TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
የሟቾች ቁጥር 100 ደርሷል፤ ኢንተርኔት በበርካታ የሀገሪቱ ከተሞችም ተዘግቷል!

በኢራቅ ዋና ከተማ ባግዳድና አከባቢዋ 6 ቀናትን ባስቆጠረው ታቀውሞ የሞቱት ሰዎች 100 ደርሰዋል። በኢራቅ የተለያዩ ክፍሎች የሀገሪቱን መንግስት በመቃውም ተቃውሞ ከተቀሳቀሰ ስድስት ቀናትን አስቆጥሯል። በዚህ ታቃውሞ በርከት ብለው በመሳተፍ ላይ የሚገኙት ወጣቶች ሲሆኑ  ሙስናን ፣ ስራ አጥነትን እና ዝቅተኛ መንግስት አገልግሎትን በመቃወም ነው ተቃውሟቸውን እያሰሙ የሚገኙት፡፡

#የኢንተርኔት_አገልግሎት በበርካታ የሀገሪቱ ከተሞች ተቋርጧል። ዛሬ ጥዋት ለጥቂት ሰዓት ተከፍቶ የነበረ ቢሆንም የኢራቅ መንግስት ዳግም እንዲዘጋ አድርጎታል። ኢንተርኔት በተከፈተበት ወቅት የኢራቅ ዜጎች #VPN በመጠቀም በርካታ አሳዛኝና ለማየት የሚከብዱ ቪድዮዎችን ሲያጋሩ ነበር።

#IRAQ

•100 ሰዎች ሞተዋል
•4000 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል
•በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ታስረዋል
•ሙሉ በሙሉ በሚል ደረጃ ኢንተርኔት ተዘግቷል

@tsegabwolde @tikvahethiopia