TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.7K photos
1.48K videos
5 files
3.41K links
加入频道
የ እረፍት ሰዓት ውጤት

ማንችስተር ዩናይትድ 0 - 0 ቪያሪያል

ጁቬንቱስ 0 - 0 ቼልሲ

ባየር ሙኒክ 2 - 0 ዲናሞ ኬይቭ
ሊዋንዶውስኪ

ቤንፊካ 1 - 0 ባርሴሎና
ኑኔዝ

ሳልዝበርግ 1 - 0 ሊል
አድዬሚ

ዎልፍስበርግ 0 - 0 ሲቪያ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የ አውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውጤቶች እና መረጃዎች !

• ክርስቲያኖ ሮናልዶ 178 ጨዋታዎችን በ ውድድሩ በ ማድረግ ቀዳሚው ተጫዋች ሲሆን 136ኛ ጎሉን አስቆጥሯል ።

• ባርሴሎና በ ምድባቸው ያደረጉትን ጨዋታዎች መሸነፋቸውን ተከትሎ በ ምድቡ የ መጨረሻ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል ።

• ሮበርት ሊዋንዶውስኪ በ ሙኒክ ባደረጋቸው ሰባ የ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታው #ስልሳ ጎሎችን ከ መረብ ማዋሀድ ችሏል ።

• አሌክስ ቴሌስ ለ ዩናይትድ ግብ ማስቆጠር የቻለ ሰባተኛው ብራዚላዊ ተጫዋች ሆኗል ።

• የ ቼልሲው የ መሐል ሜዳ ተጫዋች ጆርጂንሆ 150ኛ ጨዋታውን ለ ክለቡ አድርጓል ።

• አሌክስ ቴሌስ ለ ቀያይ ሴጣኖቹ የ መጀመሪያ ግቡን ማስቆጠር ችሏል ።

• ሊዋንዶውስኪ በ አልያንዝ አሬና ባደረጋቸው ያለፉት አስራ አራት ጨዋታዎች ሀያ ሰባት ጎሎችን አስቆጥሯል ።

• ብሩኖ ፈርናንዴዝ በ አውሮፓ መድረክ ለ ዩናይትድ ባደረጋቸው ሀያ ሁለት ጨዋታዎች አስራ ሁለት ጎሎችን አስቆጥሮ ሰባት ለ ግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል ።

• ባርሴሎና ተከታታይ ሽንፈት በ ምድብ ጨዋታዎች ሲያስተናግዱ ከ 21 ዓመታት በኋላ ነው ።

* የ ሙሉ ሰዓት ውጤቶች በ ምስሉ ላይ ተገልጿል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የ ሻምፒየንስ ሊግ የ ሳምንቱ ምርጥ ተጫዋች !

የ አውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የ ምድብ ሁለተኛ ጨዋታዎች መደረጋቸውን ተከትሎ የ ሳምንቱ ምርጥ ተጫዋች እጩዎች ታውቀዋል ።

በዚህም መሰረት ሊሮይ ሳኔ ፣ ዳርዊን ኑኔዝ ፣ ሚላን ስክሪናር እና አትናሲያዲስ በ ሳምንቱ ምርጥ ተጫዋች እጩ ውስጥ ተካተዋል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
" ይሄ ስራዬ ነው "

ፖርቹጋላዊው ኮከብ ትላንት ምሽት በ ጭማሪ ደቂቃ ግብ በ ማግባት ማንችስተር ዩናይትዶች በ ምድቡ የ መጨረሻ ደረጃ ላይ እንዳይቀመጡ ቁልፍ ሚና ተጫውቷል ።

ሮናልዶ ከ ጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ ስለ ግቧ ሲጠይቅ " ይሄ ስራዬ ነው " በማለት ሀሳቡን ገልጿል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሮናልድ ኩማን እና ባርሴሎና ልዩነታቸው እየሰፋ ነው !

የ ካታላኑ ክለብ በ ውጤት ቀውስ ውስጥ ሲገኙ ከ ሀያ አንድ ዓመታት በኋላ በ አውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ምድብ ጨዋታ ተከታታይ ሽንፈት ገጥሟቸዋል ።

ሮናልድ ኩማን ከ ምሽቱ ጨዋታ በኋላ ሲናገሩ " የ ክለቡ ተጫዋቾች ሙሉ ለ ሙሉ ከ እኔ ጎን ናቸው ፣ የ ክለቡን ግን እውነት ለ መናገር አላውቅም " ሲሉ ኮማን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#AddisAbabaCityCup

15ኛው የ አዲስ አበባ ሲቲ ካፕ ዋንጫ የ ምድብ ሁለት ሁለተኛ ጨዋታዎች ዛሬ ቀጥለው የሚካሄዱ ይሆናል ።

ባህር ዳር ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ድል የሚቀናቸው ከሆነ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸውን ያረጋግጣሉ ።

8:00 ባህር ዳር ከተማ ከ ፋሲል ከነማ

10:00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ አዳማ ከተማ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#AddisAbabaCityCup

በ ትላንትናው ዕለት ከተካሄዱ የ አዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ጨዋታዎች የተወሰዱ ምስሎችን ይመልከቱ ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
" ፈታኝ ሁኔታ ላይ ነን "

የ ካታላኑን ክለብ የ መሐል ሜዳ ተጫዋች ሰርጅዮ ቡስኬት ክለቡ ስላለበት ወቅታዊ ሁኔታ ሀሳቡን አካፍሏል ።

ሰርጅዮ ቡስኬት ይናገራል " በ እግር ኳስ ዓለም ቀላሉ ነገር አሰልጣኝን ማባረር ነው ፣ እኛ ግን ሁላችንም ኃላፊነት አለብን አሁን ፈታኝ ሁኔታ ላይ ነን እውነታው ይህ ነው " ሲል ተደምጧል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የ ዩሮፓ ሊግ የ ምድቦቹ ሁለተኛ የ ጨዋታ መርሐ ግብሮች በ ዛሬው ዕለት መካሄዳቸውን ይቀጥላሉ ።

ሙሉ የ ዛሬ መርሐ ግብሮች በ ምስሉ ላይ ተገልጿል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ያልተሸነፉት ክለቦች !

የ አውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የ ምድብ ሁለተኛ ጨዋታዎች በ ትላንትናው ዕለት ምሽት በተካሄዱ ጨዋታዎች ተጠናቀዋል ።

ይህንንም ተከትሎ ስድስት ክለቦች ብቻ እስከ አሁን #አንድም ሽንፈት ያላስተናገዱ ( ሙሉ ሶስት ነጥብ ያገኙ ) ክለቦች ሲሆኑ ሼሪፍ ፣ አያክስ ፣ ባየር ሙኒክ ፣ ዶርትመንድ ፣ ሊቨርፑል እና ጁቬንቱስ ናቸው ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የ ፕርሚየር ሊጉ የወሩ ምርጥ ተጫዋች !

የ እንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ ወርሀ መስከረም ምርጥ ተጫዋች እጩዎች ይፋ ተደርገዋል ።

ጇ ካንሴሎ ፣ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ፣ አንቶኒ ሩዲገር ፣ ሴንት ማክሲም ፣ሞሀመድ ሳላህ እና ሳር በ ወሩ ምርጥ ተጫዋችነት እጩ ውስጥ ተካተዋል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#Ethiopia🇪🇹

ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ፕሬዝዳንት ሆነች

ዶ/ር ፍትህ ወልደ ሰንበት የመጀመሪያ ኢትዮጵያዊ የ አፍሪካ እጅ ኳስ ኮንፌዴሬሽን የ ዞን አምስት ፕሬዝደንት ሆነው ተሾሙ።

የ ኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፌዴሬሽንን በ ስኬት ላለፋት 5 ዓመታት የመሩት ዶ/ር ፍትህ በ ዛሬው ዕለት በ በይነ መረብ በተደረገ የ ምስራቅ አፍሪካ ዞን 5 የ ምርጫ ኮንግረስ ስብሰባ ላይ ነው የኡጋንዳዎን እጩ ስድስት ለ ሶስት በሆነ ድምፅ በ በላይነት የዞን አምስት ፕሬዝደንት አድርጎ መርጦቸዋል።

ላለፋት ሶስት አመታት ዞኑን ሲመሩ የቆዩት የ ኡጋንዳዋ እጩ ፕሬዝደንት ወ/ሮ ሺላ ሪቻርድ ነበሩ።

#Photo Credited - Ethiopian Handball Federation

@tikvahethsport @kidusyoftahe