ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ወርቅ 🥇አገኘች !
ሀገራችን በፓሪስ ኦሎምፒክ የመጀመሪያውን ወርቅ በወንዶች ማራቶን በአትሌት ታምራት ቶላ ማሸነፍ ችላለች።
አትሌት ታምራት ቶላ በማራቶን ኦሎምፒክ ያሳካው የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳሊያው ሆኗል።
ታምራት በአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በኦሪጎን የማራቶን አሸናፊ እንደነበር የሚታወስ ነው።
አትሌት ታምራት በኦሎምፒክ ለሀገሩ
ሜዳሊያ ሲያገኝ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን በሪዮ ኦሎምፒክ 10,000ሜ የነሐስ ሜዳሊያ ባለቤት ነበር።
አትሌት ታምራት ቶሎ በፓሪስ ኦሎምፒክ ተጠባባቂ የነበረ ሲሆን የሲሳይ ለማን መጎዳት ተከትሎ በውድድሩ ሊሳተፍ ችሏል።
አትሌት ታምራት ቶላ ከአትሌት ገዛኸኝ አበራ በኋላ ( ከሀያ አራት አመታት ) የመጀመሪያውን የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳልያ ለሀገራችን ማስገኘት ችሏል።
አትሌት ታምራት ቶላ ከአበበ ቢቂላ 2x ፣ ማሞ ወልዴ እና ገዛኸኝ አበራ በመቀጠል አራተኛው የወንዶች የኦሎምፒክ የማራቶን የወርቅ አሸናፊ ለመሆን በቅቷል።
እንኳን ደስ አለን 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
@tikvahethsport @kidusyoftahe

በድጋሚ እንኳን ደስ አለን 🇪🇹
የአለማችን አራተኛ ፈጣን ሰዓት በማራቶን ያለው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ 39ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።
ሌላኛው አትሌታችን ደሬሳ ገለታ አምስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ጨርሷል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
የአለማችን አራተኛ ፈጣን ሰዓት በማራቶን ያለው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ 39ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።
ሌላኛው አትሌታችን ደሬሳ ገለታ አምስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ጨርሷል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
“ ከባድ ውድድር ነበር “ ቀነኒሳ በቀለ
ኢትዮጵያዊው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ወንዶች ማራቶን ውድድር በጣም ከባድ እንደነበር ከውድድሩ በኋላ ተናግሯል።
የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር ቦታ “ በጣም አስቸጋሪ ነበር “ ሲል የገለፀው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ " እግሮቼን የሆነ ስሜት ተሰምቶኛል “ ሲል ከውድድሩ በኋላ አስተያየቱን ሰጥቷል።
የ 42ዓመቱ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በኦሎምፒክ ማራቶን የመወዳደር እድሉ ትንሽ እንደዘገየ እና ምናልባት በሪዮ ወይም ቶኪዮ ኦሎምፒክ ቢሆን ብሎ መመኘቱን ገልጿል።
አትሌት ታምራት ቶላ አሸናፊ በሆነበት ውድድር አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ሰላሳ ዘጠነኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቁ ይታወቃል።

" ወርቅ ለሀገሬ በማስገኘቴ በጣም ተደስቻለሁ " ታምራት ቶላ
በፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ በወንዶች ማራቶን ያስገኘው አትሌት ታምራት ቶላ ባስመዘገበው ድል እጅግ መደሰቱን ተናግሯል።
" እኔ የምለው ነገር የለኝም " ያለው አትሌት ታምራት ቶላ " እኔን የረዳኝ እግዚአብሔር ነው ፤ እግዚአብሔር ይመስገን " ሲል በእምባ ታጅቦ ከድሉ በኋላ አስተያየቱን ሰጥቷል።
" ውድድሩን በማሸነፌ እና የወርቅ ሜዳልያው ለሀገሬ ኢትዮጵያ በማስገኘቴ በጣም በጣም ተደስቻለሁ " አትሌት ታምራት ቶላ
አትሌት ታምራት ቶላ በውድድሩ በ2:06:26 በሆነ ሰዓት በመግባት በወንዶች ማራቶን የኦሎምፒክ ሪከርድ ባለቤት መሆን ችሏል።

#TeamEthiopia🇪🇹
ለ ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ወርቅ ሜዳሊያ ያስገኘው ታምራት ቶላ ሜዳሊያውን ተረክቧል።
ኢትዮጵያ በወቅታዊ የሜዳሊያ ሰንጠረዥ በአንድ ወርቅ እና ሁለት ብር 4️⃣4️⃣ኛ ደረጃ ላይ እንገኛለን።

“ የእኔ የምንግዜም መጥፎው ማራቶን ነበር “ ኤሉድ ኪፕቾጌ
ኬንያዊው የረጅም ርቀት ሯጭ ኤሉድ ኪፕቾጌ ሳያጠናቅቅ የቀረውን የዛሬውን የፓሪስ ኦሎምፒክ ማራቶን ውድድር “ የምንግዜውም መጥፎው “ ሲል ገልፆታል።
“ ዛሬ መጥፎ ቀን ነው “ ያለው ኤሉድ ኪፕቾጌ “ የምንግዜም በጣም መጥፎው የማራቶን ውድድሬ ነበር ፣ ስምንተኛ እና አስረኛ ጨርሼ አውቃለሁ ነገርግን በፍፁም ሳላጠናቅቅ ቀርቼ አላውቅም ፣ ይህ ስፖርት ነው " ሲል ተደምጧል።
ያለፉትን ሁለት ኦሎምፒክ ውድድሮች የማራቶን አሸናፊ የነበረው አትሌት ኤሉድ ኪፕቾጌ ለተከታታይ ሶስተኛ ጊዜ ቢያሸንፍ አዲስ ታሪክ መፃፍ ይችል ነበር።

Forwarded from HEY Online Market
•Playstaion 5 Slim, 76,000 Birr
•PlayStation 4 Slim, 35,000 Birr
•PlayStation 4 Pro, 42,000 Birr
•Meta Quest 2, 45,000 Birr
•Meta Quest 3, 78,000 Birr
Contact
0953964175 @heymobile
0925927457 @eBRO4
@heyonlinemarket
•PlayStation 4 Slim, 35,000 Birr
•PlayStation 4 Pro, 42,000 Birr
•Meta Quest 2, 45,000 Birr
•Meta Quest 3, 78,000 Birr
Contact
0953964175 @heymobile
0925927457 @eBRO4
@heyonlinemarket
Forwarded from WANAW SPORT
✊🏾🔥 #ዋናውን ይምረጡ፣ #ዋናነትዎን አጉልተው ያውጡ! ✊🏾🔥
📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 0901138283፣ 0910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።
👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ወይም በቴሌግራም ቦት @WanawSportBot ይዘዙን።
🏅 ዋናው ወደፊት...
@wanawsportwear

“ ሰንደቅ ዓላማችን ከፍ ያለው በድል እንጂ በተሳትፎ አይደለም “
“ የተገኘው ወርቅ የጥፋት ማካካሻ መሆን የለበትም “ ሻምበል ቶሎሳ ቆቱ
በርካታ ስኬታማ አትሌቶችን ያሰለጠኑት አሰልጣኝ ሻምበል ቶሎሳ ቆቱ የተገኘውን ወርቅ ሜዳልያ የጥፋት ማካካሻ ለማድረግ “ እንዳይታሰብ “ ሲሉ አሳስበዋል።
“ አንድ ወርቅ ሪዮ እና ቶኪዮ ላይ አግኝተናል እየተባለ የሚወራው ወሬ መቆም አለበት “ ሲሉ አሰልጣኝ ሻምበል ቶሎሳ ቆቱ የተገኘው ድል ለጥፋት ማካካሻ መደረግ እንደሌለበት አሳስበዋል።
“ በአንድ ወርቅ እያሳበብን ማግኘት የምንችለውን ለምንድነው የምናጣው ? ማራቶን ከአመታት በኋላ ነው የመጣው በምንታወቅባቸው ርቀቶች ለምን አላሸነፍንም ? ሲሉ አሰልጣኙ ጠይቀዋል።
“ እኛ ለተሳትፎ በፍጹም ወደ ኦሎምፒክ አንሄድም “ ያሉት አሰልጣኝ ሻምበል ቶሎሳ ቆቱ " ለተሳትፎ የሚሄዱት አትሌት የሌላቸው እና ሚኒማ ያላሟሉ ናቸዉ ፣ ሰው አውቋል ማታለል አይቻልም " በማለት ተናግረዋል።
አሰልጣኝ ሻምበል ቶሎሳ ቆቱ አያይዘውም ስፖርት ውስጥ አምባገነንነት በፍጹም አያስፈልግም ፣ ጀግና አትሌቶቻችን ሰንደቅ ዓላማችንን ከፍ ያደረጉት በድል እንጂ በተሳትፎ አይደለም “ ብለዋል።
መረጃው ከሸገር ስፖርት የራድዮ ፕሮግራም የተወሰደ ነው።

" እኔ ለተሳትፎ አውሮፕላን አይደለም ጋሪ አልሳፈርም “
“ ኦሎምፒክ ተሳትፎ ነው የተባለው የአፍ ወለምታ ነው “ አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ
ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ ያስገኘው አትሌት ታምራት ቶላ አሰልጣኝ የሆነው ገመዶ ደደፎ “ ለኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ " ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።
“ በዚህ ድል ላይ የአትሌት ሲሳይ ለማ ሚና ከፍ ያለ ነው “ ሲል የተደመጠው አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ “ ታምራት ተጠባባቂ የነበረ ቢሆንም ሲሳይ ለማ ነው እንዲወዳደር ማመልከቻ ፅፎ የጠየቀው “ ብሏል።
“ ሌላው በሁለት በሶስት ካልተወዳደርኩ ብሎ የሀገር ውጤት ሲያጠፋ ሲሳይ ግን ማንም ያላደረገውን ከእኔ እሱ ይሻላል ብሎ በወሰነው ሀገራችን ለወርቅ በቅታለች እሱ ትልቅ ክብር ይገባዋል “ አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ
የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ “ ኦሎምፒክ ተሳትፎ ነው “ ያሉት የአፍ ወለምታ መሆን አለበት ያለው ገመዶ ደደፎ “ እኔ ለተሳትፎ አውሮፕላን አይደለም ጋሪ አልሳፈርም “ ብሏል።

TIKVAH-SPORT
ዩናይትድ በድጋሜ ከሙኒክ ጋር ሊነጋገሩ ነው ! ማንችስተር ዩናይትድ በማትያስ ዴሊት እና ናስር ማዝራዊ ዝውውር ዙሪያ በድጋሜ ባየር ሙኒክን ለማነጋገር ማሰባቸው ተገልጿል። ከቀናት በፊት ባየር ሙኒክ ማንችስተር ዩናይትድ ያቀረበውን የመጀመሪያ የዝውውር ሒሳብ ውድቅ በማድረግ የተሻለ ሒሳብ መጠየቃቸው አይዘነጋም። ማንችስተር ዩናይትድ ሁለቱንም ተጨዋቾች ለአንድ ተጨማሪ አመት የማራዘም አማራጭ ባካተተ…
ዩናይትድ ተጨዋቾች ለማስፈረም ተስማማ !
ማንችስተር ዩናይትድ ማትያስ ዴሊት እና ናስር ማዝራዊን ለማስፈረም ከቡንደስሊጋው ክለብ ባየር ሙኒክ ጋር ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።
ቀያዮቹ ሴጣኖች ማትያስ ዴሊትን ከተጨማሪ ጋር አጠቃላይ 50 ሚልዮን ዩሮ በሚደርስ ሒሳብ በአምስት አመት ኮንትራት ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተነግሯል።
በተጨማሪም ናስር ማዝራዊን ከተጨማሪ ጋር አጠቃላይ 20 ሚልዮን ዩሮ በሚደርስ የዝውውር ሒሳብ ለማስፈረም ተስማምተዋል።
ማንችስተር ዩናይትድ በሌላ በኩል አሮን ዋን ቢሳካን በ15 ሚልዮን ፓውንድ ለዌስትሀም ዩናይትድ ለመሸጥ ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

አቡበከር ናስር በውሰት ሊያመራ ነው !
ኢትዮጵያዊው የፊት መስመር አጥቂ አቡበከር ናስር በቀጣይ በውሰት ወደ ሌላ ክለብ እንደሚያመራ የማሜሎዲ ሰንዳውንስ ዋና አሰልጣኝ ማንቆባ ምንጊቲ ገልጸዋል።
አቡበከር ናስር በአሁን ሰዓት በጥሩ ሁኔታ በማገገም ላይ መሆኑን የገለፁት አሰልጣኙ “ ጥሩ ምልክቶች እያሳየ ነው ፣ ግን አሁንም ትንሽ ይቀረዋል፣ በጣም እንወደዋለን ምክንያቱም ትልቅ ተሰጥኦ አለው “ ብለዋል።
ክለቡ ያለው የውጪ ሀገር ተጨዋቾች ቦታ በጣም የሚፈልገው መሆኑን የጠቆሙት አሰልጣኙ “ እርገጠኛ ካልሆንን በውሰት በቋሚነት የሚጫወትበት ቦታ " እንመለከታለን ብለዋል።
አቡበከር ናስር ሙሉ ለሙሉ ቢያገግምም አንድ አመት አለመጫወቱን ያነሱት ማንቆባ ምንጊቲ በቀጣይ በውሰት ጥሩ ከሆነ ታህሳስ ላይ እንመልሰዋለን ሲሉ ተናግረዋል።

“ ዩናይትድ እዚህ ያለው ጋብዘነው ነው “ ጋርዲዮላ
የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ቡድናቸው በዛሬው ጨዋታ ለመጫወት የበቃው ባለፈው አመት ጥሩ ስለሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
" እዚህ ያለነው ባለፈው አመት ጥሩ ስለሰራን ነው “ ያሉት ፔፕ ጋርዲዮላ ማንችስተር ዩናይትድም እዚህ መሆን ይገባቸዋል ምክንያቱም የሆነ ነገር አሸንፈዋል ወይም ወደዚህ እንዲመጡ ጋብዘናቸዋል " ብለዋል።
የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በበኩላቸው ከጨዋታው በፊት " እኔ ሁልጊዜ እንደምለው የወዳጅነት ጨዋታዎች አልወድም ማሸነፍ ነው የምወደው " ሲሉ ተደምጠዋል።