የሕግ ባለሙያውና ጠበቃው ምን ገጠማቸው ?
" ቅስም ይሰብራል ! " - የሕግ ባለሙያና ጠበቃ አንዷለም በውቀቱ
🔴 " ሰፈሩ መፍረሱና መልሶ መልማቱ ላይ ተቃውሞ የሌለውን ኮሚኒቲ በ2 እና በ3 ሰአት እያዋከቡ ማስወጣት መውደቂያውን ሳያውቅ ማሳቀቅ መጨረሻው ይሄ ነው !! "
የሕግ ባለሙያና ጠበቃ የሆኑት አንዷለም በውቀቱ ዛሬ እጅግ ቅስማቸውን የሰበረ ክስተት እንደገጠማቸው ገልጸዋል።
ነገሩ እንዲህ ነው ...
ባለፈው አርብ " ፒኮክ መናፈሻ " አካባቢ አትክልት በማምረት ስራ የሚተዳደሩ ቤተሰቦችና ልጆቻቸው ቢሯቸው ይመጣሉ።
እነዚሁ ነዋሪዎች " ሰፈሩ ለልማት ሊነሳ ነው እየተባለ ነው። ከወላጆቻችን ዘመን ጀምሮ በአካባቢው ለ73 አመታት ቆይተናል። ድንገት ተነሱ ብንባል ምን ይዋጠን!? " ሲሉ ይገልጹላቸዋል።
እሳቸውም " መጀመሪያ የምትሄዱበትን ቦታ ማመቻቸት የመንግስት ግዴታ ነው። ያ ሳይሆን ለማስነሳት እንቅስቃሴ የሚደረግ ቢሆን ለፍርድ ቤት አቤቱታ አቅርቤ እግድ እንዲሰጣችሁ አደርጋለሁ ! " ብለዋቸው ይለያያሉ።
ቅዳሜ ጉዳዩ የሚታይበትን አግባብ ሲያዘጋጁ እንደዋሉ የሚናገሩት የሕግ ባለሙያው ፤ እሁድ ጠዋት ግን ስልክ ይደወልላቸው። በዚህም " ከቤተክርስትያን ስንመለስ ቤታችን እየፈረሰ አገኘነው " ሲሉ እነዚሁ ቤተሰቦች ይነግሯቸዋል።
እሳቸውም ከባልደረባቸው ጋር ወደ ቦታው ሄዱ።
አፅናንተዋቸው " መትረፍ የሚችለውን ለማስቆም እንሞክራለን " ይሏቸዋል።
እስከ ማታ ድረስ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጨምሮ ለሚመለከታቸው አካላት የህግ አቤቱታዎችን ሲያዘጋጁ ያመሻሉ።
ሰኞ ጠዋት ኮሚኒቲው ህጋዊ የህብረት ስራ ማህበር ያላቸው በመሆኑ በማህበራቸው ስም ሊቀመንበሩ አቶ ዱላ ኑርጋ ውክልና እንዲሰጧቸው እንደተነጋገሩ የሕግ ባለሙያው አመክተዋል።
ትላንት ከሰአት ሊቀመንበሩ የጠበቃ ውክልና ለመስጠት የማህበሩን የመመስረቻ ጽሁፍ ስላጡት ለማክሰኞ ጠዋት እንደሚሰጧቸው ቀጥሮ ይይዛሉ።
ዛሬ ጠዋት ሊቀመንበሩ አቶ ዱላ ከቤታቸው ሲወጡ ግን የማህበሩ አባላት ሰፈር ውስጥ ለማፍረሻ የመጣ ዶዘር ቆሟል።
ሌሎች አባላቶች ውክልና ለመስጠት ውልና ማስረጃ እየጠበቋቸው ነበር።
እንደ ሕግ ባለሙያው ማብራሪያ ሊቀመንበሩ አብራቸው ከቤት የወጡትን ባለቤታቸውን " መጣሁ እየሄድሽ ጠብቂኝ ! " ብለዋቸው ወደ ቤት ይመለሳሉ።
በኃላም በአንዲት ቀጭን ሲባጎ እራሳቸውን አንጠልጥለው እንደተገኘ አስረድተዋል።
የሕግ ባለሙያው ዛሬ ጠዋት 3:00 ላይ አቤቱታውን ይዘው የአቶ ዱላን ስልክ ሲጠብቁ እንደነበር ገልጸዋል። መጨረሻው ግን ፍጹም አሳዛኝ ነው የሆነ።
" ሰፈሩ መፍረሱና መልሶ መልማቱ ላይ ተቃውሞ የሌለውን ኮሚኒቲ በ2 እና በ3 ሰአት እያዋከቡ ማስወጣት መውደቂያውን ሳያውቅ ማሳቀቅ መጨረሻው ይሄ ነው " ሲሉ የሕግ ባለሙያው ሁኔታውን በሀዘን ገልጸዋል።
" አቶ ዱላ ለ20 አመት ያህል በሊቀመንበርነት ያገለገሉትን ከ70 አመት በላይ በአንድ ቦታ የቆየውን ለፍቶ አዳሪ ማህበረሰብ ' ፌይል አደርጌያቸዋለሁ ' ብለው እራሳቸውን አጥፍተዋል " ያሉት የሕግ ባለሙያው " እኔም ያንን ኮሚኒቲ ፌይል አድርጌዋለሁ። ትላንት አቤቱታውን ባስገባ ምናልባት ሊቀመንበሩ ከውሳኔው ይቆጠብ ይሆን?! ከጠዋት ጀምሮ በሰቀቀን ውስጥ ነኝ! ቀብራቸው ነገ ይፈጸማል! ነፍሳቸውን ፈጣሪ ይቀበላት!! " ሲሉ ቃላቸውን ደምድመዋል።
#AddisAbaba
@tikvahethiopia

#AddisAbaba : የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዳዲስ ሹመቶችን ሰጥቷል።
አቶ ግርማ ሰይፉ ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ተነስተው የከተማ ውበትና አረንጏዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል
ወ/ሮ ቆንጂት ደበለ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነዋል።
ከዚህ ባለፈ ወ/ሮ ኒዕመተላህ ከበደ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነዋል።
ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ ከከተማ ውበትና አረንጏዴ ልማት ቢሮ ኃላፊነት ተነስተው የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ስራ አስኪያጅ ሆነው ተሹመዋል።
አቶ ሙባረክ ከማል የባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ ፤ አቶ ሁንዴ ከበደ - የባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የባህል ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ሆነው መሾማቸው ታውቋል።
አቶ ታረቀኝ ገመቹ ደግሞ የንግድ ቢሮ ፅ/ቤት ኃላፊ ሆነዋል።

“ አንዳች ነገር ኮሽ ባላለበት ከተማ ‘ቦምብ ፈነዳ፣ ሰዎች ሞቱ ፣ የፓሊስ አባላት ሞቱ ’ እየተባለ ስለሚወራው ወሬ ራሱ ነዋሪው ነው የሚታዘባቸው ” - የአዲስ አበባ ፓሊስ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር “ ሰሚትና አያት አካባቢዎች የቦንብ ፍንዳታ ተከስቷል ” የሚሉ ወሬዎች ከትላንት ጀምሮ በX (ትዊተር) ላይ በስፋት ሲራወጡ ተስተውሏል።
ይህ መረጃ ዋና መነሻው የኢትዮጵያን ጉዳይ እየተከታተሉ ከሚፅፉ ገጾች ነው።
ጉዳዩን ግን በብዛት ሲያሰራጩት የተስተዋሉት ግብፃዊያን እና ሱማሊያዊያን ሲሆኑ፣ በቦምብ ፍንዳታው ሰዎች እደሞቱ ፣ የፓሊስ አባላት እንደተገደሉ ነው መረጃ ሲያሰራጩ የተስተዋሉት።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ በX (ቲዊተር) እየተራወጠ ያለውን መረጃ በተመለከተ የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽንን መልዕክት እንዲያስተላልፍ ጠይቋል።
የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ፣ “ በከተማዋ ያለው ሰላም አስተማማኝ ነው ” ብዋል።
እንዲህ ያለ የሐሰተኛ መረጃ በሚነዙ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ በአንክሮ ገልጸዋል።
ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ምን አሉ ?
“ ማንም በዬጫት ቤቱ ቁጭ ብሎ የሚያወራውን የመንግስት ተቋም ምላሽ የሚሰጥ ከሆነ በጣም አስቸጋሪ ነው የሚሆነው።
ማኀበራዊ ድረ ገጹ እንደሚታውቀው ነው።
በጣም ጥቂት ድረገጾች ናቸው ትክክለኛና ታማኝ መረጃ የሚዘግቡት እንጂ በአብዛኛው የከተማው ሰላም መሆን የሚያስጨንቃቸውም ስለሆኑ ዓይናቸው ደም ይለብሳል።
እንደዚህ ተወለደ ፣ እንደዚህ ተፈጠረ እያሉ ያልተፈጠረ ነገር እያወሩ ሰው በሰላም ገብቶ እንዳይወጣ ሽብር የመንዛት ሀሳብ ነው ያላቸው።
የከተማው ሰላም አስማማኝ መሆኑን 24 ሰዓት የነዋሪውን እንቅስቃሴ በማዬት ብቻ ማረጋገጥ ይቻላል። ምንም አይነት ጥናትም የሚያስፈልገው ጉዳይ አይደለም።
ከተማው 24 ሰዓት ክፍት ነው። አንዳች ነገር ኮሽ ባላለበት ከተማ ‘ቦምብ ፈነዳ፣ ሰዎች ሞቱ፣ የፓሊስ አባላት ሞቱ’ እየተባለ ስለሚወራው ወሬ ራሱ ነዋሪው ነው የሚታዘባቸው።
የተለመደ የበሬ ወለደ አይነት ወሬያቸው ነው። ዞሮ ዞሮ የከተማው ነዋሪ አሁን በጣም ገብቶታል። ለእነርሱ የሐሰት መረጃም ምንም ምላሽም አይሰጥም ትዝም አይለውም። መደበኛ ሥራውን ነው የሚምራው።
ከተማው አንዳችም የጸጥታ ችግር ያለበት ሁኔታ ላይ አይደለም። ሰላማዊ የሆነ እንቅስቃሴ ነው ያለው።
ምንም ነገር በሌለበት ሁኔታ እንደዚህ የሚሉ ግለሰቦችም ይሁኑ ቡድኖች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ነው መልዕክት ማስተላለፍ የምንፈልገው።
እንደ አዲስ አበባ ፓሊስ የከተማው የጸጥታ ጉዳይ በቀጥታ የሚመለከተው ነው። ኃላፊነትም ተቀብሎ እየተንቀሳቀሰበት ያለ ጉዳይ ነው። እንደዚህ አይነት ሥራ በሚሰሩ ሰዎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ ይወስዳል። ” ብለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA

በተለያዩ ቀናት ከሦስት ድርጅቶች ስልክና ላፕቶፕ ሲሰርቅ በካሜራ ዕይታ የገባው ግለሰብ በፖሊስ እየተፈለገ ነው።
በአዲስ አበባ ከተማ በቂርቆስ እና በቦሌ ክፍለ ከተማ በቀናት ልዩነት በ 3 ድርጅቶች የላፕቶፕ እና የሞባይል ስልኮች ስርቆት በተመሳሳይ ግለሰብ መፈጸሙን ዝርፊያው የተፈጸመባቸው የንብረቱ ባለቤቶች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል ።
ግለሰቡ የስርቆት ድርጊቱን ፈጸመ የተባለው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሁለት እና ሦስት እንዲሁም በቦሌ ክፍለ ከተማ ቦሌ መድኃኒአለም አቢሲኒያ ህንጻ አካባቢ ነው።
ለቲክቫህ ቃላቸውን የሰጡ ስርቆቱ የተፈጸመባቸው ግለሰብ "ህዳር ዘጠኝ ስምንት ሰዓት ላይ ወሎ ሰፈር አካባቢ የሚገኝ ህንጻ ስድስተኛ ፎቅ ወደሚገኝ ቢሮአችን ነጭ ቲሸርት እና ጅንስ ሱሪ አድርጎ የገባ ግለሰብ ሪሰፕሽን ላይ ሰው አለመኖሩን በማረጋገጥ ላፕቶፕ ይዞ ተሰውሯል" ብለዋል።
ግለሰቡ የስርቆት ድርጊቱን ሲፈጽም በድርጅቱ በተገጠመ የደህንነት ካሜራ የተቀረጸ ሲሆን ላፕቶፑን በቲሸርቱ ውስጥ በመደበቅ ይዞ ሲወጣ ይታያል።
ስርቆቱ የተፈጸመባቸው ግለሰብ ግለሰቡን የሚያውቀው ሰው ካለ በሚል በማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በደህንነት ካሜራ የተቀረጸውን ቪዲዮ ማጋራታቸውን ተናግረዋል።
መረጃውን በማህበራዊ ሚዲያ ካጋሩት በኋላ በቀናት ልዩነት እኛም በተመሳሳይ ሰው ተዘርፈናል የሚሉ ግለሰቦች እንዳነጋገሯቸው ገልጸውልናል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም ስርቆቱ የተፈጸመባቸው ሌላኛውን ተበዳይ በማነጋገር ዝርፊያው መፈጸሙን አረጋግጧል።
ግለሰቡ ቦሌ መድኃኒአለም አካባቢ ወደሚገኝ ህንጻ በመግባት ስርቆቱን የፈጸመው ህዳር 9 ሰኞ የስርቆት ድርጊቱን ከፈጸመ ከአምስት ቀናት በኋላ ማለትም ህዳር 14 ቅዳሜ ቀን ሲሆን በዕለቱ ጥቁር ቲሸርት እና ጅንስ ሱሪ በመልበስ ስልኮቹን ሲያነሳ በተመሳሳይ በደህንነት ካሜራ እይታ ውስጥ ገብቷል።
በቀናት ልዩነት አንድ ላፕቶፕ እና ሁለት ስልኮችን ከሁለት የተለያዩ ድርጅቶች ሰርቆ የተሰወረው ይህ ግለሰብ ጻጉሜ 4/2016 ዓም ቂርቆስ ክፍለ ወረዳ ሁለት ፍላሚንጎ አካባቢ በተመሳሳይ ሰው የስርቆት ድርጊት ተፈጽሞብኛል ያሉ ግለሰብም ቃላቸው ለቲክቫህ ሰጥተዋል።
"ፍላሚንጎ ሰንሻይን ኮንስትራክሽን አካባቢ ወደሚገኝ ቢሮአችን በመግባት ላፕቶፕ በመስረቅ ተሰውሯል ለፖሊስ ብናመለክትም ስሙንም ሆነ አድራሻውን ማወቅ አልተቻለም" ሲሉ ነግረውናል።
ሶስቱም ግለሰቦች በተመሳሳይ ሰው መሰረቃቸውን ያወቁት ወሎ ሰፈር ከሚገኝ ቢሮአቸው ላፕቶፕ የተሰረቁት ግለሰብ ተንቀሳቃሽ ምስሉን በማህበራዊ ሚዲያ ማጋራታቸውን ተከትሎ ነው።
የስርቆቱ ድርጊቱ የተፈጸመባቸው ግለሰቦች ውስጥ ሁለቱ የደህንነት ካሜራውን ምስሎች እና አስፈላጊውን መረጃዎች በመያዝ ለፖሊስ ቢያመለክቱም ግለሰቡ እስካሁን በቁጥጥር ስር አልዋለም።
ፖሊስ ምን አለ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን በመያዝ ጉዳዩን እየተከታተለ የሚገኘውን በአዲስ አበባ ፖሊስ የመስቀል ፍላወር አከባቢ ፖሊስ ጣቢያ አነጋግሯል።
ፖሊስ "በእኛ በኩል ሰውዬውን ለመያዝ በክትትል ላይ ነው የምንገኘው እስካሁን ገና አልተያዘም ቦሌ እና ቂርቆስ ላይ ወንጀሉን ፈጽሟል በክትትል ላይ ነው ያለነው " የሚል ምላሽ ሰጥቷል።
ግለሰቡን ያያቹ ወይም ያለበትን የምታውቁ ከታች በተቀመጡት ስልኮች በመጠቆም ትብብር እንድታደርጉ ጥሪ ቀርቧል።
ለጥቆማ፡ 0114621442, 0911115656

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ምንድነው ያስተላለፈው ውሳኔ ?
💡" ምሽት መብራት ማጥፋት እንዲከለከል እና ሙሉ የመብራት አገልግሎት እንዲኖር ውሳኔ ተላልፏል ! "
🌃 " ዋና እና መጋቢ መንገድ ላይ የሚገኙ የንግድ እና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት እስከ ምሽቱ 3፡30 አገልግሎት እንዲሰጡ ተወስኗል ! "
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ዛሬ 4ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ስብሰባ አካሂዶ ነበር።
የተለያዩ አጀንዳዎች ላይም ተወያይቶ አፅድቋል፡፡
ከነዚህም አንዱ ፥ በሁሉም የከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች ያሉ የንግድ እና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት እስከ ምሽቱ 3፡30 ለህብረተሰቡ የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚል ነው።
ሌላኛው የምሽት ትራንስፖርትን ይመለከታል።
በዚህም ከተማ አስተዳደሩ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች ማቅረብ በመጀመሩ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች አገልግሎት አስተዳደር ረቂቅ መነሻ ሀሳብ መርምሮ በመወያየት በመንግስት እና የግል አጋርነት (PPP) እንዲተዳደሩ ብሎም በከተማዋ የመንግስት እና የግል ትራንስፖርት አገልግሎት እስከ ምሽቱ 4፡00 ድረስ ግልጋሎት እንዲሰጡ ተብሏል።
በሁሉም የኮሪደር ልማት በሚተገበርባቸው ቦታዎች የትራንስፖርት አገልግሎት እለታዊ የጊዜ ሰሌዳ እንዲጠቀሙ እንዲደረግ ተወስኗል።
ከዚህ በተጨማሪ ካቢኔው ሁሉም ዋና መንገድ እና መጋቢ መንገድ ላይ ያሉ ተቋማት፣ ህንፃዎች እንዲሁም የግልና የመንግስት ቢሮዎች ምሽት መብራት ማጥፋት እንዲከለከል እና ሙሉ የመብራት አገልግሎት እንዲኖር ውሳኔ ተላልፏል።
በተጨማሪ ካቢኔው ፦
- የወንዝ እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ብክለት መከላከል ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ለከተማዋ ነዋሪዎች ጤና፣ ፅዳት እና ውበት ወሳኝ እና ጠቃሚ ስለሆነ ደንቡን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።
- በከተማ ፕላን ልማት ቢሮ የተዘጋጁና የሚዘጋጁ የአካባቢ ልማት ፕላን ዝግጀት፣ አፈፃፀም ቁጥጥር እና ደንብ ማሻሽያን መርምሮ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡