ኢትዮጵያ ቡና ይፋዊ አጋር የሆነው ቤቲካ - የኢትዮጵያ ቡናን አስራ ሶስተኛ የጨዋታ ቀን የዲጂታል መፅሄት ይዞ ቀርቧል። በመፅሄቱ ላይ የዕለቱ ጨዋታን የተመለከቱና ሌሎች የተለያዩ መረጃዎች የሚቀርቡ ይሆናል፡፡
መፅሔቱን ለማግኘት - https://yangx.top/betikaethiopia/5151
ቤቲካ - የኢትዮጵያ ቡና ይፋዊ አጋር

🇪🇹 ዋናው 🤝 ቢሾፍቱ ጤና ስፖርት ማህበር 🇪🇹
የቢሾፍቱ ከተማ ጤና ስፖርት ማህበር የበጋ የውስጥ እግር ኳስ ውድድር በቢሾፍቱ!
ውድድር ካለ #ዋናው አለ!
Instagram | Facebook | TikTok
🏅 ዋናው ወደፊት...
@wanawsportwear

ኬቨን ዴብሮይን መጠነኛ ጉዳት አጋጥሞታል !
የማንችስተር ሲቲው ቤልጂየማዊ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኬቨን ዴብሮይን መጠነኛ ጉዳት እንዳጋጠመው ተገልጿል።
በዚሁ ጉዳት ምክንያት ለቤልጂየም ብሔራዊ ቡድን ጥሪ እንዳልተደረገለት የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ዶምኒኮ ቴዴስኮ ተናግረዋል።
ማንችስተር ሲቲ ከሊቨርፑል በነበረው ጨዋታ ከጉዳቱ ጋር ተጫውቶ እንደነበር የጠቆሙት አሰልጣኙ በክለቡ በጥሩ ሁኔታ አገግሞ ለአውሮፓ ዋንጫው እንዲዘጋጅ ጊዜ መስጠት አለብን ብለዋል።
ቤልጂየም ከሳምንት በኋላ ከአየርላንድ እና እንግሊዝ ብሔራዊ ቡድኖች ጋር ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎች ታደርጋለች።
@tikvahethsport @kidusyoftahe

TIKVAH-SPORT
አርሰናል ተጫዋቹ ኮንትራት ለማራዘም ተስማማ ! የመድፈኞቹ የመሐል ተከላካይ ቤን ዋይት የተሻሻለ የረጅም ጊዜ ኮንትራት ከክለቡ ጋር በመፈራረም ለተጨማሪ ዓመታት በክለቡ ለመቆየት መስማማቱ ተገልጿል። የ 26ዓመቱ ቤን ዋይት ያለፉትን ወራት ከክለቡ ጋር ሲነጋገር የቆየ ሲሆን አሁን ላይ ከስምምነት መድረሳቸውን ተከትሎ በሳምንቱ መጨረሻ ስምምነቱ ይፋ እንደሚሆን ተዘግቧል። እንግሊዛዊው ተከላካይ ቤን ዋይት…
አርሰናል የተጫዋቹን ኮንትራት አራዘመ !
የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የመሐል ተከላካዩ ቤን ዋይትን ኮንትራት ለተጨማሪ አመታት ማራዘማቸውን ይፋ አድርገዋል።
የ 26ዓመቱ ተከላካይ ቤን ዋይት በመድፈኞቹ ቤት እስከ 2028 የሚያቆየውን የተጨማሪ ለሁለት አመታት ውል መፈረሙ ይፋ ሆኗል።
ተጨዋቹ ውሉን ካራዘመ በኋላ አስተያየት የሰጡት አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ " ቢን ዋይት በክለቡ ለመቆየት መወሰኑ ጥሩ ዜና ነው እሱ ቁልፍ ተጨዋቻችን ነው።"ሲሉ ተደምጠዋል።

ፊሊፕስ ለብሔራዊ ቡድኑ ጥሪ አልቀረበለትም !
የዌስትሀም ዩናይትዱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ካልቪን ፊሊፕስ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ስብስብ በአሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት ጥሪ ሳይቀርብለት ቀርቷል።
ሌላኛው የዌስትሀም ዩናይትድ የፊት መስመር ተጨዋች ጃሮድ ቦውን የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ ለሚያደርጋቸው የወዳጅነት ጨዋታዎች ጥሪ ቀርቦለታል።
እንግሊዝ ከሳምንት በኋላ ከብራዚል እና ቤልጂየም ጋር ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎችን ታደርጋለች።

ጊል ማንዛኖ የሊጉን ጨዋታዎች አይመሩም !
ከሳምንት በፊት አነጋጋሪ የነበረውን የቫሌንሽያ እና ሪያል ማድሪድ የሊግ ጨዋታ የመሩት ዋና ዳኛ ጊል ማንዛኖ በድጋሜ በሳምንቱ መጨረሻ ጨዋታ እንዲመሩ ሳይመረጡ ቀርተዋል።
ዋና ዳኛው የሁለቱ ክለቦችን ጨዋታ ከመሩ ወዲህ ምንም አይነት የሊጉ ጨዋታዎችን እንዲመሩ መመረጥ አልቻሉም።
በጨዋታው ዳኛው ምን ውሳኔ አሳልፈው ነበር ?
ሪያል ማድሪድ ከቫሌንሽያ ሁለት አቻ በተለያዩበት ጨዋታ ሎስ ብላንኮዎቹ በመጨረሻ ደቂቃ የማሸነፊያ ግብ ቢያስቆጥሩም ዳኛው ቀድሜ ፊሽካ ነፍቻለሁ በሚል ጎሉን ሳያፀድቁ መቅረታቸው ይታወሳል።
በጨዋታው በተፈጠረ አለመግባባት የተሻረውን የሪያል ማድሪድ ሶስተኛ ግብ ያስቆጠረው ጁድ ቤሊንግሀም ቀይ ካርድ ተመልክቶ ነበር።

ጃራድ ብራንዝዌት ለእንግሊዝ ጥሪ ይቀርብለታል !
የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን የመሐል ተከላካይ ጃራድ ብራንዝዌት ለመጀመሪያ ጊዜ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ እንደሚቀርብለት ተገልጿል።
በእንግሊዝ ከ 21ዓመት በታች ቡድን ሲጫወት የነበረው ጃራድ ብራንዝዌት ባለፈው ክረምት በውሰት ካመራበት ፒኤስቪ ወደ ኤቨርተን ተመልሶ በዘንድሮው የውድድር አመት ጥሩ ጊዜን በማሳለፍ ላይ ይገኛል።
የጃራድ ብራንዝዌቱ ኤቨርተን በዘንድሮው የውድድር አመት በስምንት ጨዋታዎች ግብ ሳይቆጠርበት የወጣ ሲሆን ይህም ከአርሰናል እና ሊቨርፑል ቀጥሎ ሶስተኛው ክለብ ያደርገዋል።

እንግሊዝ ስብስቧን አሳውቃለች !
የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ ከብራዚል እና ቤልጂየም ጋር ላለባቸው የወዳጅነት ጨዋታ ለተጨዋቾች ጥሪ አቅርቧል።
በስብስቡ ውስጥ ጃሮድ ቦውን ፣ ኦሊ ዋትኪንስ ፣ ጃራድ ብራንዝዌት ፣ ኢቫን ቶኒ እና አንቶኒ ጎርደን ተካተዋል።
ሙሉ የቡድን ስብስብ ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

ቤን ዋይት ብሔራዊ ቡድኑን መቀላቀል አይፈልግም !
የመድፈኞቹ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ቤን ዋይት ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ያልተመረጠው ጥሪ እንዳይደረግለት ጠይቆ መሆኑን አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት ተናግረዋል።
አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት በንግግራቸውም " ባለፈው ሳምንት ከአርሰናል ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ኤዱ ስልክ ተደውሎልን ቤን ዋይት አሁን ላይ ቡድኑን መቀላቀል እንደማይፈልግ ነግረውናል የሚያሳፍር ነው።"ሲሉ ተደምጠዋል።

የጣና ሞገዶቹ ወሳኝ ድል አሳክተዋል !
በ 2016 የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አስራ ስምንተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባህርዳር ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችልዋል።
የባህርዳር ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ቸርነት ጉግሳ ፣ ሀብታሙ ታደሰ እና ሙጂብ ቃሲም ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።
የቡናማዎቹን ብቸኛ ግብ አንተነህ ተፈራ ማስቆጠር ችሏል።
የኢትዮጵያ ቡናው የፊት መስመር ተጨዋች አንተነህ ተፈራ ስምንተኛ የሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።
በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?
5️⃣ ኢትዮጵያ ቡና :- 29 ነጥብ
6️⃣ ባህርዳር ከተማ :- 29 ነጥብ
ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?
ሐሙስ - ኢትዮጵያ ቡና ከ ፋሲል ከነማ
ቅዳሜ - ባህርዳር ከተማ ከ ወልቂጤ ከተማ

" አል ሂላል በትልቅ የአውሮፓ ሊግ መፎካከር ይችላል " ያሲን ቦኑ
ሞሮኳዊው የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ሂላል ግብ ጠባቂ ያሲን ቦኑ አል ሂላል በትልቅ የአውሮፓ ሊግ ውስጥ ለዋንጫ መፎካከር እንደሚችል ገልጿል።
አል ሂላል ጥሩ የቡድን ስብስብ መያዙን የገለፀው ያሲን ቦኑ " አል ሂላል በያዛቸው ተጨዋቾች በትልቅ የአውሮፓ ሊግ ለዋንጫ መፎካከር ይችላል። " ሲል ተደምጧል።
አውሮፓን የለቀቀው አዲስ ፈተናን ፈልጎ መሆኑን ያስረዳው ያሲን ቦኑ አል ሂላል ሁልጊዜ ዋንጫ ማሸነፍ የሚፈልግ ትልቅ ክለብ መሆኑን አውቆ መቀላቀሉን ጠቁሟል።

አዳማ ከተማ ድል አድርጓል !
ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አስራ ስምንተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አዳማ ከተማ ከሀምበሪቾ ዱራሜ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችልዋል።
የአዳማ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ቦና ዓሊ 2x እና ዮሴፍ ታረቀኝ ከመረብ ማሳረፍ የቻሉ ተጨዋቾች ናቸው።
ሀምበሪቾ ዱራሜ በውድድር ዘመኑ አስራ ሶስተኛ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።
በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?
7️⃣ አዳማ ከተማ :- 27 ነጥብ
1️⃣6️⃣ ሀምበሪቾ ዱራሜ :- 7 ነጥብ
ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?
አርብ - አዳማ ከተማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ
አርብ - ሀድያ ሆሳዕና ከ ሀምበሪቾ ዱራሜ

የኤሪክ ቴንሀግ የዩናይትድ ቆይታ ?
ኔዘርላንዳዊው የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በውድድር አመቱ መጨረሻ ከክለቡ ጋር መለያየታቸውን የሚያመላክት ነገር #አለመኖሩን ለክለቡ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ገልፀዋል።
የክለቡን ስፖርታዊ ጉዳዮች የሚቆጣጠረው አዲሱ የማንችስተር ዩናይትድ አነስተኛ ድርሻ ባለቤት ሰር ጂም ራትክሊፍ በቀጣይ አዲስ አሰልጣኝ ሊሾሙ ይችላሉ የሚል መረጃ ሲነገር እንደነበር ይታወቃል።
አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በበኩላቸው ክለቡን በሀላፊነት እየመሩ በትክክለኛው መንገድ ላይ መሆናቸውን በተደጋጋሚ መግለፃቸው አይዘነጋም።

#Europaleague
በዩሮፓ ሊግ ጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታ ኤሲ ሚላን ስላቭያ ፕራግን 3ለ1 በሆነ ውጤት ሲረታ ዌስትሀም ዩናይትድ ፍሬቡርግን 5ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
የዌስትሀም ዩናይትድን የማሸነፊያ ግቦች መሐመድ ኩዱስ 2x ፣ ፓኩዌታ ፣ ቦውን እና ግሬስዌል ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።
ለኤሲ ሚላን ክርስቲያን ፑልሲች ፣ ሉፍተስ ቼክ እና ራፋኤል ሊያኦ ሲያስቆጥሩ ጁራሴክ የስላቭያ ፕራግን ግብ ከመረብ አሳርፏል።
ይህንንም ተከትሎ ኤሲ ሚላን በድምር ውጤት ስላቭያ ፕራግን 7ለ3 እንዲሁም ዌስትሀም ፍሬቡርግን 5ለ1 በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል።
የዩሮፓ ሊግ ሩብ ፍፃሜ እነማን ተቀላቀሉ ?
- ኤሲ ሚላን
- ዌስትሀም ዩናይትድ
- ማርሴይ
- ቤኔፊካ