TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray ትናንተ የካቲት 12 /2017 ዓ.ም በትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ሰሓርቲ ወረዳ አዲስ አለም ቀበሌ በነዋሪዎችና በአከባቢው በሚገኘው የትግራይ ኃይል አባላት መካከል ግጭት ተከስተዋል። በግጭቱ ምክንያት በ20 የቀበሌው ነዋሪዎችና ቁጥራቸው ባልታወቀ የትግራይ ኃይል አባላት ላይ ጉዳት ደርሷል። ያጋጠመ ሞት የለም። ግጭቱ እንዴት እና በምን ምክንያት አጋጠመ ? በአዲስ አለም ቀበሌ ሁለት…
#UPDATE
" ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ ወደ ማንወጣው ቀውስ እንደምንገባ የቅርብም የሩቁም ሊገነዘበው ይገባል " - የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር
" ሃይል በመጠቀም የመንግስት መዋቅር ለማፍረስ የሚደረግ ህገ-ወጥ እርምጃ ተቀባይነት የለውም " አለ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ።
ጊዚያዊ አስተዳደሩ ዛሬ የካቲት 13 /2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ፤ በትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ሰሓርቲ ወረዳ አዲስ አለም ቀበሌ ገበሬ ማህበር የትግራይ ኃይል አባላት በነዋሪ አርሶ አደሮች ላይ ያደረሱትን ጥቃት አውግዟል።
" የተወሰኑ የትግራይ ሰራዊት አመራሮች የጊዚያዊ አስተዳደሩ መዋቅር ለማፍረስ ሲንቀሳቀሱ እየታዘብን ነው " ያለው መግለጫው " በሰሓርቲ ወረዳ የተከሰተው አሳዛኝ ተግባር እንደ አንድ ማሳያ መውሰድ ይቻላል " ብሏል።
" ሰራዊቱ የህዝብ ህልውና ለመጠበቅ እንጂ የአንድ ቡድን የስልጣን ጥማት ለማርካት የተሰለፈ አይደለም " ያለው ጊዚያዊ አስተዳደሩ " ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ ወደ ማንወጣው ቀውስ እንደምንገባ የቅርብም የሩቁም ሊገነዘበው ይገባል " ሲል አስጠንቅቋል።
" ማንኛውም የህግ ወይም የአስራር ክፍተት ሲኖር የሚሊሻና የፓሊስ ሃይል ከህዝባቸው በመተባበር የሚፈቱት እና የሚያርሙት እንጂ ሰራዊት ወደ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ማሰማራት የሚያስገድድ ሁኔታ ፈፅሞ እንደሌለ የለም " ሲል ገልጿል።
" ይህንን ህገ-ወጥ አካሄድ የሚያበረታቱ እና የሚያግዙ ፓለቲከኞች እና የሰራዊት አመራሮች አደብ እንዲገዙ " ሲልም አስጠንቅቋል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia