#HERQA
ከ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጀምሮ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ከከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ይሁንታ ሳያገኙ አዲስ ዲፓርትመንት ከፍተው ማስተማር አይችሉም ተባለ።
ኤጀንሲው ከዚህ ቀደም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በርቀት መርሃ ግብር የሚያስተምሯቸውን የትምህርት ክፍሎች ብቻ ይቆጣጠር ነበር።
ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ መመሪያ ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች መተላለፉን የኤጀንሲው የእውቅና አሰጣጥ ዳይሬክተር አቢይ ደባይ ተናግረዋል።
በዚህም ተቋማቱ የሚከፍቷቸው የትምህርት ክፍሎች መስፈርቶችን ያሟሉ ስለመሆናቸው ኤጀንሲው መመርመር እንደሚጀመር ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።
ኤጀንሲው በ2013 ዓ.ም በ1 ሺህ 112 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ባደረገው ማጣራት፤ 562ቱ ማሟላት የነበረባቸውን ዝቅተኛ መስፈርቶች ሳያሟሉ በመገኘታቸው ውድቅ ተደርገዋል።
ተጠሪነት ለሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሆኖ የቆየውን ኤጀንሲ፤ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ጥራት ኮሚሽን በሚል ስያሜ እንደአዲስ በማቋቋም ተጠሪነቱ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።
ምንጭ፦ #ሸገርኤፍኤም
@tikvahuniversity

#MinistryofEducation
ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የእንግሊዘኛ ቋንቋ እንዲማሩ ሊደረግ ነው ተባለ፡፡
በ2017 የትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ ባሉ የግልም ሆነ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የእንግሊዘኛ ትምህርት እንደሚሰጥ ተነግሯል፡፡
በ2015 ዓ.ም ወደ ትግበራ የገባው አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ህፃናት ወይም የቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ብቻ እንዲማሩ የሚያዝ መሆኑ ይታወቃል፡፡
አሁን ግን በመጭው የትምህርት ዘመን ህፃናት ተማሪዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት መማር እንደሚጀምሩ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት አዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ባዘጋጀው 31ኛውን ጉባኤ ላይ ነው።
" ተማሪዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ብቁ እና ተወዳዳሪ ለማድረግ ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ ከአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በተጨማሪ እንግሊዝኛ ቋንቋ እንዲማሩ እናደርጋለን ያሉት " ሚኒስትሩ ብርሀኑ (ፕ/ር) " ተማሪዎቹ የትምህርት ደረጃቸው ከፍ ሲል የሚማሯቸው ትምህርቶች በእንግሊዘኛ ቋንቋ ስለሚሆኑ ከልጅነታቸው ጀምሮ ቋንቋውን እንዲያውቁት ማድረግ አስፈላጊ ነው " ብለዋል፡፡
አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ወደ ትግበራ ከገባት 2015 ዓ.ም ጀምሮ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ሲማሩ የቆዩት በአፍመፍቻ ቋንቋቸው ነው አሁን ደግሞ በመጭው የትምህርት ዘመን የእንግሊዘኛ ቋንቋ ይማራሉ ተብሏል። #ሸገርኤፍኤም
@tikvahethiopia