ ጥቅምት የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ አራት እጩዎች ይፋ ተደርገዋል። በዚህም መሰረት :- አሰልጣኝ ኑኖ እስፕሪቶ ሳንቶ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ አሰልጣኝ ፋብያን ሁርዜለር አሰልጣኝ አርኔ ስሎት በእጩነት መቅረብ ችለዋል። @tikvahethsport     @kidusyoftahe
የፕርሚየር ሊግ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ታውቋል !

አስረኛ ሳምንቱ ላይ የደረሰው የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የወርሀ ጥቅምት የወሩ ምርጥ አሰልጣኝን ይፋ አድርጓል።

በዚህም ፖርቹጋላዊው የኖቲንግሀም ፎረስት አሰልጣኝ ኑኖ እስፕሪቶ ሳንቶ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ተብለው መመረጥ ችለዋል።

አሰልጣኝ ኑኖ እስፕሪቶ ሳንቶ ክለባቸውን እየመሩ በወሩ ካደረጓቸው ሶስት የሊጉ ጨዋታዎች #ሁለቱን በድል ሲያጠናቅቁ #በአንድ ጨዋታ ነጥብ ተጋርተዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
“ ለሁሉም ዋንጫዎች እንፋለማለን “ ካርሎ አንቾሎቲ

ተደጋጋሚ ሽንፈት የገጠማቸው ሎስ ብላንኮዎቹ ዋና አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ “ በእርግጠኝነት ለሁሉም ዋንጫዎች እንፋለማለን “ ሲሉ ተናግረዋል።

ቡድኑ ስላለበት ሁኔታ ከተጫዋቾቹ ጋር መምከራቸውን ያስረዱት አንቾሎቲ “ ነገ ባለፉት ቀናት የተነጋገርነውን እንደምናሳይ እርግጠኛ ነኝ “ ብለዋል።

“ የቡድኑ ችግር የአጥቂ ክፍሉ ሳይሆን የተከላካይ ክፍሉ ነው “ የሚሉት አሰልጣኙ “ የቪኒሰስ ጁኒየርን የመጫወቻ ቦታ አልቀይርም “ ሲሉ አረጋግጠዋል።

“ አሁን ስለዝውውር የምናወራበት ወቅት አይደለም ፤ ለገጠመን ችግር መፍትሔ እንዳገኘን አምናለሁ።“ አንቾሎቲ

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የመድፈኞቹ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የሚመሩት አርሰናሎች የወርሀ ጥቅምት የወሩ ምርጥ ተጨዋች #አራት እጩዎችን ይፋ አድርገዋል። በዚህም መሰረት :- ቡካዩ ሳካ ማርቲኔሊ ቶማስ ፓርቴ እና ካይ ሀቨርትዝ የጥቅምት ወር የአርሰናል ምርጥ ተጨዋች እጩ ሆነው መቅረብ ችለዋል። የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል @tikvahethsport    …
የመድፈኞቹ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ታውቋል !

በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የሚመሩት አርሰናሎች የወርሀ ጥቅምት የወሩ ምርጥ ተጨዋቻቸውን ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሰረት እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጨዋች ቡካዮ ሳካ የአርሰናል የወሩ ምርጥ ተጨዋች ሆኖ መመረጥ ችሏል።

ተጨዋቹ በወሩ ባደረጋቸው ጨዋታዎች 3️⃣ ግቦችን ሲያስቆጥር 2️⃣ ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

ቡካዮ ሳካ ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ድምፅ በማግኘት ማሸነፉ ሲገለፅ ሽልማቱን ሲያሸንፍ #ለስምንተኛ ጊዜ መሆኑ ተመላክቷል።

@tikvahethsport        @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሪቻርልሰን ለሳምንታት ከሜዳ ሊርቅ ይችላል ! ብራዚላዊው የቶተንሀም የፊት መስመር አጥቂ ሪቻርልሰን በእሁዱ የአስቶን ቪላ ጨዋታ ጉዳት አስተናግዶ ከሜዳ ተቀይሮ መውጣቱ ይታወሳል። አሁን ላይ ተጨዋቹ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት ከሶስት እስከ አራት ሳምንታት ከሜዳ ሊርቅ እንደሚችል ተዘግቧል። ሪቻርልሰን ስለ ጉዳቱ ለደጋፊው ባስተላለፈው መልዕክትም " በድጋሜ ተጎድቼ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ገብቻለሁ “…
ሪቻርልሰን ለረጅም ጊዜ ከሜዳ ይርቃል !

የቶተንሀሙ የፊት መስመር ተጨዋች ሪቻርልሰን በጉዳት ምክንያት ለረጅም ጊዜ ከሜዳ እንደሚርቅ አሰልጣኝ አንሄ ፖስቴኮግሉ አረጋግጠዋል።

ብራዚላዊው ተጨዋች ሪቻርልሰን የከፋ ጉዳት እንዳጋጠመው ያረጋገጡት አሰልጣኙ " እሱን ለረጅም ጊዜ የምናጣው ይሆናል " ብለዋል።

ተጨዋቹ ክለቡ ቶተንሀም ከአስቶን ቪላ ጋር ባደረገው የሊጉ መርሐ ግብር ጉዳት አስተናግዶ ከሜዳ ተቀይሮ መውጣቱ ይታወሳል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe