TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.6K videos
216 files
4.35K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል⬆️በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከአንድ የ33 ዓመት ወጣት በቀዶ ህክምና 122 ሚስማሮች፣ አንድ መርፌ ቁልፍ፣ ሁለት መርፌ፣ ሁለት ስትኪና ሁለት ስባሪ ብርጭቆዎች #መውጣታቸው ተገለፀ።

ለ10 ዓመታት የአዕምሮ ህመምተኛ የነበረ ወጣቱ ለስምንት ዓመታት መድሃኒት እየወሰደ መቆየቱ ተነግሯል።

በኋላም መድሃኒቱን በመቋረጥ ለሁለት ዓመት ፀበል ሲከታተል መቆየቱን  ቤተሰቦቹ አስታውቀዋል።

በቅርቡ ግን የወጣቱ ሆድ በማበጡና በአጋጠመው ህመም  ምክንያት ወደ ሆስፒታሉ አቅንቷል።

በዚህ  ወቅት በዶክተሮች በተደረገ ምርመራ ባልተለመደ ሁኔታ በሆዱ ውስጥ ሚስማሮችን  አግኝተዋል።

2 ሰዓት 30 ደቂቃ በፈጀው የቆዶ ህክምና  122 ሚስማሮች፣ አንድ መርፌ ቁልፍ፣ ሁለት መርፌ፣ ሁለት ስትኪና ሁለት ስባሪ ብርጭቆዎችን አውጥተዋል።

ቆዶ ህክምናውን የመሩት  የሆስፒታሉ የቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ዶክተር ዳዊት ተአረ  እንደገለፁት፥ ቀዶ ህክምናው በተሳካ ሁኔታ ተጠናቆ ወጣቱ በአሁን ወቅት በጥሩ ሁኔታ በማገገሚያ ክፍል ውስጥ ይገኛል።

ምንጭ፦ ፋና
@tsegabwolde @tikvahethiopia