TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.7K photos
1.48K videos
5 files
3.41K links
加入频道
ክርስቲያን ሮሜሮ ወደ ሪያል ማድሪድ ?

የላሊጋው ክለብ ሪያል ማድሪድ አርጀንቲናዊውን ተከላካይ ክርስቲያን ሮሜሮ የማስፈረም ፍላጎት እንዳለው ለቶተንሀም አሳውቆ እንደነበር ተገልጿል።

የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም በበኩሉ ተጫዋቹን መሸጥም ሆነ ለመሸጥ መደራደር እንደማይፈልግ ለሪያል ማድሪድ ማሳወቁ ተገልጿል።

በፕሬዝዳንት ዳኒ ሌቪ የሚመራው ቶተንሀም ተጫዋቹን ለመሸጥ ከተገደደ 150 ሚልዮን ፓውንድ እንደሚጠይቅ ሲገለፅ ሎስ ብላንኮዎቹ በበኩላቸው ሀሳባቸውን መቀየራቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ በክብር አይደለም እየገባሁ ያለሁት “

“ የይለፍ መግቢያ ጠይቄ አላገኘሁም “ መሰረት ደፋር

በሶስት የኦሎምፒክ ውድድሮች ሀገሯን ወክላ የተወዳደረችው አትሌት መሰረት ደፋር በፓሪስ ኦሎምፒክ " በክብር እየገባሁ አይደለም " ስትል ተናግራለች።

ወደ ፓሪስ በግሏ ሙሉ ወጪ ሸፍና መሄዷን የገለፀችው መሰረት “ የሚቀድመው የሀገር ውጤት እና የተበላሹት ነገሮች ናቸው “ ስትል ተደምጣለች።

ወደ ፓሪስ የሄድኩት ትልቁ ነገር በመጀመሪያ አትሌቶቹን ለመርዳት ሌላው ለልጄ ኦሎምፒክ ለማሳየት ቃል ገብቼላት ስለነበር ከቤተሰቤ ጋር ነው የሄድኩት “ መሰረት ደፋር

ለሀገሬ በሰራሁት በሶስት ኦሎምፒክ ባደረኩት ነገር ቢያንስ የይለፍ መግቢያ እንደሚገባት የጠቆመችው መሰረት “ ጠይቄ አላገኘሁም በግሌ ስለሄድኩኝ ቅሬታ ማቅረብ አልችልም አልፈልግምም “ ብላለች።

መሰረት በትላንትናው እለት አለምአቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ትኬት አዘጋጅቶላት የትላንቱን ውድድር መታደሟን ገልፃለች።

ገዛኸኝ አበራ ላይ የደረሰው ነገር እንዳሳዘናት የተናገረችው መሰረት “ ክብር የሚገባው በትክክለኛው ክብር ማግኘት አለበት “ ብላ እንደምታስብ አሳውቃለች። 

መረጃው ከሸገር ስፖርት የራድዮ ፕሮግራም የተወሰደ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
  🆕 አዳዲስ እንዲሁም በመጠኑ ያገለገሉ ስልኮችን ከተሟላ ዋስትና እና ጥገና ጋር ይዘን ቀርበናል📱ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይጎበኙ

📌 https://yangx.top/sellphone2777

📞  0929008292

📩 inbox @bina27

📍አድራሻ- ቦሌ ከሸገር ህንፃ አጠገብ
ዛሬ ከምሽቱ 4፡14 ብርቅዬ አትሌቶቻችንን በፓሪሱ ኦሎምፒክስ 3000 ሜትር መሰናክል የሴቶች ፍፃሜ ይሳተፋሉ!

💥ሀገራችንን ወክለዉ የሚሳተፉ አትሌቶቻችን:
ሴምቦ አለማየሁ
ሎሚ ሙለታ

መልካም ዕድል ለአትሌቶቻችን! 💚💛❤️

የፓሪስ ኦሎምፒክስን በ350 ብር በጎጆ ፓኬጅ ይከታተሉ! ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/dg1

#Paris2024 #LikeAChamp #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
“ 1500 ሜትር የምደምቅበት ውድድሬ ነው “

“ ኬንያውያንን ለማኩራት ተዘጋጅቻለሁ “ ፌዝ ኪፕዬጎን

ኬንያዊቷ ሯጭ ፌዝ ኪፕዬጎን በቀጣይ በሚደረገው የ 1500 ሜትር ውድድር “ ኬንያዊያን ለማኩራት በትኩረት እሰራለሁ “ ስትል አስተያየቷን ሰጥታለች።

ትላንት ምሽት በ 5000 ሜትር ፍፃሜ ስለተፈጠረው ነገር አስተያየት መስጠት እንዳማትፈልግ የገለፀችው ፌዝ ኪፕዬጎን “ ይህ ስፖርት ነው እኔ ፌዝ ነኝ ሁልጊዜም በፍትሀዊነት ነው የምሳተፈው “ ብላለች።

“ አሁን ሙሉ ትኩረቴ 1500 ሜትር ነው ፣ ርቀቱ ከትላንቱ የተለየና እኔ የምደምቅበት ባህላዊ ርቀቴ ነው ፣ ሙሉ ትኩረቴ ኬንያውያንን ማኩራት ነው ፣ ውጤቱ ጥሩ እንደሚሆን አስባለሁ።“ ፌዝ ኪፕዬጎን

በትላንቱ 5000 ፍፃሜ የብር ሜዳልያ ያሳካችው አትሌት ፌዝ ኪፕዬጎን ረፋድ ላይ በተደረገው የ 1500 ማጣሪያ አራተኛ ደረጃን በመያዝ ግማሽ ፍፃሜ ደርሳለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አትሌቲኮ ማድሪድ አልቫሬዝን ለማስፈረም ንግግር ላይ ነው ! የስፔን ላሊጋው ክለብ አትሌቲኮ ማድሪድ አርጀንቲናዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ጁሊያን አልቫሬዝ ለማስፈረም ከማንችስተር ሲቲ ጋር በንግግር ላይ መሆኑ ተገልጿል። በአሰልጣኝ ዲያጎ ሲሞኒ የሚመራው አትሌቲኮ ማድሪድ ተጫዋቹን የማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው ሲገለፅ ዝውውሩን በ46.8 ሚልዮን ፓውንድ እና ተጨማሪ ክፍያ ማጠናቀቅ ይፈልጋሉ ተብሏል።…
ሲቲ አልቫሬዝን በክለቡ ሪከርድ ዋጋ ለመሸጥ ተስማማ !

ማንችስተር ሲቲ አርጀንቲናዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ጁሊያን አልቫሬዝ የክለቡ የምንግዜም ሪከርድ በሆነ ዋጋ ለአትሌቲኮ ማድሪድ ለመሸጥ መስማማቱ ተገልጿል።

አትሌቲኮ ማድሪድ አርጀንቲናዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ጁሊያን አልቫሬዝ በ 95 ሚልዮን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ ለማስፈረም ከማንችስተር ሲቲ ጋር ከስምምነት ደርሰዋል።

ማንችስተር ሲቲ ከሁለት አመታት በፊት ጁሊያን አልቫሬዝን ከአርጀንቲናው ክለብ ሪቨር ፕሌት በ 14 ሚልዮን ፓውንድ ማስፈረማቸው አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ የትላንቱ ውጤት ጉዳፍን አይገልፃትም “

“ ጉዳፍ ጠንካራ እና የማትዋዥቅ አትሌት ነች “ መሰረት ደፋር

በርቀቱ የተለያዩ ክብሮችን ያገኘችው መሰረት ደፋር ትላንት ምሽት በተመዘገበው ውጤት “ አዝነናል “ ስትል ገልፃዋለች።

ውድድሩ ቀላል እንደማይሆን የሚገመት ነበር የምትለው መሰረት “ እንዲህ አይነት ውጤት ይመጣል ብዬ አልጠበኩም ነበር “ ብላለች።

“ በሚያሳዝን ሁኔታ ተሸንፈናል ፣ ለኔ እንደ አትሌት በተለይም 5000ሜ ሶስት ጊዜ እንደመሮጤ ወደ ሆቴል የተመለስኩት አዝኜ ነው “ መሰረት ደፋር

የጉዳፍ አቅም ይሄ ነው ብላ እንደማታምን የገለፀችው መሰረት “ ከዚህ በላይ ማሳየት ትችል ነበር ፣ ነገሮች ተደራርበው ይህን እንዳታሳካ አድርጓታል “ ብላለች።

“ ጉዳፍ ሜዳሊያ ለማግኘት የምታንስ አትሌት አልነበረችም የተፈጠረው መገፋፋት እና መመታት ተፅዕኖ አድርጎባታል ፣ በመጨረሻ ሰዓት መነካካት ከባድ ነው እግር ከተነካ ሰውነት ይደነዝዛል “ መሰረት ደፋር

ውጤቱ ጉዳፍን የሚገልፅ አለመሆኑን የተናገችው መሰረት “ የጉዳፍ ደረጃ ይሄ አልነበረም ጉዳፍ ጠንካራ እና የማትዋዥቅ አትሌት ነች ፣ የትላንቱ ውጤት ጉዳፍን አይገልፃትም “ ብላለች።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ዩጋንዳውያን አትሌቶች ከውድድር ውጪ ሆነዋል !

ዩጋንዳውያኑ አትሌቶች በፓሪስ 2024 ኦሊምፒክ ውድድር በጉጉት ከሚጠበቀው የወንዶች 5000 ሜትር ውድድር ውጪ መሆናቸው ተገልጿል።

የ 10,000 ሜትር ወርቅ ሜዳልያ ባለቤቱ አትሌት ጆሽዋ ቺፕቴጌ እንዲሁም የቡድን አጋሩ ጃኮብ ኪፕሊሞ ከ 5,000 ሜትር ውድድር ውጪ መሆናቸው ተነግሯል።

ሁለቱ አትሌቶች ከባድ ፉክክር ከታየበት የ 10,000 ሜትር ውድድር በበቂ ሁኔታ ማገገም ባለመቻላቸው ምክንያት ነገ ከሚደረገው ማጣሪያ ውጪ መሆናቸው ታውቋል።

በዚህም ምክንያት ዩጋንዳ በፓሪስ ኦሎምፒክ 5,000 ሜትር ውድድር በኦስካር ቼሊሞ ብቻ የምትወከል ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" መጪው የውድድር አመት የእኔ ምርጥ ይሆናል " ኦናና

ካሜሮናዊው የማንችስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ አንድሬ ኦናና በቀጣዩ የውድድር ዘመን በግሉ ምርጥ ብቃቱን የሚያሳይበት እንደሚሆን በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

" መጪው የውድድር ዘመን የእኔ ምርጥ አመት ይሆናል " የሚለው አንድሬ ኦናና “ የዩናይትድ ደጋፊዎች ተዘጋጁ ምክንያቱም ብዙ አደጋ ያላቸው ኳሶችን እጠቀማለሁ ፤ አመቱ ለእኔ ጥሩ ይሆናል"ሲል ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ባርሴሎና ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ስፔናዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ዳኒ ኦልሞ ከጀርመን ቡንደስሊጋው ክለብ ሌፕዚግ ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

ባርሴሎና ተጫዋቹን ሰባት ሚልዮን ዩሮ ተጨማሪ ክፍያ ባለው 55 ሚልዮን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ ለማስፈረም መስማማታቸው ተነግሯል።

የ 26ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ዳኒ ኦልሞ  በባርሴሎና ቤት የስድስት አመት ኮንትራት ለመፈረም ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሁለት ፖላንዳዊ ዳኞች ለእስር ተዳረጉ !

ዛሬ ምሽት ዳይናሞ ኬቭ እና ሬንጀርስ የሚያደርጉትን የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ማጣሪያ ጨዋታ እንዲመሩ ተመርጠው የነበሩ ሁለት ፖላንዳዊ ዳኞች ሰክረው መገኘታቸው ተገልጿል።

የጨዋታ ዳኞቹ ከጨዋታው ሰዓታት በፊት ከፍተኛ የአልኮል መጠጥ ጠጥተው የመንገድ ዳር ምልክት ሰርቀው ሲጓዙ በፖሊስ ተይዘው ለእስር መዳረጋቸው ተገልጿል።

በዚህም ምክንያት የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ዛሬ ምሽት 3:00 ለሚደረገው ጨዋታው ሌሎች ዳኞችን መምረጡ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዴንዜል ዴምፍሪ ውሉን ማራዘም አይፈልግም !

ኔዘርላንዳዊው ተጨዋች ዴንዜል ዴምፍሪ የዝውውር መስኮቱ ከመጠናቀቁ በፊት ውል በማራዘም ዙሪያ ከኢንተር ሚላን ጋር መነጋገር እንደማይፈልግ ማሳወቁ ተገልጿል።

የ 28ዓመቱ ሁለገብ ተጨዋች ዴንዜል ዱምፍሪ ኢንተር ሚላንን መልቀቅ እንደሚፈልግ ሲገለፅ ማንችስተር ዩናይትድን መቀላቀል ይፈልጋል ተብሏል።

ማንችስተር ዩናይትድ ከኢንተር ሚላን ጋር ዋን ቢሳካን በዴንዜል ዴምፍሪ ከመቀያየር ዋን ቢሳካን ለዌስትሀም ዩናይትድ ሸጠው ናስር ማዝራዊን መግዛት እንደሚመርጡ ተገልጿል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች በቃል ደረጃ ከዌስትሀም ዩናይትድ ጋር ዋን ቢሳካን ለመሸጥ ቢስማማሙም ይፋዊ ስምምነት እንደሌላቸው ተዘግቧል።

እንግሊዛዊው የመስመር ተጨዋች ዋን ቢሳካ በበኩሉ ከዌስትሀም ዩናይትድ ይልቅ ኢንተር ሚላንን እንደሚመርጥ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የ 3,000ሜ ሴቶች መሰናክል ፍፃሜ ውድድር ጀምሯል !

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚሳተፉበት የፓሪስ ኦሎምፒክ 3,000 ሜትር መሰናክል ሴቶች ፍፃሜ ውድድር መደረጉን ጀምሯል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በርቀቱ በአትሌት ሎሚ ሙለታ እና ሲምቦ አለማየሁ ተወክላለች።

መልካም እድል ለአትሌቶቻችን 🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አራት ዙሮች ይቀራሉ !

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከመሪዎች ተርታ ይገኛሉ።

መልካም እድል ለአትሌቶቻችን 🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሶስት ዙሮች ቀርተውታል።

አትሌት ሲሞቦ አለማየሁ ከመሪዎቹ ተርት ትገኛለች።

አምስት አትሌቶች ተነጥለው ፉክክራቸውን ሲያደርጉ ዩጋንዳ ዙርን በመምራት ላይ ትገኛለች።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የ 3000ሜ ሴቶች መሰናክል ፍፃሜውን ሲያገኝ ባህሬን በያቪ አማካኝነት የወርቅ ሜዳሊያውን ማሸነፍ ችላለች።

🥇ያቪ ( ባህሬን )
🥈ቼሙታይ ( ዩጋንዳ )
🥉ቼሮቲች ( ኬንያ )

ኢትዮጵያ ሲምቦ አለማየሁ #አምስተኛ እንዲሁም ሎሚ ሙለታ #ስምንተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

ኢትዮጵያ በርቀቱ ሜዳሊያ ያገኘችው እ.ኤ.አ በ 2012 ነበር።
ኢትዮጵያ ስንተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች ?

የ 2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ መካሄዱን ሲቀጥል ሀገራችን ሁለት የብር ሜዳሊያን ብቻ አግኝታለች።

68 ሀገራት በሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባት ሲችሉ ኢትዮጵያ 52ኛ ደረጃን ይዛ ትገኛለች።

ኬንያ ከአፍሪካ ቀዳሚ ስትሆን :-

አንድ ወርቅ
አንድ ብር እና
ሁለት ነሐስ በመሰብስ 29ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችለዋል።

በቀጣይ ቀናት ተጠባቂ የፍፃሜ ውድድሮች በሁለቱም ፆታዎች የሚደረጉ ይሆናል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
Photo
“ የኢትዮጵያ ህዝብ ይፍረድ “ ፍሬወይኒ ሀይሉ

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ፍሬወይኒ ሀይሉ በፓሪሱ የ 2024 ኦሎምፒክ ውድድር ውጪ መሆኗን ተከትሎ በከባድ ሀዘን ወደ ሀገሯ ለመመለስ ጉዞ መጀመሯ ተገልጿል።

አትሌቷ በቅርቡ በአመቱ ውስጥ በ 1500 እና 5000 ሜትር ከሌሎች አትሌቶች የተሻለ ውጤት እንዳላት በመግለፅ ለኦሎምፒክ ባለመመረጧ ቅሬታ አቅርባ እንደነበር አይዘነጋም።

በሁሉም ርቀቶች እንደማትሳተፍ እውን በመሆኑ ወደ ሀገር ቤት በመመለስ ላይ መሆኗ ሲገለፅ“ የኢትዮጵያ ህዝብ ይፍረደው “ ማለቷን ኢትዮ ኪክ ኦፍ አስነብቧል።

ከአትሌት ፍሬወይኒ ሀይሉ በተጨማሪም አትሌት እጅጋየሁ ታዬ እና አትሌት ኤርሚያስ ወደ ሀገራቸው በመመለስ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

የመረጃው ባለቤት ኢትዮ ኪክ ኦፍ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
"🚀 የአቪዬተር ሻሞ - በረራ በነጻ!
የአቪዬተር ሻሞ ሽጦታዎች ዛሬም ቀጥለዋል!
እስከ 4ሺብር ዋጋ ያላቸው ነጻ የመወራረጃ እጣዎች እርስዎን እየጠበቁ ነው።
አሁኑኑ የራስዎ ያርጓቸው - 👉ln.run/k_QQW