TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.7K photos
1.48K videos
5 files
3.41K links
加入频道
Forwarded from Kidus
💪🏾 ድሬዎቹ፣ #ዋናዎቹ! 💪🏾

⚽️ የ2017 የውድድር ዘመን የልምምድ ትጥቆች ከ #ዋናው! ⚽️

Instagram | Facebook | TikTok

🏅ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
💯 የድምጽ ጥቅሎችን እየገዛን በጉርሻ ደቂቃዎች እንንበሽበሽ! ከሳፋሪኮም ወደ የቴሌ የሚያስደውሉ የድምፅ ጥቅሎችን በመግዛት ከሳፋሪኮም ወደ ሳፋሪኮም 100% ጉርሻን እናጣጥም! ከሳፋሪኮም ጋር በአብሮነት አንድ ወደፊት⚡️

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ:
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቦታችንን
https://yangx.top/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይንም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን
https://yangx.top/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom
#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
የእረፍት ሰዓት !

ተጠባቂው የሰሜን ለንደን ደርቢ ጨዋታ በቶተንሀም እና አርሰናል መካከል በመደረግ ላይ ሲሆን የመጀመሪያው አጋማሽ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።

🟨 የቢጫ ካርድ የተመለከቱ ተጫዋቾች እነማን ናቸው ?

- በመጀመሪያው አጋማሽ በአርሰናል በኩል ዊሊያም ሳሊባ እና ቲምበር እንዲሁም በቶተንሀም በኩል ቤንታንኩር ፣ ቪካሪዮ ፣ ኡዶጊ ፣ ኩሉሴቭስኪ እና ሚኪ ቫን ዴ ቪን የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክተዋል።

- በመጀመሪያው አጋማሽ ጃሬድ ጊሌት ሰባት የቢጫ ካርዶችን መዘዋል።

የጨዋታው የኳስ ቁጥጥር ምን ይመስላል ?

- በመጀመሪያው አጋማሽ ቶተንሀም 67% - 33% የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ነበራቸው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
60 '

ቶተንሀም 0 - 0 አርሰናል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
64 '

ቶተንሀም 0 - 1 አርሰናል

ጋብሬል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
90 '

ቶተንሀም 0 - 1 አርሰናል

                    ጋብሬል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሰሜን ለንደን ደርቢ በአርሰናል አሸናፊነት ተጠናቀቀ !

በአራተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብር አርሰናል ከቶተንሀም ጋር ያደረገውን የሰሜን ለንደን ደርቢ ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የአርሰናልን የማሸነፊያ ግብ ጋብሬል ማግሀሌስ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

በመጀመሪያ አጋማሽ ሰባት የቢጫ ካርዶች ሲመዘዙ የሰሜን ለንደን ደርቢ በፕርሚየር ሊጉ ታሪክ የመጀመሪያው መሆኑ ተገልጿል።

ብራዚላዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ጋብሬል ማግሀሌስ አስራ አምስተኛ የፕርሚየር ሊግ ግቡን ለአርሰናል አስቆጥሯል።

እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጨዋች ቡካዩ ሳካ በጨዋታው ጉዳት አጋጥሞት ተቀይሮ ለመውጣት ተገዷል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

2️⃣ኛ አርሰናል :- 10 ነጥብ
1️⃣3️⃣ኛ ቶተንሀም :- 4 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

እሁድ - ማንችስተር ሲቲ ከ አርሰናል

ቅዳሜ - ቶተንሀም ከ ብሬንትፎርድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ በጣም ተደስቻለሁ “ ጋብሬል ማግሀሌስ

የመድፈኞቹን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ያስቆጠረው ጋብሬል ማግሀሌስ ቡድኑን በትልቅ ደርቢ አሸናፊ በማድረጉ እንደተደሰተ ተናግሯል።

“በጣም ተደስቻለሁ የደርቢ ጨዋታውን በማሸነፋችን ደስተኞች ነን አሁን መደሰት አለብን ፣ የማሸነፊያ ግብ ማስቆጠር ለእኔ ትልቅ ትርጉም አለው።“ ሲል ጋብሬል ማግሀሌስ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ደጋፊዎቻችንን ለማስደሰት አቅም አለን “ አርቴታ

የመድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸው ያለበትን የጉዳት ሁኔታ ተቋቁሞ ወሳኝ ድል በማሳካቱ እንደተደሰቱ ገልጸዋል።

“ ደጋፊዎቻችንን ለማስደሰት አቅም አለን “ ያሉት አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ያንን አሳክተናል ብዬ አስባለሁ ካለው ሁኔታ ጋር ለመላመድ ብንቸገርም ወድጄዋለሁ በማለት ተናግረዋል።

" ሰበብ ከማብዛት ፈተናውን ተጋፍጠነው በጀግንነት ተጫውተናል ፣ ለተከታታይ ሶስት አመት እዚህ መጥተን አሸንፈናል ፣ በቀጣይ ትልቅ ሳምንት እየመጣ ነው ለዛም ብርታት ይሰጠናል።" ሚኬል አርቴታ

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በንግግራቸው ወቅት ስለ ቡካዩ ሳካ ሁኔታ እንደማያውቁ እና ምን እንደገጠመው አለመረዳታቸውን ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባርሴሎና በአሸናፊነቱ ቀጥሏል !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና የስፔን ላሊጋ የአምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብሩን ከጂሮና ጋር አድርጎ 4ለ1 በሆነ ውጤት መርታት ችሏል።

የባርሴሎናን የማሸነፊያ ግቦች ላሚን ያማል 2x ፣ ዳኒ ኦልም እና ፔድሪ ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለጂሮና ስትዋኒ አስቆጥሯል።

ላሚን ያማል ባለፉት አምስት የላሊጋ ጨዋታዎች አራት ለግብ የሆነ ኳስ አመቻችቶ ማቀበል ሲችል ሶስት ግብ አስቆጥሯል።

ባርሴሎና የመጀመሪያ አምስት የሊግ ጨዋታዎችን በተጋጣሚዎቹ ላይ አስራ ሰባት ግቦችን አስቆጥሮ ማሸነፍ ችሏል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣ኛ ባርሴሎና :- 15 ነጥብ
7️⃣ኛ ጂሮና :- 7 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

እሁድ -ቪያሪያል ከ  ባርሴሎና

ቅዳሜ - ቫሌንሽያ ከ ጂሮና

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ባማቸውም አላፍርም "

“ ደራርቱ ይቅርታ በመጠየቋ አዝኜባታለሁ “ ዶ/ር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ በፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር ወቅት የአመራሮችን ድምፅ ቀርጾ ማውጣት “ ነውረኝነት ነው “ ሲሉ ገልጸዋል።

“ ሰው በምሳ ሰዓቱ የፈለገውን ቢናገር ቢጫወት ምንድነው ችግሩ “ ሲሉ የጠየቁት ዶ/ር አሸብር “ ይሄንን አሁን ቁምነገር ብሎ ቀርፆ ያወጣው ሚዲያ ሊያፍር ይገባዋል እውነት ለመናገር “ ብለዋል።

“ ስትሰባሰብ በቤተሰብ መሐል መነጋገር ይኖራል መንግስትን ልታማም ትችላለህ ይሄንን ቁምነገር ብሎ መቅረፅ የኢትዮጵያን ባህል የማይመጥን ነውረኝነት ነው “ ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ

“ በተፈጥሮዬ ሀሜት አልወድም እንጂ ጠቅላይ ሚኒስትሩንም አምቻቸው ቢሆን አላፍርም የተናገርኩትን ተናግሬያለሁ ባህሪዬ ነው “ ሲሉ ዶ/ር አሸብር ይቅርታ የሚሉት ነገር አለመኖሩንም አንስተዋል።

“ ደራርቱን አዝኜባታለሁ ይቅርታ በመጠየቋ ተገቢ አይደለም “ ያሉት ዶ/ር አሸብር “ እሷ የተናገረችውን እናውቃለን አንድም ገዛኸኝ ላይ ያነጣጠረ ነገር የለም ወይም ግለሰቦች ላይ ያነጣጠረ ነገር የለም “ ብለዋል።

የድምጽ ቅጂውን ያወጣውን ግለሰብ “ ይህንን ያደረገው ወራዳ ሰው ነው “ ሲሉ የገለፁት ዶ/ር አሸብር “ እኔ በደራርቱ ቦታ ብሆን ይቅርታ ቀርቶ ምንም አልልም “ ሲሉ ገልጸዋል።

መረጃው የሸገር ስፖርት ሬዲዮ ፕሮግራም ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ናፖሊ ድል አድርጓል !

በጣሊያን ሴርያ የአራተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ናፖሊ ከካግሊያሪ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 4ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የናፖሊን የማሸነፊያ ግቦች ሮሜሉ ሉካኩ ፣ ቅቫራትሼሊያ ፣ ቦንግዮርኖ እና ጂዮቫኒ ዲ ሎሬንዞ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ቤልጂየማዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሮሜሉ ሉካኩ ለናፖሊ ባደረጋቸው ሁለት ጨዋታዎች ሁለት ግቦች አስቆጥሮ ሁለት አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

1️⃣ኛ ናፖሊ :- 9 ነጥብ
1️⃣9️⃣ኛ ካግሊያሪ :- 2 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

አርብ - ካግሊያሪ ከ ኢምፖሊ

ቅዳሜ - ጁቬንቱስ ከ ናፖሊ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!