TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
" ለጥንቃቄ ሲባል መንገደኞች እና የበረራ ሠራተኞች በአስቸኳይ ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ ተደርጓል " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

የበረራ ቁጥሩ ET 612 የሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ታህሳስ 05 ቀን 2017 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ ወደ ዱባይ በሚያደርገው በረራ ከተነሳ ከ30 ደቂቃ በኋላ የቴክኒክ ችግር አጋጥሞታል።

በዚህም አውሮፕላኑ ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በሰላም አርፏል።

ለጥንቃቄ ሲባል መንገደኞች እና የበረራ ሠራተኞች በአስቸኳይ ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ መደረጉን አየር መንገዱ አሳውዋል።

" ሁልጊዜም ለመንገደኞቼ ደህንነት ቅድሚያ እሰጣለሁ " ያለው አየር መንገዱ መንገደኞች ለደረሰባቸው መጉላላት አየር ይቅርታ ጠይቋል።

የቴክኒክ ችግሩ በመጣራት ላይ መሆኑንም ገልጿል።

@tikvahethiopia
#DStvEthiopia

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የማንቼስተር ደርቢ በጎጆ ፓኬጅ💥
63ተኛውን ጨዋታዎቸውን የሚያደርጉት ሁለቱ ቡድኖች ማን ሲቲ 25 ጊዜ ሲያሸንፍ ማን ዩናይትድ 28 ጊዜ ድል አድርጓል! ሁለቱ ብድኖች 9 ጊዜ በአቻ ተለያይተዋል

🏆 ማን ሲቲ ከማን ዩናይትድ ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ ጨምሮ 10 የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎችን በጎጆ ፓኬጅ በ400 ብር ብቻ በቀጥታ ይከታተሉ!

ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

ደንብና ሁኔታዎች ተፈፀሚነት አላቸው! ለበለጠ መረጃ
👇
www.dstv.com/en-et
#PremierLeagueallonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው
#ዮናታን_ቢቲ_ፈርኒቸር

በዓሉን ምክንያት በማድረግ ልዩ ቅናሽ በተደረገባቸው የቤት እቃዎቻችን ቤትዎን ያድምቁ 🎁

የውበት ፣የጥራት እና የምቾት ዳር ድንበር
ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር !

🌐 የማህበራዊ ገጾቻችንን ይቀላለቀሉ

Telegram  👉 Telegram/yonatanbtfurniture
Facebook 👉 Facebook/yonatanbtfurniture
Insagram  👉 Instagram/yonatanbtfurniture
TikTok       👉 TikTok/yonatanbtfurniture

📍አድራሻችን

1. ፒያሳ እሪ በከንቱ ቢቲ ታወር (ከኢቲዮ ሴራሚክ ዝቅ ብሎ)
2. ከዊንጌት አደባባይ አለፍ ብሎ ከአቢሲኒያ ባንክ ፊትለፊት
3. ከሲኤምሲ አደባባይ ወደ አያት መንገድ መሪ ሳይደርስ (ዘመን ባንክ አጠገብ)

☎️ ይደውሉልን
+251957868686
+251995272727
+251993828282
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተመዝግበዋል? እንግዲያውስ ይህን ያስተውሉ።

#ፋይዳ #ፋይዳለኢትዮጵያ #Fayda #DigitalID
TIKVAH-ETHIOPIA
#OFC “ አሁንም ቢሆን ሀገራዊ ምክክሩ በሚሄድበት አቅጣጫ እርካታ የለንም ” - ኦፌኮ ከዚህ ቀደም በምክክሩ እንደማይሳተው ገልጾ የነበረው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ) አሁንም እየተሳተፈ እንዳልሆነ፣ ኮሚሽኑ በሚሄድበት አቅጣጫ እርካታ እንደሌለው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጿል። ፓርቲው ከዚህ ቀደም በሀገራዊ ምክክሩ እንዲሳተፍ ቢጋበዝም በምክክሩ እንዳልተገኘ አስታውሷል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ፣…
" በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ ክልል በሚደረገው ምክክር ላይ ኦፌኮ እንዲሳተፍ ጥሪ አቀርባለሁ " - ኮሚሽኑ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኢትዮጵያ የሚስተዋሉ አለመግባባቶች በሰላማዊ መንገድ ይፈቱ ዘንድ አጀንዳዎች እያሰባሰበ መሆኑ ይታወቃል። 

ኮሚሽኑ እስካሁን በ10 ክልሎች አጀንዳ እንዳሰባሰበ፣ አንዳንድ የፓለቲካ ፓርቲዎች ግን አጀንዳቸውን በማስረብ ፋንታ ከኮሚሽኑ እንዳገለሉ መግለጻቸው ይታወሳል።

የኦሮሞ ፈደራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ) ፓርቲ ከሳምንታት በፊት በሰጠን ቃል፣ " አሁንም ቢሆን ሀገራዊ ምክክሩ በሚሄድበት አቅጣጫ እርካታ የለንም " ብሎ ነበር።

ፓርቲው ይህን ያለው ኮሚሽኑ ተጠሪነቱ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቢሆንም “ምክር ቤቱም በገዢው ፓርቲ የተሞላ ስለሆነ ገልተኛነቱ ያን ያክል አስተማማኝ አይደለም” በማለት ጭምርም ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ ኮሚሽኑን ፓርቲዎችን ለማካተት ምን እየተሰራ እንደሆነ በወቅቱ ጠይቆ ምላሽ ማግኘት ሳይቻል የቆዬ ሲሆን፣ ኮሚሽኑ አሁን ምላሽ ሰጥቷል።

ምን አለ ?

" ኮሚሽኑ ገለልተኛ ተቋም ነው። ተቃዋሚ የፓለቲካ ፓርቲዎች በሂደቱ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርቧል።

ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚሰሩ ሌሎች ፓርቲዎችም በኦሮሚያ ክልል በሚደረገው ምክክር ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አድርጓል። በምክክሩ አብዛኛዎቹ የፓለቲካ ፓርቲዎች ፈቃደኛ ሆነው በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

ኦፌኮ እንደተባለው ሂደቱን ለመቀበል ፈቃኛ አይደለም። ኮሚሽኑ ፓርቲው ፈቃደኛ ያልሆነበትን ምክንያት በተደጋጋሚ ከኦፌኮ ጋር  በአካልም እንደገና በደብዳቤም እንነጋገር በሚል ጥረት አድርጓል።

 ፓርቲው ግን ፈፈቃደኛ መሆን አልቻለም። በዚህ ሂደት የኮሚሽኑ እይታ ፓርቲው በማንኛውም ሰዓት ሀሳቡን ለውጦ ለመመካከር ከመጣ ኮሚሽኑ በሩ ክፍት ነው።

ግን ኮሚሽኑ በራሱ መንገድ ለመሳተፍ ፈቃደኛ ያልሆነውን አካል አስገድዶ ማሳተፍ አይችልም። ስለሆነሞ ኦፌኮ እንደ ኦሮሚያ በምክክሩ ባለመሳተፉ ኮሚሽኑ ያዝናል።

በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ ክልል በሚደረገው ምክክር ላይ ኦፌኮ እንዲሳተፍ ጥሪ እናቀርባለን። ምክክሩ ላይ ልዩነትን ይዞ እስከመጨረሻው መሄድ ይቻላል። 

የሀሳብ የበላይነት እንጂ የኃይል የበላይነት በምክክሩ ላይ  አይንጸባረቅም። በሀገራዊ ምክክሩ የፓለቲካ ፓርቲዎች አጀንዳዎቻቸውን ለማህበረሰቡ ግልጽ ማድረግ ይችላሉ።

በሚስማሙባቸው ጉዳዮች ላይ ይስማማሉ በማይስማሙባቸው ጉዳዮች ላይ ደግሞ በልዩነት መሄድ ይችላሉ። ሀገራዊ ምክክሩ በባህሪው በትውልድ መካከል ከረጅም ጊዜ በኋላ የሚመጣ በመሆኑ ሂደቱን ከማበላሸት ይልቅ አሁንም ቢሳተፉ ይመረጣል።

ኮሚሽኑ አካታች ነው። ፈቃደኛ የሆኑትን አካቶ እየሰራ ነው። ፈቃደኛ ያልሆኑት እስከመጨረሻው እንዲመጡ በሩ ክፍት ነው፣ ይጠብቃል። ምንም አይነት አሉታዊ ተፅዕኖም እንደማይደርስባቸው ኮሚሽኑ ዋስትና ይሰጣል። ”

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅ .pdf
“ የግል ትምህርት ቤቶችን መፈናፈኛ የሚያሳጣ፣ አለመፈለጋችንን በግልጽ ያስረዳ ረቂቅ ዐዋጅ ነው ” - የኢትዮጵያ የግል ትምህርት ቤቶች ማኀበር

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወደ ቋሚ ኮሚቴ መራው የተባለው የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ ዐዋጅ ላይ ብርቱ ተቃውሞ እንዳለው የኢትዮጵያ የግል ትምህርት ቤቶች ማኀበር በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ገለጸ።

የማኀበሩ ፕሬዜዳንት አቶ አበራ ጣሰው፣ “ የግል ትምህርት ቤቶችን መፈናፈኛ የሚያሳጣ፣ አለመፈለጋችንን በግልጽ ያስረዳ ረቂቅ ዐዋጅ ነው ” ሲሉ ተችተውታል።

ፕሬዜዳንቱ በዝርዝም ምን አሉ ?

በረቂቁ ብዙ ነገሮች መሻሻል አለባቸው። አንኳር አንኮር የሆኑትን ለማንሳት፦ 

አንዱ ‘አንድ የግል ትምህርት ቤት ት/ቤት ሆኖ ለመቀጠል ‘የ6 ወራት የሰራተኞችን ደመወዝ በዝግ ሂሳብ ቁጥር ማስቀመጥ አለበት’ የሚለው ነው።

ይሄ ገንዘብ ከተቀመጠ በኋላ መቼ እንደሚወጣ አይታወቅም፣ Forever እንዲቀመጥ ነው እንድምታው። ምክንያቱም ገንዘቡ ከወጣ ፈቃድ ይነጠቃል።

አንደኛ የትምህርት ሥራ እንደንኛውም ድርጅት ንግድ ነው። በግብርና፣ በኢንዱስትሪና በላሎች የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ነጋዴዎች ያለምንም ዋስትና ስራቸውን እያከናወኑ ነው ያሉት።

ዋስትና መሠረቱ ጥርጣሬ ነው። ስለዚህ እነዚህ ሁሉ ድርጅቶች ሳይጠረጠሩ የትምህርት ሥራ ተጠርጣሪ ሆኖ ‘ዋስትና ካልያዝክ አትሰራም’ መባሉ አሳዛኝ ነው።

የገል ትምህርት ቤቶች ተርፏቸው የ6 ወራት ደመወዝ በአካውንት ማስቀመጥ አይችሉም። ስለዚህ ይሄ ረቂቅ ሕግ ሆኖ ከቀጠለ ትምህርት ቤቶች ሥራቸውን አይቀጥሉም።

ምናልባት ሌላ ንብረት ያላቸው ከባንክ ተበድረው በአካውንት ቢያስቀምጡ እንኳ 19% ወለድ ይከፍላሉ፣ ገንዘቡን በቶሎ መመለስ ስለሚያዳግት አመታት ይወስዳል። ወለዱም ዋናው ገንዘብም ተንገዳግደው ከፍለው እንኳ መቀጠል አይችሁም። ስለዚህ ይሄ ፈጽሞ የሚተገበር አይሆንም።

ሁለተኛ ማንም ሰራተኛ የትም ይስራ ዬት በአሰሪና ሠራተኛ ህግ ነው የሚዳኘው። ስለዚህ ረቂቅ ዐዋጁ ያለ ቦታው ነው የተቀመጠው። 

ሌላው የበላይ አካል ማነው? ከትምህርት ቤት ውጪ ያለ የመንግስት አካል ነው? ወይስ ትምህርት ቤት ውስጥ ያሉ የትምህርት አመራሮች ናቸው? የሚለው በረቂቁ ግልጽ አይደለም። 

ሕግ ይከበር እንላለን እዚህ አገር የሚያሳዝነው ነገር ግን በዬአካባቢው ራሳችን ሕግ አውጪ ሆነን ቁጭ እንላለን።

ሕግ ይከበር ስንል እኮ ሕግ የማውጣት ስልጣን ያለው አካል የሚያወጣውን ሕግ ለማክበር እንጂ እያንዳንዳችን እየፈበረክን የምንወጣባቸውን ሕጎች ለማክበር አይደለም።

ስለዚህ በሕግ አውጪው አካል የወጣው ህግ ‘ትምህርት ቤቶች እንደማንኛውም አይነት ንግድ ነጋዴዎች ናቸው’ ብሏል። ድርጅቶችምሕጋዊ ሰውነት ያላቸው ናቸውና መጀመሪያ ይህንን ሲመሰርቱ እኮ በአገሪቱ የሚሰራ ሥራ አለ ብለውናል። 

የኢንቨስትመንት ፓሊሲው፣ ሕገ መንግስቱ የሚያሰራ ሆኖ ሳለ በመሃል እየመጡ እንደዚህ አይነት ችግር የሚፈጥሩ ከሆነ ያሉ ትምህርት ቤቶች አይቀጥሉም፤ ሌሎች ትምህርት ሊከፈቱ አይችሉም። ምክንያቱም በዬቦታው ያለው እንቅፋት ነው ”
ብለዋል።

ጉዳዩን በሚመለከት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እንደተደረገ ይሻሻል የሚል ተስፋ እንዳለውም ማኀበሩ ገልጿል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ
በቀላሉ በስልክዎት!

#ባርኮት_ፔይ ለቤተ እምነቶች አሥራት፣ መባ፣ ልዩ ሥጦታ እና ቃል የተገቡ የቤተእምነት ገቢዎችን በተለያየ አማራጭ መሰብሰብ የሚያስችል ልዩ የብርሃን ባንክ አገልግሎት ነው!

#barkotpay #berhanbarkotpay #pay #berhanbank #bank #finance
#Stressfreebanking #bankinethiopia

ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ!
➡️ Facebook
➡️ Telegram
➡️ Instagram
➡️ Twitter
➡️ LinkedIn
➡️ YouTube
#SafaricomEthiopia

በምንፈልገው ሰዓት እና ቦታ ያለመቆራረጥ የሚሰራልን ኢንተርኔት ያስፈልገናል ፤ አሁኑኑ የM-PESA ሳፋሪኮምን የ4G ዋይ ፋይ ጥቅል ከM-PESA mini app በመግዛት የማይቆራረጠውን ኢንተርኔት እናጣጥም !

🔗የM-PESAን ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ ፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

#MPESASafaricom
#1Wedefit
#FurtherAheadTogether
#TecnoAI

ታህሳስ 10 በስካይ ላይት ሆቴል የሚካሄደው በሀገራችን ትልቁ የቴክኖ ኤ አይ ኢቬንት ጥቂት ቀናት ቀርተውቷል፡፡ ታዋቂው የቴክኖሎጂ ባለሙያ ሰለሞን ካሳ የዝግጅቱ አካል ሲሆን ስለ ቴክኖ ኤ አይ እና ስለ አዲሶቹ የቴክኖ የቴክኖሎጂ ምርት ውጤቶች ሙያዊ ማብራሪያ የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመከተል የቴክኖ ቲክቶክ ገጽ ፎሎው በማድረግ እና Bio ላይ ያለውን ሊንክ ተጭነው በመመዝገብ ታህሳስ 10 በስካይላይት ሆቴል በሚካሄደው የሀገራችን ትልቁ የኤ አይ ሁነት ላይ ይሳተፉ፡፡

https://www.tiktok.com/@tecnoet

@tecno_et @tecno_et
“ የልብ ክፍተት ህመም ያለበት ልጄን አድኑልኝ ” - አባት

በሞጆ ከተማ የሚገኙ አቶ አማረ አለማየሁ የተባሉ አባት የአንድ አመት ጨቅላ ህፃን ልጃቸው በልብ ክፍተት ህመም እየተሰቃዬ በመሆኑ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ተማጸኑ።

የህፃኑ አባት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ምን አሉ ?

“ ህፃኑን ይዤ ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተመላለስኩ። ‘የሚሆን ነገር አይደለም’ ብለው ወደ ህፃናት ልብ ህሙማን መርጃ ማዕከል መርተውኝ ነበር።

በማዕከሉ ያለው ወረፋም የሚቻል አይደለም። ‘በአስቸኳይ መሰራት አለበት ክፍተቱ ከ7 ሚሊ ሜትር የበለጠ ነው’ አሉኝና ወደ ግል ሆስፒል መሩኝ።

ቦሌ አካባቢ በሚገኘው ኢሉዜር ሆስፒታል ሄጄ ስጠይቅ ለማሳከሚያ 685 ሺሕ ብር ጠየቁኝ። በአካባቢዬ እርዳታ ብጠይቅም እስካሁን ምንም ገንዘብ አላገኘሁም።

የልጄ ህመም የተፈጥሮ የልብ ክፍተት ነው። ክፍተቱ በተፈጥሮ መዝጋት ነበረበት ሳይዘጋ ቀረ። ‘መደፈን ያለበት ደግሞ ግዴታ በህክምና ነው’ ተባለ።

ህመሙን ያወቅነው በ6 ወሩ ነው። አዳማ ኃይለማርያም ሆስፒታል ወሰድነወሰና የልብ ኬዝ እንዳለብ ነገሩን። ከዛም ወደ ጥቁር አንበሳ ሪፈር ፃፉልኝ። በሽታው እንዳይባባስበት በመድኃኒት እየተከታተለ ነው ያለው።

የኢትዮጵያ ህዝብ ልበ ቀና ነው። በመረዳዳት የታወቅን ነን። ወገኖቼ አነሰ በዛ ሳትሉ በመተባበር ልጄን አድኑልኝ ”
ሲሉ ተማጽነዋል።

ለመርዳት 1000045518586 የአቶ አማረ አለማዬሁ ደስታ የኮፕራትቭ COOP ባንክ ሒሳብ ቁጥር ሲሆን 1000263542979 የንግድ ባንክ ነው።

ለመደወል እና ዝርዝር ማስረጃዎችንም ለመጠየቅ 0915846447 የእጅ ስልካቸው ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ ክልል በሚደረገው ምክክር ላይ ኦፌኮ እንዲሳተፍ ጥሪ አቀርባለሁ " - ኮሚሽኑ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኢትዮጵያ የሚስተዋሉ አለመግባባቶች በሰላማዊ መንገድ ይፈቱ ዘንድ አጀንዳዎች እያሰባሰበ መሆኑ ይታወቃል።  ኮሚሽኑ እስካሁን በ10 ክልሎች አጀንዳ እንዳሰባሰበ፣ አንዳንድ የፓለቲካ ፓርቲዎች ግን አጀንዳቸውን በማስረብ ፋንታ ከኮሚሽኑ እንዳገለሉ መግለጻቸው ይታወሳል።…
" ኦሮሞ ሕዝብ የዘመናት ጥያቄ የሆኑት የቋንቋ፣ የወሰን ጥያቄዎች ይፈታሉ ብለን እናምናለ ፤ የአዲስ አበባ ጉዳይ የኦሮሞ ህዝብ የዘመናት ጥያቄ ነው "  - አባገዳዎቹ

የኦሮሚያ ክልል የምክክር ተሳታፊዎች የኦሮሞ ህዝብ ለ150 ዓመታት ሲጠይቅ የነበረው ጥያቄ መልስ እንዲያገኝለት አጀንዳ ሆኖ እንዲቀርብ አባገዳዎች ጠየቁ፡፡

አባ ገዳዎች ይህን የጠየቁት ዛሬ በአዳማ ከተማ የ ሀገራዊ ምክክር ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ባደረጉት የመክፈቻ መርሀ ግብር ላይ ነው፡፡፡

አባ ገዳዎቹ " የኦሮሞ ህዝብ ለ150 ዓመታት ሲጠይቃቸው የነበሩ ጥያቄዎች አንድም እንዳይዘነጉ " ሲሉ ለምክክሩ ተሳታፊዎች አሳስበዋል፡፡

" በምክክሩ የኦሮሞ ሕዝብ የዘመናት ጥያቄ ናቸው የተባሉት ፦
➡️ የቋንቋ፣
➡️ የወሰን ጥያቄዎች ይፈታሉ ብለን እናምናለን " ብለዋል፡፡

‘" የአዲስ አበባ ጉዳይ የኦሮሞ ህዝብ የዘመናት ጥያቄ ነው "  ያሉት አባገዳዎቹ ይህም በምክክሩ እንዲፈታ ጠይቀዋል፡፡

የምክክሩ ተሳታፊዎች የወከሉት የኦሮሞ ህዝብ ተቆራርጠው የቀሩት ፦
- የመሬት ጥያቄዎች፣
; የወሰን ጥያቄዎች እንዲፈቱ አጀንዳ ሆነው እንዲያቀርቡ አሳስበዋል፡፡

አፋን ኦሮሞ ቋንቋም የፌዴራል የስራ ቋንቋ እንዲሆን አባ ገዳዎቹ ለተሳታፊዎቹ " አጀንዳ " አድርጋችሁ አቅርቡ ብለዋቸዋል፡፡

አባ ገዳዎቹ የኦሮሞ ህዝብ መልስ እንዲያገኝ ጠይቁ ባሉበት ወቅት፤ በምክክር ሂደት ላይ ለመሳተፍ በስታዲየም የተገኙት ሰዎች በጭብጨባና በፉጨት ድጋፋቸውን አሳይተዋቸዋል፡፡

በዛሬ በኦሮሚያ ክልል በአዳማ ከተማ በተጀመረው የምክክር ምዕራፍ ከ356 ከክልሉ ወረዳዎች የተወከሉ ከ7,000  በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ተወክለዋል፡፡

መረጃው ከሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ የተወሰደ ነው።

@tikvahethiopia