TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.13K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
" ሐኪሞቹ ' መግቧቸው፤ የምግብ እጥረት ነው ' ይላሉ። እኛ ደግሞ ከየት እናመጣዋለን ? ጊዜው ከፋብን " - እናት በአማራ ክልል፣ ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ በተከሰተ ድርቅ እና የምግብ እጥረት ከአምስት ዓመት በታች ያሉ ህፃናትን ጨምሮ 10 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች መጎዳታቸውን ወረዳው አስታውቋል። በክልሉ ባለው ግጭት እና ተፈጥሯዊ ተፅዕኖ ምክንያት ወረዳው ለድርቅ እና የምግብ እጥረት መጋለጡን የቡግና…
🚨 “ የሚላስ የሚቀመስ የለም ” - የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ

🔴 “ ችግር እንዳለ ይታወቃል ” - የአማራ ክልል አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ በምግብ እጥረት ሳቢያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደተጎዱ፣ በተለይ ጨቅላ ህፃናት የከፋ ስቃይ ላይ እንደሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

“ ጉዳዩ በጣም አሳዛኝ ነው። በእኛ ቦታው ያልሆነ ሰው አይገባውም ” ሲሉም የሁነቱን አስከፊነት አስረድተዋል።

ስሜ ከመነገር ይቆይ ያሉ የመረጃ ምንጭ በበኩላቸው፣ “ በቡግና ወረዳ ጉልሃ ቀበሌ አንድ ህፃን በምግብ እጥረት ሞቷል ” ብለዋል።

የቡግና ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገብረ መስቀል አለሙ በበኩላቸው፣ በክልሉ ባለው ግጭትና ተፈጥሯዊ ተፅዕኖ ምክንያት ወረዳው ለድርቅና ለምግብ እጥረት በመጋለጡ ህፃናትን ጨምሮ ከ10 በላይ ሰዎች መጎዳታቸውን ሰሞኑንን ለቢቢሲ አማርኛ መናገራቸው አይዘነጋም።

በወረዳው በተከሰተ የምግብ እጥረት በተለይ ጨቅላ ህፃናት ስለተጎዱ ነዋሪዎቹ የድረሱልን ጥሪ ማሰማታቸውን በመግለጽ ችግሩን ለመቅረፍ ምን እየተሰራ ነው ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጠየቀው የቡግና ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት፣ “ እኛ ጋር ስራ የለም ” የሚል አጭር ምላሽ ሰጥቷል።

ጽሕፈት ቤቱ፣ “ እውቅናው የለኝም ” ያለ ሲሆን፣ ጉዳዩን እንደሚያውቁት ነዋሪዎች መናገራቸውን ብንገልጽለትም፣ “ እስካሁም ምንም አይነት በሪፓርትም የመጣ ነገር የለም ” ብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቡግና ወረዳ በተጨማሪም ለአማራ ክልል ስጋት አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ተመሳሳይ ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን፣ ኮሚሽኑ ችግሩ መኖሩን አምኗል።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወ/ሮ ፍቅሬ ሙሉጌ በሰጡን ቃል፣ “ ጉዳዩ በኛ ቁጥጥር ውስጥ ነው። ከእኛ አቅም ውጪ የሆነ ነገር የለም ” ሲሉ ተናግረዋል።

አክለውም፣ “ ችግር እንዳለ ይታወቃል። ድጋፍ እየቀረበ ነው። ምንም የተለዬ ነገር የለም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

“ የአምናውን ድርቅ ችግር ተቋቁመናል አሁን እንዲያውም ጥሩ ነው ምርት አምርተዋል ” ሲሉ ተናግረዋል።

ድጋፍ እየተደረገላቸው ከሆነ ምን ያክል ድጋፍ ተደርጓል ? ሰሞኑን ያደረጋችሁት ድጋፍ ነበር ? በተለይ ሰሞኑን ህፃናቱን የሚመግቡት እንደተቸገሩ ነዋሪዎቹ እየገለጹ ነው፣ ስንል ለወ/ሮ ፍቅሬ ተጨማሪ ጥያቄ አቅርበናል።

እሳቸውም በምላሻቸው፣ “ በቂ ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው በተለመደው አግባብ (ድጋፉ የሚሰጥበት ቀመር አለው) ድጋፍ እየደረሳቸው ነው ” ከማለት ውጪ የችግሩን አስከፊነት ከመግለጽ ተቆጥበዋል።

ነዋሪዎቹ የላኳቸው ፎቶዎች ህፃናቱ በምግብ እጥረት እንደተጎዱ የሚመሰክሩ እንደሆኑ ገልጸን፣ ድጋፍ ካለ ጉዳዩ እንዴት በዚህ ልክ ጉዳት እንዳደረሰ ማብራሪያ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ኃላፊዋን ጠይቋል።

በዚህም፣ “ ይለካል እኮ ማልኑውትሬሽን፣ ሞዴሬት የሆኑት እየተለካ ምግብ ሁሉ ይሰጣቸዋል ለእናቶች፣ ለህፃናት ” የሚል ምላሽ ሰጠተዋል።

“ ለዩኒሴፍም ይቀርባል። ለአዋቂዎች ደግሞ እህል ይቀርባል። የገንዘብ ደጋፍም ይሰጣልና ክትልትል እየተደረገ ነው ” ያሉት ወ/ሮ ፍቅሬ፣ “ በመሀል ደግሞ በህመምም በምንም ጉዳት ሊያጋጥም ይችላል ” ነው ያሉት።

የቡግና ወረዳ ኮሚዩኒኬሽንና ኮሚሽኑ ይህን ይበሉ እንጂ የቡግና ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ግን ለቢቢሲ አማርኛ በሰጠው ቃል፣ “ ማህበረሰቡ ምርት ባለማግኘቱ እናቶች ልጆቻቸውን ባግባቡ መግበው የተሻለ የጤና እድገት እንዳይኖራቸው አድርጓል ” ብሏል።

በሌላ በኩል ፤ የሰሜን ወሎ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለሙ ይመር ዛሬ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል " አካባቢው በፋኖ ታጣቂዎች ስር በመሆኑ ለተከሰተው የምግብ እጥረት መንግሥት በቶሎ ምላሽ መስጠት አልቻለም " ብለዋል።

የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባቶች በአደረጉት ጥረትም አሁን ላይ የርዳታ እህል ወደ ስፍራው እየተጓጓዘ መሆኑን አስታውቀዋል።

የወረዳው ነዋሪ ያለበትን የምግብና የጤና ችግር ለፋኖ ታጣቂዎችና ለመንግሥት አካላት ለማስረዳት ከተመረጡት 18 ግለሰቦች መካከል አንዱ ነበርኩ ያሉት ቄስ ገብረ እግዚአብሔር ዝናቤ ይርዳው " በአካባቢው የመንግሥት ባለሥልጣናትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተደረሰው ስምምነት መድኃኒቶችንና አልሚ ምግቦች ወደ ወረዳው እየገቡ ነው " ብለዋል።

የኤሪካ ኤምባሲ ደግሞ ፤ የምግብ እጥረት ቀውስ ሰለመኖሩ የወጡ ሪፖርቶችን እየተከታተለ እንደሆነ አመልክቷል።

ቀውሱ መወገዱን ለማረጋገጥ እንደሚሠራም ጠቅሷል።

ኤምባሲው ቀውሱን በተመለከተ ዝርዝር መረጃዎችን አላካተተም።

የኢትዮጵያን ሕዝብ ለመደገፍ ፣ አጋሮቹ በአሁኑ ሰዓት በችግሩ በተጠቁት አብዛኞቹ ስፍራዎች የምግብ እና አልሚ ንጥረ ምግቦች ስርጭትን ያጠናከሩ መሆናቸውን አክሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
" የመምህራን ደመወዝ አለመከፈልና መቆራረጥ ትምህርታችን ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እያሳደረ ነዉ "- በከምባታ ዞን የሚገኙ ተማሪዎች

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፤ ከምባታ ዞን ስር በሚገኙ ወረዳዎች ዉስጥ ባሉ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች " የበጀት  እጥረት " እየተባለ በሚነገራቸዉ ምክንያት የመምህራን ወርሃዊ ደመወዝ መቆራረጥና መዘግየት በትምህርታቸው ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እያሳደረ ስለመሆኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ቅሬታ ካሰሙ ተማሪዎች መካከል በዳንቦያ ወረዳ የፉንጦ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ፣ በቃዲዳ ጋሜላ ወረዳ ጆሬ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ እንዲሁም በሀዳሮ ጡንጦ ዙሪያ ወረዳ አመሌቃ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህረት ቤት ተማሪዎች ይገኙበታል።

ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ያሰሙ ተማሪዎች ምን አሉ ?

- በደሞዝ መዘግየትና መቆራረጥ ምክንያት መምህራን በተደጋጋሚ ከት/ት ቤት ስለሚቀሩ በየወሩ ከ5-14 ቀናት የማንማርበት አጋጣሚ እየተዘወተረ መጥቷል።

- አንዳንዶቻችን ወደ ትምህርት ቤት ከ30 ደቂቃ በላይ በእግር ተጉዘን ከደረስን በኋላ " በደሞዝ ምክንያት መምህራን አልገቡም " እንባላለን።

- አሁን አሁን በደመወዝ ወቅት መረጃ እየተቀባበልን ለመምህራን ደሞዝ አለመከፈሉን ካረጋገጥን ከትምህርት ቤት እንቀራለን።

- ይህ ተግባር እየተዘወተረ መምጣቱን ተከትሎ በርካታ ወጣቶች ዉሏቸዉን ወደ ፑልና ጆቶኒ ጫወታዎች አዙረዋል።

- ትምህርታቸውን አቋርጠዉ የሚያገቡ ሴት ተማሪዎችም አሉ።

- አከባቢያችን በብዛት ወጣቶች ወደ ዉጪ ሀገራት ከሚሰደዱባቸዉ አንዱና ዋነኛው ነዉ። ባለፈዉ ዓመት በትምህርቱ ላይ ተስፋ ቆርጦ አቋርጦ የተሰደደ ተማሪ አለ።

- ቅሬታችንን ለየትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን እና ዩኒት ሊደሮች እኛም ወላጆቻችንም በተደጋጋሚ አቅርበናል ግን " የደመወዝ ጉዳይ ከትምህርት ቤት አቅም በላይ ነዉ፤ መምህራን ሳይበሉና ሳይጠጡ አስተምሩ ብለን ማስገደድ አንችልም " የሚል ምላሽ ነው የተሰጠን።

ከቅሬታ አቅራቢዎቹ መከካል ዘንድሮ ሀገር አቀፍ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና ተፈታኞች እንደሆኑ የነገሩን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች " የዘመናት ልፋታችንና የወደፊት ህልማችን አደጋ ላይ እየወደቀ ነዉ የሚመለከታቸው አካላት አፋጣኝ መፍትሔ " ይስጡልን ብለዋል።

" ለሀገር አቀፉ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ለመዘጋጀት ተጨማሪ የቲቶሪያል ትምህርት ሊሰጠን ቀርቶ መደበኛ የትምህርት መረሃግብሮች በአግባቡ አይሸፈኑም አሁን በዚህ ወቅት እንኳን አንዳንድ የትምህርት ዓይነቶች ገና አንድና ሁለት ዩኒቶችን (ምዕራፎችን) ብቻ ነዉ በተንጠባጠበ ሁኔታ የተማርነዉ " ሲሉ ገልጸዋል።


መምህራን ምን አሉ ?

" ብዙ ጊዜ ጮኼን ሰሚ አላገኘንም " የሚሉት በከንባታ ዞን የዳንቦያ፣ ሀዳሮ ጡንጦና ቃዲዳ ጋሜላ ወረዳዎች የሚያስተምሩ መምህራን " የደመወዝ በወቅቱ አለመከፈል፣ መቆራረጥና አልፎ አልፎም በፐርሰንት የመክፈል ችግሮች ባላፉት ሁለት ዓመታት እየተባባሱ መጥተዋል ፤ በርካታ መምህራን በዚህ ምክንያት ስራ ገበታቸዉ ላይ በአግባቡ አይገኙም " ሲሉ ገልፀዋል።

የከንባታ ዞን መምህራን ማህበር ተወካይ አቶ አለሙ አቡዬ ምን አሉ ?

° የደመወዝ መዘግየትና እያቆራረጡ መክፈል በከንባታ ዞን ባሉ ሁሉም መዋቅሮች እየተለመደ መጥቷል።

° ችግሩን ለመቅረፍ የሚደረጉ ተግባራት ጉዳዩ ከሚያስፈልገዉ ትኩረትና ከሚያሳድረዉ ተፅእኖ አንፃር በጣም ዝቅተኛ ነዉ።

የከምባታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዳዊት ለገሠ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደተናገሩት ፤ ችግሩ ባለፉት ጊዜያት ዞኑ ያለበትን የብድር ዕዳ ተከትሎ በተከሰተ የበጀት እጥረት በሁሉም የመንግስት መዋቅሮች የሚስተዋል ነው።

" የዞኑ መንግስት ካቢኔ መምህራንን ጨምሮ ለፀጥታ፣ ፍትህ እና የጤና ባለሙያዎች ደመወዝ ቅድሚያ ተሰጥቶ እንዲከፈል ባሳለፈዉ ዉሳኔ መሰረት እየተተገበረ ነዉ " ብለዋል።

" አንዳንድ ወረዳዎች የኋላውን እየሸፈኑና በብድር የተጠቀሟቸዉን በጀቶች እያተካኩ በሚሄዱበት ወቅት የደሞዝ መዘግየቶች ሊያጋጥሙ ይችላሉ። የመማር ማስተማሩ ተግባር እንዳይቆራረጥ በተቻለ መጠን ሁሉ የዞኑና የክልሉም መንግስት ትኩረት ነዉ " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#Ethiopia #France

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያ ገቡ።

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከደቂቃዎች በፊት ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዝዳንቱ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ነው አዲስ አበባ የገቡት።

ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርሱ የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተቀብለዋቸዋል።

ማክሮን አዲስ አበባ ከመምጣታቸው በፊት በጎረቤት ሀገር ጅቡቲ የስራ ጉብኝት አድርገዋል።

ቪድዮ ፦ ቢኤፍኤም ቲቪ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia #France የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያ ገቡ። የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከደቂቃዎች በፊት ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ገብተዋል። ፕሬዝዳንቱ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ነው አዲስ አበባ የገቡት። ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርሱ የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተቀብለዋቸዋል። ማክሮን አዲስ አበባ ከመምጣታቸው በፊት በጎረቤት ሀገር ጅቡቲ የስራ ጉብኝት አድርገዋል።…
ፎቶ፦ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን የፈረንሳይ ፕሬዜዳንት ኢማኑኤል ማክሮንን ተቀብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማክሮንን " ወንድሜ እና የኢትዮጵያ የልብ ወዳጅ " ሲሉ ገልጸዋቸዋል።

" በሁለቱ ሀገሮች መካከል ያለው ግንኙነት የበለጠ በመጠናከር ላይ ይገኛል " ያሉት ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ፍሬያማ ውይይት እንደሚኖር እምነታቸውን ገልጸዋል።

የማክሮንን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ተከትሎ ዋና ዋና የአዲስ አበባ መንገዶች ላይ የተተከሉ የማስታወቂያ ስክሪኖች " ፕሬዜዳንት ማክሮን እንኳን ወደ ኢትዮጵያ በሰላም መጡ " የሚሉ መልዕክቶች እየተላለፈባቸው ነው።

ማክሮን ፤ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ኢትዮጵያ ለስራ ጉብኝት ሲመጡ በ6 ዓመታት ይህ ሁለተኛቸው ነው።

Photo Credit - PM Office & Oliver Liu

@tikvahethiopia
#Ethiopia #USA #Starbucks

የአሜሪካው ' ስታርባክስ / Starbucks ' ኤክስኪዩቲቭ ቫይስ ፕሬዝዳንት ሚሼል በርን ኢትዮጵያ፣ አዲስ አበባ ይገኛሉ።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማሲንጋ እና የUSAID ዳይሬክተር ሆክላንደር ለበርን አቀባበል አድርገውላቸዋል።

አሜሪካ በኤምባሲዋ በኩል የስታርባክስን አመራር " እንኳን ወደ ኢትዮጵያ፤ ወደ ቡና መገኛዋ ሀገር በደህና መጡ " ብላለች።

የስታር ባክስ አመራር ሚሼል በርን በኢትዮጵያ ቆይታቸው በኢንዱስትሪው ውስጥ ስላለው አስደናቂ እድገት፣ በምርታማነት ላይ ስላሉ ኢንቨስትመንቶች ይመክራሉ ተብሏል።

በተጨማሪም በኢትዮጵያ ላሉ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የንፁህ ውሃ አቅርቦትን ማሳደግ በተመለከተ ይወያያሉ።

ስታር ባክስ (starbucks) በቡና አቅርቦቱ በመላው ዓለም የሚታወቅ ከፍተኛ ሃብት ያለው ኩባንያ ነው።

@tikvahethiopia
#MPESASafaricom
የመብራት ክፍያችንን በM-PESA በመክፈል 10% ተመላሽ ገንዘባችንን አሁኑኑ እናግኝ ፤ መብራታችንም እንደበራ ይቆየን!

የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ ፡ https://play.google.com/store/apps/details... የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉https://yangx.top/Safaricom_Ethiopia_PLC

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም   ቻናላችን https://yangx.top/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#FurtherAheadTogether
TIKVAH-ETHIOPIA
" ትኩረት መነፈጋችን እጅጉን አሳዝኖናል " - የሽርካ ወረዳ ነዋሪዎች በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሽርካ ወረዳ ታኅሣሥ 5 እና 6 ቀን 2017 ዓ.ም የወረዳ ቤተ ክህነቱን ሥራ አስኪያጅ ጨምሮ 20 ኦርቶዶክሳውያን በታጣቂዎች ግድያና እገታ እንደተፈጸመባቸው ነዋሪዎቹን ዋቢ በማድረግ የቤተክርስቲያኒቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ከታገቱት ውስጥ የወረዳው ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅና ሌሎች 8 ሰዎች ገንዘብ…
#Update

“ 11 ሰዎች አሁንም ያሉበት አልታወቀም። አንድ ሰው መገደሉ ተረጋግጧል ” -የሽርካ ወረዳ ቤተ ክኀነት

በአርሲ ዞን፤ ሽርካ ወረዳ በታጣቂዎች ታገቱ የተባሉ በርካታ ነዋሪዎች ያሉበት እንደማይታወቅ የወረዳው ቤተ ክኀነትና ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የአካቢው ነዋሪዎች፣ “ ታጣቂዎቹ እገታውን የፈጸሙት ታኃሳስ 5 እና 6 ቀን 2017 ዓ/ም ነው። ከ20 በላይ ሰዎች ናቸው በታጣቂዎች የተወሰዱት ” ብለዋል።

የታገቱት የወረዳው ቤተ ክኀነት ስራ አስኪያጅ ጭምር መሆኑን ተናግረው፣ ሥራ አስኪያጁን ጨምሮ ዘጠኝ ሰዎች ገንዘብ ከፍለው እንደተለለቁም ሰሞኑን ገልጸውልን ነበር።

ቁጥራቸው በትክክል ባይታወቅም ከታጋቾቹ ውስጥ የተገደሉ ሳይኖሩ እንዳልቀረ፣ ቀሪዎቹ ታጋቾች ከእገታ እንዳልተመለሱ፣ ጭራሹንም ያሉበት እንደማይታወቅ ነዋሪዎቹ አስረድተዋል።

“ እንዲህ አይነት ድርጊት ሲፈጸም ይህ የመጀመሪያው አይደለም። በየጊዜው የሸኔ ታጣቂዎች በሚፈጽሙት እገታ ብዙ ሰዎች ተገድለዋል፣ እድለኛ የሆኑት በ100 ሺዎች ገንዘብ እየከፈሉ የተለቀቁ አሉ ” ሲሉ አስታውሰዋል።

“ እስከመቼ ድረስ ነው ህዝቡ በተወለደበት አገር በእንዲህ አይነት ሰቀቀን የሚኖረው ? የፍርድ ቀን እስኪመጣ ጮኸታችንን አሰሙልን ” ሲሉ ተማጽነዋል።

ስለጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የወረዳው ቤተ ክኀነት ሥራ አስኪያጅ ከቀናት በፊት በሰጡን ቃል፣ “ አሁን እቤቴ ገባሁ። ከእኔ ጋር ተይዘው የነበሩ ስምንት ሰዎች ጋር በአጠቃላይ ዘጠኝ ሰዎች ተለቀዋል ” ብለዋል።

የወረዳው ቤተ ክኀነት በዛሬው ዕለት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ደግሞ፣ “ 11 ሰዎች ያሉበት አይታወቅም። አንድ ሰው መሞቱ ተረጋግጧል ” ብሎ የሁነቱን አሳሳቢት አስረድቷል።

የተለቀቁት ሰዎች ምን ያህል ገንዘብ በመክፈል እንደተለቀቁ ላቀረብነው ጥያቄ ሥራ አስኪያጁ በሰጡት ማብራሪያ፣ የገንዘቡ ጉዳይ ለመናገር እንኳ የሚመር መሆኑን ገልጸው፣ ብቻ የተለቀቁት ገንዘብ ከፍለው መሆኑ እንዲታወቅ ገልጸዋል።

“ የተወሰድንበት አቅጣጫው ስለሚለያይ፣ እኔም ሰሞኑን ችግር ላይ ስለከረምኩ መረጃውን ገና በደንብ ሰብስቤ ተጨማሪ ማብሪራያ እሰጣለሁ ” ሲሉ ጠቁመዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#DStvEthiopia

ደማቁ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ወደ ሜዳ ተመልሰዋል💥
ቶተንሃም ከሊቨርፑል በ ቶተንሀም ስታዲየም የሚያደርጉተን ደመቅ ጨዋታ በቀጥታ በSS Premier League Ch 223 በሜዳ ፓኬጅ በቀጥታ ይከታተሉ!
👉እነዚህን ድንቅ ፍልሚያዎች ጨምሮ ሌሎች የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ይመልከቱ።

ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

ደንብና ሁኔታዎች ተፈፀሚነት አላቸው! ለበለጠ መረጃ
👇
www.dstv.com/en-et
#PremierLeagueallonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው