TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.7K photos
1.48K videos
5 files
3.41K links
加入频道
90+4 ' ኖቲንግሀም ፎረስት 2 - 1 ማንችስተር ዩናይትድ

ዶምንጉዌዝ       ራሽፎርድ
ጊብስ ዋይት

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማንችስተር ዩናይትድ ሽንፈት አስተናግዷል !

በሀያኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ ከኖቲንግሀም ፎረስት ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል።

የኖቲንግሀም ፎረስትን የማሸነፊያ ግቦች ዶምኒጉዌዝ እና ጊብስ ዋይት ሲያስቆጥሩ ለማንችስተር ዩናይትድ ማርከስ ራሽፎርድ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ማንችስተር ዩናይትድ በዘንድሮው የውድድር ዘመን በሊጉ #ዘጠነኛ እንዲሁም በሁሉም ውድድሮች አስራ አራተኛ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

7️⃣ኛ :- ማንችስተር ዩናይትድ ( 3️⃣1️⃣ ነጥብ )

1️⃣5️⃣ኛ :- ኖቲንግሀም ፎረስት ( 2️⃣0️⃣ ነጥብ )

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

ዕሁድ - ማንችስተር ዩናይትድ ከ ቶተንሀም

ቅዳሜ - ብሬንትፎርድ ከ ኖቲንግሀም ፎረስት

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ወደ ነበሩበት አቋማቸው ተመልሰዋል " ጋሪ ኔቭል

የቀድሞ የቀያይ ሴጣኖቹ ተጨዋች ጋሪ ኔቭል ማንችስተር ዩናይትድ ወጥ የሆነ አቋም ማሳየት የተሳነው ቡድን መሆኑን ከዛሬ ሽንፈት በኋላ ተናግሯል።

" ማንችስተር ዩናይትድ ወደ ነበሩበት አቋማቸው ተመልሰዋል " ያለው ጋሪ ኔቭል ወጥነት የሌላቸው አስከፊ ቡድን ናቸዉ ተሸንፈው ከሜዳ ወጥተዋል ደጋፊውም ተበሳጭቶ ወጥቷል።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አል ናስር ድል አድርጓል !

በሳውዲ አረቢያ ሊግ የአስራ ስምንተኛ ሳምንት መርሐ ግብር የክርስቲያኖ ሮናልዶው ክለብ አል ናስር አል ታውንን 4 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የአል ናስርን የማሸነፊያ ግቦች ፖርቹጋላዊው ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ ፣ ኢታቪዮ ፣ ላፖርቴ እና ብሮዞቪች ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በውድድር ዘመኑ ያስቆጠራቸውን የሊግ ግቦች ሀያ በማድረስ የሊጉን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች ደረጃ እየመራ ይገኛል።

ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በ2023 ሀምሳ አራት ግቦችን በማስቆጠር ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ተጨዋች በመሆን ማጠናቀቅ ችሏል።

አል ናስር ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን አርባ ስድስት በማድረስ ሁለተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ውጤቱ እጅግ ያበሳጫል " ቴንሀግ

የማንችስተር ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ቡድናቸው ዛሬ ምሽት ያስመዘገበው ውጤት እንዳበሳጫቸው ከጨዋታው በኋላ ተናግረዋል።

ውጤቱ እጅግ ያበሳጫል ያሉት አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ " ቡድኑ 1ለ0 ከተመራ በኋላ ወደ ጨዋታ ተመልሶ አቻ መሆንም ችሎ ነበር ነገርግን በመልሶ ማጥቃት ግብ ተቆጠረብን።"ብለዋል።

አሰልጣኙ ቀጥለውም በርካታ ተጨዋቾቻቸው ከጉዳት ሲመለሱ የቡድኑን ጥንካሬ ይጨምሩታል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
" ውጤቱ እጅግ ያበሳጫል " ቴንሀግ የማንችስተር ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ቡድናቸው ዛሬ ምሽት ያስመዘገበው ውጤት እንዳበሳጫቸው ከጨዋታው በኋላ ተናግረዋል። ውጤቱ እጅግ ያበሳጫል ያሉት አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ " ቡድኑ 1ለ0 ከተመራ በኋላ ወደ ጨዋታ ተመልሶ አቻ መሆንም ችሎ ነበር ነገርግን በመልሶ ማጥቃት ግብ ተቆጠረብን።"ብለዋል። አሰልጣኙ ቀጥለውም በርካታ ተጨዋቾቻቸው ከጉዳት ሲመለሱ…
ለሽንፈታቸው ምክንያት ጉዳት መሆኑን ቴንሀግ ገለፁ !

ማንችስተር ዩናይትድ በዚህ አመት ካደረጋቸው ሀያ ስምንት ጨዋታዎች በአስራ አራቱ የመሸነፉ ምክንያት " ጉዳት ነው " ሲሉ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ገልፀዋል።

በጨዋታዎቹ መሸነፋችን በጉዳት ምክንያት የመጣ ነው ሲሉ ያስረዱት አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ " ለሽንፈቶቹ ዋናው ምክንያት ጉዳት ነው በጥር ተጫዋቾቻችን ይመለሳሉ ውጤቱም ይሻሻላል።"ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ድንቅ አመት በማሳለፌ ደስ ብሎኛል " ሮናልዶ

በ2023 ሀምሳ አራት ግቦችን በማስቆጠር ከፍተኛ ግብ አስቀጣሪ በመሆን ያጠናቀቀው ክርስቲያኖ ሮናልዶ አመቱ ለእሱ ድንቅ እንደነበር ተናግሯል።

" በጣም ደስ ብሎኛል አመቱ ለእኔ ድንቅ ነበር " የሚለው ሮናልዶ በቀጣይ አመት ምርጡን አቋሜን ለማሳየት ጥረት አደርጋለሁ ፣ የቡድን አጋሮቼን እና ደጋፊዎችን አመሰግናለሁ።"ሲል ተደምጧል።

የአምስት ጊዜ ባሎን ዶር አሸናፊው ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ በ2023 ባደረጋቸው ሀምሳ ዘጠኝ ጨዋታዎች ሀምሳ አራት ግቦች አስቆጥሮ አስራ አምስት አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጁቬንቱስ ወሳኝ ድል አሳክቷል !

በጣልያን ሴርያ የአስራ ስምተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ጁቬንቱስ ከሮማ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የጁቬንቱስን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ አድርያን ራብዮ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ጁቬንቱስ ያለፉትን አስራ ሶስት የሴርያ ጨዋታዎች አልተሸነፉም አስሩን ሲያሸንፉ በሶስቱ አቻ ተለያይተዋል።

ጁቬንቱስ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን አርባ ሶስት በማድረስ ከሊጉ መሪ ኢንተር ሚላን ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት ማጥበብ ችሏል።

ሮማ በሀያ ስምንት ነጥቦች ሰባተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ከወዲሁ እንኳን ለገና በአል አደረሳችሁ እያልን ውበትን ከጥንካሬ ጋር የተጎናፀፉ ፤ በእራሶ ዲዛይን ወይም በድርጅቶ ሎጎ እና መረጃ ያሸበረቁ የወረቀት ዘንቢሌችን ፤ ፌስታሎችን እንዲሁም የተለያዩ ማሸጊያዎችን አዘጋጅተን እነሆ ብለናል ።

Miracle Gifts🎁

Contact
          @HiluxRom1987
          @Embrehane
            OR
📞09 24 59 59 82
📞09 94 52 07 86
Telegram = https://yangx.top/mirale1987
Facebook = https://www.facebook.com/profile.php?id=100088383633501
Instagram = https://www.instagram.com/p/CnPDKi-tNQg/?igshid=YmMyMTA2M2Y=

#papershoppingbag #plasticshoppingbag  #engreving  #silkescreenprint

Address- Gerji Roba, gerji gorigis buliding  office number 244
📢 #13ኛው_ቢጂአይ_ኢትዮጵያ_ሚዲያ_ካፕ ዛሬ ታህሳስ 21፣ 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ትንሿ ስታዲየም ይጀምራል። ተወዳዳሪ 32 ሚዲያዎችም ዋናው ስፖርት ባቀረባቸው ልዩ ማሊያዎች ደምቀው ውድድራቸውን ይጀምራሉ።

🤔 የትኛውን ማሊያ የበለጠ ወደዱት?

💬 በኮሜንት ላይ ያጋሩን!

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
የዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች !

11:00 ፉልሀም ከ አርሰናል

11:00 ቶተንሀም ከ በርንማውዝ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" መጫወት እንደምችል ራሴን አሳይቻለሁ " ኢላንጋ

የኖቲንግሀም ፎረስት የፊት መስመር ተጨዋች አንቶኒ ኢላንጋ በምሽቱ የማንችስተር ዩናይትድ ጨዋታ በትልቅ ደረጃ መጫወት እንደሚችል ያሳየበት እንደነበር ተናግሯል።

ባለፈው አመት በማንችስተር ዩናይትድ ቤት የጨዋታ ሰዓት ባለማግኘቱ ከባድ ጊዜ አሳልፎ እንደነበር አንቶኒ ኢላንጋ ተናግሯል።

ትላንት ምሽት የኖቲንግሀምን የማሸነፊያ ግብ አመቻችቶ ያቀበለው አንቶኒ ኢላንጋ " ጨዋታው በትልቅ ደረጃ መጫወት እንደምችል የማረጋግጥበት ነበር አሳይቻለሁ።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe