TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.8K photos
1.48K videos
5 files
3.42K links
加入频道
የጨዋታ አሰላለፍ !

1:30 ኖቲንግሀም ከ አርሰናል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
84' በርንማውዝ 0-1 ማንችስተር ዩናይትድ

               ካሴሚሮ

79' ሊቨርፑል 0-1 አስቶን ቪላ

                  ራምሴ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ ወሳኝ ድል አስመዝግቧል !

ማንችስተር ዩናይትድ ከበርንማውዝ ጋር ያደረገውን የሊግ መርሐ ግብር 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የማንችስተር ዩናይትድን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ካሲሜሮ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ማንችስተር ዩናይትድ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስልሳ ዘጠኝ ነጥቦችን በመሰብሰብ አራተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችለዋል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ ከ ቼልሲ እንዲሁም በርንማውዝ ከኤቨርተን የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊቨርፑል ነጥብ ተጋርቷል !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ከአስቶን ቪላ ጋር ያደረገውን የሊግ መርሐ ግብር 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ማጠናቀቅ ችሏል።

የአስቶን ቪላን ግብ ራምሴይ ከመረብ ማሳረፍ ሲችል ሮቤርቶ ፌርሚኖ የሊቨርፑልን የአቻነት ግብ አስቆጥሯል።

ሊቨርፑል በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስልሳ ስድስት ነጥቦችን በመሰብሰብ አምስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ አስቶንቪላ በሀምሳ ስምንት ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ሊቨርፑል ከሳውዛምፕተን እንዲሁም አስቶንቪላ ከ ብራይተን ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

በሌሎች የሊግ መርሐ ግብሮች ዎልቭ እና ኤቨርተን 1ለ1 እንዲሁም ክሪስታል ፓላስ እና ፉልሀም 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
21'  ኖቲንግሀም 1-0 አርሰናል

አዎኒዪ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከ ለገጣፎ ለገዳዲ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የኢትዮጵያ ቡናን ግብ መሐመድ ናስር ሲያስቆጥር ለለገጣፎ ለገዳዲ አማኑኤል አረቦ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

የኢትዮጵያ ቡናው የፊት መስመር ተጨዋች መሐመድ ናስር በውድድር አመቱ አስረኛ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ኢትዮጵያ ቡና በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ነጥቦቹን ሰላሳ አምስት በማድረስ አምስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ለገጣፎ ለገዳዲ በአስራ ሁለት ነጥብ አስራ አምስተኛ ደረጃን ይዟል።

- በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከ ሀድያ ሆሳዕና እንዲሁም ለገጣፎ ለገዳዲ ከ አዳማ ከተማ ጋር ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
87 ' ኖቲንግሀም 1-0 አርሰናል

አዎኒዪ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርሰናል ሽንፈት አስተናግዷል !

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሰላሳ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አርሰናል ከ ኖቲንግሀም ፎረስት ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

የኖቲንግሀም ፎረስትን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ አዎኒዪ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ኖቲንግሀም ፎረስት ማሸነፉን ተከትሎ በቀጣይ የውድድር አመት በሊጉ መቆየቱን ማረጋገጥ ችሏል።

አርሰናል በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ በሰማንያ አንድ ነጥቦች ሁለተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ኖቲንግሀም ፎረስት በሰላሳ ሰባት ነጥብ አስራ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር አርሰናል ከዎልቭስ እንዲሁም ኖቲንግሃም ፎረስት ከክሪስታል ፓላስ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🏆🏆🏆 CHAMPION 🏆🏆🏆

በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የሚመሩት ማንችስተር ሲቲዎች የ 2022/23 የውድድር ዓመት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

ማንችስተር ሲቲዎች በዛሬው ዕለት ተከታያቸው አርሰናል መሸነፉን ተከትሎ ቀሪ ጨዋታዎች እየቀሯቸው ሻምፒዮን ለመሆን ችለዋል።

ማንችስተር ሲቲዎች ለሶስተኛ ተከታታይ ዓመት የሊጉ ሻምፒዮናነትን ሲያሸንፉ በክለቡ ታሪክ ዘጠነኛው ሆኗል።።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፔፕ ጋርድዮላ አዲስ ታሪክ ፅፈዋል !

ስፔናዊው የማንችስተር ሲቲ ዋና አሰልጣኝ ከሲቲ ጋር ለሶስተኛ ተከታታይ ዓመት የሊጉን ዋንጫ ማሳካታቸውን ተከትሎ ቀዳሚው አሰልጣኝ በመሆን ታሪክ ፅፈዋል።

አሰልጣኙ ከሶስት የተለያዩ ክለቦች ጋር ለተከታታይ ሶስት ዓመታት የሊግ ዋንጫዎችን በማሳካት አዲስ ታሪክ ማስመዝገባቸው ተዘግቧል።

በዚህም መሰረት :-

ባርሴሎና :- 2009 - 2010 - 2011 የውድድር ዓመት

ባየር ሙኒክ :- 2014 - 2015 - 2016 የውድድር ዓመት

ማንችስተር ሲቲ :- 2021 - 2022 - 2023 የውድድር ዓመት ላይ የሊግ ዋንጫውን ከተለያዩ ክለቦች ጋር አሳክተዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የፔፕ ጋርድዮላ የስኬት ጉዞ !

ስፔናዊው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርድዮላ ስኬታማ የሚባል ጉዞ ሲቀጥል በአሰልጣኝነት ዘመናቸው አስራ አንደኛ የሊግ ዋንጫቸውን በዛሬው ዕለት ማሳካት ችለዋል።

አሰልጣኙ በአስራ አምስት ዓመት የአሰልጣኝነት ዘመን ቆይታቸው ያሳኩት አስራ አንደኛው የሊግ ዋንጫ ሆኖ ተመዝግቧል።

ፔፕ ጋርድዮላ በሊጉ ታሪክ ሶስት ተከታታይ የሊግ ዋንጫዎችን በማሸነፍ የሰር አሌክስ ፈርጉሰንን ሪከርድ መጋራት ችለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሲቲዎች እንኳን ደስ አላችሁ " ሚኬል አርቴታ

የመድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በኖቲንግሀም ከደረሰባቸው ሽንፈት በኋላ በሰጡት አስተያየት የሊጉን አሸናፊዎች " እንኳን ደስ አላችሁ " ብለዋል።

" ማንችስተር ሲቲዎች የሊጉን ዋንጫ በማሸነፋችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ፣ ለእኛ ቀኑ የሀዘን ነው ነገር ግን እውነታውን መቀበል ይኖርብናል " በማለት ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" በሲቲ ደረጃ አይደለንም "

የመድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ከምሽቱ ሽንፈት በኋላ በሰጡት አስተያየት ቡድናቸው በማንችስተር ሲቲ ደረጃ ላይ እንደማይገኝ ተናግረዋል።

ሚኬል አርቴታ በንግግራቸውም " ለሶስት ሰዓታት እንኳን ብንጫወት ግብ ማስቆጠር የምንችል አይመስልም ነበር ለሽንፈቱ ሀላፊነቱን እኔ እወስዳለሁ።

በማንችስተር ሲቲ ደረጃ እንዳልሆንን አውቃለሁ ፣ ይህ በሶስት ወራት ውስጥ የሚለወጥ አይመስልም መፍትሔ መፈለግ አለበት።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባርሴሎና ሽንፈት አስተናግዷል !

የላሊጋውን ዋንጫ ማሸነፉን ያረጋገጠው ባርሴሎና ከሪያል ሶሴዳድ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

የሪያል ሶሴዳድን የማሸነፊያ ግብ መሪኖ እና ሶርሎት ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለባርሴሎና ሮበርት ሊዋንዶውስኪ አስቆጥሯል።

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና በውድድር አመቱ አራተኛ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

የባርሴሎናው የፊት መስመር ተጨዋች ሮበርት ሊዋንዶውስኪ በውድድር አመቱ ሀያ ሁለተኛ የሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

የሊጉ አሸናፊ ባርሴሎና ሰማንያ አምስት ነጥቦችን ሲሰበስብ ሪያል ሶሴዳድ በስልሳ አምስት ነጥቦች አራተኛ ደረጃን ይዟል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ባርሴሎና ከ ሪያል ቫላዶሊድ እንዲሁም ሪያል ሶሴዳድ ከ አልሜሪያ የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው! እንዳያመልጥዎ!
Man City-Chelsea
Napoli-Inter
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
የዛሬ ተጠባቂ መርሐ ግብሮች !

9:00 ባህር ዳር ከተማ ከ ሀድያ ሆሳዕና

10:00 ብራይተን ከ ሳውዝሀምፕተን

12:00 ወላይታ ድቻ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

12:00 ማንችስተር ሲቲ ከ ቼልሲ

12:30 ኦግስበርግ ከ ዶርትመንድ

1:00 ናፖሊ ከ ኢንተር ሚላን

1:30 ቫሌንሽያ ከ ሪያል ማድሪድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የርገን ክሎፕ ሚልነርን ማቅየት ይፈልጉ ነበር !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ዋና አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ የመስመር ተጨዋቹ ጄምስ ሚልነር በሊቨርፑል ቤት ለተጨማሪ አመት እንዲቆይ ፍላጎት እንደነበራቸው ተገልጿል።

ይሁን እንጂ የርገን ክሎፕ ተጨዋቹን ማቆየት ቢፈልጉም የክለቡ አስተዳደር ውሳኔውን አለመቀበሉ እና ውድቅ ማድረጉን ጄምስ ሚልነር ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe