TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.7K photos
1.48K videos
5 files
3.41K links
加入频道
#BKEthPL 🇪🇹

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ስምንተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ ከ ኢትዮጵያ መድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ኢትዮጵያ መድን በአርባ ዘጠኝ ነጥቦች ሶስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ፋሲል ከነማ በሰላሳ ዘጠኝ ነጥቦች ስድስተኛ ደረጃን መያዝ ችሏል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ እንዲሁም ኢትዮጵያ መድን ከ አዳማ ከተማ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

ከቀናት በኋላ ሐሙስ በሚጀምረው የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ላለመውረድ በሚደረገው አጓጊ ፉክክር ሁለት ጨዋታዎች በእኩል ሰዓት እንዲደረጉ አወዳዳሪው አካል ከውሳኔ ደርሷል።

ይህንንም ተከትሎ አርባምንጭ ከተማ ከ ድሬዳዋ ከተማ በአዳማ አበበ በቂላ ስታዲየም እንዲሁም ወላይታ ድቻ ከ ወልቂጤ ከተማ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም በእኩል 9:00 ሰዓት እንዲደረጉ ከውሳኔ ተደርሷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የ 2015 ዓ.ም የውድድር አመት የመጨረሻ ጨዋታቸውን ያደረጉት ኢትዮጵያ ቡና እና ፋሲል ከነማ ጨዋታቸውን 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ኢትዮጵያ ቡና የውድድር አመቱን አርባ ሶስት ነጥቦች በመሰብሰብ ማጠናቀቅ የቻሉ ሲሆን በአመቱ ውስጥ አስራ ሶስት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተው አስር አሸንፈው ሰባት ደግሞ ሽንፈት አስተናግደዋል።

ፋሲል ከነማ በበኩሉ በተመሳሳይ አርባ ሶስት ነጥቦች በመሰብሰብ የውድድር አመቱን ያጠነቀቀ ሲሆን በአመቱ ውስጥ አስራ አንድ ጨዋታዎች አሸንፈው አስር አቻ ተለያይተው ዘጠኝ ጨዋታዎች ተሸንፈዋል።

በሊጉ ወቅታዊ የደረጃ ሰንጠረዥ መሰረት ቡናማዎቹ አራተኛ እንዲሁም አፄዎቹ በግብ ክፍያ ተበልጠው አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe