TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" ' የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን ' በሚል የተሰጠው መግለጫ የሰራዊቱ እና የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ሃሳብ እና ውሳኔ እንዳልሆነ ለኢትዮጵያ መንግስት  እናሳውቃለን "  - የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ 

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል የተሰጠው መግለጫ ተፈፃሚነት እንዳይኖረው (null and void እንዲሆን) ወስኗል። 

" በሰራዊቱ የኮር አመራር የሚል አደረጃጀት እውቅና የለውም " ሲል የወሰነው ካቢነኔው  " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል ጥር 14/2017 ዓ.ም የተሰጠውን መግለጫ ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርጎታል።

ካቢኔው ዛሬ ቅዳሜ ጥር 17/2017 ዓ.ም በሰጠው መግለጫ ፤ "የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል የተሰጠው መግለጫ ፦
- ለአንድ ቡድን የወገነ
- መንግስት የሚፈርስ
- ሰራዊት የሚበትን
- የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የሚያፈርስ እና መሰረታዊ ችግር ያለው በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲታረም እና ታች ወርዶ እንዳይተገበር ወስኗል። 

" የተሰጠው መግለጫ ከሰራዊት ተልእኮ ያፈነገጠ ፣ ተቋማዊ አሰራር የጣሰ " ነው "ሲል የገለፀው ካቢኔው ፥ " ' አመራር ነኝ ' በሚል በዚህ ሁኔታ ተሰብስቦ ውሳኔ ለማሳለፍ የሚያስችል ስልጣን የለውም " ብሏል።

" ' የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን ' በሚል በተሰጠው መግለጫ መንግስታዊ ማስተካከያ እንዲደረግ አስመልክቶ የቀረበው አቋም የአንዱ ቡድን የስልጣን ጥማት ለማርካት ሲባል የፕሪቶሪያ ውል የሚያፈርስ ሃላፊነት የጎደለው ውሳኔ ነው " አደገኛ ነው ' ሲል ገልጾ በአስቸኳይ የሚታረምበት አቅጣጫ ማስቀመጡን አሳውቋል።
  
ካቢኔው ባወጣው የውሳኔ መግለጫ ለኢትዮጵያ መንግስት ባስተላለፈው መልእክት " ' የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን ' በሚል በተሰጠው መግለጫ የሰራዊቱ እና የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ሃሳብ እና ውሳኔ አይደለም በመሆኑም ወድቅ አድርጎታል ፤ ሰራዊቱ እና የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር  አሁንም ለፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ተገዢ በመሆን ጅምር ሰላሙ እንዲጎለብት የትግራይ ሉአላዊ ግዛት ተከብሮ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ የጀመረውን ትግል አጠናክሮ ይቀጥላል " ብሏል።

" የትግራይ ህዝብና ጊዚያዊ አስተዳደሩ ፍላጎት ሰላም ነው " ሲል ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ መልእክት ያስተላለፈው ካቢኔው ፤ " የፕሪቶሪያ የሰላም ውል በአፈፃፀም ብዙ ችግሮች ቢኖሩትም በስምምነቱ አፈፃፀም የሚነሱ ችግሮች በሰላማዊ እና ፓለቲካዊ ትግል እንዲመለሱ የአለም አቀፍ ማህበረሰብ የተሟላ ድጋፍ እንዲያደርግ " ሲል ጥሪ አስተላልፏል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray ዛሬ በደጋፊዎች እና በተቃዋሚዎች በኩል የፓሊስ ትእዛዝ የጣሱ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሂደዋል። በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የጠራቸው ሰልፈኞች ፥ " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል  ጥር 14/2017 ዓ.ም የወጣውን የውሳኔ ሃሳብ የሚደግፉና እና ሌሎች መፈክሮች አስተጋብተዋል። በራሳቸው ተነሳሽነት ሰልፍ መውጣታቸው የሚናገሩት በብዛት ወጣቶች…
" መንግስታችን እንዳይፈርስ እስከ ሞት ድረስ እንታገላለን ፤የጦርነት ነጋዴዎች ከድርጊታችሁ ታቀቡ " - አቶ ብርሃነ ገ/የሱስ

ዛሬ በመቐለ  " እምቢ ለጦርነት እምቢ ለመፈንቅለ መንግስት !! " በሚል መሪ ቃል የሰሞኑን የወታደራዊ አመራሮች መግለጫ የሚቃወም ሰልፍ ተካሂዶ ነበር።

በሰልፉ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገኝተው ነበር።

በጊዚያዊ ኣስተዳደሩ ከንቲባ ሆነው የተሾሙት ብርሃነ ገ/የሱስ በሰልፉ ላይ ተገኝተው " የሰላም ዋስ የሆነው ሰራዊት የቡድኖች መጫወቻ አይሆንም ፥ የጦርነት ነጋዴዎች ይብቃችሁ " ብለዋል።

" የሻዕብያ ተላላኪዎች አቁሙ !" ሲሉ በምሬት የተናገሩት ከንቲባው " መንግስት ለማፍረስ የተሄደው ርቀት አይሳካም ፤ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ውሳኔዎች ይከበሩ ህዝቡም እንዲከበሩ ያግዝ " ብለዋል።

" የፌደራል መንግስት የፕሪቶሪያ ስምምነት በሙሉነት እንዲተገበር ፣ የትግራይ ሉአላዊ ግዛት እንዲከበር እና ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ  ቁርጠኛ መሆን አለበት " ያሉት ከንቲባው " የትግራይ ህዝብ ጥቅም የሚረጋገጠው በሰላም ብቻ መሆኑን በማመን ወጣቱ ትግሉ አጠናክሮ ይቀጥል " የሚል ጥሪ አቅርበዋል።

ዛሬ ከመቐለ በተጨማሪ በሌሎችም ከተሞች ጊዚያዊ  አስተዳደሩን ለመደገፍ እና " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል  የተሰጠው መገለጫ እና ውሳኔና በመቃወም  ወጣቶች በበዙባቸው ሰልፎች  ተካሂደው ነበር።

በዚህም ፦
- መንግስት ለማፍረስ የሚደረግ እንቅስቃሴ ይቁም !
- የትግራይ ህዝብ ጥቅም በሰላም ብቻ ነው የሚረጋገጠው !
-  ጊዚያዊ አስተዳደሩ እንደግፋለን !
- የጊዚያዊ አስተዳደሩ ውሳኔዎች ይከበሩ !
- የፕሪቶሪያ ስምምነት ይከበር !!
- የትግራይ ሉአላዊ ግዛት ይከበር !!
- ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ይመለሱ !!

የሚሉ እና ሌሎች መፈክሮች ተደምጠዋል።

ትላንትና ዛሬ መቐለ ጨምሮ በተለያዩ የትግራይ ከተሞች የትግራይ ኃይል መኮንኖችን የሚደግፉና የሚቃወሙ ሰልፎች እየተካሄዱ የሚገኝ ሲሆን ሰልፎቹ የፖሊስን ክልከላ በጣሰ መንገድ ነው እየተካሄዱ ያሉት።

በህወሓት የፖለቲካ አመራሮች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት እና መከፋፈል ወደ ፀጥታ ኃይል አመራሮች መዛመቱ ህዝቡን ከፍተኛ ስጋት ላይ ጥሏል።

ትግራይ ከአስከፊው እና አውዳሚው ጦርነት ገና በቅጡ ሳታገግምና ችግሮች ሳይፈቱ ወደ ሌላ ቀውስ ውስጥ ሊያስገባ የሚችል ሁኔታ እየታየ መሆኑ በርካቶችን አሳስቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia 
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
በመቐለ ኤፍ ኤም 104.4 ምንድነው የተፈጠረው ?

" በመቐለ ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ ላይ የአፈና እና የስራ አመራር የማባረር ሙከራ " መደረጉን ጣቢያው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።

ሙከራው በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የመቐለ ከንቲባ እንዲሆኑ በተሾመቱ ረዳኢ በርሀ (ዶ/ር) ያስተባበሩት ነው ተብሏል።

ዛሬ ጥር 21/2017 ዓ.ም የተካሄደው የአፈናና አመራር የመቀየር ሙከራ ለጊዜው ከሽፏል።

የ104.4 ኤፍኤም መቐለ ስራ አስኪያጅ በመሆን በማገለገል ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ሹመይ ረብሶ ስለሁኔታው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ መረጃ አካፍሏል።

መሩከራው
እንዴት እና መቼ ተፈፀመ ?

አቶ ዘመንፈስ ቅዱስ ፍስሃ የሚባሉ የመቐለ ከተማ አመራር አባል ዛሬ ጥር 21
/2017 ዓ.ም ጠዋት ሦስት ታጠቂዎች ይዘው በመመጣት የስራ አስኪያጅ ፀሃፊዋ የሬድዮ ጣብያው ማህተም እንድታስረክባቸው ይጠይቃሉ።

አስረክቡ አናስረክብም በሚል ሰጣ ገባ መሃል የሬድዮ ጣብያው አመራሮች ወደ ከተማው ፓሊስ ደውለው ሃይል እንዲመጣላቸው ሆነ።

ፓሊሶቹ ከመቐለ አስተዳደር የመጣው ግለሰብ እና ታጣቂዋቹ ከሬድዮ ጣብያው እንዲወጡ እና ተግባራቸው እንዲያቆሙ በማድረግ ወደ ህግ ቦታ ወስደዋቸዋል።

በአሁኑ ወቅት 104.4 የመቐለ ኤፍኤም የተለመደ ስራው በመቀጠል ላይ እንደሆነ ስራ አስኪያጁ ገልፀው የአፈና እና የስራ አመራር መቀየር ሙከራ ባደረጉት ላይ ክስ መጀመሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቀዋል።

104.4 የመቐለ ኤፍ ኤም ሬድዮ በከተማው አስተዳደር ስር የሚተዳደር በትግራይ የመጀመሪያው የኤፍኤም ሬድዮ ጣብያ ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
በመቐለ ኤፍ ኤም 104.4 ምንድነው የተፈጠረው ? " በመቐለ ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ ላይ የአፈና እና የስራ አመራር የማባረር ሙከራ " መደረጉን ጣቢያው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል። ሙከራው በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የመቐለ ከንቲባ እንዲሆኑ በተሾመቱ ረዳኢ በርሀ (ዶ/ር) ያስተባበሩት ነው ተብሏል። ዛሬ ጥር 21/2017 ዓ.ም የተካሄደው የአፈናና አመራር የመቀየር…
#Update

🔴" በ104.4 የመቐለ ኤፍኤም ያጋጠመው ችግር በመግባባት እንዲፈታ አድርጊያለሁ  ስልጣን መረከብ የሚፈልግ አካል እና ግለሰብ ህግ እና ስርዓት ያክብር  " - የመቐለ ከተማ ፓሊስ 

" ሬድዮ ጣቢያችን ለሁለት የተሰነጠቁ ቡድኖች መጫወቻ እንዲሆን አንፈቅድም " - የመቐለ FM አመራር

ጥሪ 21 / 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4:00 ሰዓት 5 ታጣቂዎች አስከትሎ የመቐለ ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያን ለመቆጣጠረ ሙከራ ያደረገው ሬድዮ ጣብያውን እንዲመራ የመቐለ አስተዳደር " ሹሞኛል " የሚል ግለሰብ እንደሆነ የሬድዮ ጣቢያው አመራሮች ተናግረዋል።

ታጣቂዎች አስከትሎ ሬድዮ ጣብያውን ለመረከብ ሲሞክር የተፃፈለት ደብዳቤ በቦታው ለነበሩ አመራሮች ማሳየት ባለመቻሉ ምክንያት ግርግር እንዲነሳ ምክንያት መሆኑ አመራሮቹ ያብራራሉ።

ዘግይቶ በተደረገው ማጣራት የሹመት ደብዳቤ ማቅረብ ያልቻለውና ሬድዮውን ለመምራት መመደቡ የጠቀሰው ግለሰብ  በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በሚመራው ህወሓት የከተማዋ ከንቲባ እንዲሆኑ በተሾሙት ረዳኢ በርሀ (ዶ/ር) መመደቡ በቃል እንደጠቀሰላቸው አመራሮቹ ገልጸዋል።

ጉዳዩን ወደ መቐለ ፓሊስ በመውሰድ ጊዚያዊ መፍትሄ ማግኘት መቻላቸው ከምስጋና ጭምር አስታውቀዋል።

የጣቢያው አመራሮች " በደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት በተሾመ ከንቲባ ሬድዮ ጣብያውን ለማስተዳደር መመደቡን የሚናገረው ግለሰብ የአገሪቱዋ የሚድያ ህግ በሚጥስ አካሄድ ከአንድ ክፍለ ከተማ ያሰባሰባቸው ታጣቂዎች በማስከተል የአፈና ተግባር ለመፈፀም መመኮሩ የህወሓት በሁለት መሰንጠቅ በክልሉ እያደረሰ ያለው ዘርፈ በዙ ችግር አንዱ ማሳያ ነው " ሲሉ አክለዋል።

" ከ15 ዓመት በላይ ያስቆጠረ እና ከ60 በላይ ሰራተኞች ያሉት የመንግስት የኤፍኤም ሬድዮ ለሁለት የተሰነጠቁ ቡድኖች መጫወቻ አይሆንም " ያሉት አመራሮቹ በአገሪቱ የብሮድካስት ህግ የሚተዳደር ሚድያ መሆኑ በመግለፅ ተመሳሳይ አፈና እንዳይፈፀም በግለሰቡ እና በላከው አካል ላይ ክስ እና አገዳ እንዲጣል እንቅስቃሴ መጀመራቸው አስታውቀዋል።

የመቐለ ፓሊስ በፅሁፍ ባወጣው መግለጫ የአፈና ተግባሩን አውግዞ  ፤ ችግሩ በመግባባት መፍታቱን እና ወደ ሃላፊነት መምጣት የሚፈልግ አካል እና ግለሰብ ህግ እና ስርዓት አክብሮ መሆን ይገባዋል ብሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በመቐለ ከተማ በከንቲባ ስም ማንኛውም ተግባር እንዳይፈፅም አስጠነቀቁ።

አቶ ጌታቸው በእፅንኦት ያስጠነቀቋቸው ባለፈው ጥቅምት 2017 ዓ.ም በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በሚመራው ህወሓት እጩ አቅራቢነት ከንቲባ በመሆን የተሾሙትን ረዳኢ በርሀ (ዶ/ር) ነው።

ፕሬዜዳንቱ ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም ፅፈውት  ጥር 23 ቀን 2017 ዓ.ም በተለያዩ የማህበራዊ የትስስር ገፆች ይፋ በሆነው የማስጠንቀቅያ ደብዳቤ ፤ በከተማዋ የሚገኙ የመንግስት መዋቅሮች በጊዚያዊ አስተዳደሩ ቅቡልነት ባጡ ከንቲባ ረዳኢ በርሀ (ዶ/ር) በተፃፈ ደብዳቤ ማንኛውም ስራ መፈፀም የህግ ተጠያቂነት አንደሚያስከትልባቸው ያትታል።

ዶክተሩ ህገ-ወጥ ተግባራቸው እንዲያቆሙ የሚያሳስበው እና የሚያስጠነቅቀው ደብዳቤው ጊዚያዊ አስተዳደሩ የሚፃረር አቋም በመያዝ ከተማዋ መምራት አግባብነት የለውም ይላል። 

ስለሆነም በመቐለ ከተማ የሚገኙ የመንግስት መዋቅሮች በጊዚያዊ አስተዳደሩ ቅቡልነት በሌላቸው ከንቲባ የሚሰጣቸው ማንኛውም ዓይነት ትእዛዝ እንዳይቀበሉ የፕሬዜዳንቱ ደብዳቤ አስጠንቅቋል።

ህወሓት ለሁለት በመሰንጠቁ ምክንያት የመቐለ ከተማ ላለፉት 60 ቀናት ቢሮ ገብቶ የሚደራ ከንቲባ የላትም።

ህዳር 23/2017 ዓ.ም በጊዚያዊ አስተዳደሩ ደብዳቤ የተሾሙ ብርሃነ ገ/የሱስ አንድ ቀን ብቻ በአስተዳደሩ ግቢ ታይተው ለሁለተኛ ጊዙ አልተመለሱም።

በደብረፅዮኑ ህወሓት የተሾሙ ረዳኢ በርሀ (ዶ/ር) ከህዳር 23 /2017 ዓ.ም ጀምሮ ቢሮ አልገቡም።

የመቐለ ከንቲባ ቢሮ አሁንም ታሽጎ በፓሊሶች ይጠበቃል፤ የከተማዋ ነዋሪ ደግሞ ከከንቲባ ማግኘት የሚገባውን አገልግሎት አጥቶ አቤቱታውን ለማን ማቅረብ እንዳለበት ግራ ገብቶት ይገኛል። 

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
#Update

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር የአማካሪ ካውንስል ምክር ቤት በይፋ ተመሰረተ።

ምክር ቤቱ ሰብሳቢ እና ምክትል ሰብሳቢ የመረጠ ሲሆን የትግራይ ነፃነት ፓርቲ ሊቀመንበር ደጀን በርሀ (ዶ/ር) በከፍተኛ ድምፅ ምክትል ሰብሳቢ ሆነው ተመርጠዋል። 

የአማካሪ ካውንስል ምክር ቤት የማቋቋም ሃሳብ የክልሉ ምክር ቤት የሚያፈርሰው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ተከትሎ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ማቋቋምያ ሰነድ ጥር 2015 ዓ.ም ሲፀድቅ የተነሳ ሃሳብ ነው።  

ሃሳቡ በድጋፍ እና በተቃውሞ ለሁለት አመታት ያህል ሲናጥ ቆይቶ ዛሬ ጥር 25/2017 ዓ.ም በይፋ ተመስርቶ መሪዎቹ መርጠዋል። 

በምስረታ ካውንስሉ መልእክት ያስተላለፉት ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ፤ በክልሉ የሚገኙ የኢሮብ እና ኩናማ ብሄረሰቦች የተወከሉበት ካውንስሉ ዘግይቶም ቢሆንም መመስረቱ መልካም ሆኖ አቃፊ ፣ አሳታፊ እና የሃሳብ ብዙህነት የሚንሸራሸሩበት መድረክ መሆን ይገባዋል ብለዋል። 

የአማካሪ ካውንስል ምክር ቤቱ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የተቀመጡት የትግራይ ህዝብ ጥቅሞች በተሻለ እና በአስተማማኝ እንዲመለሱ አጋዥ ሃይል ለማሰባሰብ አልሞ መቋቋሙን የጠቆሙት ፕሬዜዳንቱ " ልዩነቶቻችን በማጠበብ ለተሻለ ነገ በጋራ መስራት ወቅታዊ የትግራይ ጥያቄ ነው "  ብለዋል። 

የካውንስሉ እድሜ የጊዚያዊ አስተዳደሩ የቆይታ ጊዜ መሆኑ ያስረዱት ፕሬዜዳንት ጌታቸው ይህንን ታሳቢ በማድረግ የትግራይ ፓለቲካዊ ምህዳር ማስፋት እና ለነገ ማመቻቸት ዋነኛ ስራው መሆን እንደሚገባ አክለዋል።   

ካውንስሉ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ስራዎች መሬት ላይ እንዲወርዱ አጋዥ ሚና ከመጫወት በተጨማሪ የትግራይ ተደማጭነት እና የመደራደር አቅም የሚያጠናክር አቅጣጫ መከተል ይገባዋል ብለዋል ፕሬዜዳንቱ። 

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አማካሪ ካውንስል ምክር ቤት ለመምራት ሰብሳቢ እና ምክትል ሰብሳቢ ሆነው የተመረጡት ቃለ ማህላ ፈፅሟል።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አማካሪ ካውንስል ምክር ቤት መመስረት በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት እና ሳልሳይ ወያነ ፓርቲ እና ሌሎች ተቃውሞውታል

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ከፕሬዜዳንቱ እና ካቢኔው በላይ የሆነ የማይታዘዝ ሃይል ተፈጥሯል "- አቶ ብርሃነ ገ/ኢየሱስ

በትግራይ ከጊዚያዊ አስተዳደር " ከፕሬዜዳንቱ እና ከካቢኔው በላይ የሆነ የማይታዘዝ ሃይል ተፈጥሯል " ሲሉ በጊዜያዊ አስተዳደሩ የተሾሙት የመቐለ ከንቲባ ብርሃነ ገ/ኢየሱስ ተናገሩ።

" ጊዚያዊ አስተዳደሩ በግልፅ ባያውጅም መቐለ ጨምሮ በመላ ትግራይ በስሙ መጠራት ያለበት ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት አለ " በማለት አክለዋል።

ከህዳር 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ የመቐለ ከንቲባ ሆነው በጊዚያዊ አስተዳደሩ ደብዳቤ የተሾሙት እና ህዳር 23/2017 ዓ.ም አንድ ጊዜ ብቻ ቢሯቸው ከገቡ በኋላ ያልተመለሱት ከንቲባው " ላዛ ትግርኛ " ለተባለ ሚድያ ሰፊ ቃለመጠየቅ ሰጥተዋል።

" ወታደራዊ ሃይል በመጠቀም ከመንግስት በላይ ሆኖ ከንቲባ ስራውን እንዳይሰራ ፤ ህዝብ ከከንቲባ ማግኘት ያለበት አገልግሎት እንዳያገኝ መከልከል የህግ ተጠያቂነት ከማስከተል በተጨማሪ በታሪክ ያስወቅሳል " ብለዋል።

ከ8 ወራት በፊት ሰሜናዊ ምዕራብ ትግራይ ዞን ፤ ከ4 ወራት በፊት ማእከላዊ ዞን እንዲያስተዳድሩ በጊዚያዊ መንግስት ፕሬዜዳንት ፊርማ የተመደቡ ሃላፊዎች ተግባራቸው እንዳይፈፅሙ ስሙ ባልጠቀሱት ወታደራዊ አዛዥ የሚታዘዙ ጠበንጃ ባነገቡ ታጣቂዎች እንደተስተጓጎሉ ጠቅሰዋል።

እሳቸውም " ከፓሊሰ አቅም በላይ ያልሆነውን ጉዳይ የመቐለ አስተዳደር ዙሪያ በታጣቂዎች በማጠር ወደ ቢሮ እንዳይገቡ ከሁለት ወር በላይ መከልከላቸው እጅግ አሳዛኝ እና የመንግሰት ትእዛዝ የጣሰ ሃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው " ብለዋል። 

ፕሬዜዳንቱና ካቢኔው ሦስት ጊዜ ወደ ስራ ገበታቸው ገብተው ስራቸው እንዲሰሩ ቢያዝም አስተዳደሩን እንዲጠብቁ በታዘዙ ታጣቂዎች መከልከላቸው እጅግ እንዳሳዘናቸው እና እንዳበሳጫቸው ተናግረዋል።

" መንግስት መንግስት መምሰል አለበት ትእዛዝ እና ውሳኔ በማክበር እና በማስከበር ከመንግስት በላይ መሆን የሚፈልገውን አካል ማቆምን ማስታገስ  ይገባዋል " ብለዋል።

" ከፕሬዜዳንት እና ከካቢኔ በላይ በመሆን ታጣቂዎች በአስተዳደሩ ዙሪያ ያስቀመጠ አካል የወጣቶች ቁጣ እና መልእክት ተቀብሎ ያሰማራቸው ታጣቂዎች በአስቸኳይ ማንሳት አለበት " ያሉት ከንቲባው " ጉዳዩ ፓሊስን ይመለከታል ከፓሊስ አቅም በላይ ከሆነ የአድማ ብተና ሃይል ይሰማራል ፤ ከዚህ ውጭ ከአቅሜ በላይ ሆኗል የሚል ጥያቄ ባልቀረበበት ታጣቂ ሰራዊት ማስቀመጥ ከህግ በላይ መሆንን ያመለክታል " ሲሉ ስሙ ያልጠቀሱት ታጣቂዎች አሰማርተዋል ያሉትን አካል ተችተዋል።

መቐለ ካሉዋት 7 ክፍለ ከተሞች እና  33 ቀበሌዎች ዙሪያዋ የተወጣጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ወደ አደባባይ በመውጣት ከንቲባ ስራውን እንዲጀምር ፤ ህዝቡ መንግስታዊ አገልግሎት እንዲያገኝ ፤ የጊዚያዊ አስዳደሩ ትእዛዝ እንዲከበር ድምፃቸው አስምተዋል ያሉት ከንቲባ ብርሃነ  " አሁንም መልስ ካላገኙ ከበፊት በላቀ ቁጥር ወጥተው ድምፃቸው ማሰማታቸው ይቀጥላሉ " ሲሉ ዝተዋል።

መቼ ወደ ተመደቡበት ስራ እንደሚገቡት ለቀረበላቸው ጥያቄ የተቆረጠ ቀን እንደማያወቁ  ተናግረዋል።

" ትግራይ ከገባችበት ፓለቲካዊ ቀውስ የምትወጣበት እንዱ እና ዋነኛ መንገድ መንግስት ሲኖራት የመንግስት ትእዛዝ እና ውሳኔ ሲከበሩ ነው ስለሆነም ከህግ እና መንግስት በላይ በመሆን ታጣቂ ያሰማሩ አካላት ከድርጊታቸው ይቆጠቡ " ሲሉ አሳስበዋል።

በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ህወሓት እና በጊዚያዊ አስተዳደሩ የተመደቡላት ከንቲባዎች ከስራ ውጭ ሆኖዉባት ከንቲባ ያጣቸው የትግራይ የፓለቲካ እና የኢኮኖሚ ከተማ የሆነችው መቐለ የከንቲባዋ ፅህፈት 'ታሽገዋል ' የሚል ወረቀት ተለጥፎለት   በግራና ቀኝ በቆሙ ፓሊሶች እንዲሁም ዙሪያዋ በታጣቂዎች ለ24 ሰዓት መጠበቅ ከጀመረች 64 ቀናት ተቆጥረዋል ሲል የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ መረጃውን አድርሶናል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#መቐለ " ተጠርጣሪው ተይዞ ለክልሉ ፖሊስ ተላለልፎ ተሰጥቷል " - ፖሊስ የ19 ዓመትዋን ወጣት በመግደል የተጠረጠረው ግለሰብ በፓሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል። የመቐለ ሓወልቲ ክፍለ ከተማ ፓሊስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለጸው ፥ ጥቅምት 19 /2017 ዓ.ም ሓበን የማነ የተባለች ፍቅረኛውን በተከራዩት የሆቴል ክፍል በጬቤ በመግደል የተጠረጠረው ግለሰብ ከቀናት ፍለጋ በኃላ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል። በአሰቃቂ…
#Update

የዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት ተፈርዶበታል !

ሓበን የማነ የተባለች ወጣትን በጭካኔ በመግደል ክስ የተመሰረተበት ዳዊት ዘርኡ የተባለ ወንጀለኛ ዛሬ ጥር 28/2017 ዓ.ም በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተፈርዶበታል።

ፍርዱን ያሳለፈው የመቐለ ማእከላዊ ፍርድ ቤት ነው።

አሰቃቂ ግድያው በትግራይ ፣ መቐለ ሓወልቲ ክፍለ ከተማ ዓዲሓ ተብሎ በሚጠራው ልዩ ሰፈር በሚገኝ የአንድ ሆቴል ክፍል ነበር የተፈፀመው።

ሓበን የማነ የ19 ዓመት ወጣት ስትሆን በሆቴል ክፍል በቢላዋ ተገድላ መገኘቷንና ጥቅምት 20 /2017 ዓ.ም ከሰአት በኋላ የቀብር ስነ-ሰርዓት መከናወኑ በወቅቱ መረጃ አድርሰናችሁ ነበር።

ፓሊስ አሰቃቂ የግድያ ተግባሩ አስመልክቶ በወቅቱ በሰጠው መረጃ ፤ የነፍስሄር ወጣት ሓበን የማነ አስከሬን ከ2 ቀን በኋላ ነው በተገደለችበት የሆቴል ክፍል የተገኘው።

ገዳይ ወንጀለኛው አሰቃቂ ተግባሩ በመቐለ ከተማ ከፈፀመ በኋላ በአማራ ክልል በኩል በድብቅ ለውጣት ሲያሴር ደሴ ከተማ በአማራ ክልል ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውሎ ለትግራይ ክልል ፓሊስ ተላልፎ ተሰጥቷል።

በወቅቱም ለደሴ ህዝብና ለአማራ ክልል ፖሊስ ምስጋና ቀርቦ ነበር።

ፓሊስ ጉዳዩ  አጣርቶ አቃቤ ህግ ክሰ መስርቶ ሲከራከር ከቆየ በኋላ ዛሬ እሮብ ጥር 28/2017 ዓ.ም የመቐለ ማእከላይ ፍርድ ቤት ባዋለው ችሎት ወንጀለኛው በዕድሜ ልክ ፅኑ አስራት እንዲቀጣ ወስኗል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia