" በትግራይ ከተሞች የሚታየው የፀጥታ ስጋት ልዩ ትኩረት ያሻዋል " - ነዋሪዎች
በሳምንት ውስጥ 2 ወጣቶች ተገድለዋል ፤ ገዳዮቹ አስከ አሁን አልተያዙም።
በመቐለ ከተማ በሳምንት ውስጥ 2 ወጣቶች " ማንነታቸው አልታወቀም " በተባሉ ሰዎች መገደላቸውን የመቐለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የላከው መረጃ ያሳያል።
ሟቾች በክልሉ ጦርነት በነበረበት ወቅት በትጥቅ ትግል ተሳታፊ የነበሩ ናቸው ተብሏል።
ወጣት በሪሁ ኪዱ ባለፈው ሳምንት ሌሊት ላይ ተገድሎ መንገድ ላይ ተጥሎ የተገኘ ሲሆን ፤ ወጣት ሃይሉሽ መሰረት ደግሞ የካቲት 28 /2016 ዓ.ም ሌሊት በመዝናኛ ቦታ " ማንነታቸው አልታወቀም " በተባሉ ሰዎች #በቢላዋ ተወግቶ ተገዷል።
ቃላቸውን የሰጡ የመቐለ ነዋሪዎች ፤ ገዳዮቹ አለመያዛቸው እጅግ እንዳሳሰባቸው ገልጸው በትግራይ ከተሞች የሚታየው የፀጥታ ስጋት ልዩ ትኩረት ያሻዋል ብለዋል።
መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የመቐለው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው።
@tikvahethiopia