TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.13K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray በእንዳስላሴ ሽረ ከተማ በህዝብ መዝናኛ ስፍራ በተጣለ የእጅ ቦምብ 10 ሰዎች ከባድ እና ቀላል ጉደት ደረሰባቸው። የሰው ህይወት አለማለፉን ለመረዳት ተችሏል። የቦምብ ጥቃቱ አድራሾች እና ግብረ አበሮቻቸው ለመያዝ የተጠናከረ ክትትል እና ምርመራ እያደረግኩ ነው ብሏል ፖሊስ። ጥቃቱ መቼና ? የት ? እንዴት አጋጠመ ? ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ፤ በስፍራው የነበሩ የአይን እማኞችን…
" 4 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል " - ፖሊስ

በቦንብ ፍንዳታ የተጠረጠሩ 4 ሰዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉ ፓሊስ አስታውቋል።

ትናንት የካቲት 3/2017 ዓ.ም በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን እንዳስላሰ-ሽረ ከተማ በአንድ የህዝብ መዝናኛ ስፍራ በተጣለ ቦምብ በ13 ሰዎች ላይ ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሷል።

ሞት አላጋጠመም።

አደጋው ከተከሰተበት ጀምሮ ከክልል እስከ ወረዳ የተቀናጀ የወንጀል አጣሪ ቡድን አቋቋሞ መንቀሳቀስ መጀመሩ የጠቀሰው ፓሊስ ፤ ከፍነዳታው ጋር በተያያየ 4 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉ አስታውቀዋል። 

የቢንጎ ማጫወቻ መሆኑ በተጠቀሰው የህዝብ መዝናኛ ማእከሉ ሰዎች በብዛት እንደሚሰባሰቡበት የጠቀሰው ፓሊስ ባለፈው ጥር ወር በተመሳሳይ ቦንብ ተጥሎ ሳይፈነዳ በመቅረቱ አደጋ አላደረሰም ብሏል።

ፓሊስ " ጥቃቱን አድርሰዋል " በማለት በጠረጠራቸው ሰዎች ላይ ውጤታማ የሆነ የማጣራት በማካሄድ ጉዳዩ ለህዝብ እንደሚያሳውቅ ገልፆ የህዝቡ ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
" 26 ሰዎች ወዲያ ነው ህይወታቸው ያለፈው። ቁጥሩ ሊጨምር ይችላል " - ፖሊስ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ፤ ጉዳያ ቢላ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ26 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ። አደጋው ከሻምቡ ከተማ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በመገልበጡ ነው የተከሰተው፡፡ በደረሰው አደጋ የ26 ወገኖቻችን ሕይወት ወዲያው ሲያልፍ 42 ወገኖቻችን ላይ ደግሞ…
#Update

“ አደጋው በጣም አሰቃቂ ነው። 28 ሰዎች ሞተዋል። 45ቱ ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል ” - የኦሮሚያ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ጉደያ ቢላ ወረዳ ደረሰ በተባለው የትራፊክ አደጋ፣ እስካሁን የሟቾች ቁጥር 28 መድረሱን የኦሮሚያ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ኮሚሽኑ ስለአደጋው መንስኤ በሰጠን ቃል፣ “የፊት ጎማው በሮ ወጥቶ ነው። በፍጥነት ላይም ነበር። የፍሬን ቴክኒክ ችግር እንዳለም መረጃ አለ” ብሏል።

የሟቾች ቁጥር ከ26 ጨመረ እንዴ? ስንል የጠየቅናቸው የክልሉ ፓሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋና መረጃ ክፍል ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር መሰለ አበራ፣ “እስካሁን ባለው መረጃ የሟቾች ቁጥር 28 ነው” ብለዋል።

“ ከባድ አደጋ የደረሰባቸው 45 ሰዎች ናቸው። እነርሱም በባኮ ሆስፒታል ህክምና ላይ ናቸው ” ነው ያሉት።

የደረሰባቸው ጉዳት ቀላል ጭምር ነው ወይስ ከባድ ብቻ ነው ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ ዋና ኢንስፔክተሩ፣ “ 45ቱም ከባድ አደጋ ነው የደረሰባቸው ” ሲሉ መልሰዋል።

“ ከሻምቡ ወደ አዲስ አበባ ተሳፋሪዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ማርሴዲስ ኮድ 3A 12661 መኪና ጉደያ ቢላ ወረዳ ጎንካ ኢጃ ቀበሌ ጅማ ወንዝ የሚባል ልዩ ቦታ ነው የፊት ጎማው በሮ ገደል የገባው ” ሲሉም የአደጋውን መንስኤ ጨምር አስረድተዋል።

አክለው፣ “ የፊት ለፊት ጎማው በሮ ወጥቶ ነው። በፍጥነት ላይም ነበር። የፍሬን ቴክኒክ ችግር እንዳለም መረጃ አለ። ፓሊስ በማጣራት ላይ ይገኛል ” ነው ያሉት።

የተሳፈሩ ሰዎች ስንት ነበሩ ? ጉዳት ሳይደርስባቸው የተረፉ ይኖሩ ይሆን? ስንል ላቀረብነው ጥያቄም፣ “ አሁን ባለው መረጃ 28 ሟች፣ 45 ከባድ ጉዳት አጠቃላይ ሹፌርና ረዳት፣ ተሳፋሪን ጨምሮ ነው። መኪያው ውስጥ የነበሩት እነዚሁ ናቸው ” ብለዋል ዋና ኢንስፔክተሩ።

“ አደጋው የደረሰበት ማርሴዲስ ተሽከርካሪ ስሪቱ በጣም የቆዬ በመሆኑ ለረጅም ርቀት መመደብ አልነበረበትም ” የሚል አስተያዬት ሲሰጥ ተስተውሏል፤ የፓሊስ አስተያዬት ምንድን ነው ? የሚል ተጨማሪ ጥያቄም አቅርበናል። 

ኢንስፔክተሩ፣ “እኛ ይሄ መረጃ አልደረሰንም። መንገድ ትራንስፓርት መረጃውን አይቶ ከመናኸሪያ የሚመድበው ስለሆነ ከትልቁ መናኸሪያ ነው ይሄ ስምሪት የሚሰጠው” ብለዋል።

“የሚመለከተው አካል፣ ፌደራል መንገድ ትራንስፓርት አይቶ ስሞሪት የሚሰጥ ስለሆነ እንደኛ እንዲህ አይነት ችግር ካለ እነርሱም ፍተሻ እንዲያደርጉና እንዲህ አይነት ርቀት ቦታም ባይመደብ ጥሩ ነው” ሲሉም አክለዋል።

የፍጥነትም ሆነ የቴክኒክ ችግር እንዲህ አይነት አደጋዎች እንዳይደገሙ ባስላለፉት መልዕክት፣ “ይሄ አሰቃቂ አደጋ ነው። እንደ ኦሮሚያ የደረሰው ከባድ አደጋ ነው። በድጋሚ እንዳይከሰት ባለ ባለንብረቶችና አሽከርካሪዎች ሳይሰማሩ በፊት የቲክኒክ ችግር ቢመረምሩ” ሲሉ አሳስበዋል።

ዋና ኢንስፔክሩ በምላሻቸው፣ “የቲክኒክ ችግር በጣም ለአደጋ ስለሚያጋልጥ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ነው መልዕክት የማስተላልፈው” ሲሉም አስገንዝበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

አዲስ አበባ በሚከናወነው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እና ሌሎች ተያያዥ ስብሰባዎች ምክንያት ከነገ ማለትም ረቡዕ የካቲት 5/ 2017 ዓ.ም ረፋዱ 4፡00 ጀምሮ እስከ መጪው ሰኞ ማለትም የካቲት 10/2017 ዓ.ም ድረስ :-

1. አረቄ ፋብሪካ አጠገብ የነበረው ተርሚናል ወደ ዲያፍሪክ ሆቴል አካባቢ ፤

2. ዋቢ ሸበሌ ሆቴል አጠገብ የነበረው ተርሚናል ወደ ለገሐር ተርሚናል፤

3. በተለምዶ ጠማማ ፎቅ የሚባለው አካባቢ የነበረው ተርሚናል ወደ ሳር ቤት ድልድይ ስር መዘዋወራቸውን እና ስብሰባዎቹ እንደተጠናቀቁ ወደ ቀድሞ ቦታዎቻቸው እንደሚመለሰ የአዲስ አባባ ከተማ አስታዳደር አሳውቋል።

#AU #ADDISABABA

@tikvahethiopia
በአፖሎ ዲጂታል ባንክ ከአካውንትዎ ገንዘብ ሲልኩ ደቂቃ አይፈጅም።
አሁኑኑ መተግበሪያውን በማውረድ ይጠቀሙ።
ለአንድሮይድ ስልኮች: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.apollo&hl=en&gl=US
ለአፕል ስልኮች: https://apps.apple.com/eg/app/apollo-digital/id1601224628
ለህዋዌ ስልኮች ፡https://appgallery.huawei.com/app/C108966741
TIKVAH-ETHIOPIA
“የተነሳበትን አካባቢ ጉዳት አድርሷል። ግን አሁንም ሙሉ ለሙሉ አልጠፋም” - ባለስልጣኑ በአፋር ክልል ሃላይዳጌ አሰቦት ብሔራዊ ፓርክ ከተነሳ ቀናት ያስቆጠረው ቃጠሎ በቁጥጥር ሥር ባለመዋሉ ለማጥፋት ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ባለስልጣን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ። የተቋሙ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ ናቃቸው ብርሌው በሰጡን ማብራሪያ፣ የእሳት ቃጠሎ በተነሳበት…
#Update

" እሳቱ በቁጥጥር ስር ውሏል " - የኢትዮጵያ የዱር እንሰሳት ጥበቃ ባለስልጣን 

በሃላይደጌ አሰቦት ዕጩ ብሔራዊ ፓርክ ተከስቶ የነበረው የእሳት ቃጠሎ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር እንደዋ ለየኢትዮጵያ የዱር እንሰሳት ጥበቃ ባለስልጣን አሳውቋል።

ላለፉት ሶስት ቀናት በብሔራዊ ፓርኩ ውስጥ ተከስቶ ነበረው የእሳት ቃጠሎ ለመቆጣጠር የኢትዮጵያ የዱር እንሰሳት ጥበቃ ባለስልጣን መ/ ቤቱ  የሃላይደጌ እና የአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ ሠራተኞች፣ የገቢ ራሱ ዞን እና አሚባራ ወረዳ ነዋሪዎችና አመራሮች እንዲሁም የሃላይደጌና አንዲዶ ቀበሌ ነዋሪዎች ርብርብ ማድረጋቸው ተገልጿል።

" እሳቱን ለማጥፋት በተደረገው ርብርብ ትናንት ከሰዓት ጀምሮ በፓርኩ ላይ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር ተችሏል " ሲል ባለስልጣን መ/ቤቱ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እና ተያያዥ ስብሰባዎች እስከሚጠናቀቁ ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ክልክል መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

የመሪዎች ጉባኤ እስከሚጠናቅ ድረስ ባሉ ቀናቶች ውስጥ በየትኛውም የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ፍፁም ክልክል መሆኑን ነው ፖሊስ አሳስቧል።

ትእዛዝ በመተላለፍ ሲንቀሳቀሱ በሚገኙ የሞተር አሽከርካሪዎች ላይ ሆነ ባለ ንብረቶች ላይ እርምጃ እንዳሚወሰድ አስገንዝቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" እያጠፋን በነበርንበት ወቅት የኤሊና እባብ ዝርያዎች ተቃጥለው አግኝተናል። ከ350 እስከ 400 ሄክታር ሳራማ ቦታ ተቃጥሏል ብለን እንገምታለን " - ፓርኩ

በሃላይደጌ አሰቦት እጩ ብሔራዊ ፓርክ ተከስቶ የቆየውና ለቀናት ከቁጥጥር ውጪ ለማድረግ አስቸግሮ የነበረው ቃጠሎ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፓርኩና የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ባለስልጣን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።

ይህን ተከትሎም ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ በአደጋው የደረሰው የጉዳት መጠን ምን ያክል እንደሆነ የጠየቀ ሲሆን፣ እንስሳት መቃጠላቸውንና ከ350 እስከ 400 ሄክታር የሚገመት ሳራማ ቦታ መቃጠሉን ሰምቷል። 

የፓርኩ ኃላፊ አቶ አሕመድ እንድሪስ ምን አሉ ? 

" የካቲት 1/2017 ዓ/ም መንስኤው ባልታወቀ ምክንያት የእሳት ቃጠሎ ተነስቶ ነበር። ትላንት 10 ሰዓት በቁጥጥር ስር ተደርጓል። ዛሬም ከጠዋቱ 11 ሰዓት ጀምረን ጫካ ነበርን ሙሉ በመሉ መጥፋቱን አረጋግጠናል።

ተራማጅ የሆኑና መሮጥ የሚችሉ የዱር እንስሳት ብዙዎቹ አምልጠዋል። ግን መራመድ የማይችሉ፣ አዲስ የተወለዱ የዱር እንስሳት ጉዳት ሊያደርስ ችሏል።

እያጠፋን በነበርንበት ወቅት የኤሊና እባብ ዝርያዎች ተቃጥለው አግኝተናል። ግን የጉዳቱን መጠን ሰርቨይ መሰራት አለበት "  ብለዋል።

የፓርኩ ምን ያክል ክፍል እንደተቃጠለ ታውቋል? ለሚለው ጥያቄ በሰጡን ምላሽ፣ " መለካት ያስፈልጋል። ከ350 እስከ 400 ሄክታር ሳራማ ቦታ ተቃጥሏል ብለን እንገምታለን "  የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

" ደረቃማ ሳር ስላለ በትንሹ ነው የሚቀጣጠለውና በሰው ኃይል ለመቆጣጠር አስቸጋሪ አድርጎት፣ በሰው ኃይል ከመቆጣጠር በላይ ሆኖ ነው በግሬደርና፣ ከእሳቱ ርቆ በሎደር የማስራብ ሥራ የተሰራው” ሲሉ አስታውሰዋል።

ፖርኩ ወደ 244 የአእዋፍ ዝርያዎች፣ 42 አጥቢዎችና ሌሎች እንስሳት እንዳሉበት አስረድተው፣ “የተመሰረተው በኬንያና በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኘውን ትልቁ የሜዳ አህያ ለመጠበቅ ነው” ብለዋል።

ኮቪድ ከመከሰቱ በፊት እስከ 200 ሺሕ፣ ኮቪድ ተከስቶ ከቆዬ በኋላ የቱሪስት ቁጥር በመቀነሱ ከ50 ሺሕ እስከ 100 ሺሕ ገቢ የሚገኝበት እጩ ፓርክ መሆኑ ተነግሯል።

ፓርኩ ከአዲስ አበባ በ27ዐ ርቀት ላይ ያለ፣ ኤሪያው 1099 ስኩየር ኪሎሜትር የሆነ፣ ወይራ፣ የሀበሻ ጽድ፣ ዝንባ የመሳሰሉ እፅዋቶች ያሉበት፣ 40 ኪሎሜትር የሚሸፍን ሜዳ ላይ ያረፈ ሳር ያለበት ነውም ተብሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia

የየእለቱን ዜናዎችን በSMS እናግኝ! 🗞📲
ከሳፋሪኮም ቁጥራችን 'A’ ብለን ወደ 30000 SMS አሁኑኑ በመላክ ወይም ወደ *779# በመደወል የቲክቫህ ትኩስ መረጃዎችን እናግኝ! በቀን 1ብር ብቻ! ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት ⚡️

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ:
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

#MPESASafaricom
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
" ከጦርነቱ በፊት ነጋዴዎች ተበድረውት የነበረው 32 ቢሊዮን ብር አሁን ከነወለዱ ወደ 80 ቢሊዮን ብር  አድጓል " - ከትግራይ ክልል ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት

የትግራይ ክልል ነጋዴዎች ከጦርነቱ በፊት ተበድረውት የነበረው 32 ቢሊዮን ብር አሁን ከነወለዱ ወደ 80 ቢሊዮን ብር ማደጉን የትግራይ ክልል ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አሳውቋል።

ም/ቤቱ ይህን ያሳወቀው ለሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ በሰጠው ቃል ነው።

የትግራይ ክልል ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዘዳንት አቶ በሪሁን ሃፍቱ ምን አሉ ?

➡️ ነጋዴዎች ከጦርነቱ በፊት ከባንክ ወስደውት ነበረው የባንክ እዳ በ5 አመት ወስጥ ከ32 ቢሊዮን ብር አሁን ከነወለዱ ወደ 80 ቢሊዮን ብር ደርሷል።

➡️ ተከስቶ የነበረው ጦርነት ብዙ ሀብት አውድሟል የንግድ እና ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን አጥፍቷል፣ ቀሪዎችንም ከንግድ እንቅስቃሴ ውጭ አድርጎ የገበያ ትስስራቸውን እንዲያጡ አድርጓል።

➡️ የወደሙ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች የጠፉት የባንክ ብድር ይዘው ነው።

➡️ የባንክ እዳ ይዘው የወደሙ የንግድ ተቋማትን ወደ መደበኛ ሥርዓት ለመመለስ ከባድ ነው ፤ ምክንያቱም ባለሀብቱ ፈልጎ ባላመጣው ጦርነት ተዳክሟል።

➡️ በክልሉ ያሉ ባለሀብቶች ንብረታቸው መውደሙ እና ሀብታቸው መጥፋቱ ሳያንስ እዳቸውን ከነወለዱ እና ከነቅጣቱ እንዲከፍሉ እየተገደዱ ነው። ይህም አግባባብ አደለም። ምክኒያቱም ባለሃብቶች ጦርነቱን ፈልገውት አይደለም ያመጡት።

➡️ የወደሙ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ተቋማት ተመልስው ወደስራ የሚገቡበት ሁኔታ ሳይፈጠር ባለሃብቶች ባልሰሩበት የተበደሩትን እዳ ከነወለዱ እንዲከፍሉ መደረጉ ተገቢ አይደለም። መከፈል ግዴታም ከሆነም ደግሞ ቢያንስ እየሰሩ እንዲከፍሉ ልዩ ማበረታቻ ያሰፈልጋቸዋል።

➡️ የወደሙትን በአዲስ ለመተካት የተዳከሙትን ደግሞ ለማነቃቃት ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል። ያን ማድረግ የሚቻል ከሆነ ነጋዴው ነግዶ አትርፎ አዲስ ግብር ከፋይ ብቻ ሳይሆን ከዚህ በፊት የነበረበትን እዳም የመክፈል አቅም ይኖረዋል።

➡️ አሁን ያለብን ትልቁ ችግር ተጨማሪ ድጋፍ አለማግኘት ነው። ባንኮች ተጨማሪ ብድር ለመስጠትም እየተቸገሩ ነው።

➡️ ባለሃብቶች ከጦርነቱ በፊት የተበደሩት እዳ ወለዱም ከዛሬ ነገ እየጨመረ ነው ያለው ፤ አይደለም ሰርቶ ማትረፍ ይቅርና ስራ በቆመበት እና ንብረት በወደመበት ወቅትም ወለዱ እየታሰበ ነው ያ ወለድ ደግሞ የወለድ ወለድ ቅጣት እየታሰበበት ነው።

➡️ ያለው ችግር የተለየ የብደር ጥቅል ካልተዘየደለት አሁን ባለው አሰራር የሚፈታ አይደለም።

➡️ የወደመው ንብረት በቢሊዮን የሚገመት ነው በዚህ ላይ ደግሞ የኢኮኖሚው ማሻሽያ ሲጨመር ችግሩን የከፋ አድርጎታል።

➡️ ጦርነቱ ከቆመ ወዲህ ባለፉት ሁለት አመታት ለክልሉ ባለሃብቶች የቀረበው ብድር 2 ቢሊዮን ብር የማይሞላ ነው ይህም ከችግሩ ስፋት ጋር አብሮ የሚሄድ አይደለም።

➡️ በቅረቡ ከብሄራዊ ባንክ ጋር ውይይት ተደርጎ ነበር በዚህም ነጋዴዎች በሐራጅ ለመሸጥ ጊዜውን ለአንድ አመት እንዲራዝም ተደርጓል ግን ይህ በቂ አይደለም።

የመረጃው ባለቤት ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ነው።

@tikvahethiopia
#AU #Ethiopia

46ኛው የአፍሪካ ሕብረት መደበኛ የአስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ ዛሬ ተጀምሯል።

በዚህም ዛሬ በተካሄደው ምርጫ #ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና ጸጥታ ምክር ቤት አባል ሆና ተመርጣለች።

@tikvahethiopia
" ከታክስ በፊት 34.4 ቢሊዮን ብር አትርፊያለሁ " - ኢትዮ ቴሌኮም

ኢትዮ ቴሌኮም 3.24 ሚሊዮን አዳዲስ ደንበኞች በማፍራት አጠቃላይ የቴሌኮም አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞቹን ብዛት 80.5 ሚሊዮን ማድረሱን አስታወቀ።

በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ መንፈቅ ሪፖርት ያቀረቡት የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ምን አሉ ?

➡️ 3.24 ሚሊዮን አዳዲስ ደንበኞች አፍርተናል።

➡️ 9.3 ሚሊዮን የአዳዲስ ሲም ካርድ ሽያጭ የተከናወነ ሲሆን ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ8% ጭማሪ እንዲሁም ከእቅድ ጋር ሲነጻጸር የ113% አፈጻጸም አለው።

➡️ የሞባይል ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር 7.5 % እድገት በማሳየት የተጠቃሚዎች ቁጥር 43.5 ሚሊዮን ደርሷል።

➡️ የሞባይል ኢንተርኔት ትራፊክ ማለትም (በሞባይል ኔትወርክ የተላከ እና የተቀበለው የዲጂታል መረጃ መጠን) በተመለከተ በበጀት አመቱ እስከ ህዳር ወር ድረስ 642.2 ቢሊዮን ሜጋ ባይት ትራፊክ ተመዝግቧል። ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ48.8 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

➡️ የብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት 5% ጭማሪ በማሳየት የተጠቃሚዎቹ ቁጥር 784.1 ሺ ደርሷል።

➡️ በአጠቃላይ ከባለፈው የበጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የደንበኞች እድገቱ በ7.9 በመቶ አድጓል።

ኩባንያው ምን ያህል አተረፈ ?

➡️ በመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት 61.9 ቢሊዮን ገቢ አግኝተናል። ይህም የዕቅዳችን 90.7 በመቶ ያሳካ ነው።

➡️ ከታክስ መሰል ወጪዎች በፊት ያለው ምጣኔ (EBITDA) 55.5 በመቶ ነው። ከታክስ በፊት 34.4 ቢሊዮን ትርፍ ተመዝግቧል።

➡️ ከአጠቃላይ ከገቢ ውስጥ 72.61 ሚሊዮን ዶላር የሚሆነውን በውጭ ምንዛሬ የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia