TIKVAH-SPORT
259K subscribers
52.1K photos
1.48K videos
5 files
3.45K links
加入频道
አሸናፊዎች ተለይተዋል።

የአርሰናል እና ብራይተን ጨዋታ ትክክለኛ ምላሽ ቀድመው የሰጡት ከስር የተገለፁት የቤተሰባችን አባላት ናቸው።

ትክክለኛ ምላሽ የሰጡትን በመፈለጉ ሂደት የተዘለለ እና ያልታየ ካለ ማሳወቅ ይቻላል። Edit የተደረገ መልስ ተቀባይነት አይኖረውም።

1ኛ. @amdee29
2ኛ. @Samsam1e
3ኛ. @The_endxyz

@tikvahethsport
" ባለማሸነፋችን ተበሳጭቻለሁ “ ፋብያን ሁርዜለር

የብራይተኑ ዋና አሰልጣኝ ፋብያን ሁርዜለር ቡድናቸው ከአርሰናል ጋር ያደረገውን ጨዋታ ማሸነፍ ባለመቻሉ መበሳጨታቸውን ገልጸዋል።

“ ጨዋታውን ባለማሸነፋችን ተበሳጭቻለሁ “ ሲሉ ስሜታቸውን የገለፁት አሰልጣኝ ፋብያን ሁርዜለር የዴክላን ራይስ ሁለተኛ ቢጫ የሚገባው ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

የ 31ዓመቱ ጀርመናዊ አሰልጣኝ ፋብያን ሁርዜለር የሊጉ የመጀመሪያ ሶስት ጨዋታዎችን አልተሸነፉም ሁለቱን በአሸናፊነት መወጣት ችለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የዩናይትድ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የሚመሩት ማንችስተር ዩናይትዶች የወርሀ ነሐሴ የወሩ ምርጥ ተጨዋች #ሶስት እጩዎችን ይፋ አድርገዋል። በዚህም መሰረት ናስር ማዝራዊ ፣ አማድ ዲያሎ እና አሌሀንድሮ ጋርናቾ የአመቱ የመጀመሪያ ወር የማንችስተር ዩናይትድ ምርጥ ተጨዋች እጩ ሆነው መቅረብ ችለዋል። የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል @tikvahethsport    …
የዩናይትድ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ታውቋል !

በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የሚመሩት ማንችስተር ዩናይትዶች የወርሀ ነሐሴ የወሩ ምርጥ ተጨዋቻቸውን ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሰረት ኮትዲቯራዊው የፊት መስመር ተጨዋች አማድ ዲያሎ የአመቱ የመጀመሪያ ወር የማንችስተር ዩናይትድ ምርጥ ተጨዋች ተብሎ መመረጥ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ የዳኛው ውሳኔ ጨዋታውን ሙሉ ለሙሉ ቀይሮታል “ አርቴታ

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸው አቻ በተለያዩበት ጨዋታ የዳኛው ውሳኔ ቅር እንዳሰኛቸው ገልጸዋል።

“ የራይስ መውጣት ጨዋታውን ሙሉ ለሙሉ ቀይሮታል “ ሲሉ ከጨዋታው በኋላ የተናገሩት ሚኬል አርቴታ የዳኛው ውሳኔ ሙሉ ጨዋታው ላይ ቢታይ ጥሩ ነበር ግን አላደረገውም ብለዋል።

በመጀመሪያው አጋማሽ ተመሳሳይ ነገሮች በብራይተን ተጨዋቾች በኩል መደረጋቸውን ያስረዱት አሰልጣኙ ነገርግን ምንም ካርድ እንዳልተሰጠ ገልጸዋል።

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አያይዘውም የመስመር ተጨዋቹ ቲምበር ጉዳት አጋጥሞታል ብለው እንደማያስቡ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ይገምቱ ይሸለሙ

የማንችስተር ሲቲ እና ዌስትሀም ዩናይትድን ጨዋታ ውጤት ገምተው በትክክል ላወቁ ሶስት ቤተሰቦቻችን የአንድ መቶ ብር ካርድ የምንሸልምዎ ይሆናል።

የውድድሩ ህጎች ምን ይመስላሉ ?

√ ተሳታፊዎች ግምቶቻቸውን ከዚህ ፖስት ስር ባለው የሀሳብ መስጫ ሳጥን #ብቻ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

√ ኤዲት የተደረጉ ምላሾች በፍፁም ተቀባይነት አይኖራቸውም።

√ ግምትዎን መላክ የሚቻለው እስከ 1:30 ሰዓት ብቻ ነው።

መልካም ዕድል !

@tikvahethsport    
የጨዋታ አሰላለፍ !

1:30 ዌስትሀም ከ ማንችስተር ሲቲ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🌼🌼🌼 እንኳን አደረሳችሁ🌼🌼🌼

🆕አዳዲስ እንዲሁም በመጠኑ ያገለገሉ ስልኮችን ከተሟላ ዋስትና እና ጥገና ጋር ይዘን ቀርበናል 🍏 ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይጎበኙ

📣 https://yangx.top/sellphone2777

📞 0929008292

✉️ inbox @bina27

📌 አድራሻ- ቦሌ ከሸገር ህንፃ አጠገብ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ሲቲ ተጨዋቹ ጉዳት አጋጥሞታል !

ብራዚላዊው የማንችስተር ሲቲ የፊት መስመር ተጨዋች ሳቪንሆ የጉልበት ጉዳት እንዳጋጠመው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ አረጋግጠዋል።

ተጨዋቹ በዚሁ ጉዳት ምክንያት ከደቂቃዎች በኋላ ከዌስትሀም ዩናይትድ ጋር ከሚያደርጉት የሊግ ጨዋታ ውጪ መሆኑን አሰልጣኙ አስረድተዋል።

ይህንንም ተከትሎ ሳቪንሆ በአስር ቀናት ውስጥ ካጋጠመው ጉዳት አገግሞ ወደ ሜዳ ሊመለስ እንደሚችል ፔፕ ጋርዲዮላ ጠቁመዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#PremiereLeague

በሶስተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብር አስቶን ቪላ ፣ ብሬንትፎርድ እና በርንማውዝ ተጋጣሚዎቻቸውን መርታት ችለዋል።

በአሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ የሚመራው አስቶን ቪላ በአማዱ ኦናና እና ዱራን ግቦች ሌስተር ሲቲን 2ለ1 ማሸነፍ ችሏል።

ብሬንትፎርድ በምቤሞ 2x እና ዊሳ ግቦች ከሳውዝሀምፕተን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 3ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ፉልሀም ከኢፕስዊች ታውን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

በርንማውዝ ከኤቨርተን ጋር ያደረገውን ጨዋታ በመጨረሻ ደቂቃዎች ባስቆጠራቸው ሁለት ግቦች 3ለ2 ማሸነፍ ችሏል።

ዎልቭስ እና ኖቲንግሃም ፎረስት ጨዋታቸውን በአቻ ውጤት አጠናቀዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ተጀመረ

ዌስትሀም 0-0 ማንችስተር ሲቲ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
9 ' ዌስትሀም 0 - 1 ማንችስተር ሲቲ

ሀላንድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
19 ' ዌስትሀም 1 - 1 ማንችስተር ሲቲ

ዲያስ ( በራስ ላይ )         ሀላንድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባርሴሎና በሰፊ የግብ ልዩነት አሸነፈ !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና የስፔን ላሊጋ የአራተኛ ሳምንት መርሐ ግብሩን ከሪያል ቫላዶሊድ ጋር አድርጎ 7ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት መርታት ችሏል።

የባርሴሎናን የማሸነፊያ ግቦች ራፊንሀ 3x ፣ ሌዋንዶውስኪ ፣ ኩንዴ ፣ ዳኒ ኦልሞ እና ቶሬስ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ፖላንዳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሮበርት ሌዋንዶውስኪ በአራት የላሊጋ ጨዋታዎች አራተኛ ግቡን አስቆጥሯል።

ላሚን ያማል ባለፉት አራት የላሊጋ ጨዋታዎች አራት ለግብ የሆነ ኳስ አመቻችቶ ማቀበል ሲችል አንድ ግብ አስቆጥሯል።

ባርሴሎና የመጀመሪያ አራት የሊግ ጨዋታዎችን በማሸነፍ ሊጉን በአስራ ሁለት ነጥቦች በበላይነት እየመራ ይገኛል።

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

እሁድ - ጂሮና ከ  ባርሴሎና

እሁድ - ሴልታ ቪጎ ከ ሪያል ቫላዶሊድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
29 ' ዌስትሀም 1 - 2 ማንችስተር ሲቲ

ዲያስ ( በራስ ላይ )           ሀላንድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
40 ' ዌስትሀም 1 - 2 ማንችስተር ሲቲ

ዲያስ ( በራስ ላይ )           ሀላንድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እረፍት

ዌስትሀም 1 - 2 ማንችስተር ሲቲ

ዲያስ ( በራስ ላይ )           ሀላንድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
57 '

ዌስትሀም 1 - 2 ማንችስተር ሲቲ

ዲያስ ( በራስ ላይ )           ሀላንድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢትዮጵያ በፓራሊምፒክ የመጀመሪያ ወርቅ አሳካች !

ለ 17ኛ ጊዜ እየተካሄደ በሚገኘው የ 2024 ፓሪስ ፓራሊምፒክ ውድድር ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ ማሳካት ችላለች።

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትዕግስት ገዛኸኝ በ 1,500 ሜትር ጭላንጭል አንደኛ ደረጃን በመያዝ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያ ወርቅ አስገኝታለች።

አትሌት ትዕግስት ገዛኸኝ በፓራሊምፒክ ውድድር ታሪክ ለሀገራችን ኢትዮጵያ እና ለራሷ ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳልያ አስገኝታለች።

አትሌቷ ከአመታት በፊት በቶኪዮ ፓራሊምፒክ ውድድር በተመሳሳይ ርቀት ለ ሀገራችን በታሪክ የመጀመሪያ የ ፓራሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ማስገኘቷ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe