TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.7K photos
1.48K videos
5 files
3.41K links
加入频道
በሰው መግደል የተከሰሰው ኔዘርላንዳዊ ተጫዋች !

የ ኔዘርላንድ ብሄራዊ ቡድን እና የ ስፓርትክ ሞስኮ የመስመር ተጫዋች ኩዊንሲ ፕሮምስ ከ አመት በፊት ፈፀመ በታበለው የሰው መግደል ወንጀል ክስ ሊመሰረትበት መሆኑ ተገልጿል ።

ፖሊስ በ ግንቦት ወር ምርመራውን አጠናቆ ፋይሉን በ አምስተርዳም ወደሚገኘው ፍርድ ቤት ማስተላለፉ ሲገለፅ ከ ክረምቱ የ አውሮፓ ዋንጫ በኋላ አቃቤ ህግ ምርመራውን አድርጎ ክስ መመስረቱ ተገልጿል ።

ፕሮምስ በ ቤተሰቡ አንድ ግለሰብ ላይ በስለት በመመውጋት ከባድ ጉዳት ማድረሱ ሲገለፅ ጥፋተኛ ሆነ ከተገኘ በሀገሪቱ መቅጫ ህግ ከ 24 እስከ 42 ወራት የሚደርስ እስራት እንደሚቀጣ ተዘግቧል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የ ቡንደስሊጋው የወሩ ምርጥ ተጫዋች !

የ ጀርመን ቡንደስሊጋ የወርሀ ጥቅምት የሊጉ ምርጥ ተጫዋች ይፋ ሆኗል ።

ይህንንም ተከትሎ አስደናቂ የውድድር ዓመትን እያሳለፈ የሚገኘው የ ሌፕዚጉ ክሪስቶፈር ንኩንኩ የ ሊጉ የወሩ ምርጥ ተጫዋች በመባል መመረጡ ተገልጿል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
" ቤንዜማ ባሎን ዶርን ማሸነፍ አለበት "

ስፔናዊው የቀኝ መስመር ተጫዋች አልቫሮ ኦድሪዮዞላ የ ቡድን አጋሩ የ ባሎን ዶርን ማሸነፍ እንደሚገባው ጠቁሟል ።

" የ ቤንዜማ የ ባሎን ዶር ሽልማት ማሸነፍ ለ እግር ኳስ ድል ነው " ሲል ኦድሪዮዞላ ከ ስፔን መገናኛ ብዙሀን ጋር ባደረገው ቆይታ ተናግሯል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሬንጀርስ አዲስ አሰልጣኝ ሾመ !

ከ ስቴቨን ጄርራድ ጋር ከ ተለያዩ በኋላ አዲስ አሰልጣኝ በመፈለግ ላይ ይገኙ የነበሩት ሬንጀርሶች አዲስ አሰልጣኝ መሾማቸው ይፋ ሆኗል ።

ኔዘርላንዳዊው ጆቫኒ ቫን ብሮኮስት አምስት ቀናት ከፈጀ ድርድር በኋላ የ ግላስኮውን ክለብ ለማሰልጣን መስማማታቸውን ክለቡ ይፋ አድርጓል ።

ቫን ብሮንኮስት ሬንጀርስን በቋሚነት ለማሰልጠን የተስማማው አስራ ሰባተኛው አሰልጣኝ መሆኑን ክለቡ አሳውቋል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የፈረንሳይ ሊግ የወሩ ምርጥ ተጫዋች !

የ ፈረንሳይ ሊግ የወርሀ ጥቅምት የሊጉ ምርጥ ተጫዋች ይፋ ሆኗል ።

ብራዚላዊው የ ሊዮን ተጫዋች ሉካስ ፓኩዌታ የ ሊጉ የወሩ ምርጥ ተጫዋች በመባል መመረጡ ተገልጿል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
" ከ ቱርክ ወደ ጣልያን በእግሬ እሄዳለው "

ጣልያናዊው የፊት መስመር አጥቂ ማርዮ ባላቶሊ በ ቱርክ የ እግር ኳስ ህይወቱን እየመራ ሲገኝ ዳግም ወደ ጣልያን ብሄራዊ ቡድንን መመለስ እንደሚያልም ተናግሯል ።

" ካለፉት ሁለት ዓመታት ተኩል ወዲህ በእግር ኳስ ህይወቴ ጥሩ ስሜት ይሰማኛል ፣ ወደ ጣልያን ብሄራዊ ቡድን ለመመለስ ዝግጁ እንደሆንክ ይሰማኛል።

ህልም ይሆን ይሆናል ፣ በመጋቢት ወር በ ጣሊያን ቡድን ውስጥ እንደምሆን ካወቅኩ ከ አሁኑ ከ ቱርክ ወደ ጣልያን በእግር እሄዳለው " ሲል ተደምጧል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
መድፈኞቹ ተጫዋቻው ከጉዳቱ አገግሟል !

የ ሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሴናል ጋናዊው የመሐል ሜዳ ተጫዋች ቶማስ ፓርቴ ካጋጠመው ጉዳት ሙሉ ለሙሉ በማገገም ለጨዋታ ብቁ መሆኑ ተነግሯል ።

የ 28 ዓመቱ ቶማስ ፓርቴ መድፈኞቹ ወደ መርሲሳይድ አቅንተው ሊቨርፑልን በሚገጥሙበት ጨዋታ ተሰልፎ መጫወት እንደሚችል ተገልጿል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ኔይማር ወደ ሜዳ መቼ ይመለሳል ?

ብራዚላዊው የ ፒኤስጂ የ መስመር ተጫዋች ኔይማር ከ ጉዳቱ ሙሉ ለሙሉ አለማገገሙን የፈረንሳይ የመገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል ።

ይህንንም ተከትሎ ኔይማር በነገው ዕለት ፒኤስጂ ከ ናንትስ የሚያደርጉት ጨዋታ እንደሚያመልጠው ሲገለፅ በቀጣይ ከ ማንችስተር ሲቲ ጋር የሚያደርጉት የ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ላይ መድረሱ አጠራጣሪ መሆኑ ተገልጿል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ዚነዲን ዚዳን የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ አደረገ !

የቀድሞው የ ሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን ስሙ ከበርካታ ክለቦች ጋር ቢገናኝም የቀረቡለትን ጥያቄዎች ውድቅ እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል ።

አሰልጣኙን ዣቪ ያጣው የ ኳታሩ ሀያል ክለብ አል ሳድ ዚዳንን ለመቅጠር ከፍተኛ ፍላጎት ቢያሳይም ዚዳን ጥያዌውን ውድቅ ማድረጉ ተነግሯል ።

ዚዳን ከ ፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን አልያም ፒኤስጂ የሚቀረቡ ጥያቄዎች ለመቀበል ዝግጁ መሆኑ በመረጃው ተያይዞ ተዘግቧል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሞሀመድ ሳላህ ማልያውን ለጨረታ አቀረበ !

ግብፃዊው የ ሊቨርፑል የ ፊት መስመር ተጫዋች ሞሀመድ ሳላህ ማንችስተር ዪናይትድን 5 ለ 0 ሲያሸንፉ የለበሰውን ማልያ ለጨረታ ማቅረቡ ተገልጿል ።

ሳላህ ከጨረታው የተሰበሰበው ገንዘብ በ ግብፅ ውስጥ የ እንስሳትን ጉዳይ ለሚከላከል ማህበር እንደሚለግስ ተዘግቧል ።

ጥቅምት 14 በ ኦልድ ትራፎርድ በተደረገው በዚህ ጨዋታ ሞሀመድ ሳላህ ቀያይ ሴጣኖቹ ላይ ሀትሪክ መስራቱ የሚታወስ ነው ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#Ethiopian_PremierLeague

የ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከ #አራተኛ እስከ #ዘጠነኛ ሳምንት በሀዋሳ ከተማ መካሄዱን ሲቀጥል የጨዋታ ሰዓቶች እና የደጋፊዎች የስታዲየም አገባብ አስመልክቶ አክስዮን ማህበሩ ወቅታዊ መረጃ አጋርቷል ።

በፕሮግራሙ መሰረት በየሳምንቱ ስምንት ጨዋታዎች ላይ የመጀመሪያው ጨዋታ በ 9፡00 ሰዓት እንዲሁም ሁለተኛው በ 12፡00 ሰዓት የሚደረጉ ይሆናል ።

በ ሁሉም ጨዋታዎች የኮቪድ ፕሮቶኮሉ ተጠብቆ የ ሐዋሳ ዩንቨርስቲ ስታዲየም ለደጋፊዎች ክፍት ሲሆን ማንኛውም ተመልካች ወደ ስታዲየም ሲመጣ ከመግቢያ ትኬት በተጨማሪ ማንነቱን የሚገልፅ #መታወቂያ መያዝ ይኖርበታል ።

የስታዲየም መግቢያ ትኬት ባለ ሜዳ ክለቦች በሚያመቻቹት መንገድ የሚሸጥ መሆኑን የ አክስዮን ማህበሩ አሳውቋል ።

* ሙሉ የውድድር መርሐ ግብሩ በምስሉ ላይ ተያይዟል ።

#Betika
#CentralHawassaHotel

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ስፔናዊው ተስፈኛ ጋቪ ቀጣይ እጣ ፈንታ ?

በ ካታላኑ ክለቡ ባርሴሎና በዘንድሮው የውድድር ዓመት ከታዩ ተስፈኛ ወጣት ተጫዋቾች መካከል አንዱ ጋቪ ሆኖ ይገኛል ።

የ 17 ዓመቱ የ መሐል ሜዳ ተጫዋች ጋቪ የበርካታ ክለቦችን ቀልብ ሲስብ ቼልሲን ጨምሮ በርካታ ቡድኖች አይናቸውን ጥለውበታል ።

ሆኖም ግን አሁን ላይ ባርሴሎና ተስፈኛ ተጫዋቻቸውን አሳልፈው ላለመስጠት ኮንትራቱን ለማራዘም በቀዳሚነት እየሰሩ መሆኑ ተገልጿል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ቼልሲ ሁለት ተጫዋቾቹን በጉዳት አያሰለፍም !

የ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በዚህ ሳምንት በ ፕርሚየር ሊጉ ሌስተር ሲቲን ሲገጥሙ ሁለት ተጫዋቾቻቸውን እንደማያሰልፍ እርግጥ ሆኗል ።

የ ፊት መስመር አጥቂው ሮሜሎ ሉካኩ ከ ጉዳት ተመልሶ ልምምድ ቢጀምርም ለዚህ መርሐ ግብር እንደማይደርስ ሲገለፅ ማትዮ ኮቫቺች ሌላኛው ከዚህ ጨዋታ ውጪ የሆነው ተጫዋች ነው ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#Ethiopia🇪🇹

ለ አፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው ቶታል ኢነርጂስ ካፍ የሴቶች ቻምፒዮንስ ሊግ ከሁለት ሳምንታት በፊት በግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ ተጀምሯል። ፍፃሜው ደግሞ ዛሬ አርብ ኅዳር 10/2014 ዓ.ም ይሆናል።

ለመሆኑ አፍሪካ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የሴቶች ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ እንታዘጋጅ ካደረጉት መካከል አንዷ የሆነችው መስከረም ታደሰ ማናት ?👇

ያንብቡ :- https://bbc.in/30ALR5l

#BbcAmharic

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ማንችስተር ሲቲ ተጫዋቹ በ ኮቪድ ተያዘ !

ቤልጅዬማዊው የ ማንችስተር ሲቲ የመሐል ሜዳ ተጫዋች ኬቨን ዴብሮይነ በ ኮቪድ መያዙ ይፋ ተደርጓል ።

ይህንንም ተከትሎ ማንችስተር ሲቲ በ ሊጉ እሁድ ከ ኤቨርተን እንዲሁም በ ሻምፒየንስ ሊግ ከ ፒኤስጂ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ የሚያመልጠው ይሆናል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጋሪዝ ቤል ተቃውሞ አጋጠመው !

የ ሪያል ማድሪዱ የ መስመር ተጫዋች ጋሪዝ ቤል በ ክለቡ ጥቂት ደጋፊዎች በዛሬው ዕለት ተቃውሞ እንደገጠመው ተገልጿል ።

ጋሪዝ ቤል ከክለቡ የልምምድ ማዕከል ቫልዴባስ በሚወጣበት ወቅት ደጋፊዎች አፀያፊ ስድቦችን ሲሰነዝሩበት ተስተውሏል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
" አርሴናል ትልቅ ተጨዋቾች ያሉት ትልቅ ክለብ ነው "

መድፈኞቹን በ ክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ከተቀላቀሉ ተጫዋቾች መካከል አንደኛው የሆነው ኑኖ ታቫሬስ በወቅታዊ የ ክለቡ ሁኔታ ከ እንግሊዝ መገናኛ ብዙሀን ጋር ቆይታ አድርጓል ።

ባደረገው ቆይታም " አርሴናል ትልቅ ተጨዋቾች ያሉት ትልቅ ክለብ ነው ፣ ጨዋታዎችን ማሸነፍ ለእኛ የተለመደ ነው ፣ ሰዎች ለምን በጣም እንደሚገረሙ አላውቅም " ሲል በሰጠው አስተያየት ተደምጧል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ዩራጋይ አሰልጣኟን አሰናበተች !

የ ደቡብ አሜሪካዋ ሀገር ዩራጋይ ያለፉትን አስራ አምስት አመታት ብሄራዊ ቡድኑን ያሰለጠኑትን ኦስካር ታባሬዝን ማሰናበታቸው ይፋ አድርገዋል ።

ዩራጋይ ለ ኳታሩ የአለም ዋንጫ ለማለፍ አጣብቂኝ ውስጥ ሲገኙ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠው ይገኛሉ ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ተጠባቂ የዛሬ መርሐ ግብሮች !

9:30 ሌስተር ሲቲ ከ ቼልሲ

12:00 ዋትፎርድ ከ ማንችስተር ዩናይትድ

1:00 ፒኤስጂ ከ ናንትስ

2:00 ላዚዮ ከ ጁቬንቱስ

2:30 ሊቨርፑል ከ አርሴናል

5:00 ባርሴሎና ከ እስፓኞል

@tikvahethsport @kidusyoftahe
" ሳላህ ታዳጊ ተጫዋች ስለሆንኩኝ ላያውቀኝ ይችላል "

የመድፈኞቹ የግራ መስመር ተከላካይ ኑኖ ታቫሬዝ ከዛሬው ተጠባቂ ጨዋታ አስቀድሞ በሰጠው አስተያየት በሜዳ ላይ ለማሸነፍ እንደሚጫወቱ ተናግሯል ።

ታቫሬዝ ሲናገር " እኛ ጥሩ ቡድን አለን ፤ በተመሳሳይ ሊቨርፑልም ጥሩ ቡድን ነው ፣ በሜዳ ላይ የምንችለውን ሁሉ ማድረግ ይኖርብናል " ።

ታቫሬዝ አክሎም ስለ ግብፃዊ ኮከብ ሞሀመድ ሳላህ ሀሳቡን ሲሰጥ " ሳላህ ታዳጊ ስለሆንኩኝ ላያውቀኝ ይችላል " ሲል ከ ጋዜጠኞች ጋር የነበረውን ቆይታ አገባዷል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe