TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.13K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
🔊 #የጤናባለሙያዎችድምጽ 🔴 “ የጸጥታ አካላት ሆስፒታል ድረስ በመምጣት ድብደባ ፈጽመዋል፣ ዘጠኝ ሠራተኞችና የማኔጅመንት አባላትን አስረዋል ” - የሆስፒታሉ ሠራተኞች ➡️ “ እነርሱ ጋ ብቻ አይደለም ያልተከፈለው፤ ከ2000 በላይ ሠራተኞች እንደ ዞን ያልተከፈላቸው አሉ ”  - የጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ከተማ፣ የይርጋጨፌ ሆስፒታል ጤና ባለሙያዎችና የአስተዳደር ባለሙያዎች “ በጸጥታ…
#Update

🔴 “ ወደ አራት ጤና ባለሙያዎች ገና አልተፈቱም። የጠየቁት መብታቸውን ስለሆነ ሊፈቱ ይገባል ” - ቤተሰቦች

➡️ “ ሰልፍ ላይ ስለተገኙ ብቻ ነው የተያዙት ” - ጤና ባለሙያ


የአራት ወራት አዲሱ ደወመዝ ክፍያ ስላልተፈጸመላቸው የሥራ ማቆም አድማ በመምታታቸው ከታሰሩት የይርጋጨፌ ሆስፒታል ጤና ባለሙያዎች መካከል አራቱ እንዳልተፈቱ ቤተሰቦቻቸውና የጤና ባለሙያዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

መጀመሪያ የታሰሩት ዘጠኝ እንደነበሩ ሠራተኞቹ ከቀናት በፊት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ከዚያ በኋላ እስራቱ ቀጥሎ በአጠቃላይ 12 ሰዎች ታስረው እንደነበርና አራቱ እንዳልተፈቱ ነግረውናል።

የታሳሪ ቤተሰቦችና ጤና ባለሙያዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?

አንድ ጤና ባለሙያ በሰጡን ቃል፤ “ የተፈቱና ሌሎቹም በሥራ ገበታ ላይ ናቸው። የነዚህ የአራቱ አለመፈታት ግን እስካሁን ምስጢር ሆኖብናል። ሰልፍ ላይ ስለተገኙ ብቻ ነው የታሰሩት ” ሲሉ ተናግረዋል።

የታሳሪ ቤተሰቦች በበኩላቸው “ አራት ጤና ባለሙያዎች ገና አልተፈቱም። የጠየቁት መብታቸውን ስለሆነ ሊፈቱ ይገባል ” ብለዋል።

“ ጥያቄው የሆስፒታሉ አካላት ሁሉ ነው። የፓለቲካ ጉዳይ የሌለበት የደመወዝ ጥያቄም ነው። ከደመወዝ ይከፈለን ውጪ ያነሱት ጥያቄ የለሞ ” ሲሉም ሞግተዋል።

አንዲት የታሳሪ ቤተሰብ በሰጡን ቃል፣ ባለቤታቸው ከታሰሩ ቀናት እንዳስቆጠሩ፣ እስካሁንም እንዳልተፈቱ፣ ያሉበትን ሁኔታም እንደማያውቁ ገልጸዋል።

ሌላኛው የታሳሪዋ የቅርብ ሰው የ10 ወር ጨቅላ ህፃን ያላት ጤና ባለሙያ እንደታሰረች ገልጸው፣ በዋስ እንደትለቀቅ እንኳ ቢሞከር ፈቃደኛ አካል አለመኖሩን ጠቁመዋል።

“ አጥቢ ከመሆኗ አንፃር ቀነ ገደብ ተጠይቆ ነበር። ፍርድ ቤት ዋስትና እንዲሰጣት ውሳኔ ቢያስተላልፍም እንዳትወጣ በፓሊስ ተከልክላለች ” ሲሉ ነው የወቀሱት።

የታሳሪ ቤተሰቦች፣ የታሰሩት የጤና ባለሙያዎች እንደሆኑ፣ ብዙ የህክምና ተገልጋዮች መጉላላታቸውም ከግምት ሊገባ እንደሚገባ አሳስበው፣ በፍጥነት እንዲፈቱ ጠይቀዋል።

የታሰሩት ለምን እንዳልተፈቱ ምላሽ ለማግኘት የጸጥታ አካላትን ለማካተት የተደረገው መከራ ስልክ ለማንሳት ፈቃደኞች ባለሆናቸው ለጊዜው አልተሳካም።

የጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ ከዚህ ቀደም  ጠይቀነው፣ በሌሎች ሆስፒታሎችም ጭምር ከ2000 በላይ ሠራተኞች ክፍያው እንዳልተፈጸመላቸው፣ የታሰሩትን ለማስፈታትም እየተሰራ መሆኑን ገልጸው ነበር።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ አርብቶአደሮች ተፈናቅለዋል " - የዳሰነች ወረዳ አስተዳደር 🚨" አሁንም ከኬንያ ቱርካና ግዛት በኩል ዛቻዎች ስላሉ ስጋት ዉስጥ ነን ጥበቃና ከለላ ይደረግልን " - አርብቶአደሮች በኢትዮጵያና ኬንያ ድንበር ደቡብ ኦሞ ዳሰነች ወረዳና በኬንያ ቱርካና ግዛት አዋሳኝ አከባቢ ባለፉት ሁለት ቀናት በአሳ ማስገሪያ መረብና ጀልባ ስርቆቶች እንደተቀሰቀሰ በተነገረዉ ግጭት የበርካቶች…
" ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እየተመለሱ ነዉ ፤ የአስክሬን ፍለጋዉም ተጠናክሮ ቀጥሏል " - የዳሰነች ወረዳ አስተዳደር

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ እና በሰሜን ኬንያ ቱርካና የድንበር አከባቢ ተከስቶ በነበረዉ ግጭት ምክንያት ስየስ ከተባለ የዳሰነች መንደር ተፈናቅለዉ የነበሩ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ አርብቶአደሮች ወደ ቀያቸዉ መመለስ መጀመራቸዉን የዳሰነች ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ሀቴ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

በቀጠናዉ በአሳ ማስገሪያ መረብና ጀልባ ስርቆቶች መነሻ እንደተቀሰቀሰ በተገለፀዉ ግጭት ከሁለቱም ሀገሮች ከ30 በላይ አርብቶአደሮች ሕይወት መጥፋቱን መዘገባችን አይዘነጋም።

ግጭቱን ተከትሎም ኬንያን ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስናት የቱርካና ሀይቅ ሰሜናዊ ጠረፍ ላለፉት አምስት ቀናት ከእንቅስቃሴ ዉጪ ሲሆን ከዳሰነች ወረዳ ስየስ መንደር በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ አርብቶ አደሮች በአቅራቢያቸዉ ወደሚትገኘዉ ሌላ መንደር ተፈናቅለዉ ነበር።

በትናትዉ ዕለት የዳሰነችና የቱርካና አከባቢ አስተዳደሮች ባሉበት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ እና የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር የተመራ ልዑክ ከኢትዮጵያ በኩል በኬንያ የቱርካና ካውንቲ የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነርና የአከባበው የፓርላማ ተወካይ የተመራ ልዑክ በሁለቱ ሀገራት የድንበር አከባቢ ተፈጠሮ የነበረዉን ግጭት በፍጥነት ለመፍታትና አከባቢውን ወደነበረበት ሰላም ለመመለስ መነጋገራቸዉን ተከትሎ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸዉ የመመለስ እየተሰራ እንደሆነ አቶ ታደለ ሀቶ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ከዚሁ ጎን ለጎን በሀይቅ ዉስጥ የጠፉ አስከሬኖች የማፈላለጉ ስራም ተጠናክሮ መቀጠሉን ያነሱት አቶ ታደለ በሁለቱም ወገን የተወሰዱ ንብረቶችን የማስመለስና በአከባቢዉ ጠንካራ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ሥራዎችን ተጠናክረዉ በሚቀጥሉበት ዙሪያ ዉይይት ማድረጋቸዉን አስታዉቀዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
" ከየካቲት 24 በኋላ የፋይዳ መታወቂያ የሌለው ደንበኛ የኢትዮ ጅቡቲ የባቡር ትኬት መቁረጥ አይችልም " - የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር አክስዮን ማህበር

የኢትዮ ጅቡቲ የባቡር መንገድ አክስዮን ማህበር ለመንገደኞች የጉዞ ትኬት የሚያገኙበትን መንገድ ከሰኞ የካቲት 17/2017 ዓ/ም ጀምሮ  ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይዝ ማድረጉን ገልጿል።

ከሁለት ቀን በፊት የተጀመረውን በኦንላይን ትኬት የመቁረጥ ሂደት አገልግሎቱን ለማግኘት የፋይዳ መታወቂያ ግዴታ መደረጉን የኢትዮጵያ ጅቡቲ የባቡር መንገድ አክስዮን ማህበር የኮምዩኒኬሽን ባለሞያ የሆኑት ወ/ሮ እስራኤል ወልደ መስቀል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ወ/ሮ እስራኤል " ማስታወቂያዎችን ስንሰራ የቆየን በመሆኑ የፋይዳ መታወቂያ ግዴታ ነው ነገር ግን ይሄንን ሳምንት ልዩ በሆነ መንገድ እና ሰውም የአጠቃቀም ጉድለት ስላለ የጉዞ ትኬት እየቆረጥን እንገኛለን ከሚቀጥለው ሳምንት ሰኞ በኃላ ግን ያለ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የባቡሩን ትኬት ማግኘት አይቻልም " ብለዋል።

ክፍያው የሚፈጸመው በቴሌ ብር ሲሆን አገልግሎቱን ለማግኘት ለሃገር ውስጥ ተጠቃሚዎች የፋይዳ የምዝገባ ቁጥራቸውን ኢትዮጵያዊ ላልሆኑ ተጠቃሚዎች ደግሞ ፓስፖርታቸውን በመጠቀም ትኬት ማግኘት እንደሚችሉ አሳውቀዋል።

ባለሞያዋ በትኬት ዋጋ ላይ ምንም አይነት ጭማሪ አለመኖሩን አንስተው በነባሩ ዋጋ ዲጂታላይዝ ብቻ መደረጉን ጠቁመዋል።

ከዚህ ቀደም አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ ፉሪ የሚገኙ የትኬት ሽያጭ ቢሮዎች አሰራሩ ዲጂታላይዝ ስለሆነ የመንገደኞችን የአገልግሎት ትኬት የመቁረጥ ስራ እንደማይሰሩ ወ/ሮ እስራኤል ገልጸዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ ፦ ከሌሊቱ 10:35 ሰዓት ላይ በአዲስ ከተማ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 7 ሀብተጊዮርጊስ ድልድይ አካባቢ በመኖሪያና ንግድ ቤቶች ላይ የእሳት አደጋ አጋጥሞ እንደነበር የእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር የኮሚሽን አሳውቋል።

የእሳት አደጋው በቁጥጥር ስር ማዋል የተቻለ ሲሆን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ፣ የጸጥታ አካላት የአካባቢዉ ማህበረሰብ እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ርብርብ ማድረጋቸውን ገልጿል።

ኮሚሽኑ " አደጋ የደረሰበት ቦታና አካባቢ በከተማ ደረጃ ለእሳት አደጋ ተጋላጭ ተብለዉ ከተለዩ የመኖሪያና የንግድ አካባቢዎች አንዱ ነው " ያለ ሲሆን " ቤቶቹ የተገነቡበት ግብአት የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታዉ እንዲሁም የአደጋ ጊዜ ተሽከርካሪዎችን አለማስገባቱ ተደማምሮ የእሳት አደጋዉ እንዲሰፋ ምክንያት ሆኗል " ብሏል።

በእሳት አደጋዉ በሰዉና በንብረት ላይ የደረሰዉን ጉዳት እንዲሁም የአደጋዉ መንስዔ ተጣርቶ እንደሚገለጽ አመልክቷል።

@tikvahethiopia
#ዛሬ

" ዝክረ አድዋ ኢትዮጵያዊነት "

“ ዝክረ አድዋ ኢትዮጵያዊነት ” የተሰኘ ልዩ የኪነ-ጥበብ መርሃ ግብር፣ ዛሬ አርብ የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ  በአድዋ ሙዚየም ይካሄዳል፡፡ 

የመርሃ ግብሩ አዘጋጅ አብርሃም  ግዛው  ኢንተርቴይንመንት ሲሆን በመርሃ ግብሩ ላይ ‹‹ኢትዮጵያዊነት ዝክረ አድዋ” የተሰኘ  ጥናታዊ ፅሁፍና ዲስኩር በምሁራን ይቀርባል ብሏል።

የግጥም ምሽትና የስታንዳፕ  ኮሜዲም እንደተሰናዳ ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም ፖለቲከኞች በሰላምና አንድነት ዙሪያ አነቃቂ ንግግር፣ እንዲሁም ጀግኖች አርበኞች ሽለላና ፉከራ በባህላዊ ባንድ ታጅበው  ያቀርባሉ ተብሏል።
  
በመርሃ ግብሩ ፦
- ደራሲ፣ ገጣሚና ፀሀፌ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ፣
- አምባሣደር ዲና ሙፍቲ፣
- ዶ/ር ወዳጄነህ ማህረነ፣
- ኡስታዝ አቡበከር አህመድ፣
- መምህር ዲያቆን ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል፣
- ጋዜጠኛና ደራሲ ጥበቡ በለጠ፣
- መጋቢ ቸርነት በላይነህ ፣
- አርቲስት ተስፋዬ ሲማ፣
- አርቲስት አዳነች ወ/ገብርኤልና ሌሎችም እንደሚሳተፉ  ተነግሯል፡፡

የመግቢያ ዋጋ መደበኛ 300 ብር፣ VIP ደግሞ 500 ብር እንደሆነ አዘጋጆቹ ጠቁመዋል። ትኬቱን በቴሌ ብር፣ በጃፋር ቤተ-መፅሐፍት፣ በ2 ሺህ ሐበሻ የባህል ምግብ አዳራሽ እንደሚገኝ አብርሃም  ግዛው  ኢንተርቴንመንት ጠቁሟል፡፡
TIKVAH-ETHIOPIA
" ዜለንስኪ ጥሩ የነበረበት ብቸኛው ነገር ባይደንን ማታለል ብቻ ነበር " - ፕሬዜዳንት ትራምፕ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪን " ትሁትና ውጤታማ ኮሜዲያን ነው " ሲሉ ወረፏቸው። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትሩዝ በተባለው የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው የዩክሬኑን ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪን " ያለ ምርጫ የተቀመጠ አምባገነን ነው " ብለዋል። ትራምፕ…
" ይህን ተናግሬያለሁ ብዬ ማመን ይከብደኛል፤ ዘሌንስኪን በጣም ደፋር መሪ ነው " - ዶናልድ ትራምፕ

አወዛጋቢው የአሜሪካው ፕሬዝዳነት ዶናልድ ትራምፕ ከዚህ ቀደም " አምባገነን " ሲሉ የጠሯቸውን የዩክሬኑን ፕሬዜዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪን " ጀግና መሪ ነው " ሲሉ አሞካሿቸው።

ፕሬዝዳት ትራምፕ በዛሬው ዕለት ከዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

ትራምፕ አስቀድመው በዋይት ኃውስ በሰጡት አስተያየት፤ " ለቮሊድሚር ዘለንስኪ ትልቅ ክብር አለኝ " ብለዋል።

በቅርቡ ዘለንስኪን " አምባገነን " ብለው በመጥራታቸው ይቅርታ እንደሚጠይቁ ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ትራምፕ " ይህን ተናግሬያለሁ ብዬ ማመን ይከብደኛል፤ ዘሌንስኪን በጣም ደፋር መሪ " ነው ሲሉ አሞካሽተዋል።

በዛሬው እለት ከዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘሌንስኪ ጥሩ ውይይት እንደሚኖራቸው የገመቱት ትራምፕ፤ በዩክሬን ሰላም ለማምጣት የሚደረገው ጥረት በጥሩ ሁኔታ እና በፍጥነት እየሄደ መሆኑን አስታውቀዋል።

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር ለመነጋገር እና በዩክሬን ውድ ማዕድናት ዙሪያ ስምምነት ለመፈራረም ትናንት ምሽት ወደ አሜሪካ አቅንተዋል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባሳለፍነው ሳምንት የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪን " ትሁትና ውጤታማ ኮሜዲያን እንዲሁም ያለ ምርጫ የተቀመጠ አምባገነን ነው " ማለታቸው ይታወሳል።

" ዘለንስኪ አሜሪካን 350 ቢሊየን ዶላር በማስውጣት መጀመር ያልነበረባቸው እና የማያሸንፉት ጦርነት ውስጥ ገብተዋል " ብለዋቸው ነበር።

" ዜለንስኪ ጥሩ የነበረበት ብቸኛው ነገር ባይደንን ማታለል ብቻ ነበር " ሲሉም ነበር የገለጹት።

ትራምፕ " ያለ ምርጫ የተቀመጠ አምባገነን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በፍጥነት መንቀሳቀስ ይኖርበታል፤ ካልሆነ ግን የሚያተርፈው ሀገር አይኖርም " ብለውም ነበር።
#AlAin #BBC

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ በመጪው ዓመት / 2018 የትምህርት ዘመን ተማሪዎች ለትምህርት ለመመዝገብ ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ወይንም ፋይዳ መያዝ አስገዳጅ ሆነባቸው፡፡

የከተማው ትምህርት ቢሮ የልደት እና የፋይዳ ምዝገባ የ2018 ዓ.ም የተማሪዎች የትምህርት ቤት ምዝገባ ቅድመ ሁኔታ እንደሆነ ይፋ አድርጓል።

ተማሪዎች የፋይዳ ምዝገባ አንዲያካሂዱ በዘመቻ መልክ ለመሰራት የታሰበ ሲሆን እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በላይ የሆናቸው ህፃናትን  ምዘገባ በዘመቻ እንደሚከናወን መነገሩን ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" በነገው ዕለት አንድ ቡድን ወደ ስፍራው ያቀናል " - አምባሳደር ነብያት ጌታቸው

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግለጫ ፤ በማይናማር ታግተው የነበሩ 246 ዜጎችን በቀጣይ ሳምንት ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን ነው አሳውቀዋል።

" በማይናማር በከፍተኛ ችግር ውስጥ ያሉ ዜጎችን ለማስወጣት በቶኪዮ እና በኒውዴሊ ባሉ ኤምባሲዎች በኩል ሥራዎች እየተሠሩ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" አሁን ላይ 246 ኢትዮጵያዊያን ከማይናማር ወጥተው ወደ ታይላንድ ደርሰዋል " ሲሉ ጠቅሰዋል።

" እነሱን ለመርዳትና የማጣራት ሥራ ለመሥራት በነገው ዕለት አንድ ቡድን ወደ ስፍራው ያቀናል " ብለዋል።

በተመሳሳይ በመካከለኛው ምስራቅ በችግር ውስጥ ያሉ ዜጎችን ለማስወጣት የሚደረገው ጥረት ቀጣይነት እንዳለውም ጠቁመዋል።
#ኤፍኤምሲ

@tikvahethiopia