TIKVAH-SPORT
259K subscribers
52.5K photos
1.48K videos
5 files
3.5K links
加入频道
#PremiereLeague

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ከሚቀጥለው የውድድር ዘመን ጀምሮ በጨዋታ ቀን የቀጥታ ስርጭት ላይ አዲስ ነገሮችን ለመጨመር ማሰቡ ተገልጿል።

ሊጉ ለመጀመር ያሰባቸው አዲስ ነገሮች በሁሉም የፕርሚየር ሊጉ ክለቦች ላይ እንደሚተገብሩ ተነግሯል።

ሊጉ በቀጣይ ምን ለመጨመር አሰበ ?

- በእረፍት ሰዓት ከተጨዋች ወይም አሰልጣኝ ጋር ቃለ መጠይቅ

- ከተቀየሩ ተጨዋቾች ቃለ መጠይቅ ማድረግ

- ከመልበሻ ቤቱ ስርጭት መጨመር እንደሚገኙበት ተገልጿል።

በእረፍት ሰዓት ቃለ መጠይቁን የሚያደርጉት የክለቦቹ ምክትል አሰልጣኞች ሊሆኑ እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

በተጨማሪም ክለቦቹ በየሳምንቱ ከሶስቱ አንዱን መምረጥ ሊገደዱ እንደሚችሉ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#PremiereLeague

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በቆመ ኳስ ጎሎች በዘንድሮው የውድድር ዓመት ሰባት ጎሎችን ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ቡድኑ ከተጠናቀቀው የውድድር ዘመን አንስቶ ሀያ አራት ጎሎችን ከቆመ ኳስ ማስቆጠር ችለዋል።

መድፈኞቹ የቆሙ ኳስ አሰልጣኙን ኒኮላስ ሆቨርን ከቀጠረ ወዲህ በርካታ ጎሎችን ያስቆጠረ ቀዳሚው ክለብ ሆኗል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Premiereleague 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ በተመሳሳይ ስዓት በተደረጉ መርሐግብሮች ፉልሀም ፣ ብሬንትፎርድ እና ዎልቭስ አሸንፈዋል።

- ፉልሀም ክሪስታል ፓላስን 2ለ0 ሲረታ ግቦቹን ስሚዝ ሮው እና ዊልሰን አስቆጥረዋል።

- ዎልቭስ በበኩሉ ሳውዝሀምፕተንን በሳራብያ እና ኩንሀ ግቦች 2ለ0 ማሸነፍ ችሏል።

- አምስት ግቦች በተቆጠሩበት ጨዋታ ብሬንትፎርድ በርንማውዝን 3ለ2 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

- ለብሬንትፎርድ የማሸነፊያ ግቦችን ዊሳ 2x እና ዳምስጋርድ እንዲሁም ለበርንማውዝ ኢቫኒልሰን እና ክሉይቨርት አስቆጥረዋል።

- ዌስትሀም ዩናይትድ ከኤቨርተን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
#premiereleague 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በአሰልጣኝነት ህይወታቸው ለመጀመሪያ ጊዜ አራት ጨዋታዎችን በተከታታይ ተሸንፈው ወጥተዋል።

ማንችስተር ሲቲ ከአስራ ስምንት አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ተከታታይ አራት ጨዋታዎችን ተሸንፈዋል።

ማንችስተር ሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ ኤርሊንግ ሀላንድ ግብ አስቆጥሮ ጨዋታውን ማሸነፍ ሳይችል ቀርቷል።

ሲቲ በቀጣይ እነማንን ያገኛል ?

ማንችስተር ሲቲ በቀጣይ በሊጉ :-

- ከ ቶተንሀም
- ሊቨርፑል እና
- ኖቲንግሀም ፎረስት ጋር በተከታታይ የሚገናኙ ይሆናል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
#PremiereLeague

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የዛሬውን ተከትሎ ከተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ስምንት ከፍ አድርጓል።

ሊቨርፑል በሊጉ ታሪክ ከአስራ ሁለት ጨዋታዎች በኋላ ብዙ ነጥቦችን የሰበሰበ ሁለተኛው ክለብ መሆን ችለዋል።

ከዚህ በፊት ማንችስተር ዩናይትድ 1993 በአሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን እየተመራ ዘጠኝ ነጥቦችን በመሰብሰብ ቀዳሚው ክለብ ነው።

ማንችስተር ዩናይትድ በዛን አመት የፕርሚየር ሊጉን ዋንጫ አሳክተው ነበር።

በተጨማሪም ኔዘርላንዳዊ አሰልጣኝ አርኔ ስሎት በሊጉ ታሪክ በትንሽ ጨዋታዎች አስር የሊግ ድሎችን ማሳካት የቻሉ ቀዳሚው አሰልጣኝ ሆነዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
#PremiereLeague

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ አስራ ሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ብሬንትፎርድ ፣ ኖቲንግሀም እና በርንማውዝ ተጋጣሚዎቻቸውን ረተዋል።

ኒውካስል ዩናይትድ በመጨረሻ ደቂቃ በተቆጠረበት ግብ ከክሪስታል ፓላስ ጋር 1ለ1 ተለያይቷል።

ብሬንትፎርድ በበኩሉ በስቻድ 3x እና ዊሳ ግቦች ሌስተር ሲቲን 4ለ1 ማሸነፍ ችሏል።

በሌሎች ጨዋታዎች ኖቲንገሀም ኢፕስዊች ታውንን 1-0 እንዲሁም በርንማውዝ ዎልቭስን 4ለ2 አሸንፈዋል።

የበርንማውዙ ተጨዋች ጀስቲን ክሉይቨርት በፍፁም ቅጣት ምት ሀትሪክ መስራት ችሏል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
#PremiereLeague 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿

በአሰልጣኝ ቶማስ ፍራንክ የሚመራው ብሬንትፎርድ በዘንድሮው የውድድር ዘመን በሜዳቸው ያደረጓቸውን ጨዋታዎች አልተሸነፉም።

ክለቡ በሜዳው ካደረጋቸው ስምንት የሊግ ጨዋታዎች ሰባቱን ሲያሸንፍ በአንዱ አቻ ተለያይቷል።

ብሬንትፎርድ በውድድር ዘመኑ በሜዳው 2️⃣2️⃣ ነጥቦችን በመሰብሰብ ቀዳሚው ክለብ ሲሆን ከየትኛውም ክለብ በላይ በሜዳው 2️⃣6️⃣ ግቦችን አስቆጥሯል።

የብሬንትፎርዱ ጂ ቴክ ኮምዩኒቲ ስታዲየም በዚህ አመት አርባ ግቦች ተቆጥረውበታል ።

በዘንድሮው የውድድር ዘመን በፕርሚየር ሊጉ በብሬንትፎርድ ሜዳ በአማካይ በጨዋታ አምስት ግቦች ተቆጥረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የፕርሚየር ሊግ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ታወቀ ! የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የወርሀ ኅዳር የደጋፊዎች የወሩ ምርጥ ተጨዋች ይፋ አድርጓል። በዚህም መሰረት የሊቨርፑሉ የፊት መስመር ተጨዋች መሐመድ ሳላህ የወርሀ ህዳር የወሩ ምርጥ ተጨዋች ተብሎ መመረጡ ተገልጿል። መሐመድ ሳላህ በወሩ ባደረጋቸው ሶስት የሊግ ጨዋታዎች አራት ግቦችን አስቆጥሮ አንድ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል። ሳላህ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ…
#PremiereLeague

መሐመድ ሳላህ ለስድስተኛ ጊዜ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ተብሎ መመረጡን ተከትሎ ሁለተኛው ብዙ ጊዜ የወሩ ምርጥ ሽልማት የተቀበለ ተጨዋች መሆን ችሏል።

ብዙ ጊዜ የወሩ ምርጥ የተባሉ ተጨዋቾች እነማን ናቸው ?


7️⃣ ሀሪ ኬን እና ሰርጂዮ አጉዌሮ

6️⃣ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ፣ ስቴቨን ጄራርድ እና መሐመድ ሳላህ

ተጨዋቾቻቸው ብዙ የወሩ ምርጥ ሽልማት ያሸነፉ ክለቦች ?

1ኛ. ማንችስተር ዩናይትድ :- 4️⃣7️⃣ ጊዜ
2ኛ. ሊቨርፑል :- 3️⃣5️⃣ ጊዜ
3ኛ. አርሰናል :- 3️⃣2️⃣ ጊዜ
4ኛ. ቶተንሀም :- 2️⃣6️⃣ ጊዜ
5ኛ. ቼልሲ :- 2️⃣1️⃣ ጊዜ
6ኛ. ማንችስተር ሲቲ :- 2️⃣0️⃣ ጊዜ

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
#PremiereLeague 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿

የእንግሊዝ ፕርሚየር መርሐግብሮች ሲካሄዱ ኒውካስል ኢፕስዊች ታውንን 4ለ0 እንዲሁም ኖቲንግሀም ፎረስት ብሬንትፎርድን 2ለ0 ማሸነፍ ችለዋል።

የኒውካስል ዩናይትድን የማሸነፊያ ግቦች አሌክሳንደር አይሳክ 3x እና ጃኮብ ሙርፊ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ለኖቲንግሀም ፎረስት የድል ግቦችን አንቶኒ ኢላንጋ እና ኦላ አይና አስቆጥረዋል።

በሌላ ጨዋታ ዌስትሀም ዩናይትድ ከብራይተን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።

ኖቲንግሀም ፍረስት ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን 3️⃣1️⃣ በማድረስ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ 3️⃣ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችለዋል።

ስዊድናዊው የፊት መስመር ተጨዋች አሌክሳንደር አይሳክ በኒውካስል ዩናይትድ የመጀመሪያ ሀትሪክ መስራት ችሏል።

አሌክሳንደር አይሳክ በውድድር ዘመኑ 1️⃣0️⃣ኛ የፕርሚየር ሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

የኢፕስዊች ታውኑ ተጨዋች ሳም ሞርሲ ቢጫ ካርድ መመልከቱን ተከትሎ በቅጣት ምክንያት በቀጣይ የአርሰናል ጨዋታ የሚያመልጠው ይሆናል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
#premiereleague

አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ማንችስተር ዩናይትድን በሁሉም ውድድሮች በአሰልጣኝነት ከመሩባቸው ዘጠኝ ጨዋታዎች #አራተኛ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

ማንችስተር ዩናይትድ ከአስራ ሰባት ቀናት በኋላ ወደ አስራ ሶስተኛ ደረጃ ተመልሰዋል።

ጥሩ የውድድር አመት በማሳለፍ ላይ የሚገኘው በርንማውዝ ማንችስተር ዩናይትድን ማሸነፉን ተከትሎ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

ማንችስተር ዩናይትድ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አመት በፊት ከፕርሚየር ሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ግማሽ በታች ሆነው አጠናቀዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
#PremiereLeague 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿

በአሰልጣኝ ማርኮ ሲልቫ የሚመራው ፉልሀም ከ 4️⃣5️⃣ አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ቼልሲን በሜዳው ስታምፎርድ ብሪጆ ስታዲየም አሸንፎታል።

ኖቲንግሀም ፎረስት ከ 2️⃣9️⃣ አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አራት ተከታታይ ጨዋታዎች ማሸነፍ ችሎል።

የአሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካው ቡድን ቼልሲ ከአስራ ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ጉዞ በኋላ ተሸንፏል።

በዘንድሮው የውድድር አመት ቶተንሀም ከሳውዝሀምፕተን እና ዎልቭስ በመቀጠል ሶስተኛው ብዙ የሊግ ጨዋታ የተሸነፈው ክለብ ሆኗል።

ኖቲንግሀም ፎረስት በ1️⃣8️⃣ ጨዋታዎች 3️⃣4️⃣ ነጥቦችን በመሰብሰብ 3️⃣ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችለዋል።

ቶተንሀም ከ 2️⃣3️⃣ አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በቦክሲንግ ደይ መርሐግብር ያደረገውን ጨዋታ ተሸንፏል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
#Premiereleague 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐግብር ማንችስተር ሲቲ ፣ ቼልሲ እና ሊቨርፑል ጨዋታዎቻቸውን በአቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የሊጉ መሪ ሊቨርፑል ከኖቲንግሀም ፎረስት ጋር  ያደረገውን ተጠባቂ የሊግ ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል።

የኖቲንግሀምን ግብ ክሪስ ውድ ሲያስቆጥር ዲያጎ ጆታ ሊቨርፑልን አቻ አድርጓል።

ማንችስተር ሲቲ በበኩሉ ከብሬንትፎርድ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የማንችስተር ሲቲን ግቦች ፊል ፎደን 2x ሲያስቆጥር ለብሬንትፎርድ ዊሳ እና ኖርጋርድ ከመረብ አሳርፏል።

ቼልሲ ከበርንማውዝ ያደረገውን ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት ማጠናቀቅ ችለዋል።

የሰማያዊዎቹን ግብ ኮል ፓልመር እና ሬስ ጄምስ ሲያስቆጥሩ ክላይቨርት እና ሴሜኒኖ ለበርንማዝ ከመረብ አሳርፈዋል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣ ሊቨርፑል :- 47 ነጥብ
2️⃣ ኖቲንግሀም ፎረስት :- 41 ነጥብ
4️⃣ ቼልሲ :- 37 ነጥብ
6️⃣ ማንችስተር ሲቲ :- 35 ነጥብ

ቀጣይ መርሐግብር ?

ቅዳሜ - ብሬንትፎርድ ከ ሊቨርፑል

እሁድ - ኢፕስዊች ታውን ከ ማንችስተር ሲቲ

ሰኞ - ቼልሲ ከ ዎልቭስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#PremiereLeague 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐግብር አርሰናል ከኖቲንግሀም ፎረስት ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ማንችስተር ዩናይትድ ከኢፕስዊች ታውን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የማንችስተር ዩናይትድን የማሸነፊያ ግቦች ሀሪ ማጓየር ፣ ዴሊት እና ሞርሲ ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለኢፕስዊች ጃደን 2x አስቆጥሯል።

ማንችስተር ሲቲ በበኩሉ ከቶተንሀም ጋር ያደረገውን ጨዋታ በኤርሊንግ ሀላንድ ግብ 1ለ0 ማሸነፍ ችሏል።

የማንችስተር ሲቲው የፊት መስመር አጥቂ ኤርሊንግ ሀላንድ በውድድር ዘመኑ 2️⃣0️⃣ኛ የሊግ ግቡን አስቆጥሯል።

በሌላ ጨዋታ ብሬንትፎርድ ከኤቨርተን ጋር 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

2️⃣ አርሰናል :- 54 ነጥብ
3️⃣ ኖቲንግሀም ፎረስት :- 48 ነጥብ
4️⃣ ማንችስተር ሲቲ :- 47 ነጥብ
1️⃣4️⃣ ማንችስተር ዩናይትድ :- 33 ነጥብ

ቀጣይ መርሐግብር ?

እሁድ - ማንችስተር ዩናይትድ ከ አርሰናል

ቅዳሜ - ኖቲንግሀም ፎረስት ከ ማንችስተር ሲቲ

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe