TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE : በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን መወሰኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳወቀ። የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ በጀት ማስተካከያ መደረጉንም ይፋ አድርጓል። " ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎች የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን የምግብ ሜኑ ተቀራራቢ እንዲሆን እየሰሩ ነው " ሲል ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል። ወቅታዊውን የምግብ ዋጋ መጨመር መነሻ በማድረግ ትምህርት ሚኒስቴር…
#MoE

በወጥነት ይተገበራል የተባለው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምግብ ሜኑ ምን ይመስላል ?

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዕለታዊ የምግብ ወጪ ከታህሳስ 01/2017 ዓ.ም ጀምሮ 100 (መቶ ብር) እንዲሆን መወሰኑ ይታወቃል።

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ ሜኑም ሁሉም ጋር ወጥ እንዲሆንብ እየተሰራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር መግለጹ አይዘነጋም።

ይህንን ተከትሎ ፤ የተማሪዎች የምግብ አቅርቦት በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በወጥነት እንዲከናወን ትምህርት ሚኒስቴር ከምግብ ተመን ማሻሻው ጋር የተጣጣመ ስታንዳርድ የምግብ ሜኑ በማዘጋጀት ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ልኳል።

የምግብ ሜኑው ዝቅተኛውን መስፈርት መሠረት በማድረግ መዘጋጀቱን የገለጸው ሚኒስቴሩ ተቋማት ከባቢያዊ ነባራዊ ሁኔታን ከግምት ውስጥ በማስገባት በአንድ ተማሪ ሳምንታዊ ወጪው ከ700 (ሰባት መቶ) ብር ባልበለጠ መልኩ ስራ ላይ መዋል እንዳለባቸው ማሳሰቢያ አስተላልፏል።

ለዩኒቨርሲቲዎች በተላከው የምግብ ሜኑ ከላይ የተያያዘ ሲሆን ፦

👉 ቁርስ ላይ ፦ እንጀራ ፍርፍር / ሩዝ + ዳቦ + በሻይ ፣ ቅንጬ ፣ ስልስ ፣ ማካሮኒ ተካተለዋል።

👉 ምሳ ላይ ፦ ምስር/አተር ክክ/ሽሮ / አተር / ባቄላ / ድንች / አትክልት ማለትም ጎመን ፣ድንች፣ ካሮት የመሳሰሉ / ፓስታ /  + እንጀራ / ዳቦ ፣ ከዚህ በተጨማሪም በሳምንት 1 ቀን ስጋ በምስር/በድንች/ በክክ (በዳቦ ወይም በእንጀራ) ተካተዋል።

👉 እራት ላይ ፦ ምስር/ክክ/ፓስታ / ሽሮ + በእንጀራ/ዳቦ ፣ ከዚህ በተጨማሪ በሳምንት 1 ቀን ስጋ በምስር/በድንች/ በክክ (በዳቦ ወይም በእንጀራ) ተካተዋል።


🔵 ለበለጠ መረዳት ከሰኞ እስከ እሁድ የተከፋፈለውን የምግብ ሜኑ ከላይ መመልከት ይቻላል።

አጠቃላይ ትምህርት ሚኒስቴር ለዩኒቨርሲቲዎች በላከው የምግብ ሜኑ መሰረት ለቁርስ ፣ ለምሳ፣ ለእራት ለአንድ ተማሪ የተመደበው 100 ብር ነው።

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት / ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎች የተመደበው ዕለታዊ የምግብ በጀት በየጊዜው እየጨመረ ያለውን የምግብ ዋጋ ንረት ሊሽፍን ባለመቻሉ መንግሥት በፊት የነበረውን ዕለታዊ የተማሪ ምግብ ወጪ 22 ብር ወደ 100 ብር ከፍ አድርጎታል።

(በትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ኮራ ጡሸኔ ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተላከው ሰርኩላር ከላይ ተያይዟል)

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
ሕብር ብሩህ የቁጠባ ሒሳብ

ለልጆችዎ የህፃናት ተቀማጭ ሒሳብ  ይክፈቱላቸው፡፡ የሕብር ብሩህ የህፃናት ተቀማጭ ሒሳብ ተጠቃሚ በመሆን ለነጋቸው ጥሪት ያስቀምጡላቸው፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

📞  For more information call our free call center - 995. 
🤳 To receive new information join our Telegram page. https://yangx.top/HibretBanket
🌐 Visit our other social media pages and wesite on   linktr.ee/Hibret.Bank

#childrenssavings  #teachkidstosave #HibretBank
#EthioTelecom

🤩 ታላቅ ቅናሽ!! እንዳያመልጥዎ!

💁‍♂️ እስከ 50% በሚደርስ ቅናሽ ያቀረብናቸውን የስልክ ቀፎዎች፣ ስማርት ሰዓቶች፣ ቻርጀሮችና ኬብሎች እንዲሁም የኢንተርኔት ሞደሞችና ራውተሮች የራስዎ ያድርጓቸው!!

🗓 እስከ ጥር 19/2017 ዓ.ም ብቻ!

📍 በሁሉም የአገልግሎት ማዕከሎቻችን ያገኟቸዋል።

በተጨማሪ የአዲስ አበባ ደንበኞቻችን በቴሌገበያ https://telegebeya.ethiotelecom.et ማግኘት ይችላሉ፡፡

#Sale #Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #SmartAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ምንድነው ያስተላለፈው ውሳኔ ?

💡" ምሽት መብራት ማጥፋት እንዲከለከል እና ሙሉ የመብራት አገልግሎት እንዲኖር  ውሳኔ ተላልፏል ! "

🌃 " ዋና እና መጋቢ መንገድ ላይ የሚገኙ የንግድ እና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት እስከ ምሽቱ 3፡30 አገልግሎት እንዲሰጡ ተወስኗል ! "

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ዛሬ 4ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ስብሰባ አካሂዶ ነበር።

የተለያዩ አጀንዳዎች ላይም ተወያይቶ አፅድቋል፡፡

ከነዚህም አንዱ ፥ በሁሉም የከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች ያሉ የንግድ እና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት እስከ ምሽቱ 3፡30 ለህብረተሰቡ የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚል ነው።

ሌላኛው የምሽት ትራንስፖርትን ይመለከታል።

በዚህም ከተማ አስተዳደሩ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች ማቅረብ በመጀመሩ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች አገልግሎት አስተዳደር ረቂቅ መነሻ ሀሳብ መርምሮ በመወያየት በመንግስት እና  የግል አጋርነት (PPP) እንዲተዳደሩ ብሎም በከተማዋ የመንግስት እና የግል ትራንስፖርት አገልግሎት እስከ ምሽቱ 4፡00 ድረስ ግልጋሎት እንዲሰጡ ተብሏል።

በሁሉም የኮሪደር ልማት በሚተገበርባቸው ቦታዎች የትራንስፖርት አገልግሎት እለታዊ የጊዜ ሰሌዳ እንዲጠቀሙ እንዲደረግ ተወስኗል።

ከዚህ በተጨማሪ ካቢኔው ሁሉም ዋና መንገድ እና መጋቢ መንገድ ላይ ያሉ ተቋማት፣ ህንፃዎች እንዲሁም የግልና የመንግስት ቢሮዎች ምሽት መብራት ማጥፋት እንዲከለከል እና ሙሉ የመብራት አገልግሎት እንዲኖር  ውሳኔ ተላልፏል።

በተጨማሪ ካቢኔው ፦

- የወንዝ እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ብክለት መከላከል ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ለከተማዋ ነዋሪዎች ጤና፣ ፅዳት እና ውበት ወሳኝ እና ጠቃሚ ስለሆነ ደንቡን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

- በከተማ ፕላን ልማት ቢሮ የተዘጋጁና የሚዘጋጁ የአካባቢ ልማት ፕላን ዝግጀት፣ አፈፃፀም ቁጥጥር እና ደንብ ማሻሽያን መርምሮ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡

#AddisAbaba

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የፈረሙት ሁለቱ አገራት ናቸው፣ እኛ ሶማሊላንድ ነን ! " - ሞሐመድ ፋራህ አብዲ

ሶማሌላንድ ስለ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ስምምነት ምን አለች ?

በአንካራው ስምምነት ዙሪያ የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን ሞሐመድ አብዱላሂ (ኢሮ) ዋዳኒ ፓርቲ ቃል አቀባይ ሞሐመድ ፋራህ አብዲ የሶማሌላንድ መንግሥትን አቋም ለቢቢሲ ሶማሊኛ ተናግረዋል።

ቃል አቀባዩ ፤ " የፈረሙት ሁለቱ አገራት ናቸው፣ እኛ ሶማሊላንድ ነን። ሁለቱ ወንድማማች አገራት የራሳቸውን ስምምነት ነው የተፈራረሙት። እነሱ ተነጋግረው ከስምምነት ላይ መድረሳቸው የተለመደ ነገር ነው። እኛን የሚመለከት አይደለም " ብለዋል።

በተጨማሪ ቀደም ሲል በሶማሊላንድ ሥልጣን ላይ የነበረው መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር የተፈራረመው የመግባቢያ ሰነድ (MoU) ያለበትን ሁኔታን በተመለከተ ተናግራዋል።

ሞሐመድ ፋራህ ፥ " ገና ሥልጣን መረከባችን ነው፤ ከኢትዮጵያ ጋር የተደረገውን ስምምነት አልተመለከትነውም። ነገር ግን የምናየው ይሆናል፤ አይተነው የሶማሊላንድን ጥቅም የሚያስጠብቅ ከሆነ እንሠራበታለን፤ ካልሆነ ግን የሚቀር ይሆናል። ስለዚህ ምን እንሚሆን ለማወቅ መጠበቅ አለብን፣ ከዚያ በኋላ ውሳኔ ይሰጥበታል " ብለዋል። #BBCSOMALI

@tikvahethiopia
#ደመወዝ

🚨 " የሚከፈለው ክፍያና እንከፍላለን ብለው የሚያሳውቁት በጣም የሚያስቅ ልዩነት ያለው ነው " - ገቢዎች ቢሮ

🔴 " ቢሮው የፈጸመው ህገወጥ ድርጊት ነው " - የህግ ምሁር


የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ሆቴሎች እና መጠጥ ቤቶችን ጨምሮ በተመረጡ የንግድ መስኮች የሚሰሩ ሰራተኞችን ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እና የሰራተኞቻቸውን ብዛት የሚተምን ተመን አውጥቶ ስራ ላይ አውሏል።

ሆቴሎች፣ ስጋ ቤቶች፣ መጠጥ ቤቶች ፣ ምግብ ቤቶች፣ ካፍቴሪያዎችን ጨምሮ ሌሎች የንግድ ዘርፎች ላይ የሰራተኞች ደመወዝን በተመለከተ አሰሪዎች ትክክለኛ መረጃ ስለማይሰጡ ግብር እያጭበረበሩ ነው ብሏል።

ይህንን ተከትሎም ነው ይህን አሰራር መዘርጋቱን ገልጻል።

ስራ ላይ በዋለው ተመን መሰረት ፦
👉 የሆቴሎች ከ32 እስከ 50 ሰራተኞች
👉 ባርና ሬስቶራን ከ20 እስከ 24 ሰራተኞች
👉 ካፍቴሪካ ከ17 እስከ 25 ሰራተኞች
👉 ምግብ ቤት ከ17 እስከ 22 ሰራተኞች
👉 ምግብ፣ መጠጥ እና ስጋ ቤት ከ28 እስከ 48
👉 ስጋ ቤት እና መጠጥ ንግድ ከ20 እስከ 28 ሰራተኞች ይኖራቸዋል ተብሎ ተተምኗል።

በዚህ መሰረት የደመወዝ ግብር በተጠቀሰው የሰራተኛ ቁጥር ልክ ይጠየቃሉ።

ከአስተናጋጅ፣ ጥበቃና የፅዳት ሙያ ውጭ ላሉ ሰራተኞች ትንሹ የሚከፍሉት ደመወዝ 5,000 ብር ሆኖ ተተምኗል።

የወር ደመወዝ ተመኑ ምን ይመስላል ?

ስጋ ቤት እና መጠጥ ንግድ
° የስራ አስኪያጅ /ተቆጣጣሪ/ ከ5,000 እስከ 9,500
° ካሸር 5,000 እስከ 6,000
° ዋናው ሼፍ ከ5,000 እስከ 18,000
° አስተናጋጅ ከ3,000 እስከ 3,500
° ፅዳት ከ2,500 እስከ 3,000
° ጥበቃ ከ2,500 እስከ 3,000
° ዋና ስጋ ቆራጭ ከ5,000 እስከ 7,000
° ረዳት ስጋ ቆራጭ ከ5,000 እስከ 5,500
° ስጋ ጠባሽ ከ6,000 እስከ 9,000

ምግብ፣ መጠጥ እና ስጋ ቤት
° የስራ አስኪያጅ /ተቆጣጣሪ/ ከ8,000 እስከ 13,500
° ካሸር 5,000 እስከ 7,000
° ዋናው ሼፍ ከ6,000 እስከ 18,000
° አስተናጋጅ ከ2,500 እስከ 4,000
° ፅዳት ከ3,000 እስከ 3,500
° ጥበቃ ከ3,500 እስከ 4,000
° ዋና ስጋ ቆራጭ ከ5,000 እስከ 6,000
° ረዳት ስጋ ቆራጭ ከ5,000 እስከ 5,500
° ስጋ ጠባሽ ከ6,000 እስከ 9,000

ምግብ ቤት
° የስራ አስኪያጅ /ተቆጣጣሪ / ከ6,000 እስከ 10,000
° ካሸር 5,000 እስከ 6,000
° ዋናው ሼፍ ከ5,000 እስከ 7,000
° አስተናጋጅ ከ2,000 እስከ 3,000
° ፅዳት ከ2,500 እስከ 3,000
° ጥበቃ ከ2,500 እስከ 3,000

ካፍቴሪያ
° የስራ አስኪያጅ /ተቆጣጣሪ/ ከ6,000 እስከ 7,000
° ካሸር 5,000 እስከ 7,000
° ዋናው ሼፍ ከ5,500 እስከ 7,000
° አስተናጋጅ ከ2,500 እስከ 3,000
° ፅዳት ከ2,500 እስከ 3,000
° ጥበቃ ከ2,500 እስከ 3,000
° ሻይ ቡና / ጁስ አስተናጋጅ ከ5,000 እስከ 8,000

ባርና ሬስቶራንት
° የስራ አስኪያጅ /ተቆጣጣሪ/ ከ7,000 እስከ 10,000
° ካሸር 5,000 እስከ 6,000
° ዋናው ሼፍ ከ5,000 እስከ 7,000
° አስተናጋጅ ከ2,000 እስከ 2,500
° ፅዳት ከ2,500 እስከ 3,000
° ጥበቃ ከ3,000 እስከ 3,500

ሆቴል
° የስራ አስኪያጅ /ተቆጣጣሪ/ ከ8,000 እስከ 13,500
° ካሸር 5,000 እስከ 7,000
° ዋናው ሼፍ ከ6,000 እስከ 18,000
° አስተናጋጅ ከ2,500 እስከ 4,000
° ፅዳት ከ3,000 እስከ 3,500
° ጥበቃ ከ3,500 እስከ 4,000
° ዋና ስጋ ቆራጭ ከ5,000 እስከ 6,000
° ረዳት ስጋ ቆራጭ ከ5,000 እስከ 5,500

ወርሃዊ ደመወዝ ተተምኗል።


ይህ ለአንድ ሰራተኛ ይከፈላል ተብሎ የተተመነ ነው።

በዚህ ተመን ባለቤቶቹ የደመወዝ ግብር ሲከፍሉ ለተጠቀሱት የስራ መደቦች " ከዚህ ያነሰ ነው የምከፍለው " ማለት አይችሉም።

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ምን አሉ ?

ቢሮው ተመን ማውጣቱን አረጋግጠዋል።

ዳይሬክተሩ " በጥናት ላይ ተመስርቶ ነው ውሳኔው የተቀመጠው።

ከደመወዝ ግብር ጋር በተያያዘ የሚከፈለው ክፍያና እንከፍላለን ብለው የሚያሳውቁት በጣም የሚያስቅ ልዩነት ያለው ነው። በጣም ትልቅ ክፍተት ነው ያለው እኛ በከተማችን ያሉ የስራ መደቦችን በዝርዝር ጥናት አድርገን አብዛኛው በትንሹ የሚከፈላቸው ከ5000 ብር በላይ መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም።

ለፅዳት እና የቤት ሰራተኛ እንኳን ስንት እንደሚከፈል ይታወቃል።

እነሱ እንከፍላለን ብለው የሚያቀርቡት ዋጋ በጣም በጣም ዝቅተኛ ነው። ያንን ምንቀበልበት ሁኔታ የለም አሰራሩም አይፈቅድም። ጥናት ላይ ተመስርተን ዝቅተኛውን ተመን አስቀምጠናል " ብለዋል።

ገቢዎች ቢሮ ከተማውን የምታመነጨውን ገቢ አሟጦ ለመሰብሰብ ኃላፊነት እንደተጣለበትና በዚህም ምክንያት ዝቅተኛ የደመወዝ ተመን ስራ ላይ እንዳዋለ አሳውቋል።

ጉዳዩ በሚመለከተው አካል ህግ ሆኖ ሳይወጣ ገቢዎች ቢሮ ዝቅተኛ የደመወዝ መጠን አስቀምጦ ግብር መሰብሰብ ይቻላል ወይ ? የሚለው የህግ ጥያቄ ተነስቶበታል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ንግድና የኢኮኖሚ ህጎች መምህር አቶ ጌዲዮን ወ/ዮሐንስ ምን ይላሉ ?

" ድርጊቱ ህገወጥ ነው።

እስካሁን ባለው ነባራዊ  ሁኔታ በገቢዎች በኩል አነስተኛ ደመወዝን መወሰን ያንን ተከትሎ ግብር መሰስበብ እስካሁን ባለው የህግ ማዕቀፍ ይህንን የሚፈቅድ ነገር ስለሌለ ህጋዊ አይደለም።

በተለይ ከግብር ጋር ተያይዞ ህገመንግስቱ ግብር የሚጣለው በህግ ነው ይላል። በአንድ አስፈጻሚ / በአንድ የስራ ክፍል ኃላፊ ወይም እንደ ገቢዎች ቢሮ አይነት ደብዳቤን መሰረት አድርጎ ደመወዝን መወሰን አይቻልም።

ደመወዝ ግብር የሚከፈልበት አንድ ገቢ ነው። ይሄም ታክስ ቤዝ / ግብር የሚጣልበት አንድ ገቢ እንለዋለን። እሱ በህግ ተወስኗል። ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ከዚህ እስከዚህ ሲሆን ይሄን ያህል ... ከዚህ እስከዚህ ይሄን ያህል ... ብር እየተባለ በግብር አዋጃችን ላይ ተቀምጧል።

በዚህ በገቢ ግብር አዋጅ ላይ በተለያዩ የስራ ክፍሎችና አይነቶች የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ዝቅተኛውን የደመወዝ መጠን ለመወሰን ስልጣን ተሰጥቶታል የሚል ህግ የለም ኢትዮጵያ ላይ።

በህግ ባልተከለከለበት / አይቻልም ባልተባለበት ሁኔታ አንድ ሰው 10,000 ብር ነው ዝቅተኛ መቅጠር የምትችለው ፣ በ8,000 ነው በ18,000 እያሉ ሰንጠረዥ ማውጣት የሰዎችን የመዋዋል ነጻነት ይጎዳል።

ድርጊቱ፦
- የመዋዋል ነጻነትን የሚገድብ
- ህገመንግስታዊ ድንጋጌን የሚጥስ ተግባር ነው።

ቢሮው ' ግብር እየተጭበረበርኩ ነው ' ብሎ ካሰበ የተለያዩ የምርመራ ስራዎችን በመስራት ፣ የስራ ውሉን ከአሰሪዎቹ በመቀበል ይሄም ደግሞ በህግ አነስተኛ ደወመዝን በማውጣትና በመደንገግ ነው። እንጂ የግብር ማጭበርበር ለመከላከል ተብሎ የገቢ ግብርን በዚህ መንገድ ለማስተዳደር መሞከር የታክስ ህግን፣ መርሆችን የሚጥስ ነው። "

NB. በኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ መንግሥት ለግሉ ዘርፍ ለተቀጣሪዎች ዝቅተኛ ደመወዝ ወለል አላስቀመጠም። ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲያስቀምጥ ጥረቶች እየተደረጉ እነደሆነ ይታወቃል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው። #ሸገርኤፍኤም

@tikvahethiopia