TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.7K photos
1.48K videos
5 files
3.41K links
加入频道
አርሰናል አዲስ ታሪክ ፅፈዋል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በዘንድሮው የውድድር አመት በርካታ ቀናትን በሊጉ መሪነት መቆየት ቢችልም በመጨረሻም የሊጉን ዋንጫ በማንችስተር ሲቲ ተቀምቷል።

መድፈኞቹ በፕርሚየር ሊጉ ታሪክ በርካታ ቀናቶችን በሊጉ መሪነት ቆይተው ዋንጫውን ማሸነፍ ያልቻሉ የመጀመሪያው ክለብ የመሆን ችለዋል።

በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የሚመራው አርሰናል በዘንድሮው የውድድር አመት ፕርሚየር ሊጉን ለ 248 ቀናት መምራት መቻላቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ዘጠና ነጥቦች ያስፈልጋሉ "

የቀድሞ እንግሊዛዊ ተጨዋች ጄሚ ካራገር ከዚህ በኋላ የሊጉን ዋንጫ ማሸነፍ የሚፈልግ ክለብ ከዘጠና በላይ ነጥቦችን መሰብሰብ እንደሚጠበቅበት ገልጿል።

ጄሚ ካራገር በንግግሩም " በማንችስተር ሲቲ ምክንያት አሁን በሁሉም የውድድር አመቶች ዋንጫ ማንሳት የሚፈልግ ክለብ ከዘጠና በላይ ነጥቦችን መሰብሰብ አለበት።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" እነሱም ሻምፒዮን አይሆኑም "

የቀድሞ የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም የመስመር ተጫዋች ሰርጂ አሪየር በአሁን ሰዓት በኖቲንግሀም ፎረስት እየተጫወተ ሲገኝ ቡድኑ በሊጉ መቆየቱን ካረጋገጠ በኋላ መልዕክቱን አስተላልፏል።

ሰርጂ አሪየር በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባስተላለፈው መልዕክትም ቶተንሀም ሻምፒዮን ካልሆነ አርሰናልም ሻምፒዮን መሆን እንደሌለበት ተናግሯል።

በመልዕክቱም " የቶተንሀም ቤተሰቦቼ እኛ ሻምፒዮን ካልሆንን እነሱም ሻምፒዮን አይሆኑም " ሲል የአርሰናልን የሻምፒዮንነት ጉዞ ስለማስቀረቱ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#TikvahImages🇪🇹

ሀገራዊ ስፖርታዊ ውድድሮች ላይ የሚነሱ ምስሎችን በፌስቡክ ፣ ኢንስታግራም እና ትዊተር ማህበራዊ ትስስር ገፆቻችን ያገኛሉ።

ኢንስታግራም :- https://instagram.com/kidusyoftahe?igshid=ZDdkNTZiNTM=

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዋናው....... የታለ ማሊያው ?


ይኸው ማልያዎት 599 ብቻ

• እርጥበት በማይዝ

• ቀላልና ምቾት የሚሰጥ

• ቶሎ የሚደርቅ

•እንዲሁም አየር በሚያስወጣ ምርጥ ጨርቅ ተዘጋጅቶ ለእርስዎ ቀርቦልዎታል።

📞 ይደውሉን :- 📱0910 851 535   
                      📱0901138283

ቻናላችን :- https://yangx.top/wanawsportwear
" ሊቨርፑል ላይ ካገባሁ ደስታዬን አልገልፅም "

በትላንትናው ዕለት ከሊቨርፑል ጋር በይፋ የተለያየው አሌክስ ቻምበርሌን በቀጣይ በሌላ ክለብ በሚኖረው ቆይታ ወደ አንፊልድ በሚመለስበት ወቅት ደስታውን እንደማይገልፅ ተናግሯል።

አሌክስ ቻምበርሌን በንግግሩም " በሆነ ወቅት ወደ አንፊልድ እንደምመለስ እርግጠኛ ነኝ ፣ ከዚህ በፊት እንዳደረኩት ከሊቨርፑል ደጋፊዎች ፊት እጫወታለሁ።

በጨዋታው ግብ የማስቆጠር ከሆነ ደስታዬን እንደማልገልፅ ቃል እገባለሁ ፣ እዚህ ያሳለፍኩትን ነገር ሁሉ አከብራለሁ።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማድሪድ የተጨዋቾቹን ውል ሊያራዝም ነው !

ሪያል ማድሪድ የመሐል ሜዳ ተጨዋቾቹ ቶኒ ክሩስ እና ሉካ ሞድሪችን ኮንትራት ለተጨማሪ አመት ለማራዘም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

ሁለቱም የመሐል ሜዳ ተጨዋቾች በሎስ ብላንኮዎቹ ቤት እስከ 2024 የሚያቆያቸውን አዲስ ውል እንደሚፈርሙ ሲገለፅ በቅርቡም ይፋ እንደሚደረግ ተነግሯል።

ሎስ ብላንኮዎቹ በተጨማሪ የፊት መስመር ተጨዋቹ ቪንሰስ ጁኒየርን ኮንትራት በቅርቡ ማራዘማቸውን ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" አንዳንዶች ከሲቲ የበለጠ አውጥተዋል "

እንግሊዛዊው የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋች ጋሪ ኔቭል ማንችስተር ሲቲ እያስመዘገበ የሚገኘው ስኬት በገንዘብ ብቻ የመጣ እንዳልሆነ ተናግሯል።

ጋሪ ኔቭል በንግግሩም " ማንችስተር ሲቲ ባለፉት አራት ወይም አምስት አመታት ያወጡትን ገንዘብ ከተመለከትነው ሌሎች ክለቦች ካወጡት ብዙም የተለየ አይደለም ፣ እንደውም አንዳንዶች ከእነሱ የበለጠ አውጥተዋል።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ተሻሽዬ እመለሳለሁ " ፖል ፖግባ

ፈረሳዊው የጁቬንቱስ ተጨዋች ፖል ፖግባ በዚህ አመት የገጠመው ጉዳት በቀጣይ አመት ጠንክሮ እንዲመለስ እንደሚያግዘው በማህበራዊ ትስስር ገፁ ለደጋፊዎቹ ባስተላለፈው መልዕክት ገልጿል።

ፖል ፖግባ በመልዕክቱም " አመቱ ለእኔ ከሜዳ ውጪ እና በሜዳ ላይ ባሉ ችግሮች በጣም ከባድ ሆኖብኝ ነበር ፣ በዚህ አንድ አመት ውስጥ ብዙ ነገር ተምሬያለሁ።

ያጋጠመኝ ነገር ሁሉ የበለጠ ተጠናክሬ እንድመለስ ይረዳኛል ፣ በአእምሮም በአካልም በጥሩ ሁኔታ ተመልሼ ክለቤን ለመርዳት እና ዋንጫ ለማሸነፍ የምችለውን ሁሉ አደርጋለሁ።"ሲል ለደጋፊዎቹ ባስተላለፈው መልዕክት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሀድያ ሆሳዕና ድል አድርጓል !

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሀድያ ሆሳዕና ከ ባህር ዳር ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የሀድያ ሆሳዕናን ግቦች ሰመረ ሀፍታይ እና ተመስገን ብርሀኑ ሲያስቆጥሩ ለባህር ዳር ከተማ ቻርለስ ሪቫኖ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ባህርዳር ከተማ ሽንፈት ማስተናደገዱን ተከትሎ የሊጉን መሪነት ከቅዱስ ጊዮርጊስ መረከብ የሚችልበትን ዕድል ሳይጠቀም ቀርቷል።

ሀድያ ሆሳዕና በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ነጥቦቹን ሰላሳ ስድስት በማድረስ #አምስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ባህር ዳር ከተማ በሀምሳ ነጥብ #ሀለተኛ ደረጃን ይዟል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ባህር ዳር ከተማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲሁም ሀድያ ሆሳዕና ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

12:00 ማንችስተር ሲቲ ከ ቼልሲ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ከምንግዜውም በላይ አስደሳች ነው "

የማንችስተር ሲቲው ተከላካይ ካይል ዎከር ቡድናቸው ለተከታታይ ሶስተኛ ጊዜ ሻምፒዮን መሆኑ የተለየ ስሜት እንደሚፈጥር ተናግሯል።

ካይል ዎከር በንግግሩም " ሻምፒዮን ስትሆን ሁልጊዜም ተመሳሳይ ስሜት ነው የሚሰማው ነገር ግን ይህ ለተከታታይ ሶስተኛ ጊዜ በመሆኑ ይለያል ፣ ይህንን ማድረግ የቻለው አንድ ሌላ ክለብ ብቻ ይመስለኛል።

ከቶተንሀም ወደ ማንችስተር ሲቲ ስመጣ አምስት የፕርሚየር ሊግ ዋንጫ አሳካለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር ከምንግዜውም በላይ አስደሳች ነው።" ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" እዚህ የመጣነው ለማሸነፍ ነው "

የለንደኑ ክለብ ቼልሲ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሉፍተስ ቼክ ቡድናቸው ወደ ማንችስተር የመጣው ማንችስተር ሲቲን ለማሸነፍ መሆኑን ተናግሯል።

ሉፍተስ ቼክ በንግግሩም " የራሳችንን ዕቅድ ይዘን ነው የመጣነው እንደሚሰራ ተስፋ አደርጋለሁ ወደዚህ የመጣነው ለማሸነፍ ነው።"ሲል ከጨዋታው በፊት በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ተከታታይ ሶስት ዋንጫ ማሸነፍ የተለየ ነው "

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ቡድናቸው ተከታታ ሶስት የሊግ ዋንጫዎችን ከከባድ ተፎካካሪዎች ጋር ተፋልሞ ማሸነፍ የተለየ መሆኑን ተናግረዋል።

" እያንዳንዱ ፕርሚየር ሊግ ዋንጫ ልዩ ነው ፣ ለተከታታይ ሶስተኛ ጊዜ በተለይ ከሊቨርፑል እና በዚህ አመት ደግሞ ድንቅ ቡድን ከነበረው አርሰናል ጋር ተፎካክሮ ማሸነፍ የተለየ ነው።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#PremiereLeague 🇬🇧

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሰላሳ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብሮች ቀጥለው ሲደረጉ ብራይተን ሳውዝሀምፕተንን 3ለ1 እንዲሁም ዌስትሀም ሊድስን በተመሳሳይ 3ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የብራይተንን የማሸነፊያ ግቦች ፈርጉሰን እና ግሮስ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

የዌስትሀም ዩናይትድን የማሸነፊያ ግቦች ዴክላን ራይስ ፣ ቦውን እና ላንዚኒ አስቆጥረዋል።

ብራይተን ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ስልሳ አንድ በማድረስ የዩሮፓ ሊግ ተሳትፎ ቦታን ማግኘታቸውን ማረጋገጥ ችለዋል።

ሊድስ ዩናይትድ ሽንፈት ማስተናገዳቸውን ተከትሎ በሰላሳ አንድ ነጥብ ወደ ሻምፕዮን ሽፑ ለመውረድ ተቃርበዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
5' ማንችስተር ሲቲ 0-0 ቼልሲ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe