TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.7K photos
1.48K videos
5 files
3.41K links
加入频道
" ሀሜስ ሮድሪጌዝ የእኔ አርኣያ ነው " ሉዊስ ዲያዝ

የኮሎምቢያ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጨዋች ሉዊስ ዲያዝ ለብሔራዊ ቡድኑ አምበል ሀሜስ ሮድሪጌዝ ትልቅ አድናቆት እንዳለው ተናግሯል።

ኮሎምቢያ ትላንት ሌሊት ዩራጓይን 1ለ0 በማሸነፍ ከአርጀንቲና ጋር ለሚደረገው የ2024 ኮፓ አሜሪካ ፍፃሜ ጨዋታ ማለፍ ችለዋል።

በጨዋታው ጥሩ እንቅስቃሴ ማድረግ ስለቻለው የቡድን አጋሩ ሀሜስ ሮድሪጌዝ አስተያየቱን የሰጠው ሉዊስ ዱያዝ “ የብሔራዊ ቡድኑ የመጀመሪያ ጨዋታዬን ሳደርግ ጀምሮ እሱ የእኔ አርኣያ እንደሆነ ነግሬዋለሁ " ሲል ተደምጧል።

የቡድኑ አምበል ሀሜስ ሮድሪጌዝ በኮፓ አሜሪካ ጥሩ ጊዜን እያሳለፉ ከሚገኙ ተጨዋቾች አንዱ ሲሆን ካደረጋቸው አምስት ጨዋታዎች በአራቱ የጨዋታው ኮከብ ተብሎ መመረጥ ችሏል።

ሀሜስ ሮድሪጌዝ በተጨማሪም በአንድ የኮፓ አሜሪካ ውድድር ስድስት ለግብ የሆኑ ኳሶች አመቻችቶ በማቀበል በሊዮኔል ሜሲ በአምስት ተይዞ የነበረውን ሪከርድ ሰብሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሲፋን ሀሰን በአራት ርቀቶች ልትወዳደር ነው !

ለኔዘርላንድ የምትሮጠው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሲፋን ሀሰን በቀጣዩ የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር በአራት ርቀቶች ልትወዳደር መሆኑን የሀገሪቱ ፌዴሬሽን አረጋግጧል።

አትሌቷ በፓሪስ ኦሎምፒክ በ10000 ፣ 5000 ፣ 1500 ሜትር እና ማራቶን ውድድሮች እንደምትሳተፍ ተገልጿል።

የ 31ዓመቷ አትሌት ሲፋን ሀሰን በሁሉም ውድድሮች ፍፃሜ የምትደርስ ከሆነ በድምሩ በዘጠኝ ቀናት ውስጥ 65.5 ኪሎ ሜትር ያህል መሮጥ የሚጠበቅባት ይሆናል።

አትሌት ሲፋን ሀሰን በቶኪዮ ኦሎምፒክ ውድድር በሶስት ርቀቶች መሳተፏ የሚታወስ ሲሆን ሁለት የወርቅ እና አንድ የነሀስ ሜዳልያ ማስመዝገቧ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የባየር ሙኒክ ጥያቄው ተቀባይነት አገኘ ! የጀርመን ቡንደስሊጋው ክለብ ባየር ሙኒክ የፉልሀሙን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጇ ፓልሂንሀ ለማስፈረም ከክለቡ ጋር ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። ከተጨዋቹ ጋር ቀደም ብለው በግል ከስምምነት የደረሱት ባየር ሙኒኮች አሁን ላይ ለፉልሀም ያቀረቡት 56 ሚልዮን ዩሮ የሚደረሰስ ሒሳብ ተቀባይነት ማግኘቱ ተገልጿል። ፉልሀም ከተጨዋቹ ዝውውር የሚያገኙት 51 ሚልዮን…
ባየር ሙኒክ በይፋ ተጨዋች አስፈረሙ !

የጀርመን ቡንደስሊጋው ክለብ ባየር ሙኒክ የፉልሀሙን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጇ ፓልሂንሀን ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ፖርቹጋላዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጇ ፓልሂንሀ በባየር ሙኒክ ቤት እስከ 2028 የሚያቆየውን የአራት አመት ኮንትራት መፈረሙ ይፋ ተደርጓል።

ፉልሀም ከተጨዋቹ ዝውውር 50 ሚልዮን ዩሮ ቋሚ ክፍያ እና ተጨማሪ ታይት የሚከፈል ክፍያ እንደሚቀበሉ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የዩራጓይ ተጨዋቾች ከደጋፊዎች ጋር ለምን ተጋጩ ?

በትላንት ምሽቱ የኮሎምቢያ እና ዩራጓይ ኮፓ አሜሪካ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ዳርዊን ኑኔዝ እና ሌሎች የዩራጓይ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ከኮሎምቢያ ደጋፊዎች ጋር ፀብ ውስጥ ገብተው ነበር።

ዩራጓይ ሽንፈት ካስተናገደችበት ጨዋታ በኋላ ዳርዊን ኑኔዝ እና የቡድን አጋሮቹ ወደ ተመልካች መቀመጫ ወንበሮች በማምራት ከደጋፊዎች ጋር ሲደባደቡ ተስተውለዋል።

ተጨዋቾቹ ይህንን ያደረጉት የኮሎምቢያ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች የዩራጓይ ተጨዋቾች ቤተሰቦች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል።

የዩራጓይ አምበል ጆዜ ሂሚኔዝ በሰጠው አስተያየትም " የተፈጠረው አደገኛ ነበር ምንም ፖሊስ አልነበረም እኛም ቤተሰቦቻችንን መጠበቅ ነበረብን " ሲል ሁኔታውን አስረድቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜን ማን ይመራዋል ?

የፊታችን እሁድ በስፔን እና እንግሊዝ መካከል የሚደረገውን የአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ የሚመሩት ዳኛ ታውቀዋል።

በግዙፉ ኦሎምፒያስታድዮን ስታዲየም የሚደረገውን ተጠባቂ የፍፃሜ ጨዋታ ፈረንሳዊው ዳኛ ፍራንኮይስ ሌቴዤር በመሀል ዳኝነት እንደሚመሩት ይፋ ተደርጓል።

ጨዋታውን ማን ያሸንፋል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ምባፔ የዘጠኝ ቁጥር ማልያ ይለብሳል ! ሪያል ማድሪዶች ለሚቀጥለው የውድድር ዘመን ለስድስት ተጨዋቾች አዲስ ቁጥር ማልያ አስተዋውቀዋል። ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ የዘጠኝ ቁጥር ማልያ እንደሚለብስ ሲገለፅ ከነገ ጀምሮ በማድሪድ የሽያጭ ሱቅ በገበያ ላይ ይቀርባልም ተብሏል። በተጨማሪም በሚቀጥለው አመት :- ካማቪንጋ 6 ቁጥር ፣ ቫልቬርዴ 8 ቁጥር ፣ ቹዋሜኒ 14 ቁጥር ፣…
የምባፔ ማልያ ከፍተኛ ፈላጊዎች ማግኘቱ ተገለጸ !

በቅርቡ ሪያል ማድሪድን የተቀላቀለው ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ማልያዎች በክለቡ የሽያጭ ሱቅ ከፍተኛ ፈላጊዎች ማግኘቱ ተገልጿል

የማልያው ፈላጊዎች ቁጥር ከተጠበቀው በላይ በመሆኑ ምክንያት ማልያውን ለመረከብ ከአራት እስከ ስድስት ሳምንታት ሊወስድ እንደሚችል ሪያል ማድሪድ አሳውቋል።

በዚህም ምክንያት ዛሬ ማልያውን የሚያዙ የሪያል ማድሪድ ደጋፊዎች እስከ ላሊጋው የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር ድረስ እንደማይቀበሉ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
📢 #ዋናው በቴሌግራም የስፖርት አልባሳትን እንዴት ያዛሉ?

👉🏾 በቴሌግራም ሊንክ @Wanawsales በመጠቀም የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ይዘዙን።

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
ቡናማዎቹ ተጋጣሚያቸውን አውቀዋል !

ሀገራችን ኢትዮጵያን በመወከል በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ውድድር የሚሳተፈው ኢትዮጵያ ቡና የቅድመ ማጣሪያ ተጋጣሚውን አውቋል።

ይህንንም ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና የመጀመሪያ ዙር የማጣሪያ ጨዋታውን ከኬንያው ኬንያ ፖሊስ እግርኳስ ክለብ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

ቡናማዎቹ ይህንን ጨዋታ ካሸነፉ በሁለተኛው ዙር ማጣሪያ ጨዋታ ከግብፁ ክለብ ዛማሊክ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

ጨዋታዎቹ መቼ ይደረጋሉ ?

የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች :- የመጀመሪያው ጨዋታ ከነሀሴ 10-12/2016 ዓ.ም እንዲሁም የመልስ ጨዋታ ከነሀሴ 17-19/2016 ዓ.ም ባሉት ቀናቶች ይደረጋሉ።

ሁለተኛ ዙር :- የመጀመርያ ጨዋታዎች ከመስከረም 3-5/2017 ዓ.ም ባሉት ቀናቶች እንዲሁም የመልስ ጨዋታ ከመስከረም 10-12/2017 ዓ.ም ባሉት ቀናቶች እንደሚደረጉ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ንግድ ባንኮች ተጋጣሚያቸውን አውቀዋል !

ሀገራችን ኢትዮጵያን በመወከል በአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር የሚሳተፈው የሊጉ ሻምፒዮን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቅድመ ማጣሪያ ተጋጣሚውን አውቋል።

ይህንንም ተከትሎ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመጀመሪያ ዙር የማጣሪያ ጨዋታውን ከዩጋንዳው ቪላ ጆጎ ክለብ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

ንግድ ባንክ ይህንን ጨዋታ ካሸነፉ በሁለተኛው ዙር ማጣሪያ ጨዋታ የታንዛኒያው ያንግ አፍሪካ እና የቡሩንዲውን ቪታሎ እግርኳስ ክለብ አሸናፊን የሚያገኙ ይሆናል።

ጨዋታዎቹ መቼ ይደረጋሉ ?

የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች :- የመጀመሪያው ጨዋታ ከነሀሴ 10-12/2016 ዓ.ም እንዲሁም የመልስ ጨዋታዎች ከነሀሴ 17-19/2016 ዓ.ም ባሉት ቀናቶች ይደረጋሉ።

ሁለተኛ ዙር :- የመጀመርያ ጨዋታዎች ከመስከረም 3-5/2017 ዓ.ም ባሉት ቀናቶች እንዲሁም የመልስ ጨዋታዎች ከመስከረም 10-12/2017 ዓ.ም ባሉት ቀናቶች እንደሚደረጉ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ ዝውውሮቹን በፍጥነት ማጠናቀቅ ይፈልጋሉ !

በዝውውር መስኮቱ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ የሚገኙት ማንችስተር ዩናይትዶች የማትያስ ዴሊትን እና ጆሽዋ ዚርክዜን ዝውውር በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየሰሩ መሆኑ ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትድ አሁን ላይ ከባየር ሙኒክ ጋር በማትያስ ዴሊት የዝውውር ሒሳብ ዙሪያ ለስምምነት መቃረባቸው ተነግሯል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች በተጨማሪም ጆሽዋ ዚርክዜን ዝውውር ለማጠናቀቅ የተወሰኑ ስራዎች እንደሚቀሯቸው ተነግሯል።

ተጨዋቹ የህክምና ምርመራውን ለማድረግ ወደ ማንችስተር ለመጓዝ በዝግጅት ላይ መሆኑ ሲገለፅ በሚቀጥሉት ቀናት ዝውውሩ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የርገን ክሎፕ ወደ አሜሪካ ያመሩ ይሆን ?

የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን ጀርመናዊውን አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ በቀጣይ የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አድርገው በሀላፊነት ለመሾም ጥረት ሊያደርጉ መሆኑ ተገልጿል።

አሜሪካ ካዘጋጀችው የዘንድሮው የኮፓ አሜሪካ ምድብ ጨዋታ መሰናበቷን ተከትሎ አሰልጣኝ ግሬግ ቤርሀልተርን ከአሰልጣኝነት ማሰናበቷ ይታወቃል።

አሜሪካ በቀጣይ በጣምራ በምታዘጋጀው የ2026 አለም ዋንጫ ውድድር አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ቡድኑን እንዲመሩ ፍላጎት እንዳላት ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዩናይትድ ዝውውሮቹን በፍጥነት ማጠናቀቅ ይፈልጋሉ ! በዝውውር መስኮቱ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ የሚገኙት ማንችስተር ዩናይትዶች የማትያስ ዴሊትን እና ጆሽዋ ዚርክዜን ዝውውር በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየሰሩ መሆኑ ተገልጿል። ማንችስተር ዩናይትድ አሁን ላይ ከባየር ሙኒክ ጋር በማትያስ ዴሊት የዝውውር ሒሳብ ዙሪያ ለስምምነት መቃረባቸው ተነግሯል። ቀያዮቹ ሴጣኖች በተጨማሪም ጆሽዋ ዚርክዜን ዝውውር ለማጠናቀቅ…
ጆሽዋ ዚርክዜ ዛሬ ምሽት ወደ እንግሊዝ ያመራል !

ኔዘርላንዳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ጆሽዋ ዚርክዜ ከቦሎኛ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ የሚያደርገውን ዝውውር ለማጠናቀቅ ዛሬ ምሽት ወደ እንግሊዝ እንደሚያመራ ተገልጿል።

የ 23ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ጆሽዋ ዚርክዜ በነገው ዕለት የህክምና ምርመራውን በማድረግ በይፋ ማንችስተር ዩናይትድን ይቀላቀላል።

ማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋቹን በ 42.5 ሚልዮን ዩሮ በሆነ የዝውውር ሒሳብ በአምስት አመት ኮንትራት እንደሚያስፈርሙት ተገልጿል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች በተጨማሪም ሩድ ቫን ኔስትሮይ እና ሬኔ ሀኬን በክለቡ የአሰልጣኞች ቡድን ውስጥ ማካተታቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዩናይትድ ከቫን ዴ ቢክ ዝውውር ስንት ያገኛል ? የማንችስተር ዩናይትዱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ዶኒ ቫን ዴቢክ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊውን የስፔን ክለብ ጂሮና ለመቀላቀል ከጫፍ መድረሱ ተገልጿል። ቀያዮቹ ሴጣኖች ከተጨዋቹ ዝውውር 500,000 ዩሮ እንደሚቀበሉ ሲገለፅ በውሉ ውስጥ ታይቶ የሚጨምር እስከ አራት ሚልዮን ዩሮ የሚሆን ክፍያ እንደሚካተት ተነግሯል። ኔዘርላንዳዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች…
ዶኒ ቫን ዴ ቢክ በይፋ ጂሮናን ተቀላቀለ !

የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊው የስፔኑ ክለብ ጂሮና ኔዘርላንዳዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ዶኒ ቫን ዴቢክ ከማንችስተር ዩናይትድ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ጂሮና ለተጨዋቹ ዝውውር 500,000 ዩሮ የዝውውር ሒሳብ ለማንችስተር ዩናይትድ መክፈላቸው ተገልጿል።

ዶኒ ቫን ዴቢክ በጂሮና እስከ 2028 የሚያቆየውን የአራት አመት ኮንትራት መፈረሙ ይፋ ተደርጓል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe